Dr. Eyob Mamo

Description
Life skill development!
You can contact me
@DrEyobmamo
Advertising
We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 2 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 3 days, 13 hours ago

1 month, 1 week ago
**መውደድ ወይስ ፍቅር?**

መውደድ ወይስ ፍቅር?

ወጣቱ ለጠቢቡ አዛውንት፡- “ጋሼ፣ በመውደድ እና በፍቅር መካከል ያለው ልዩነት ምንድን ነው?”

ጠቢቡ አዛውንት፡- “ልጄ፣ አበባን ስትወደው ነቅለህ ታሸትተዋለህ፤ አንተ ከእሱ የምታገኘው ነገር ላይ ከማተኮርህ የተነሳ የእሱ መጠውለግ ትዝም አይልህም፡፡ አበባን ስታፈቅረው ግን ባለበት ውኃ እያጠጣህ ትንከባከበዋለህ፣ እግረ መንገድህንም በውበቱና በመዓዛው ትደሰታለህ፡፡”

ወጣቱ፡- “ልዩነቱ በደንብ አልገባኝም አስረዱኝ”

ጠቢቡ፡- “ምንም እንኳን አልፎ አልፎ ለአንተ ህልውናና እድገት የሚጠነቀቁ፣ እንዲሁም በምንም አይነት ሁኔታ ብትሆን የሚወዱህ ሰዎች ብታገኝም፣ አብዛኛውን ጊዜ የሚወዱህን ሰዎች ትክክለኛ ማንነት የምታውቀው እንዲወዱህ ያደረጋቸው ውበትህ እና መዓዛህ የቀነሰ ሲመስላቸው ነው፡፡ የሚያፈቅርህ ሰው ምንም እንኳን ውበትህንና መዓዛህን ቢወደውም፣ በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ብትሆን “ውኃ እያጠጣ” እና ተገቢውን እንክብካቤ እያደረገልህ ከአንተ ጋር ይቆያል፡፡”

ወጣቱ፡- “አሁን ገባኝ!”

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

1 month, 1 week ago
ስሜትን መቆጠብ!

ስሜትን መቆጠብ!

ሶስቱ ሊቆጠቡ የሚገባቸው ነገሮች (ክፍል ሁለት)

ስኬታማ ሕይወት ለመኖር መቆጠብ ስለሚገቡን ነገሮች በጀመርነው ሃሳብ መሰረት ባለፈው ፖስት ስለ ጊዜ ቁጠባ አስፈላጊነት ተመልክተናል፡፡ ዛሬ የምንመለከተው ስሜትን ስለመቆጠብ ነው፡፡

ብዙ ሰዎች ስሜት የሚቆጠብ አይመስላቸውም፡፡ በቀን ውስጥ የሚገጥሙን ነገሮችና ያለን የስሜት አቅም ካልተመጣጠነ ስሜት እየባከነ ነው ማለት ነው፡፡ የዚህ ምልክቱ የውስጥ ዝለት፣ ነገን ለመጋፈጥ አለመፈለግ፣ ድብርትና የመሳሰሉት ስሜቶች ናቸው፡፡

ስሜትን ለመቆጠብ . . .

  1. መተው የሚገባንን ነገር መለየትና መተው፡፡
    አንዳንድ ሰዎችና ሁኔታዎች ትተናቸው ዘወር ካላልን በስተቀር በመጨረሻ ስሜትን ከማዛልና ከማድክም ውጪ ፋይዳ የላቸውም፡፡ በጭቅጭቅ፣ በእልህና በመሳሰሉት ሁኔታዎች እንድንቆይ ከሚያደርጉን ሰዎችና ሁኔታዎች ዘወር ማለት ስሜትን ይቆጥባል፡፡

  2. አሉታዊ ሃሳቦችን አለማሰላሰል፡፡
    ሁል ጊዜ ያልተሳኩልንንና የሚያስፈሩንን ማሰላሰል ይህ ነው የማይባል ስሜትን የማባከን አቅም አለው፡፡ አሉታዊ ሃሳቦች እንዳይመጡብን ማድረግ ባንችልም፣ እነሱን ከማሰላሰል ቀነስ በማድረግና በአዎንታዊው መቀየር ስሜታችንን እንዳያሟጥጡት መከላከል እንችላለን፡፡

  3. ስሜትን ማስተንፈስ ፡፡
    በየእለቱ የሚገጥሙንን የስሜት ውጥረቶች ለማረጋጋት በየእለቱ መንፈሳዊ ልምምድን ማዳበርና ጸሎት ማድረግ፣ ከተለመደው የአካባቢ ኡደት ዘወር በማለት ፈታ ማለት፣ ለቅርብና የልባችን ለሆነ ሰው የስሜታችንን ሁኔታ ማካፈል ይገኙበታል፡፡
    ከላይ የተጠቀሱትን ነጥቦች በመለማመድ ስሜታችሁን ስትቆጥቡ ይህ ልምምድ ከሌላቸው ሰዎች የላቀ ነገርን ማከናወን ትጀምራላችሁ፡፡

ስሜት ይቆጠብ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

1 month, 1 week ago

ጥያቄ፡-

ሴት ልጃችን ጥፋት ስትሰራና ስትገረፍ ብዙም የመታረም ሁኔታ ስለማታሳይ ከምንገርፋት ይልቅ ከስህተቷ እንድትታረም ሌላ መንገድ መጠቀም ጀመርንና ለውጥ ያየን ይመስለናል፡፡ በምታጠፋ ጊዜ “አልወድሽም” ስትባል ለማስተካከል ትሞክራለች፡፡ ከዚያም እንደምንወዳት ለማረጋገጥ ትጠይቀናለች፡፡ ስትታረም ደግሞ እንደምትወደድ እንነግራታለን፡፡ ይህ ሁኔታ ችግር ይኖረው ይሆን?

መልስ፡-

የልጆችን ዲሲፕሊን አስመልክቶ የተለያየ አቋምና ግንዛቤ ያላቸው ቤተሰቦች አሉ፡፡ አንዳንድ ቤተሰቦች ልጆቻቸውን ፈጽመው ዲሲፕሊን ስለማያደርጉ ብልሹ ባህሪ ያላቸውን ልጆች ያሳድጋሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ ልጆችን ዲሲፕሊን በማድረግ ቢያምኑም የሚያደርጉበት መንገድ ግን ከጥቅሙ ጉዳቱ ያመዝናል፡፡

የእናንተ መንገድ ከሁለተኛው የሚመደብ ነው፡፡ ልጃችሁ ስትሳሳት እንደማትወደድ፣ ትክክለኛ ስትሆን ደግሞ እንደምትወደድ ስትነገግሯት ህሊናዋን ለአደገኛ ቀውስ እያሰለጠናችሁት መሆኑን አትዘንጉ፡፡ ይህቺ ልጅ ቀስ በቀስ የመደነቅና ተቀባይነት የማግኘት ሱሰኛ ሆና ነው የምታድገው፡፡ ይህም ማለት ሰዎች እንዲወዷትና እንዲቀበሏት የግድ ሰዎቹን ማስደሰት እንዳለባት የማሰብ ዝንባሌን ይዛ ስለምታድግ የወደፊት ሕይወቷ ሰዎችን በማስደሰት ዙሪያ ይሆናል፡፡

የዚህ ውጤቱ፡-

• ካለማቋረጥ ሰዎች እንደሚወዷትና እንደማይወዷት ለማወቅ የመሞከር ዝንባሌ፣

• ሰዎች እንደማይወዷት ካሰበች ድብርት ውስጥ የመግባት ሁኔታ፣

• ስህተት ስትሰራ ሰዎች እንደሚጠሏት በማሰብ ስህተትን በመፍራት ከእንቅስቃሴ መገታት፣

• ሰዎች እንዲወዷት የመጦዝና ሰዎች እንደልባቸው የሚያደርጓት አይነት ሰው መሆን . . . እና የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡

ልጆችን መቅጣት (ዲሲፐልን ማድረግ) ተገቢ የሆነ ልምምድ ቢሆንም “ቅጣት” እና “ጥቃት” የተለያዩ መሆናቸው ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡ ማንኛውም አካላዊ ጥቃት፣ የስሜት ጥቃት፣ የስነ-ልቦና ጥቃት . . . ከትክክለኛ ዲሲፕሊን ጋር ሊምታታ አይባውም፡፡ ይህ የእናንተ ልምምድ ከስትና ከስነ-ልቦና ጥቃት ዘርፍ የሚመደብ ነው፡፡

ልጃችሁ ብታጠፋም ሆነ ባታጠፋ የእናንተ ፍቅር የማይለዋወጥ መሆኑን ወደማሳወቅ ልምምድ ውስጥ መግባት አስፈላጊ ነው፡፡ ሆኖም ግን ለስህተቷ እርማት፣ ሆን ብላ ለምታጠፋቸው ሁኔታዎች ደግሞ ትክክለኛውን ቅጣት መስጠት አስፈላጊ ነው፡፡ የተለያዩ ልጆች ለተለያየ የቅታት መንገድ ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

ለምሳሌ፣ አልታዘዝ ሲሉ፣ ለተወሰነ ጊዜ የሚወዱትን መጫወቻ መከልከል፣ ማየት የሚፈልጉትን የቴሌቭዢን ወይም የድህረ-ገጽ ፕሮግራም ለተወሰነ ጊዜ መከልከል፣ ማግኘት የሚፈልጉትን ጓደኛ ለተወሰነ ጊዜ እንዳየገኙ ማገድና የመሳሰሉት መንገዶች ከጥቃት በመቆጠብ ህሊናን ለማሰልጠን ይረዳሉ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

**ጥያቄ፡-**
1 month, 1 week ago

ጥያቄ፡-

ዶ/ር ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ከ2 አመት በኻላ በድጋሚ ማውራት ጀምረናል፡፡ እናም ይቅርታ ተደራርገን አብረን እንድንሆን ጠየቀኝ እኔ ግን በፊት ካደረገው ነገር አንፃር ከልቡ መሆኑን ስለ ተጠራጠርኩኝ ጊዜ እንዲሰጠኝ ጠይቄዋለው እሱም የፈለኩትን ጊዜ ወስጄ እንድወስን ተስማምቷል። እኔ ግን እንዴት ብዬ እና ምን ተጠቅሜ ከልቡ እንደተፀፀተ እና በድጋሚ ታማኝነቱን እንደማያጓድል ማረጋገጥ እንዳለብኝ አላውቅም። ወይስ ግንኙነቱን ማደሱ ስህተት ነው?

መልስ፡-

አንድ የፍቅር ግንኑነት ከተበላሸ በኋላ እንደገና ለመመለስ የመፈለግ ሁኔታ የተለመደ ሲሆን ውሳኔውም ከባድ ነው፡፡ ስለዚህ ውሳኔውን በማመዛዘን ሂደት ላይ ተጽእኖ የሚያመጡ ነገሮችን በሚገባ ማመዛዘን አስፈላጊ ነው፡፡

  1. እንደገና ወደፍቅር ግንኙነቱ ለመመለስ ያለሽ ፈቃደኝነት፡- በሁኔታዎች ተገድደሽ ሳይሆን ግንኙነቱን ከልብሽ የመፈለግሽ ሁኔታ፡፡

  2. ለመለያየት ያበቃችሁ የስህተት አይነት፡- ስህተቶቹ ቀላል አለመግባባቶች የመሆናቸውና በተቃራኒው ለመለወጥ ጊዜ የሚፈጁ ጥልቅ የባህሪ ችግሮች የመሆናቸውን ሁኔታ የመለየቱ ጉዳይ፡፡

  3. ወደቀደመው ግንኙነት ለመመለስ ጥያቄውን ያቀረበው ሰው ማን መሆኑና ለምን መመለስ እንደፈለገ፡- አንቺ ካቀረብሽው ለምን? እሱ ካቀረበውስ ለምን?

  4. ስህተታችሁ መታረሙ የመመዘኑ ጉዳይ፡- አንቺም ሆንሽ እሱ ለመለያየት ያበቃችሁን ስህተቶች ማረማችሁ የሚረጋገጥበት መመዘኛዎች የማስቀመጣችሁ ጉዳይለ፡

  5. ለዚህ ሂደት በቂ ጊዜ በመስጠት በሚገባ የመግባባታችሁ ጉዳይ፡፡

በመጀመሪያ እነዚህን ሂደቶች ለጠቅላላ እውቀትና በጉዳዩ ለመብሰል መጠቀምሽን እርግጠኛ ሁኚ፡፡ ከዚም በኋላ ስህተቱ መታረሙን የምታረጋግጪባቸውን ነጥቦች አስቀምጪ፡፡ ያንን ለማስቀመጥ ቀላሉ መንገድ ስህተቱ መሰራቱን ያመለከቱሽን ንግግሮች ወይም ተግባሮ ደግመው አለመሰራታቸውንና ያንን ለማረጋገጥ የሚኖርን ግልጽነት መመልከት ነው፡፡

ፍቅረኞች በእውነተኛ ይቅር መባባል ካደረጉትና ትክክለኛውን ሂደት ከተከተሉ ሁል ጊዜ ግንኙነትን ማደስ የሚመከር ነው፡፡

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

1 month, 1 week ago
ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ከ2 አመት በኻላ …

ከድሮ ፍቅረኛዬ ጋር ከ2 አመት በኻላ በድጋሚ ማውራት ጀምረናል . . . እኔ ግን በፊት ካደረገው ነገር አንፃር ከልቡ መሆኑን ተጠራጠርኩኝ ::

1 month, 2 weeks ago

የውሳኔህና የፍርሃትህ ግንኙነት

ከዚህ በፊት የወሰንካቸውን ያልሆኑ ውሳኔዎች በመሚገባ ከተመለከትካቸው አንድ ነገር ይጠቁሙሃል፡- የፈራኸውን ነገር፡፡ አብዛኛዎቹ የተሳሳቱ ውሳኔዎቻችን የአንድ የምንፈራው ነገር ውጤቶች ናቸው፡፡

ከአንድ ነገር የመሸሽ ውሳኔህ፣ ገንዘብ የማውጣትና ያለማውጣት ውሳኔህ፣ እውነቱን ሳታጣራ ከሰው ጋር ለመጣላት ያደረከው ውሳኔህ፣ አንድን ነገር ለማቋረጥ ያደረከው ውሳኔህ፣ ያለመማር ውሳኔህ፣ ንግድን ያለመጀመር ውሳኔህ፣ የምታፈቅራትን ሴት ላለመጠየቅ ያደረከው ውሳኔህ፣ ስለሰዎች ክፉ የማውራትን የሕወት ዘይቤ የመከተል ውሳኔ . . . ፡፡

ከዚህ በፊት ያደረካቸው ውሳኔዎችህ ውጤታቸው ካላማረና መወሰን እንዳልነበረብህ ካመንክ ውሳኔውን የነዳው የሆነ ነገር ፍርሃት ነው፡፡ ይህንን እውነታ መገንዘብ ለወደፊቱ ለምታደርጋቸው ውሳዎችህ በበቂ ሁኔታ እንድትዘጋጅ ይረዳሃል፡፡ ምንም አይነት ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት ከፍርሃት ነጻ መሆንህን ወይም ደግሞ ፍርሃቱን በሚገባ ተቆጣጥረኸው ለትክክለኛ ውሳኔ መጠቀምህን እርግጠኛ ሁን፡፡

አንድን ነገር ካለልክ ከመፍራት የሚመጣ ውሳኔ አብዛኛውን ጊዜ ዒላማውን የመሳት ባህሪይ አለው፡፡ ይህ የሚሆንበት ዋነኛ ምክንያት ያልተቆጣጠርነው የፍርሃት ስሜት ምክንያታዊ የሆነን እሳቤ የመጋረድ አቅም ስላለው ነው፡፡

ስለዚህ ምን እናድርግ?

• በአንድ ነገር ፍርሃት በመነዳት ምንም ውሳኔ ከመወሰንህ በፊት የፍርሃቱ ስሜት እስኪሰክንና በምክኒያታዊነት እስክታስብ ድረስ ጊዜ ስጠው፡፡

• የምትፈራው ነገር የማይደርስብህ ቢሆን ምን አይነት ውሳኔን እንደምትወስን አስብና ለማመዛዘን ተጠቀምበት፡፡

• ይህንን ከፍርሃት ውጪ ብትሆን ልትወስን የምትችለው ውሳኔን ብትወስን የሚደርስብህን ነገር እንዴት ልታሸንፈው እንደምትችል አስብ፡፡

• በጉዳዩ ላይ ጥበብን በማካፈልም ሆነ የውሳኔህን ውጤት አብሮህ በመጋፈጥ ሊያግዝህ የሚችል ታማኝ ሰው አማክር፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

**የውሳኔህና የፍርሃትህ ግንኙነት**
1 month, 2 weeks ago

በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!

የአንድ ሰው ከልብ የመነጨ ጥያቄ . . .
ጠዋት እንደነቃሁ ከአልጋዬ ሳልወጣ የመጀመሪያ ስራዬ ሶሻል ሚዲያ በመክፈት ምን እንደተለጠፈና ምን እንደተባለ ማየትና ማድመጥ ነው፡፡ ከአልጋዬ ወጥቼ ለመውጣት ስዘጋጅ የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ከሰዎች ጋር እያወራሁ መዘገጃጀት አዘውትራለሁ፡፡

ከቤቴ ስወጣም አሁንም የጆሮ ማድመጫ (Earphone) በጆሮዎቼ ላይ ሰክቼ ጠዋት የጀመርኩትን የሚዲያ ጉብኝት መቀጠል ወይም የሞቀ ሙዚቃ እያደመጡ መሄድ የየእለት ልምምዴ ነው፡፡

ስራዬ ቦታ ግር-ግር ነው፡፡ በሻይ ጊዜ ካፌው ጫጫታ ነው፡፡ ምሳ የምንሄደው በቡድን ሲሆን እዚያም ካለው ጫጫታ ጋር እኛም እንደመርና እየተንጫጫን እንመገባለን፡፡

ከስራ በኋላ ወደቤቴ ከመሄዴ በፊት ከጓደኞቼ ጋር ስንንጫጫ አምሽተን እቤት እገባለሁ፡፡ ማታም እቤት ስገባ ቴሌቭዥኑ ካልጮኸ ቅር ይለኛል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ቲቪው እንደበራና እንዳወራ ሲያድር ደስ ይለኛል፡፡

ለማሰብ፣ ለማሰላሰል፣ ለማቀድ፣ ራስን ለማየት . . . ጊዜ እስከማጣ ደረስ በጫጫታ ተደብቄ ይሆን?

ማናልባት ትኩረት የማጣው፣ አንድን ነገር የማልጀምረው፣ የጀመርኩትን ነገር የማልቀጥለውና የማልጨርሰው፣ ሕይወቴ ከእለት እለት እድገት የማይታይበት ለዚያ ይሆን?

ከአንዱ ጫጫታ ወደሌላው፣ ከአንዱ ማሕበራዊ ግንኙነት ወደሌላው፣ ከአንዱ የማሕበራዊ ሚዲያ ወደሌላው . . . የሚል ሰው ለራሱ የማሰቢያ ጊዜ ስማያገኝ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምን ያህል ኋላ እንደቀረ ይደርስበታል፡፡ ይህንን ለማረም ከተፈለገ . . .

  1. በቀን ውስጥ ቢያንስ 30 ደቂቃ፣ ከተቻለ የአንድ ሰዓት ጊዜ በመውሰድ ማሰብ፣ ራስን ማየት፣ ስራን መገምገም፣ እቅድ ማውጣ፡፡

  2. የነገን እቅድ ማታ አውጥቶ ማደርና ጠዋት ወደ ስራ ወይም ወደ ማሕበራዊ ሕይወት ከመሰማራት በፊት የማታውን እቅድ አየት በማድረግ ማስታወስ፡፡

  3. ትኩረታችንን፣ ስሜታችንንና ጊዜያችንን የምንሰጥበት ሁኔታ በጥንቃቄ መምረጥ፡፡

  4. ለብቻ ስንሆን የሚያስጨንቀንን ሃሳብ ከመሸሽ ይልቅ መጋፈጥና መፍትሄ መፈለግ፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

**በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!**
1 month, 2 weeks ago
**በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!**

በጫጫታ የተደበቀ ማንነት!

1 month, 2 weeks ago
የምትታገሱትን ሁኔታ ለዩ!

የምትታገሱትን ሁኔታ ለዩ!

በሕይወታችሁ ለመታገስ የወሰናችሁት ነገር ነው እናንተው ጋር የሚከርመው፡፡ አንድ ነገርም ሆነ አንድ ሰው ምንም ያህል አስቸጋሪ ቢሆንና ለእናንተ እንደማይበጃችሁ ብታውቁም ሁኔታው ከእናንተ ጋር ያለው እድሜ ከትእግስታችሁ መጠን ጋር የተያያዘ ነው፡፡

• ለምንድን ነው ያንን ለጤንነታችሁ አደገኛ የሆነን ነገር ደጋግማችሁ የምታደርጉት? ሕመሙን ስለታገሳችሁት!

• ለምንድን ነው ያንን ሆን ብሎ ስሜታችሁን የሚጎዳውን ሰው ደጋግማችሁ የምታገኙት? የሰውዬው ባህሪይ የሚያስከትልባችሁን የስሜት ቀውስ ስለታገሳችሁት!

• ለምንድን ነው ከዚያ በገቢም ሆነ በሁለንተናዊ እድገት ከማደግ ይልቅ ጭራሹኑ እያሽቆለቆላችሁ እንደትሄዱ የሚያደርጋችሁን ስራ ያላቆማችሁት? እየደረሰባችሁ ያለውን ክስረት ስለታገሳችሁ!

ምሽቱ ጥሩ የሆነ ራስን የመመልከቻ ምሽት ይሁንላችሁ!

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

1 month, 3 weeks ago

ችቦው እንዳይጠፋ!
(“ጀምሮ መጨረስ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተወሰደ)

“በፍጥነት የሚጀምሩ ብዙዎች፣ በብቃት የሚጨርሱ ግን ጥቂቶች ናቸው” - Gary Ryan Blair

የጥንት ግሪክ የኦሎምፒክ ሯጮች “ላምፓዲድሮሚያ” (lampadedromia) በመባል በሚታወቅ የቅብብሎሽ ሩጫ ይወዳደሩ ነበር፡፡ በዚህ ውድድር ላይ ሯጮቹ አንድን የበራ ችቦ (ፋና) በእጃቸው ይዘው በመሮጥና ከሚቀጥሉት ተረካቢ ሯጮች ጋር በማቀበል የመጨረሻው ተቀባይ የድል መስመሩ ጋር እስከሚደርስ ድረስ ይሮጣል፡፡ በዚህ የችቦ-ቅብብል ሩጫ ላይ ሽልማቱ የሚሰጠው ቀድሞ ለገባው ቡድን አይደለም፡፡ ሽልማቱ የሚሰጠው ችቦው ሳይጠፋበት ቀድሞ ለገባው ቡድን ነው፡፡

የሽልማቱ ዋና መልእክት፡- አንድን ሩጫ መጀመር ብቻ ሳይሆን መቀጠልም አስፈላጊ ነው፣ መቀጠልም ብቻ ሳይሆን መጨረስም አስፈላጊ ነው፣ መጨረስ ብቻ ሳይሆን ችቦው ሳይጠፋ መጨረስ አስፈላጊ ነው፡፡ ስለሆነም፣ አንድ ቡድን ሩጫውን በብቃት ጨረሰ የሚባለው ችቦው ሳይጠፋ ከደረሰ ነው፡፡ አንዳንድ ነገር ጀምረን በብቃት የመጨረሰን ሂደት ከስራውና ከእኛ አንጻር መመልከት ስንጀምር ብቻ የችቦው እውነታ ይገባናል፡

1. ስራው

ጀምሮ የመጨረስ ጉዳይ ሲነሳ በመጀመሪያ ወደሃሳባችን የሚመጣው መጠናቀቅ የሚገባው ስራ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ በዙሪያችን እንደምናስተውለው አንዳንድ ስራዎች በጥሩ ውይይትና እቅድ ይጀምሩና ሲጠናቀቁ ግን ተዝረክርከው፣ ከታሰበለት ገጽታ ውጪ ሆነውና ዋጋ ቢስ እስከሚሆኑ ድረስ ጊዜያቸው ተራዝሞ ይጠናቀቃሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በምንሰራበት መስሪያ ቤት፣ ሰዎችን ቀጥረን በምናሰራው ስራና በሌሎች ዘርፎችም በየጊዜው የምንጋፈጠው ጉዳይ ነው፡፡

ከራሱ ከስራው አንጻር ስንመለከተው፣ አንድን ስራ ጠንክሮ መጨረስ ማለት ስራው ከመጀመሩ በፊት በታቀደለት የጊዜ ገደብና በወጣለት የጥራትና የብቃት ደረጃ ማጠናቀቅ ማለት ነው፡፡ አንድን ስራ ጨረስን ለማለት ያህል መጨረስ ብቻውን በቂ አይደለም፣ ከላይ በተጠቀሰው አውድ አንጻር ስራውን በብቃትና ጠንክሮ መጨረስም ሊታሰብበት ይገባል፡፡ ይህንን እውነታ አለመገንዘብ ወይም ደግሞ አውቀነው አስፈላጊውን መስዋእትነት ላለመክፈል በማለት የምንሰራቸው ስራዎች ናቸው እንግዲህ

2. እኛ

አንዳንድ ሰዎች አንድን ስራ ለመጨረስ ካላቸው ትጋትና ፍላጎት የተነሳ ስለራሳቸው ህልውና ማሰብ እስከሚያቆሙ ድረስ ይደርሳሉ፡፡ ይሰራሉ፣ ይሰራሉ፣ አሁንም ይሰራሉ! በስራ ስለባከነው፣ ስለደከመውና የእረፍትና የጥገና ጊዜ ስለሚያስፈልገው ማንነታቸው ግን ፈጽሞ ትዝ አይላቸውም፡፡ ስለሆነም ስራውን ሲጨርሱ እነሱም አብረው ያልቃሉ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰዎች የሚታያቸው ስራቸውና ስራቸው ብቻ ስለሆነ በሂደቱ ውስጥ ስለሚያጡት የግላቸው አስፈላጊ ነገር ትዝም አይላቸው፡፡

አንድን ስራ ጠንክሮ የመጨረስ ሂደት የግልን ጤንነት የሚያጠቃልል ጉዳይ ነው፡፡ ይህ ጤንነት የአካል፣ የስነ-ልቦና፣ የስሜትና የአእምሮ ገጽታዎች አሉት፡፡ ምንም እንኳን ስራውን በተሳካለት ሁኔታ ጥጉ ድረስ ብንወስደውና ብናጠናቅቀውም በሂደቱ ግን ከተጠቀሱት የማንነት ዘርፎች አንጻር ደክመንና ከጥቅም ውጪ ሆነን ከጨረስነው ይህ ሁኔታ ጠንክሮ የመጨረስን ሃሳብ አይወክልም፡፡ አንድ ስራ በመጠናቀቁ ምክንያት የሚሰጠንን መልካም ፍሬ የምንበላው እኮ በመጀመሪያ እኛ ጤና ስንሆን ነው፡፡

የተጀመረውን የፍቅር ግንኙነት ጥጉ ለማድረስ ያለን ትግል፣ የትምህርቱ ውጤት በስኬታማ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ያለን ጭንቀት የንግዱን አትራፊነት ለማረጋገጥ ያለን እንቅልፍ ማጣት፣ ያሰብነው ስኬት ላይ ለመድረስ ያለን ሩጫ … በሂደቱ ውስጥ እኛነታችንንና ጤንነታችንን ካሳጣን (ችቦውን ካጠፋው) የጀመርነውን ነገር የመጨረሳችን ትርጉሙ በዜሮ ይባዛል፡፡

https://t.me/Dreyob

https://m.youtube.com/user/naeleyob623

https://www.facebook.com/Dr-Eyob-Mamo-1050816404958639/

Telegram

Dr. Eyob Mamo

Life skill development! You can contact me @DrEyobmamo

**ችቦው እንዳይጠፋ!**
We recommend to visit

The official Telegram on Telegram. Much recursion. Very Telegram. Wow.

Last updated 2 days, 1 hour ago

Stay connected with the latest iPapkorn Bots and News 🗞️

Bots: https://t.me/iPapkornBots/2

Last updated 4 months ago

Breaking News | Observing world events unfold in the grand theater of our time.

Last updated 3 days, 13 hours ago