Infinity Vibes🇪🇹

Description
No trash post only reality for any questions dm

@heyecani_yok7
Advertising
We recommend to visit

The official Yescoin™
Probably something.

Play🕹️: @realyescoinbot
Player support: @yescoincare
Business: @advertize_support

Last updated 1 месяц назад

Https://grandjourney.io

Last updated 23 часа назад

The village was built by UXUY with hard work and was incubated and invested by Binance Labs.

Every Bitcoin wizard 🧙 has a @UXUYbot:
- ⚡️ Bitcoin Lightning Support
- 0⃣ TX Fee for fast transfers
- 🔒 Relying on the security of the BTC network

22 hours ago

...እና አንዴ አውሎ ነፋሱ ካለፈ በኋላ እንዴት እንዳለፋችሁት፣ እንዴት መትረፍ እንደቻላችሁ አታስታውሱም። አውሎ ነፋሱ በእርግጥ ማለቁን እንኳን እርግጠኛ መሆን አትችሉም። አንድ ነገር ግን እርግጥ ነው; ከአውሎ ነፋሱ ስትወጡ በፊት የነበራችሁትን አይነት ሰው አትሆኑም። ይህ አውሎ ነፋስ የሚያመጣው ነገር ነው።@Infinity_vibee

1 day, 8 hours ago

ዛሬ የመጀመሪያ ፍቅረኛዬን መቃብሯን ጎበኘሁት እንደዚ የማደርገዉ ሲከፋኝ እና ብቸኝነት ሲሰማኝ ነዉ . ይሄ ግን ህይወት ነዉ..መቃብሯ ላይ ተቀመጥኩ ብዙ ልጠይቃት ብዙ ልወቅሳት ነበር አካሄዴ ግን አልቻልኩም ዝም አልኩ...ሙታን አይወቀስም የሚለዉ ብሂል ይዞኝ ይሁን ወይም ሌላ አላዉቅም ብቻ ብዙ ዝምታን ዝም አልኩ።...እሷ ጋር ስደርስ አንደበቴ ተዘጋ...እንባዬ ሳላስተዉለዉ በጉንጬ ላይ ዝም እንዳለ እየፈሰሰ ነዉ...ከአፌ ቃላቶች አፈትልከዉ መዉጣት ጀመሩ በድንገት መናገር ጀመርኩ...
"እዉነት የት ነዉ ያለዉ..? በእኔ እና አንቺ ልብ ዉስጥ ወይስ ሌላ ቦታ...?
አምላካችን...እኔ እና አንቺ ወይስ በስሜቴ የተሳለቁብኝ እነዛ ሰዎች የትኞቹ ነን ትክክል...? ያሳየሽኝ መንገድ ወይስ አሁን እየሆንኩ ያለሁት የቱ ነዉ ልክ...? ለምን ነገዬን አሳየሽኝ...ለምን ይሄን መንገድ አስመረጥሽኝ...ለየትኛዉ እዉነት ነዉ ጥለሺኝ የሄድሽዉ...? ለምን...ለምን..ለምን...!! ብዙ ጩኸቶች ብዙ ለምኖች.. ብዙ ዝምታ... ልትመልስልኝ አልቻለችም..ጠበቅኩ መልስ የለም.. ዝም አለች...ለደቂቃዎች ፀፅ ብለን ተነጋገርን..የታፈነዉ እንባዬ ዛሬ ገንፍሎ ስለፈሰሰ ትንሽ ቀለል አለኝ።...
....ማእበሉ እንደመጣ አላወቅኩም ፣ ለማሰላሰል ጊዜ ሳይኖረኝ በድንገት ከተፍ አለ..ልመክተዉ አልቻልኩም..ለትንፋሼ ስታገል ድንዛዜ በሰውነቴ ውስጥ ገባ...ለመጀመሪያ ጊዜ የሞትን ትርጉም ተረዳሁ፡፡..ሰዉ የሚሞተዉ ዉስጡ ባዶ ሲሆን እንደሆነ አወቅኩ...
ለቀናት እዛዉ ማእበሉ ዉስጥ ዳከርኩ.. ቀዝፌ ለመትረፍ ሞከርኩ..ማእበሉ ግን አሸነፈኝ..ጉልበቴ ደከመ...እጆቼ ዛሉ... ሰዉነቴ ከዉሃዉ በላይ ተንሳፈፈ..ለካስ አንድ ንጋት እኔን ለማዉደም በቂ ነበረች።
  ቀን የሰጠዉ ለት ቅል ድንጋይን ሰብሮ ወትሮስ እንደ ጀግና ያዉቃል ወይ ፎክሮ.....እንኳን ሰዉ ደካማዉ ቀርቶ የፈጠረዉ ጌታ ተስሞ ተሽጥዋል በወዳጁ ማታ......ፍቅርን ብዬ እንጂ የምተናነሰዉ ባመረረማ በኔ ነዉ ሚብሰዉ.....

@Infinity_vibee

1 day, 21 hours ago

የአንዳንድ ሠው ድድብና ግን ይለያል ኸረ በስመአብ

6 days, 22 hours ago

የ 85 አመት አዛውንት ናቸው፣ እና በሚሄዱበት ቦታ ሁሉ የሚስታቸውን እጅ አጥብቀው ይይዛሉ። ሚስታቸው ለምን ዞር ብላ እንደምትመለከት ስጠይቃቸው፣ “አልዛይመርስ ስላለባት ነው” ብለው መለሱልኝ። ከዚያም ሚስቶትን ብትፈቷት ትጨነቅ ይሆን? ስል ጠየኳቸው።  “ምንም ነገር አታስታውስም፣ ማን እንደሆንኩ አታውቅም፣ እናም እኔን ለዓመታት እረስታኛለች፡ አታውቀኝም” አሉኝ። ገርሞኝ፣ “እና አርሶ ባታውቆትም በየቀኑ መንከባከብ እና መምራት ቀጠሉ?” ስል ጠየኩ። አዛውንቱ ፈገግ ብለው አይኖቼን እያዩ "እኔ ማን እንደሆንኩ ላታውቅ ትችላለች እኔ ግን ማንነቷን አውቃለው እሷም የህይወቴ ፍቅር ናት❤️****

@Infinity_vibee

1 week, 1 day ago

Ere expire liyareg new voice package slkachun askemtulgn zm blen enaweralen expire kemiyareg
..... help

1 week, 1 day ago

**ገላዋ ልስልስ ያለ ነው:: ከሴቶች ይበልጥ ሴትነት የሰፈረበት፤ የግብረ ስጋ መቅደስ ያቀፍኩ መሰለኝ:: ትንፋሿ አንገቴ ላይ የፍትወት ነበልባል ያቀጣጥላል፡፡ ሁለታችንም ወጣት ነን፣ ሁለታችንም ሰክረናል፣ ሁለታችንም ምስጢራዊ ጭለማ ውስጥ ተደብቀናል፣ ሁለታችንም የምኞት ማእበል የሚያናውፀው ሙቀት ውስጥ ተጠቅልለናል፣ የሁለታችንም ደም ፈልቷል። እጄን ከትከሻዋ ወረድ ባደርግና የማባብላት አስመስዬ ወገቧን ጥብቅ አድርጌ ባቅፈው... እንደዚህ! — ደስ ማለቱ!, . . ቀስ አድርጌ በቸልታ እጄን ወደታች ሰደድ ባደርገውና ዳሌዋ ላይ ባሰፍረውስ?. . እንደዚህ! ከፑንቲዋ ጠርዝ ከእጄ ስር ታወቀኝ፡ ከገላዋ ሙቀት የባሰ የሙታንቲዋ ጠርዝ በምኞት ወጠረኝ፡፡ እኔ ሳላውቀው እጄ ሙታንቲዋ ውስጥ እየገባ አፌ አፏን ጎረሰው:: የት እንደሆንኩና ማን እንደሆንኩ ረሳሁ:: በመርሳቴ ደመና ላይ የባህራም ፈገግታ ብልጭ አለ።

እጄን ከሙታንታዋ እያወጣሁና አፌን ከአፏ እያላቀቅኩ፤ በሹክሹክታ

«ደግ አይደለም» አልኳት

«አዎን ደግ አይደለም» አለችኝ እሷም በሹክሹክታ

«ግን በጣም በጣም እፈልግሻለሁ፡፡ አንቺም ፈልገሽኛል፣

አይደለም?»

«አዎን›

«ምን ይሻላል?>>

«እኔ 'ንጃ»

«እኔ በበኩሌ ልተውሽ አልችልም»

ዝም

«ደሞ ልተውሽ አልፈልግም:: አንቺን መተው ራስን መኮነን ነው

ዝም

«ምን ይሻል ይመስልሻል?»

«እኔ 'ንጃ»

«ባስገድድሽስ?»

«ማስገደድ አያስፈልግህም»

«እስከ ዛሬ ድረስ ያንቺን ያህል ያማረችኝ ሴት አጋጥሞኝ አያውቅም፡፡ ደሞ እስከ ዛሬ ድረስ ሴት አግኝቼ ለሌላ ሰው ስል ትቼያት አላውቅም፡፡ ዛሬ ግን እንዴት ልበልሽ»

«አሁን ሁለታችንም የማናምንበት ነገር ብናደርግ በኋላ ይቆጨናል፡፡ ግን እንድትለዪኝ አልፈልግም:: ምን ይሻላል?»

«እኔ 'ንጃ:: መብራቱን አብርተን የተረፈንን ካልቫዶ እየጠጣን ብናወራስ?»

በመብራቱ ስንጠጣ ስናወራ ምን ያህል እንደቆየን አላስታውስም፡፡ እንዲያውም ከዚያ በኋላ ምን እንዳደረግን ወይም ምን እንደተባባልን የማስታውስ አይመስለኝም፡፡ ብቻ፤ ከአንድ አመት በፊት እንዳየሁት ህልም ሆኖ ትዝ የሚለኝ አንድ ነገር አለ:: ጠርሙሱ ውስጥ የቀረውን መጠጥ ከጨለጥነው በኋላ፤ ራሴን ደረቷ ላይ እያንተራስኩ

«ይሄ ጡት መያዣሽ ይቆረቁረኛል» አልኳት

«ቆይ ላውልቅልህ» ብላ አውልቃው እንደገና ራሴን ደረቷ ላይ አንተራሰችልኝ፡፡ «ጡትሽ እንደ ሞቃት ሰማይ ነው፤ ሰማዩ ላይ በፅጌረዳ ብርሀን የተከበበች ወይን ጠጅ ጨረቃ አለች» አልኳት

«ውሸታም! መቼ አየኸው?» አለችኝ

«ማየት የለብኝም»

«አሁን ዝም ብለህ ተኛ» አለችኝ

ከዚያ ወዲያ ምንም አላስታውስም በነጋታው፣ ከሰአት በኋላ ወደ ስምንት ሰአት ላይ ስነቃ፣ ኒኮል ደረቴን ተንተርሳ ተኝታለች፡፡ አፌ ውስጥ የፋንድያ ጣእም ተሰማኝ፡፡ ኒኮልን ቀሰቀስኳት

«ደህና ነሽ?» አልኳት

«ደህና»

አፈርኩ

«ሳናውቅ የማንፈልገውን ነገር ስራን 'ንዴ?» አልኳት

«የለም»

«ጎሽ»

ትኩሳት
ስብሀት ገብረእግዚአብሔር**

@Infinity_vibee

2 weeks ago

**ካፈቀርኩት አመት ከሞላኝ ሰው ጋር በቴክስት እያወራን ነው...

<ታውቃለህ ወጣትነቴን ቢያንስ በፎቶ ባስቀምጠው ደስ ይለኛል>

<ታድያ ብዙ ፎቶዎች አሉሽ እኮ>

<አይ እንደሱ አይነት ፎቶ ሳይሆን አለ አይደል ሰውነቴን... ይሄ መሸብሸብ ያልደረሰበት ... ሸንተረር ያላየው ሰውነቴን አንስቼ ባስቀምጥ ደስ ይለኛል። በኋላ ልጅ እና እርጅና ሲመጣ መልሼ የማላገኘውን ሰውነቴን...>

<ለሱ አታስቢ እኔ ጋር ... > ዝም አለ

<አንተ ጋር ምን?... ንገረኝ... አንተ ጋር ምን?>

ከሳምንት በፊት የፍቅረኛሞች ቀን <ከቤት ወጥቼ ማደር አይፈቀድልኝም > ስለው <የታደሉ ፍቅረኛሞች ተቃቅፈው ይተኛሉ... እኔ ግን በምወዳት ልጅ ምክንያት እዚሁ አልጋዬ ላይ ተኮራምቼ...> ምናምን እያለ አለቃቀሰ። የምር አሳዝኖኛል። እወደዋለሁ። ይሄኔ ሌላ ሴት ቢያፈቅር እኮ አብራው ታድር ነበር እኔን በመምረጡ እና በማፍቀሩ ብቻ እየተቀጣ ነው... ብዬ አሰብኩ

<እሺ ምን ላድርግልህ?> ስለው <በቃ እያሰብኩሽ ልተኛ ቢያንስ ፎቶሽን ላኪልኝ> ብሎኝ ለዚህ እየቀጣሁት ላለሁት ሰው መካሻ ይሆነው ዘንድ እርቃን ፎቶዬን ላኩለት። አሁን እሱ ትዝ አለኝ። ግን ሲነጋ ወዲያው አጠፋዋለሁ ብሎኝ ስለነበር ያልጠበኩት የአፍ ወለምታ ስለሆነብኝ በጣም ደነገጥኩ

<አላጠፋኸውም እንዴ? > አልኩት

<አጥፍቼዋለሁ በእውነት... ማለቴ... ሃሳቤ ውስጥ አንቺ አለሽ ለማለት ነው> ምናምን ብሎ ቀባጠረ። ብዙም ሳንቆይ... የፍቅረኛሞች ቀን ላይ እኔ እንዳሰብኩት የላኩለትን ፎቶ አቅፎ በናፍቆት ተኮራምቶ ሳይሆን ... ከሌላኛዋ ሴት ጭን ስር ሲዋኝ እንዳደረ ሰምቼ ተለያየን።

ያ አሁን ሳይሆን ወደፊት... ካረጀሁ እና ከወለድኩ በኋላ ማየት የምፈልገው ገላዬ አሁን ላይ በየሶሻልሚዲያው ሲዘዋወር ተመለከትኩት። በእኔ እና በሱ መሃል ብቻ የነበረው ገላዬ የሁሉም ሆነ። ከሁሉም ያመመኝ እንደኔ ሴት የሆኑት ሴቶች እንኳን በገላዬ ሲዘባበቱበት ሳይ ነው... ከሁሉም ነገር ከባድ እንደኔ በአንድ ወቅት አፍቅረው አምነው የነበሩ ሴቶች አሁን የኔን ሃጥያት ሲገልጡ መፍረዳቸው ነው። ከሁሉም ህመሙ በራሳቸው ሲደርስ እንኳን ማየት ማሰብ የሚከብዳቸው ሴቶች ዛሬ የእኔን ነውር ሲቀባበሉት ሳይ ነው። ራሴን በራሴ ስቀጣው ቆይቻለሁ... በመላኬ ስሳቀቅም ስፀፀትም ቆይቻለሁ... አሁን ግን የመሰሎቼን ሳቅ እና ፌዝ መቋቋም አልቻልኩም። ከጥፋቴ ይልቅ ጥፋቴን ባገነኑት ታመምኩ... አንዲት ደቂቃ <የኔ ገላ ቢሆን ሲባዛብኝ እና ሲዘባበቱብኝ ምን ይሰማኝ ይሆን> ብለው አለማሰባቸው ያማል። እንደዛች እንደመቅደላዊት ... ሃጥያቷን አምና ይቅርታ ጠይቃ እግሩ ስር ድፍት ስትል ... ይፈረድባት እንጂ እያሉ እንደመሰከሩባት እንደዛች ስሆን ከበደኝ።**@Infinity_vibee

2 weeks, 2 days ago

አሁን የገባኝ ነገር ቢኖር ለፀጉር እንክብካቤና መፋፋት ጫካ መግባት ብቸኛው መፍትሄ ሳይሆን አልቀረም 🤔****

3 weeks ago

**ባልና ሚስት ጎረቤት አሉኝ፤ ባልየው ሁለት አይነት ሰው ነው። ቀን ቀን ለእግዜር ሰላምታ እንኳን ቀና የማይልና ሲራመድ እንኳን ነፍሳትን እንዳይረግጥ የሚጠነቀቅ የሚመስል ትሁት! ማታ ማታ ደግሞ ጠጥቶ ሲመጣ፣ ጨዋታው ሰላምታው ሳቁና ሁሉ ነገሩ ሞቅና ፈታ ያለ ነው። ከመጠጥ ጋር ያለውን ፍቅርና ወዳጅነት ላየ፣ ሳትቀምስ ካደርክ፣ ነገ ትሞታለህ የተባለ ነው የሚመስለው።

ማታ ማታ ጠጥቶ ሲመጣ፣ ጠርቶ ሰላም ሳይለኝ ወደቤቱ አይገባም፤ በሬ ላይ ቆሞ በተኮላተፈ አንደበቱ፣ በየቀኑ የሆነች ጨዋታና አንድ ቁምነገር ጣል ሳያደርግልኝ አይቀርም።

የሆነ ቀን በሬ ላይ ቆሞ፣ "ኧረ ዛሬ ጨብሲ ቤት የሰማሁትን ጭዌ ልንገርህ,,,,ሰውዬው ከቸርች አጠገብ ጠጅ ቤት ከፈተ፤ በዚህ የተናደደው የቸርቿ ፓስተር አባላቱን ሰበሰበና 'ሰይጣን አጠገባችን ጠጅ ቤት ከፍቷል፤ ይህንን ሁኔታ እንቃወማለን፤ ስለዚህ ከአሁን በኋላ ጠጅ ቤቱ እስኪፈርስ ድረስ፣ ፆም ፀሎት አውጀናል' አላቸው፤ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ ከባድ እሳት ተነሳና ጠጅ ቤቱን አመድ አደረገው፤ በዚህ ሁኔታ የተናደደው የጠጅ ቤቱ ባለቤት፣ ቸርቿን ፍርድ ቤት ከሰሰ።
ዳኛው ፓስተሩንና የጠጅ ቤት ባለቤቱን አስቀርቦ ጠየቃቸው፤ 'ከሳሽ ክስህ ምንድነው?' አለው፤ ከሳሽም 'በቸርቿ ፆም ፀሎት የተነሳ፣ ጠጅ ቤቴ ተቃጥሎብኛልና ቸርቿ ካሣ ትክፈለኝ' አለ፤ ዳኛውም ወደ ፓስተሩ ዞሮ፣ 'አንተስ ፓስተሩ ምን ትላለህ?' አለው፤ ፓስተሩም 'እኛ ጥፋተኛ አይደለንም፤ በእኛ ፀሎት ጠጅ ቤቱ አልተቃጠለም።' ብሎ ክዶ ተከራከረ።
በመጨረሻም ዳኛው በጣም ተገርሞ እንዲህ አለ አሉ፤ 'የገጠመኝ ክስ በጣም ከባድ ስለሆነ ለውሳኔ ተቸግሬያለሁ፤ ጉዳዩ በፀሎት ኃይል በሚያምን ባለ ጠጅ ቤትና በፀሎት ኃይል በማያምን ፓስተር መካከል ሆኖብኛል። እኛም ልክ እንደዚህ ነው፣ አንዳንድ ነገሮችን ለመወሰን ግራ የገባን',,,,ብሎ እየተኮለታተፈ አውርቶ አዝናንቶኝ፣ ሚስቱን እያቆላመጠ እየተጣራ ወደ ቤቱ ሄደ፤ ሁሌም ሲገባ ሚስቱን፣ 'የኔ ፍቅር' 'የኔ ታጋሽ' 'የኔ ተሸካሚ' 'የኔ ምርኩዝ' በሚሉ ቁልምጫዎች እየጠራት ነው የሚገባው።

ቤታችን የተያያዘ ስለሆነ፣ ከሹክሹክታ ወሬ እስከ ጩኸት፣ ከእቃ ኳኳታ እስከ አልጋ ሲጥሲጥታ፣ ጥርት አድርጎ ይሰማኛል። አብዛኛውን ጊዜ ሰክሮ ሲመጣ፣ ቤታቸው ውስጥ የሚሰማው የጭቅጭቅ ድምፅ ሳይሆን፣ የሱ የተኮለታተፈ አፍ ጫወታና የሷ ጮክ ያለ ሳቅ ነው። ፍቅራቸውና ይሄ ነገራቸው ሁሌም ያስደንቀኛል።

የሆነ ቀን ትንሽ ራሱን አሞት፣ ከስራ እንደወጣ በጊዜ ወደ ቤት ገብቶ ጋደም ብሏል፤ ሚስቱ እየተንጎዳጎደች ነው፤ ድንገት አንዷ ነገረኛ ጎረቤት በበራቸው አጠገብ እያለፈች፣ ስሟን ጠርታ ሰላም ካለቻት በኋላ፣ 'ያ ለፍዳዳ ሰካራም ባልሽ አልገባም?' አለቻት፤ ይሄኔ ሚስትዬው፣ ጎረቤት እስኪሰበሰብ ድረስ፣ ለያዥ ለገላጋይ ያስቸገረች ነብር ሆነች፤ ነገረኛዋ ሴትዮ ራሱ አፏን እስከምትዘጋ ድረስ፣ የምታወራው እሷ ብቻ ሆነች፣ "ሰካራም ቢሆን ባይሆን አንቺን ይመለከትሻል? ምንሽ ላይ ደረሰ? ምንሽን ነካ? ምንም ቢያደርግና ምንም ቢሆን፣ ልሸከመውና ልችለው ወስኜ ያገባሁት፣ ውድ ባሌ ነው፤ መስከሩ ቢረብሸኝና ባልደግፈውም ራሴው እችለዋለሁ እንጂ፣ ማንም አፉን እንዲከፍትበትና እንዲናገረው አልፈቅድም፤ የውሸታሞች ጊዜ ሆኖ፣ እውነተኛና ታማኝነቱ እዚህ አስቀርቶት በአንቺ አፍ ተንቆ ተጠራ እንጂ፣ እንደ ብስለትና እውቀቱ ቢሆን፣ በእንደዚህ አይነት ኑሮ እዚህ ሆኖ በአንቺ አፍ ተደፍሮ እንዲህ ባልተባለ...." እያለች እየተንቀጠቀጠች እንባ እያነቃት ያለማቋረጥ ስትናገር፣ እኔም ጎረቤቶችም ተባብረን፣ እንደምንም አረጋግተን ወደ ቤት አስገባናት፤ ቤት ስንገባ ባሏ በደነገጠና ግራ በተጋባ ሁኔታ ውስጥ ሆኖ፣ አይኖቹ እንባ አቅርሮ፣ ውጪ የነበረውን ነገር አንድ በአንድ ሲሰማ ነበር።
ሚስቱም ተደናግጣ፣ 'ምነው የኔ ውድ በጣም አመመህ እንዴ?' አለችው፤ ሳግ እየተናነቀውና እንባውን እንዳናይ አይኑን ከአይናችን እያሸሸ፣ 'ኧረ ደህና ነኝ' አላት።
ከዛን ቀን ወዲህ፣ አይደለም ሊሰክር፣ መጠጥ በዞረበት ዞሮ አያውቅም። አቆመ። አቆመ።

አንዳንዴ እንዲሁ በዋዛ የማይሸነፉና የማይፈርሱ የሚመስሉ፣ የአጓጉል ባህሪና ማንነት ቁልሎች፣ ፅናትን በተሞላ ንፁህ የፍቅር አጋርነት ይደረመሳሉ።**@Infinity_vibee

3 months, 2 weeks ago

ሚስቶች ተሰበሰቡና እግዜርን ሊያናግሩ ሄዱ አሉ....
እግዜር - ምን ሆናችሁ ልጆቸ
ሚስቶች -መረረን !
እግዜር - ምነው ምን የሚያማርርነገር ተፈጠረ
ሚስቶች - እኛ ሴቶች ጫናው በዛብን አንገፈገፈን እኛ አርግዘን፣ እኛ
አምጠን ፣እኛው አጥብተን... አልቻልንም ! ይሄ ጉዳይ ስራ እንዳንሰራ ሆነ
ተብሎ ወንዶችን ለመተባበር የተደረገ ሴራ ነው ይስተካከልልን አሉ
እያለቀሱ፡፡
እግዜር -ጥሩ! ምን እንዲደረግላችሁ ትወዳላችሁ ታደያ
ሚስቶች -ቢያንስ ከማርገዝ ፣ከማማጥ ወይም ከማጥባት ወንዶች አንዱን
የተፈጥሮ ግዴታ ያግዙን
(እግዜር ቅዱስ ገብኤልን ጠራና‹‹ እስቲ ወንዶችን ጥራልኝ ››አለው
ወንዶች ገቡ)
እግዜር - ሴቶቻችሁ ተማረዋል ተመካከሩና ከማርገዝ ፣ከማማጥ ወይም
ከማጥባት አንዱን አግዟቸው
ወንዶች ተመካከሩ 9 ወር መሸከም ይደብራል ....ማጥባትማ የባሰ ነው
....ያው ቢያምም ምጥ ይሻለናል አጠር ያለ ሰአት አምጠን ወደድራፍት
ቤት በቃ!! ወሰኑ!
እግዜር- ‹‹እንግዲህ ይህ ውሳኔ ከተወሰነበት ቀን ጀምሮ ሴቶች ያረግዛሉ
ልክ ምጥ ሲጀምር ያስረገዘው ወንድ ያምጣል !በሰላም ሂዱ›› ብሎ
ሸኛቸው !!
ከውሳኔው በኋላ የመጀመሪያዋ እርጉዝ በመንደሩ ስሟ የተጠራ ቆንጆ እና
ሃብታም ወ/ሮ ሄለን ነበረች ባለቤቷ አቶ ዘሩ ጋር ያላቸው ፍቅር ሁሉን
የሚያስቀና እግዜር ሁሉን ያሟላላቸው የተራበ የሚያበሉ የታረዘ
የሚያለብሱ ወዘተ ነበሩ .....ይህን ደግነታቸውና ፍቅራቸው ነው የአዲሱ
ህግ አስጀማሪ ያደረጋቸው ተብሎ በመንደሩ ተወራ...6..7..8...9 ወር
ሞላት ወ/ሮ ሄለን ! ባለቤቷ አቶ ዘሩ ተዘጋጀ የህዝብ ጆሮ አይን አቶ ዘሩ
ላይ ሆነ ወንድ ሲያምጥ ለማየት .....ቀኑ ገፋ ምጥ የለም !ልክ 9 ወር
ከ9 ቀን ሆነ ምንም የለም! ....በቀጣዩ ቀን ማታ ይህን ተአምር ሊያይ
ግቢውን የሞላው ሰው ሁሉ ግቢው በር ላይ ተንጫጫ... ምንድነው
ብለው ቤት ውስጥ ያሉት ሲወጡ የነወይዘሮ ሄለንን ‹‹ ዘበኛ ምጥ
እያጣደፈው ነበር !›› ያስረገዘው ወንድ ያምጥ አልነበር ውሳኔው ! አቶ ዘሩ
ማሪያም ማሪያም በሚለው ህዝብ መሃል ‹‹ በማሪያም ውርደት›› ብለው
እራሳቸውን ሳቱ!!
ሴቶችም ያኔውኑ ማታ ይሄ ውሳኔ ይነሳልን ሲሉ ወደግዜር ቀርበው ጮሁ
የሚበዙት ቀናቸው የደረሰ ነፍሰ ጡር ሴቶች ነበሩ!

@Infinity_vibee

We recommend to visit

The official Yescoin™
Probably something.

Play🕹️: @realyescoinbot
Player support: @yescoincare
Business: @advertize_support

Last updated 1 месяц назад

Https://grandjourney.io

Last updated 23 часа назад

The village was built by UXUY with hard work and was incubated and invested by Binance Labs.

Every Bitcoin wizard 🧙 has a @UXUYbot:
- ⚡️ Bitcoin Lightning Support
- 0⃣ TX Fee for fast transfers
- 🔒 Relying on the security of the BTC network