የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 Monate her
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 Monate, 2 Wochen her
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 Monate, 2 Wochen her
" የMokeypox በሽታ መስፋፋት ለኢትዮጵያም ስጋት ነው "
በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ እና መረጃ ስርዓት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ዘውዱ አሰፋ ለአል ዓይን ኒውስ በሰጡት ቃል የተናገሩት ፦
" ቫይረሱ ከዚህ በፊት ፈንጣጣ መሰሉ በሽታ ተጠቂ የሌለባቸው ሀገራት ሳይቀር እየተስፋፋ ነው፡፡
እንደማንኛውም ሀገር እኛም በቫይረሱ ስርጭት ስጋት አለን። በኢትዮጵያ የመግቢያ እና መውጫ በሮች ላይ የተለመደው ክትትል እየተደረገ ይገኛል።
በሀገሪቱ የየብስ እና የአየር ትራንስፖርት መግቢያ እና መውጫ ላይ ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ እና ወደ ሌሎች ሀገራት እንዳይሄድ የተላላፊ በሽታዎች ክትትል እየተደረገ ነው።
የበሽታው ተጠቂ በኢትዮጵያ ቢገኝ ማድረግ ስለሚገባን ስራዎች፣ ለህብረተሰቡ መሰጠት ስለሚገባው የግንዛቤ ፈጠራ መልዕክት እና የህክምና ክትትል ስራዎችን ለመለየት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በመሰራት ላይ ነው "
በዲማ ወረዳ " ማንነታቸው አልታወቀም " በተባሉ ግለሰቦች በተፈፀመ ጥቃት የ6 ዜጎች ህይወት አልፏል።
ከትላትን በስቲያ ፤ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ በሚገኘው ስደተኛ መጠለያ ጣቢያና በመርከስ ቀበሌ ለጊዜው ማንነታቸው አልታወቀም በተባሉ ግለሰቦች የ6 ሰዎች ህይወት ማለፉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ፤ " ቅዳሜ ምሽት 3:30 አካባቢ ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት የ4 ሰው ህይወት አልፏል " ብሏል።
ግለሰቦቹ ከዲማ ከተማ 7 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በሚገኘው ኡኩጎ የስደተኛ መጠለያ ጣቢያ በመግባት ጥቃት ማድረሳቸውን ፖሊስ ገልጿል።
ከዚህም በተጨማሪ ከቀኑ 10:30 አካባቢ በመርከስ ቀበሌ " ለጊዜው ማንነታቸው ያልታወቁ " ግለሰቦች በፈጸሙት ጥቃት በሞተር ሳይክል እየተንቀሳቀሱ የነበሩ ሁለት ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ከሰሞኑን በአሶሳ ከተማ ውስጥ በግለሰቦች ቤት በተደረገ ፍተሻ የተከማቸ 50 በርሜል ነዳጅ ከነተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር ውሏል።
የአሶሳ ከተማ ፖሊስ ለኢዜአ በሰጠው ቃል ፤ በህገ-ወጥ መንገድ የተከማቸው 50 በርሜል ነዳጅ (ቤንዚን እና ናፍጣ) ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በህብረተሰብ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን አስረድቷል።
በተጠርጣሪዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑንም ገልጿል።
በአሁኑ ወቅት በከተማው #ቤንዚን እና #ናፍጣ በጥቁር ገበያ በሊትር እስከ 200 ብር እየተሸጠ መሆኑን ፖሊስ የጠቆመ ሲሆን የዚህ ህገ-ወጥ የነዳጅ ግብይት ምንጭ በህጋዊ መንገድ ከነዳጅ ማደያዎች ተቀድቶ በህገ-ወጥ መንገድ ወደ ጥቂት ግለሰቦች እጅ መግባት መሆኑን አስረድቷል።
በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የኢፌዴሪ አየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ በአውሮፕላን አብራሪነት እና በቴክኒሽያንነት ሙያ ፍላጎት ያላቸውንና የምልመላ መስፈርቱን የሚያሟሉ ወጣቶችን መልምሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
ለዚሁ የተለያዩ መስፈርቶች የወጡ ሲሆን ከነዚህ መካከል የትምህርት መመዘኛ #ለአብራሪዎች፦ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ሆና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሃገር አቀፍ ፈተና ወስዶ/ወስዳ አጠቃላይ ውጤት 350 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ የትምህርት አይነት አማካኝ ውጤት 70% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት መሆን አለበት / አለባት።
እንዲሁም የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የወሰደበትን/የወሰደችበትን የትምህርት ማስረጃ ኦርጅናልና ፎቶ ኮፒ ማቅረብ የሚችል/የምትችል መሆን አለበት / አለባት።
ከሌሎች መመዘኛዎች መካከል ቁመት 1.65 ሜ እና ከዛ በላይ የሆነ/የሆነች፣ ክብደት ከ50-60 ኪ.ግ የሆነ/የሆነች፣ የአየር ኃይል አካዳሚን የመግቢያ ፈተና ወስዶ/ዳ ማለፍ የሚችል/የምትችል መሆን አለበት/አለባት።
#የቴክኒሽያኖች መመልመያ፦ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪ ሆኖ/ና በ2012 እና በ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ፈተና ወስዶ/ዳ አማካይ ውጤት 300 እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት እንዲሁም በእንግሊዘኛ፣ በሂሳብ እና በፊዚክስ ትምህርት አማካኝ ውጤት 60% እና ከዚያ በላይ ያለው/ያላት መሆን አለበት / አለባት።
ሌሎች መመዘኛዎች ከላይ የተገለፀው ጋር ተመሳሳይ ነው።
የምዝገባ ቦታ ከላይ በዝርዝር የተቀመጠ ሲሆን የምዝገባ ጊዜ ከግንቦት 10 ጀምሮ እስከ ግንቦት 20/2014 ዓ.ም ድረስ ባሉ ተከታታይ የስራ ቀናት መሆኑን ተገልጿል።
NB. እድሜ ከ18-24
(ተጨማሪ ዝርዝር መረጃዎችን ከላይ ያንብቡ)
በአዲስ አበባ የስምንተኛ ክፍል (የሚኒስትሪ) ፈተና ከሰኔ 27 እስከ 30 ይሰጣል ተብሏል።
ከተማ አቀፍ የሆነው የስምንተኛ ክፍል ፈተና ከ71ሺ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን ከሰኔ 27 እስከ ሰኔ 30 2014 ዓ.ም ለመፈተን መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡
በአጠቃላይ ሰባ አንድ ሺ ስድስት መቶ ስልሳ አንድ የስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች ለማስፈተን ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን በትምህርት ቢሮ ፈተና ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዲናኦል ጫላ ተናግረዋል።
የፈተና ዝግጅቱ ተጠናቆ የህትመት ስራዉ የተዘጋጀ ሲሆን በእለቱ የማሰራጨት ስራ ብቻ እንደሚቀርም ገልጸዋል፡፡
የፈተናዉን ምዝገባ በተመለከተ የተማሪዎች የአድሚሽ ካርድ በሚቀጥለው ሳምንት በየትምህርት ቤቶቹ እንደሚላክ እና ለተማሪዎቹም እንደሚተላለፍ ተናግረዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለስምንተኛ ክፍል ፈተና 211 የመፈተኛ ጣቢያዎች የተዘጋጁ ሲሆን ጣቢያዎቹን ምቹ ናቸው የሚለውን ምልከታ እየተደረገ መሆኑን በማንሳት ቁጥሩ ከፍ አልያም ዝቅ ሊደረግ እንደሚችል አቶ ዲናኦል አብራርተዋል።
ፈተናው በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች እንደሚሰጥ መታወቁን ብስራት ኤም ሬድዮ ዘግቧል።
ምንጭ፦ ብስራት ኤፍ ኤም 101.1 ሬድዮ
የአሳማ መኖን ከሌሎች በዓድ ነገሮች ጋር በመቀላቀል የምግብ ዘይት ሲያመርቱ የተገኙ ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ፡፡
ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሰሜን ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ከአማራ ጤና ቢሮ እና ከደቡብ ጎንደር ዞን መስተዳደር ጋር በመሆን በማህበረሰቡ ጥቆማ መሰረት በተደረገው ክትትልና ፍተሻ ነው።
ለምግብነት ሊውል የማይችል ህገ-ወጥ የዘይት ምርቱ የተያዘው በደቡብ ጎንደር ዞን በወረታ ከተማ ሲሆን በጥሬ ግብዓትነት የሚጠቀሙት የአሳማ መኖ፣ የዘይት ተረፈ ምርትን (ፋጉሎን)፣ ሱፍን እና ሌሎች ለጊዜው ምንነታቸው ያልተለዩ በማዳበሪያ ታስረው የተቀመጡ ነገሮችን በመቀላቀልና በማፍላት በሰው እግር በመርገጥ ህገ-ወጥ የዘይት ምርቱን እንደሚያመርቱ ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን የሰሜን ምዕራብ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሉጌታ ቆየ እንደገለጹት የምርቱ ናሙና ተወስዶ በላብራቶሪ የተመረመረና ሦሰቱም ፓራሜትር የወደቀና ከፍተኛ የአሲድ ክምችት በውሰጡ መገኘቱን አስታውቀዋል፡፡
አክለው ምርቱ በምንም መመዘኛ ለምግብነት ሊውል የማይችል፣ለተለያዩ በሸታዎች የሚያጋልጥ እንደሆነ ህዝባችን እንዲገነዘብልን እንፈልጋለን ሲሉ ገልፃዋል፡፡
ህገ-ወጥ ምርቱ ምንም አይነት የብቃት ማረጋገጫ ያልተሰጠውና ምርቱን ለህብረተሰቡ የሚያከፋፍሉት ሳይታሸግ፣ ምንም የምርት መለያ ሳይለጥፉ ከበርሜል በመቅዳት እንደሚያሰራጩ ተደርሶባቸዋል ብለዋል።
በሀገርቱ የተከሰተውን የምግብ ምርቶች ዋጋ መናርን ተከትሎ ጥራትና ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ምርቶች የጤና ጉዳት እንዳያደርሱ ህብረተሰቡ በየአካባቢውና በግብይት ወቅት ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርግ አስገንዝበዋል።
ጥቆማ መስጫ፦ 8482
ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን
ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የጥሪ ማስታወቂያ ያወጡ ዩኒቨርስቲዎች
- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሪፖርት ማድረጊያ ሚያዚያ 24 እና 25/2014 ዓ/ም ፤ በረመዷን በዓል ምክንያት መድረስ ለማይችሉ እስከ አርብ ሚያዚያ 28 /2014 ዓ/ም ድረስ
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የኦንላይን ምዝገባ ግንቦት 01 እስከ 05/2014 ዓ/ም ፤ ወደ ዩኒቨርሲቲ መግቢያ እና ሪፖርት ማድረጊያ ግንቦት 8 እና 9/2014 ዓ/ም
- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 08 እና 09/2014 ዓ.ም
- ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 27 እና 28/2014 ዓ/ም
- ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2 /2014 ዓ/ም
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 01 እና 02/2014 ዓ/ም
- ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 29 እና 30 /2014 ዓ/ም
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እስከ 30 /2014 ዓ/ም
- ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ ሚያዚያ 28 እና 29/2014 ዓ/ም
- ASTU / AASTU ሚያዚያ 28 እና 29 /2014 ዓ/ም በቅጣት ግንቦት 1 /2014 ዓ/ም
- ኦዳ ቡልቱም ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 8 እና 9 ፤ ምዝገባ ግንቦት 10 እና 11
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ የመግቢያ ቀን ግንቦት 01 እና 02 /2014 ዓ/ም
- ሐረማያ ዩኒቨርስቲ ግንቦት 12፣ 13 እና 14
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 1 እና 2/2014 ዓ/ም
- መቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 10 እና 11 /2014 ዓ/ም
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ ግንቦት 03 እና 04 ቀን 2014 ዓ.ም
SUBSCRIBE ON YOUTUBE
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
https://www.youtube.com/c/Ethiopia24
አስተያየት ለመስጠት? @Ethnewbot
?➹share &Join Us
??????
@ethiopia_24 @ethiopia_24
@ethiopia_24 @ethiopia_24
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 Monate her
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 Monate, 2 Wochen her
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 Monate, 2 Wochen her