📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
[ ማህሙድ ጋ ጠብቂኝ ]
ወጣት ሆኜ ሳለሁ
ችዬ ባላስነሳ የለውጡን አብዮት
ራሴን ላጠፋ ስትመረኝ ህይወት
እያሰብኩ እያለ
ስብሀት ከፃፈው
ትኩሳት መፅሀፍ ያ ምክር ትዝ አለኝ
ከውሳኔህ በፊት ፒያሳ ሂድ ያለኝ ።
ያኮረፍኳት ፍቅሬን አራዳ ቀጠርኳት
ገና ሳንገናኝ
ማህሙድ ጋ ስትመጣ በሀሳቤ ሳልኳት
ኖቬት የተገዛ ነጭ ቀሚስ ለብሳ
የካራቢያኑን
ጥቁር ጫማ አድርጋ ትመጣለች እሷ
እኔማ ቀጥሬያት አትቀርም ፒያሳ
በሀኪም ቦራ አሳንሰር እየተንሸራተትኩ
ጴጥሮስን ጠምዝዤ ቁልቁል እንደወረድኩ
በፓስታ ቤት በኩል
ሀሳቦቼን ፅፌ ሳልክልሽ ብቀር
የትም አትጠብቂኝ
የትም አልቀጥርሽም ከማህሙድ ጋ በቀር
እስክትመጪ ድረስ ከቸርቸል ጎዳና ዱካሽን ስቆጥረው
ከማህሙድ ፊት ለፊት ወደ ወርቅ ቤቱ አካሌን ወሰደው
በሀሳብ ፈዝዤ
አይኖቼን አንስቼ ከወርቅ ቤቶቹ ጀርባ ብጥላቸው
ከዶሮ ማነቂያ ቅያስ ገብተዋሉ ከስጋው ላይ ናቸው
ስጋና ስጋትን
ሀዘንና ሀሴትን
በአንድ ላይ የየያዘች
በፍቅር ደግነት ሰዎችን ያነቀች
የፒያሳ እምብርት ተዐምረኛ መንደር ትጠብቀናለች
ሸግዬ ቶሎ ነይ
ከፒያሳ እግር ስር
ማኪያቶ እየጠጣን ተቀምጠን ቼንትሮ
አንቺን ደስ ካለሽ
የሆድ እያወጋን ጁሱን በ'ስትሮ
መጠን ስንጨርስ በኢንተር ላንጋኖ
ከንፈሬ ከንፈርሽ በአንድ ላይ ሆኖ
ሰዓት ስለሚሄድ
ገብተን መኮንን ባር
ከሰፈሩ ካበው ከሰፈሩ አድባር
ትንሽ አመሻሽተን
ከሰንሻይን ሻምፓኝ ካንቺ ባልራጭም
ጣይቱ ሆቴል ብናድር ዘበት አልቆጭም
ባ'ዲስባ መሐል ባ'ዲስባ ሰማይ
አልተቃጠርንም ወይ ፒያሳ አደባባይ
ትንሽ ብታረፍጁ ከአራት ኪሎ በኩል ከመጣች ኮበሌ
ወዝ ወዝ...... ወዝ ወዝ ከሚል ሽንጥና ባት ዳሌ
ተመለከትኩ እንጂ አልዘሞተም አይኔ
ይህን የታዘብኩት
አንቺን ማህሙድ ጋ ስጠብቅ ነው እኔ
የህፃኑ ብዛት 'ሚጫወተው በአፈር
እንቅልፍ አይተኙም ወይ ሠራተኛ ሰፈር
እንዳትገረሚ ንግግሬ በዝቶ ፈላስፋ ብመስል
ብታረፍጂ ጊዜ ገብቼ ይሆናል ብሪትሽ ካውንስል
ፈዘዝ ያለን ሁሉ
ኑሮ አድክሞት ጫንቃው
ዲሞክራሲ አይደለም
የኔና አንቺን አካል ቡና ነው ሚያነቃው
ከቡናም ቡና አለ
የደስታ ጠረፉን ጣራ የሚለካ
ነይ እንሂድ ማንኪራ አትቅሪ ቶሞካ
እንድታስታውሺው እንዳትረሺው ሁሌ
ማህሙድ ወረድ ብለን
ኩርት ያለ ምሳ ልጋብዝሽ ካስቴሌ
ውዴ
አትደርሺም እንዴ ፍቅር ቆየሽ እኮ
ጣፋጭ ኬክ እንብላ ገብተን ኤንሪኮ
አንድ እንጨምርለት ወሬ ለሚያበዛ
ወይ ፒዛ ኮርነር ከናፈቀሽ ፒዛ
ይሻላል እንደዛ
ለካ አንቺ ቫቅላባ ትወጃለሽ በጣም
ወረፋ ልጠብቅ
ናፍቀው የጠበቁት ሁሌም ቶሎ አይመጣም
ማህሙድ ጋ ብትቆዪ ወዲያ ተሻግሬ
አይኔን ከስክሪኑ ጆሮዬን ከዳላስ ሰቅዤ ሰካሁት
አንቺሆዬ ባቲ አምባሰል ትዝታ ቅኝቱን ሰማሁት
በመጠብቅ ብዛት አልቀልጥም እንደ ሰም
ጊዜውም ለጋ ነው
አምፒር ለሲኒማው ሰዓቱ አልደረሰም
ግድየለም አርፍጂ
በእርግጥ ስትመጪ
ማህሙድን ከቦታው ፈልገሽ ብታጪው
ከእርምጃሽ ቆመሽ መንገድሽን አትቋጪው
ምናልባት ስትመጪ
አራዳ ብቻውን ቆሞ ብታገኚው
ፊት ለፊቱ አልቅሰሽ ቅር እንዳታሰኚው
ፒያሳ እንደ ተረት አይቀርም ደብዝዞ
ከመሬት ቢፈርስም
ልባችን ውስጥ አለ እልፍ ቦታ ይዞ
ብቻ ግን የኔ ዓለም
ማህሙድ ጋ ቀጠሮ እንዳለን እንዳትረሺ
በልባችን ጉያ ፒያሳ አለች ዛሬም
ትዝታችን አለ ቀዬው ፈርሷል ብለሽ እንዳትመለሺ
[ በረከት_#ውዱ ]
ጌታዬ
አትቁጠርብኝ የአፌን
አትይብኝ የመዳፌን
አትክፈለኝ የስራዬን
አትመርምረኝ ጨጓራዬን
አትፈትሸው ኩላለቴን
አትለካብኝ እምነቴን
" ግን
እጄን አትልቀቀኝ
በምህረት አፅድቀኝ
የለም ሌላ መንገድ
ወደ አንተ የሚወስድ
ይብቃኝ መንገዳገድ
አስጨክነኝ አልበድልህ
ከስሜቴ ገጥሜ እልህ
አቆራኘኝ ከነፍሴ ጋ
ለፆም ፀሎት እንደተጋ
ያ'ረቢ ልቤን አርግልኝ ገር
ብልህ አድርገኝ እንዳልፎገር
ሀጃዬን አቅናው እንዳልቸገር
አስተዋይ አርገኝ
የማላውቀውን እንዳልናገር
ብርታትም ሁነኝ እንዳልበገር
በረከት_#ውዱ
insፓየሩ
ሰላም ዋላችሁ " እንዴት ዋልክ ዜማ " እቴት በስሜ ጠራሽኝ ወይስ ጆሮዬ ነው " ውይ ይቅር በለኝ አያልቅበት በል ተቀመጥ ቡናውን ቅጂው ነፂ " አንድ ሲኒ ብቻ ጠጥቼ ልግባ " ምነው አያልቅበት አትጫወትም " ትንሽ ደክሞኛል እቴት ገብቼ ራሴን ላዳምጥ " ኧረ ዜናዬ ይቅርብህ ይደክምሀል ይህን የሚያክል አናት ይዘህ ራሴን ላዳምጥ የባሰ እንዳያምህ " አንቺ አሁን ከኔ እኩል ታወሪያለሽ በተደራራቢ ባስ ስንሄድ የላይኛው የት ነው ሚሄደው ብለሽ እንዳልጠየቅሽኝ ተይ እንጂ ሰነድ አታስከፍቺኝ " ውይ እናንተ ሁል ጊዜ መተራረብ መች ይሆን ሚሰለቻችሁ አያልቅበት እንደዚህ የመነታረክ አቅም ካለህማ ቡናውን ባትደግም ትንሽ ተጫወት " ይቺ እያለች በየት በኩል ልጫወት " አይገርምህም እንደውም እኔ ስኖር ነው ምትጫወተው " አፍ አፌን እያልሽ ጨዋታ እያስጠፋሽኝ እንዴት ልጫወት " ።
አያልቅበት ተጫወት እንጂ ሰላም ከሌለች ተረብ ብቻ ነው እንዴ ምታወራው " ሰላም ስትኖርማ ይጠነቀቃል ለዛ ያለው ወሬ ለማውራት ይሞክራል ለኛ ሲሆን ነው እንጂ ሚዘባርቀው " እኔስ ግርም የሚለኝ ያንቺ ሞራል እራስሽን ከ ሰላም ጋ ስታወዳድሪ ትንሽ አታፍሪም የሆንሽ የሰላም ጠር " አይ እንግዲ እንከባበር አያልቅበት እኔ ከሰላም በምን አንሳለሁ " ስጋ ጥራ ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ አለች እቴት ¡ ያው በቁመትም ፣ በቁንጅናም ፣ በአስተሳሰብም ትበልጥሻለች አንቺ በእድሜ ብቻ ነው ምትበልጫት ሁለቱም እግሮችሽ ወደ ግራ ተንሻፈው የእንግሊዘኛዋን ጄ ፊደል ነው ምትመስይኝ የሆንሽ ፆም አቋም " ሁሁይ ፆም አቋም ዛሬ ደሞ ምን አይነት ተረብ አመጣህ አያልቅበት " ፀጉርህ አፍሮ ነው ወይስ ተሸማቆ ነው ኢንስፓየሩ " ልክ ነሽ አንዳንድ ሰወ መሳይ ሾካኮችን ሲያይ ይሸማቀቃል ነፂ " አይ እንግዲ አበዛችሁት ተረባችሁ ቢያዝናናኝም ብቻውን ሲሆን ደስ አይልም በይ ቡናውን ቅጂው ነፂ " እኔ ልተኛ በቃ እቴት " እንደሱ ይሻልሀል ተኛ " ።
ደራሲ #ንባባ
ይቀጥላል
መዳን ትፈልጋለህ
"""""""" """"""""""""""
ለብዙ ዘመናት አይኖቼ ተጋርደው ስኖር በጭለማ
የዓለም መድሀኒት በአጠገቤ በኩል ማለፉን ብሰማ
የናዝሪቱ እየሱስ ብዬ ተጣራሁኝ
ከበውኝ የቆሙት አይሰማም እያሉኝ
የናዝሪቱ እየሱስ
ደግሜ ጠራሁት አይኖቼ ባያዩ
ጆሮዎቼ ሰሙት መምጣቱንም ለዩ
የከበበውን ሰው መንገድ አስከፍቶ
ወደ እኔ ተጠጋ ተማፅኖዬን ሰምቶ
አይሰማህም ብለው
የናቁኝን ሁሉ መጥቶ አሳፈራቸው
አልጠሩትም እና እያየም አይናቸው
ወደ እኔ ተጠጋ
የጠራሁት ጌታ ዘመናት ጠብቄው
ሳይፈውሰኝ በፊት
" መዳን ትሻለህ ወይ ? " ነበረ ጥያቄው
ስለ ምን ጠራሁት መዳንን ብጠማ
ብርሀን እንዲሆን የዋጠኝ ጨለማ
አዎ አልኩት ጌታዬን መዳን ነው ምኞቴ
ብርሀን እንዲሆን ጨለማው ህይወቴ
ስለ ምን ጠየቀኝ
የጠሩት በሙሉ
የጮሁ በሙሉ ወደ አምላካቸው
ለመዳን አይደለም
አለሁ ለማለት ነው ሚሰማው ድምፃቸው
በአንደበት ብቻ ልብን ሳይፈተሹ
መዳንን ያይደለ መታየት የሚሹ
አለሁ ባዮች ሆነን ጠርተን የምንለግም
ፍላጎታችንን ሳይጠይቀን በፊት ታ'ምር አያደርግም
እሺታዬን ሰምቶ
ፍላጎቴን አይቶ በእጆቹ ዳበሰኝ
ድነሀል እይ አለኝ ማየት ቻልኩ ፈወሰኝ
ከሚሰሙት ሁሉ
ከከቡት ሁሉ ፍላጎት ያለውን ለመዳን ከልቡ
ያድናል ፈጣሪ ልጆቹን መጠበቅ ነውና ሀሳቡ ።
በረከት_#ውዱ
ፈታሽ አሉ !
""""""" """""""
" ወዳጅ አጊኝቻለሁ ሁሉ የሞላለት "
ብለሽ የሄድሽ 'ለት
ውሳኔሽን ብቻ ልትነግሪኝ ስትመጪ
ምን ምርጫ ነበረኝ ከመቀበል ውጪ
ጥለሽኝ ስትሄጂ
ወደ ሞቀ ጎጆ ወደ ቀና ትዳር
ከደህና ሁኝ ውጪ አልወጣኝ ክፉ ቃል
ያዘንኩብሽን ግን ልቤ ብቻ ያውቃል
ትዝታሽን ይዤ ያንቺን ትላንትና
" ሄድኩ " አልሽኝ ይ..ሁ...ና
" እንዳትመጣ ዳግም ውጣ ከህይወቴ
እንዳትረብሽብኝ የሞቀ ነው ቤቴ "
ብለሽ የሄድሽ 'ለት ቢከፋኝም በጣም
አንቺን ደስ ይበልሽ ተመልሼ አልመጣም
ሄድሽ አይደል
በይ ይቅናሽ አንቺ እንዳልሽው ይሁን
እቱ ምን በወጣኝ
እኔ ላንቺ ትዳር አልመኝም ክፉን
" ወዳጅ አጊኝቻለሁ ሁሉ የሞላለት "
ብለሽ የሄድሽ እለት
አፍቃሪ እና ጨዋ የሚንከባከብሽ
ከሁሉም አብልጦ እጅግ የሚያፈቅርሽ
ሰው ካገኘሽማ ሸኘሁሽ መርቄ
ሚሊዮን እርምጃ ከህይወትሽ 'ርቄ
ከወጣሁኝ ወዲያ ጆሮ አይሰማው የለ
የሚወድሽ ባልሽ ፈቶሻል ተባለ !
አበስኩ ገበርኩ በእንተ እግዝትነ
ኧረ አስተፍሯላህ ትዳርሽ ምን ሆነ ?
ብዬ አልጠይቅሽም እኔ ምን አገባኝ
እንኳን ተለይቼሽ
አብረሽኝ እያለሽ ባህሪሽ መች ገባኝ !
በረከት_#ውዱ
ሴት ሆይ
"""""""""""
ገና ዓለም ሳይፈጠር የዓዳም መኖር ሳይታሰብ
አሁን ያለው ሳይኖር በፊት ፍጡር ሳይሰበሰብ
አምላክ በህሊናው አስቦ ያኖረሽ
የአዳም ግራ ጎን ሄዋን እንደምን ነሽ
ባዶነቱን አይቶ
ሰው ብቻውን ቢሆን መልካም ስላልሆነ
ከአዳም ጋ አብረሽ........ተፈጥረሽ ነበረ
ስጋሽም ከስጋው
አጥንትሽ ከአጥንቱ.......አንድ በመሆኑ
ሴት ብሎ ሰየመሽ.........አዳም በልሳኑ
ሴት ሆይ እንደምን ነሽ
አዳም ሁሉ ሞልቶት ምድርን ቢገዛ
መጉደልሽ አጉድሎት ሀዘኑ ቢበዛ
ከባድ እንቅልፍ ወስዶት ብትኖሪ ሲነቃ
ደስታው እጥፍ ሆነ ለሙሉነት በቃ
" ሄዋን " አላት አምላክ የህያዋን እናት
" እንስት " አለ አዳም ከውስጡ ሲያገኛት
የአምላክ ጥበቡ
ሚስትና እናትን አርጎ ባንድ ስጋ
ባንድ አካል መፍጠሩ
ተዐምር ነው ሲመሽ ድንቅ ነው ሲነጋ
ሄዋን ሆይ እንዴት ነሽ
አዳም በለስ በልቶ መቼ ሞትን ጠራ
እንደውም እንደውም
ሰላሳ እና ስልሳ መቶ ፍሬ አፈራ
እንዳሸዋ በዛ ምድርን ሁሉ ሞላ
የብቸኝነቱ ሀዘን ተሽቀንጥሮ ተተካ በተድላ
ሄዋን ሆይ እንዴት ነሽ
የባለቤቷ ዘውድ የንግስናው ሚዛን
ውብ እናትነትሽ
ንፁህ ሚስትነትሽ ልባችንን ገዛን
ሴት ሆይ እንደምነሽ
ለአዳም መኖሩ ምክንያት አንቺ ነሽ ።
በረከት_#ውዱ
#መልካም የሴቶች ቀን
የደም ድል ቀን
በዚህ ቀን በኩር ገድል የተፃፈበት
እሉፋን ጨርቅ አገልድመው
አእላፋት የማረኩበት
በዚህ ቀን
ገበዘ ኢትዮጵያ ጠላት አንበርክኮ
ሰማዕቱ ጊዮርጊስ ውጊያ ወጥቶአል እኮ
ይሄስ ቀን የታጠቀ የደም ድል
ሚንሊክን ያደረሰው እስከመማል
በዚህ ቀን በኩር ገድል የሚፃፍበት
ብዙዎች ሚዘከሩበት
አ-አያውቁም ባንቺ ድርድር ሰማዕታት
ድ- ድሉ ነው የሚነበበው ላንቺ የሚሞት
ዋ- ዋ ማርያምን ብለናልና አንችልም ኋላን ማየት
መፈክር አልነበረውም ሰይፍ
እንጂ ሰልፍ አይታወቅ የበፊቱማ
አሁንስ ትውልድ ሽሮ እን'ማርክ ሲባል
ከወቶ አደርሽ ጠላት ነው ቀድሞ ሚሰማ
አሁንስ ግዜ ገልብጦ የፈሪ እናት
በለው ትላለች
የጀግና እናት እሩጥ 'አምልጥ እያለች
እውነት በህግ ፊት ስትጥል ስላየች
የአሁኑ ይቅር
ከእልፍኝ ቤትሽ ዘጋኝ ብዙ ነው
ፈቃዳቸው ነው ፈቃድሽ ነበር ውሉ የቱ ነው
እ'ይው እማ
ገሀድ ሳይወጣ ሀዘን ሚስጢሩ
ታስታውሻለሽ መፍተሔ ነበርሽ ለዳር ድንበሩ
በጊዜሽ የኔ ባልሽው ቀን
አየን በጉያሽ እናትም ልጇን ስትቀብር
ወጥቼ ልደር ብሎ ሲነሳ አጥታ ስትመክን
በዘመኔ
የጀግና እናት አምልጥ ትላለች
የፈሪ እናት አይዞህ እያለች
አበስኩ ገበርኩ አንቺ እቴጌ
የሴቱን ነገር ዛሬ ባየሽው
ነጭ ባመጣው ተማርኮ ወድቆ
ለ tik tok ዉጊያ ሽምቆ ታጥ'ቆ
ባሏን አልብሳ ዝመት አትልም
እሷም አትዘምትም
በሀገሯ ላይ ጠፍታ ቀርታለች
ሀገር የላትም
ምን ይሰማሻል ትውልድሽ መክና
ተጥላ ባየሽ
ሀገሯን ሽጣ ኋላ ስትሸሽ
ምንስ ይለቀስ ለእኛ ትውልድ
ምኑ ሊዘከር የዘመኔ ሰው ምንስ ይወለድ
በቃ ሚዘሩ ማዕፀን የሚሸልቱሽን
በቀን ያፈራሉ
ነገ አፍር ሊከቱሽ በፍሬሽ ያድጋሉ
አልስትም
የቃልኪዳን ሀገር መሆንሽን አልረሳም
ግን ፍቅር ትህትና በታጣበት ቦታ
ቃልኪዳን አይፀናም
ማርያም ካማለደች የምኒሊክ ማህተብ
ለአስራት ሀገሯ
እግዜር ዝም ካለ ግፍ ባማጠች ሀገር
ስሙ እየተጠራ
ለምን ይሆን ወገን እኛ እለት ከእለት
መሀት የምንጠራ
የቀደምቱ አምላክ የነገብሬዬ አባት
የሰማዕቱ ወዳጅ ገባሪ አመታት
ለመከነው ትውልድ በኔ ቀን ያለን ሰው
እባክህ ቀን ይውጣ ልቡ ላይ እረሰው
አመት መቶ በአዲሱ አመት
በአድዋ ድል እንዲኮራ
ልቡን አይደል አሁን ደሞ አፉን ግራ
ሚንሊክን የተማለድሽ የአምላክ እናት
ለዘመኔ ቀስትን አድርገሽ በደመና
ዙሪያ ቅጥሩን እሰሪለት
በቀናችን ለተነሱ አልዐውያን ነገስታም
ቀን ይውጣ እንጂ ጦር ጎመድን አንመዝም
ቀን ካንተ ነው አመት መጥቶ ሚፈራረቅ
ኢትዮጵያን የምንወዳት ትንሳኤዋን እስከምናውቅ
በዚህ አድዋ ድልን ስጠን አንድ ብቻ
ልባችንን ለፈቀድህ እስቲ አስገዛ አቻ ላቻ
ze.....fasi13
Ebakachun like bemadreg erdugn endashenf tnsh bcha newu yekeregn please
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
?? @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc