꧁❀✰﷽✰❀꧂
In The Name Of God
تبلیغات👇 :
https://t.me/+TJeRqfNn3Y4_fteA
Last updated 3 days, 22 hours ago
☑️ Collection of MTProto Proxies
? تبليغات بنرى
@Pink_Bad
? تبليغات اسپانسری
@Pink_Pad
پینک پروکسی قدیمی ترین تیم پروکسی ایران
Last updated 4 months, 3 weeks ago
Official Channel for HA Tunnel - www.hatunnel.com
Last updated 2 months, 2 weeks ago
እንቁጣጣሽ
2017 E.C
፳ ፻ ፲ ፯ ዓ.ም
????
ለውድ ቤተሰቦቻችን፣ ተከታዮቻችን፣ ለኢንስቲትዩታችን ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳቹ!
የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የስራ ላይ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ
(ጳጉሜ 4/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ከፍትሕ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ሲሰጥ የቆየው የስራ ላይ ስልጠና ዛሬ ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው ማጠናቀቂያ ዕለት በመገኘት ንግግር ያደረጉት በሚንስትር ማዕረግ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ክቡር አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ተቋሙ የሚሰጣቸው ተግባርና ሃላፊነቶችን ለተሳታፊዎቹ በማስተዋወቅ የጀመሩ ሲሆን ይህ ስልጠናም የኢንስቲትዩቱ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የፌዴራል የፍትሕና ኢንስቲትዩት በዋናነት እውቀት ላይ ሳይሆን ዋና የትኩረት አቅጣጫው ችሎታ እና ሥነ - ምግባር ላይ ነው ያሉት አምባሳደሩ እዚህ ያሉ ሰልጣኞች በመሉ እውቀትን ከዩንቨርሲቲ ይዘው የመጡ ስልሆነ እኛ ትኩረታችንን በተግባር የተደገፈ የዕለት ከዕለት ክንውኖች ላይ እናደርጋለን ብለዋል፡፡
በስራ ውስጥ ሆናቹህ መማርና መሰልጠን ተገቢ ነው፣ ማንበብና እራስን ማዳበር ደግሞ ብልህነት ነው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በመሆኑም እዚህ ደረስኩኝ ብላቹህ መማርና ምንበብን ልታቆሙ አይገባም ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋ፡፡
የፍትሕ ሚኒስቴር ሚንስትር የሆኑት ክቡር አቶ ጌዲዮን ጢሞቲዎስ በንግግራቸው ደግሞ ሙያዊ መቀንጨር እንዳያጋጥማቹህ እድሜ ልካቹህን መማር፣ እራሳቹህን ማሳደግና ብቁ አድርጎ መገኘት ይጠይቃል በማለት የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን እውቀት ያለው፣ ክሂሎት ያዳበረ፣ ጽናት ያለው እና ህዝብና ሃገርን ለማገልገል የቆረጠ ባለሙ መሆን ይጠበቅባቹሃል ሲሉ በአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡
ስልጠናው ከነሃሴ 6/2016 - ጳጉሜ 01/2016 ዓ.ም የተሰጠ ሲሆን በአስራ አንድ የተለያዩ ርዕሶች ለ102 የቅድመ ስራ ሰልጣኞች ተሰጥቷል፡፡
============================
ዘገባው ፡- የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ የባለ ድርሻ አካላት የውይይና የማረጋገጥ አውደ ጥናት አካሄደ
(ሚያዚያ 04/08/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዓመታዊ የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ውጤቶች ላይ ትኩረት በማድረግ የተዘጋጀ የባለ ድርሻ አካላት የውይይና የማረጋገጥ አውደ ጥናት አካሄደ፡፡
በአውደ ጥናቱ ላይ የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ምትኩ ማዳ የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉ ሲሆን መድረኩ ስኬታማ ለማድረግ የሚቻለውን ሁሉ እንደሚደርጉ በማሳሰብ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ከዚሁ ጋር ተያይዞ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አምባሳደር ደግፌ ቡላ በንግግራቸው ኢንስቲትዩቱ ከተሰጡት አበይ ተግባራት ነካከል አንዱኛ ዋነኛው ችግር ፈቺ የፍትሕና ሕግ ጥናትና ምርምር ማድረግ እንደሆነ በመጥቀስ ባለፉት አመታትም ብዙ ስራዎች መሰራታቸውን ተናግረዋል፡፡
ምንም እንኳን መንግስት በሀገራችን የፍትሕና ሕግ ዘርፍ ላይ የተለያዩ ሪፎርሞችን ቢደርግ የማህበረሰቡን የፍትሕ ጥያቄ ግን እስካሁን ማርካት አልቻልንም ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ በመሆኑም በተቋማችን የሚሰሩ ጥናትና ምርምሮች በዋናነት የህብረተሰቡን ጥያቄ መነሻ በማድረግ የሚሰሩ ናቸው ብለዋል፡፡
ጥናትና ምርምሮች በዋናነት በሁለት መንገድ ይሰራሉ ያሉት አምባሳደሩ፣ አንድም በውስጥ አቅም በሌላ በኩል ደግሞ ከተለያዩ አጋር አካላት ጋር በጥምረት እንደሚሰራ በመጠቆም ዛሬ የሚቀርቡት ጥናቶችም ከደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲና ከባህር ዳር ዩንቨርሲቲ ጋር በጥምረት የተሰሩ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በዕለቱ በፌዴራል መንግስት ደረጃ የሙስና እና የኢኮኖሚ ወንጀሎች የፍትሕ አሰጣጥ ሁኔታ እና በፌዴራል መንግስት ደረጃ ከልክ ያለፈ ውንጀላ በሚል ርዕስ የተጠኑ ሁለት ጥናቶች በደብረ ብርሃንና በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ አጥኙ ቡድኖች የቀረቡ ሲሆን የተለያዩ ሃሳብና አስተያዬቶችም ተሰጥቶባቸዋል፡፡
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ ነው!
(በዕለቱ የነበረው ሙሉ የፎቶ መረጃዎችን ወደፊት የምናጋራቹህ ይሆናል!)
ለተጨማሪ መረጃ ከታች ያሉትን ማስፈንጠሪዎች በመጫን በፈለጉት አማራጭ መቀላቀል ይችላሉ!
ቴሌግራም ቻ፡- https://t.me/jlrtinet
ድረ-ገጽ፡- www.fjli.gov.et
ዩቱብ ቻ፡- https://www.youtube.com/channel/UCikT_TglFkIrcYEaqeU492A
ፌስቡክ ፔጅ፡- https://www.facebook.com/profile.php?id=61556809798719
የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ ሚኒስቴር መምሪያ ሃላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ሕግ ባለሙዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው
(ሚያዚያ3/2016 ዓ.ም) የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ለመከላከያ ሚኒስቴር መምሪያ ሃላፊዎች፣ ዳይሬክቶሬቶችና ሕግ ባለሙዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው፡፡
በስልጠናው ላይ በመገኘት የእንኳን ደህና መጣቹህ ንግግር ያደረጉት በመከላከያ ሚኒስቴር የወታደራዊ ፍትሕ ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮሌኔል አሰፋ ደበሌ በንግግራቸው የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት እንደዚህ አይነት ስልጠናዎችን እያመቻቸልን በመሆኑ እናመሰግናለን ያሉ ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናውን በወታደራዊ ዲሲፕሊን እንዲጨርሱ አሳስበዋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተከበሩ አቶ ዘካርያስ ኤርኮላ በንግግራቸው ሁሌም እንደምለው ማንኛውም የሃገሪቱ ዜጋ ቢያንስ የሁለት ዓመት የመከላከያ ስልጠና መውሰድ ነበረበት የሚል አመለካከት አለኝ ያሉ ሲሆን በዚህም የወታደራዊ ዲሲፕሊንን በማድነቅ ንግግራቸውን ቀጥለዋል፡፡
ይህ ስልጠና በህግ ማርቀቅ ላይ እደመሆኑ መጠን ሕጎች ሁሉ ሕግ ከመሆናቸው በፊት ያለው የመጀመሪ ምዕራፍ ነውና፣ ሕግ ማርቀቅ ላይ በቂ እውቀትና ክህሎት ካለን ለሃገር የሚጠቅም ለዜጋም የሚበጅ ሕግ ማውጣት እችላለን ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ እዚህ ላይ የተበላሸ ሕግ ብዙ ነገሮችን ያበላሽብናል ብለዋል፡፡
በመሆኑም አዳዲስ ሕጎች፣ ነባር ሕጎችና የሚሻሸሸሉ ሕጎችን በሚገባ ማስተዋልና መለዬት ያስፈልጋል ያሉ ሲሆን ለዚህ ስልጠና ደግሞ መሰረታዊው ነገር የጥናትና ምርምር ዘርፍና የሕግ አርቃቂ አመራሮችና ባለሙያዎች አብረው መሰልጠናቸው እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡
በመጨረሻም ስልጠናው የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን በመግለጽ ንግግራቸውን የቋጩት የተከበሩ አቶ ዘካሪስ የሃገር ሰላምን በማስከበር አገርን በማጽናት ትልቅ ሃላፊነት ያለበት ተቋም ጋር አብረን በመስራታችን ደስተኛ ነን፤ ወደፊትም በጋራ መስራትና መተባበር ባሉብን ጉዳዮች ሁሉ አብረናቹህ ነን ሲሉ ቃል ገብተዋል፡፡
====================================
መረጃው፡- የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ስራ አስፈጻሚ ነው!
ብልሹ አሰራርና ሙሥና ነክ መረጃዎችን ለመጠቆም ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ! https://www.epfs.gov.et/
꧁❀✰﷽✰❀꧂
In The Name Of God
تبلیغات👇 :
https://t.me/+TJeRqfNn3Y4_fteA
Last updated 3 days, 22 hours ago
☑️ Collection of MTProto Proxies
? تبليغات بنرى
@Pink_Bad
? تبليغات اسپانسری
@Pink_Pad
پینک پروکسی قدیمی ترین تیم پروکسی ایران
Last updated 4 months, 3 weeks ago
Official Channel for HA Tunnel - www.hatunnel.com
Last updated 2 months, 2 weeks ago