Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

Daregot Media

Description
ዳረጎት ከራት በኋላ እንደጭማሪ፣ እንደማጠንከርያ የሚቀመስ ቀለል ያለ መብል ነው፡፡ እናንተም ዋናውን መንፈሳዊ መብል ከሊቃውንት አባቶቻችን አንደበት፣ ከመጻሕፍት ምስክርነት፣ ከደጋግ አበው ሕይወት፣ ከቤ/ክ ተጋድሎዋና ድሏ እየተማራችሁ ይህችን የኛን ዳረጎት ቅመሱልን፡፡
ለአስተያየት @DaregotMediaComment_bot

www.daregot.com
@daregotmedia
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month, 2 weeks ago

https://youtu.be/_RJvWe2E2hU?si=zRw4MeGzEnnMrt-v

YouTube

ሕመም ፣ ስቃይና ክርስቲያናዊ ኑሮ - Illness, suffering and Christian life | ኤማሁስ ፖድካስት Ep13

ከዚህ ቀደም በኤማሁስ የተዘጋጁ መደመጥ ያለባቸው መርሐግብራት። ደጉ ሳምራዊ - https://youtu.be/1YRXDDfNkcA?si=mbqIlUo3h\_wgzTvE ሑረ ወመሀሩ - የቤተክርስቲያን ተልእኮ ከየት ወዴት https://youtu.be/adwG8ZlG5gc?si=atqr6EO03R\_kpfVf የቅዱስ ዮሐንስ ምስክርነት በእንተ ወንጌል https://youtu.be/bYcwvyga3CA?si=5gCFR-Mor9el0auO…

1 year, 1 month ago

ፊርማ ለወዳጅ

ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ክላስ ሜቶች ፣ ወዳጆችና የመንፈስ ልጆች በሙሉ።

አንዳንዶቻችሁ በቅርብ ለገበያ የቀረበውን መጽሐፌን " አዘጋጁ ካልፈረመበት አንገዛም ሙተን እንገኛለን" ማለታችሁን ሰምቻለሁ። ሌሎቻችሁ ደግሞ "ለበዓል መጥተን ሰኞ ፣ ማክሰኞ ሂያጅ ነን። መጽሐፉን አስቀምጥልን" እያላችሁ በውስጥ መስመር እየወተወታችሁኝ ነው። እኔ የሺህ ወዳጅ ወንድማችሁ ወገቤ እስቲንቀጠቀጥ ጥፌ ማዘጋጀቴ አንሶ እናንተን እግር በእግር እየተከተልኩ መጣፍ ማቀብልበት ጊዜውም ጉልበቱም የለኝምና የግቢ ጉባኤ ፣ የዓለም ት/ቤት ፣ የፕሪፕ ፣ የሚካኤልና የሌላም ሌላም የሰፈር ወዳጅ ፣ ጓደኛ ፣ ደቀ መዝሙርና ደቂቀ መዝሙር ሁሉ በትንሣኤ ዋዜማ በቀዳም ሥዑር ዕለት በደብረ መድኃኒት ሰ/ት/ቤት አዳራሽ ከ4 ሰዓት ጀምሮ ከትተህ ላግኝህ። ማኅተምና ፊርማዬን ከስምህ ጋር ከትቤ እንዳስፈላጊነቱም በሥዕል አስውቤ ዘላለማዊ የወዳጅነት ማስታወሻ ይሆን ዘንድ መጽሐፈ መሠረትን አበረክትልሃለሁ። መርኃ ግብር አይደለም ደግሞ መጥቶ መሄድ ነው። አንድ የጋራ መገናኛ ለመፍጠር ያመች ዘንድ ነው። ማን ያውቃል በስንት እግዚኦታ ፣ ሠርግና ምርቃት መገናኘት ያልሆነለትን ጀማ ማገናኛ ሰበብ ይሆናል። ዘር ፣ ቀለም ፣ ጾታ ፣ እድሜ ፣ ባች ፣ ጸባይ ፣ የአመራርነትና የሥራ እርከን አይለይም። "ከሣችን አውቀዋለሁ" የሚል ሁሉ ጎራ ይበል።
https://www.instagram.com/p/Cq8b-10oXh8/?igshid=MDJmNzVkMjY=

Instagram

173 likes, 4 comments - dn.\_dr.\_kesatebirhan on April 12, 2023: "ፊርማ ለወዳጅ ለመላው አብሮ አደጎች ፣ አብሮ አገልጋዮች ፣ ...

ፊርማ ለወዳጅ
1 year, 1 month ago

እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ ጉጉትና ምኞት የወለደው ሃሳብ በጉባኤ መሃል ወርወር ባደረግላቸው ቁጥር እንዲህ ብለው ይመልሱ ነበር።
“መጽሐፍ ልጻፍ ብል ቤት መቀመጥ ፣ መጻሕፍት ማገላበጥ ግድ ይሆናል። ይህ ደግሞ የእናንተን የትምህርት ጊዜ ይሻማል። ስለዚህ እኔ እናንተው ላይ መጻፉን መርጫለሁ። እናንተ ደግሞ መጽሐፉን ትጽፉታላችሁ።”
ይህ አነጋገራቸው “ሰዎች ሁሉ በሚያውቁትና በሚያነቡት በልባችን የተጻፈ መልእክታችን እናንተ ናችሁ። እናንተም በሕያው እግዚአብሔር መንፈስ እንጂ በድንጋይ ጽላት ያልተጻፈ ፥ በእኛም የተገለገለ የክርስቶስ መልእክት እንደሆናችሁ የተገለጠ ነው።” የሚለው የቅዱስ ጳውሎስን ኃይለ ቃል ይመስላል።
እንዳሉትም እስከ መጨረሻይቱ ሕቅታ ድረስ አንድነትን ሦስትነትን ማመንን የሚያጸና ትምህርት እየጻፉ አረፉ። “መጽሐፉን እናንተ ትጽፉታላችሁ” የሚለው ትንቢትም ከዐሥር ዓመታት በፊት በበኩር የመንፈስ ልጃቸው በዲ/ን ዶ/ር አቤል ኃይሉ “የማእዘን ራስ” መጽሐፍ ተፈጽሟል። እነሆ አሁን ደግሞ የገዛ ብዕራቸው ውጤት “መጽሐፈ መሠረት” በሚል ርእስ ለኅትመት ብርሃን በቃ።

ይኼን መጽሐፍ የማዘጋጀት እድሌን አደንቃለሁ። ከፈቃደ እግዚአብሔር ጋር ይኼ ኃላፊነት ወደ እኔ እንዲመጣና እኔም በልዩ ትኩረት እንድፈጽመው ያደረጉኝ ክስተቶች ግን አሉ። በሕይወተ ሥጋ ሳይለዩን የአብነት ትምህርት የምስክር ወረቀት ከሰጧቸው የመጨረሻ ልጆቻቸው ማካከል አንዱ መሆኔ ፣ የመጨረሻ የጉባኤ ስብከታቸውን ያደግሁበትና በሰ/ት/ቤት አመራርነት ያገለገልኩበት ደብሬ ባዘጋጀው የኅዳር ሚካኤል ጉባኤ ላይ ጋብዣቸው ያስተማሩ መሆኑ ፣ በመጨረሻ በግል ሄጄ የተቀበልኩት የ”ዕዳ አለብህ” ቃላቸው ፣ የጊዜ ዕረፍታቸው የዓይን እማኝነት ዕጣ ከመንፈስ ልጆቻቸው መካከል እኔ ጋር የወደቀ መሆኑ በአጋጣሚ የሆነ አይመስለኝም።

ይልቁንም ዜና ሕይወታቸውንና ሥራዎቻቸውን ይዞ የወጣው የዳረጎት ልዩ ዕትም ዋና አዘጋጅ መሆኔ እኔ በግሌ ካሰባሰብኳቸው ሰነዶች በብዙ እጥፍ የሚበልጡ የልዩ ልዩ ዘመን አበርክቶአቸው እጄ እንዲገባ ምክንያት ሲሆን አንድ ላይ ሰብስቦ መጽሐፍ የማድረግ ሐሳብ ተፀነሰ። በፈቃደ እግዚአብሔርም እዚህ ደረሰ።

መጽሐፉ ሦስት አበይት ምእራፎች ያሉት ሲሆን በመጀመሪያው ምእራፍ ለኮርስ ስልጠና የተዘጋጁ ወጥ ሥራዎች ቀርበዋል። በሁለተኛው ምእራፍ በልዩ ልዩ ጉዳዮች ላይ በጽሑፍ ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች በጽሑፍ የሰጡትን ምላሽ ይዟል። የመጨረሻው ምእራፍ የሕይወት ታሪክ አምድ ሆኖ የግላቸውን የጉባኤ ቤት ቆይታ በወፍ በረር ፣ ለስንክሣርና ግብረ ሕማማት መተርጉም ወዳጃቸው ለሊቀ መዘምራን ላእከ ማርያም ወልደ ኢየሱስ የጻፉትን በቅኔ የተዋዛ ጽሑፍ ፣ እንዲሁም ዜና ሕይወታ ለማርያም ድንግልን አካቷል።
በቅጽ አንድ የተካተቱት ሥራዎቻቸው ለኅትመት በሚበቃ ምሉዕነት ስለተገኙ ብቻ እንጂ በቀጣይ ተሟልተው የሚዘጋጁ ብዛት ያላቸው ርእሰ ጉዳዮች እንደሚኖሩ ይታወቅልኝ።
በተረፈ ስለ ብዕራቸው የሥነ ጽሑፍ ውበት ፣ የምሥጢር ጉልበትና የሐሳብ ፍሰት እየተነተኑ ሊቁን ለእናንተ ማስተዋወቁ አስፈላጊ አልመሰለኝም። “ከፍሬያቸው ታውቋቸዋላችሁ” ይላልና ቃሉ ከፍሬያቸው ዕወቋቸው። የቻልኩትን ያህል ለቅሜ በያዛችሁት ቅርጫት አኑሬላችኋለሁ። የተባረከ ማዕድ ይሁላችሁ።
https://www.instagram.com/p/CqYPYpXIA4T/?igshid=MDJmNzVkMjY=

Instagram

150 likes, 5 comments - ከሣቴ ብርሃን (@dn.\_dr.\_kesatebirhan) on Instagram: "እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለ...

እኔና የቆሎ ጓደኞቼ የአብነት መምህራችን መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሠረት ተሰማን ቢያንስ በወር አንደዜ “ለምን መጽሐፍ አይጽፉም?” የሚል የልጅነት ቅንዓት ፣ …
1 year, 1 month ago
Daregot Media
1 year, 2 months ago
«ተዋሕድዋ» - ኦርቶዶክስ እና አድዋ

«ተዋሕድዋ» - ኦርቶዶክስ እና አድዋ
+++++++++++++++++++++++++++++++
ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው።
👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs

1 year, 2 months ago

Watch "ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል" on YouTube
https://youtu.be/7_6A_kMAvSs

YouTube

ተዋሕድዋ - የአድዋ ድል እና ተዋሕዷዊ ገድል | Victory Of Adwa and EOTC

ይኽ ጥናት ቀመስ አድዋዊ ጽሑፍ ከሦስት ዓመት በፊት የዳረጎት ዲጂታል መጽሔት ላይ የወጣና ዛሬ ለ127ኛው የዓድዋ ድል መታሰቢያ በጸሐፊው ተተርኮ የቀረበ ነው። #eotc #adwa #victoryofAdwa

1 year, 3 months ago

#ስለምንታገልለት_ዕውቀት_ይኑረን

ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ በKesatebirhan Ze Tewahdo Telegram Channel በLive stream በሰሞናዊ የቤተ ክርስቲያን ትኩሳት መነሻነት መታወቅ ያለባቸውን መሠረታዊ ነጥቦች እንማማራለን።

#የሚነሡ_ጉዳዮች

  1. ዶግማ ፣ ቀኖና ፣ ትውፊት ምንድናቸው? ዶግማ ፈረሰ ፣ ቀኖና ተጣሰ ፣ ትውፊት ተፋለሰ ሲባል ምን ማለት ነው። ቅጣቱስ ምንድን ነው?

  2. ምሥጢር ክህነት ፣ ምን? ለምን? እንዴት? ፣ ክብረ ክህነት።

  3. መፈንቅለ ክህነት በዘመነ ሙሴ ፣ የደብተራ ኦሪት ግርግርና መዘዙ

  4. አቤሴሎማዊነትና ዖዝያናዊነት በቤተ ክህነት

  5. የጵጵስና ታሪክ በኢትዮጵያ

  6. የጳጳሳት ስም ፣ ብፁዕ አቡነ እገሌ መባልና የስም ለውጥ የአስኬማ ፣ የጽሕምና የልብሳቸው ፣ የበትራቸውም ምሥጢርና ውክልና

  7. ኦርቶዶክስ በኦሮሞ ታሪክና ፖለቲካ መነጽር

  8. የአሁኑን ፈተና እንዴት እንመልከተው? እንዴትስ እንመክተው?

#ሰዓት_ከምሽቱ_3_ሰዓት

#ዕለታት_ቅዳሜና_እሑድ

የስሜት ብቻ ሳይሆን የዕውቀትም ጦር ዕቃ ለውጊያው ያስፈልገናል።

#ሊንኩን ተጭነው የChannelu Member በመሆን ይጠብቁ።
👇👇👇👇👇👇👇

https://t.me/KesatebirhanZeTewahdo

Telegram

Kesatebirhan Ze Tewahdo

ይህ የዲ/ን ከሣቴብርሃን ግጥሞች፣ወጎች፣ትረካዎች፣ተውኔቶች ፣ ስብከቶችና ወረቦች የሚተላለፉበት ሕጋዊ ገጽ ነው። እናንተም ከመንፈሳዊ አቅርቦቶቹ እንዲቋደሱና share በማድረግ ሌሎች እንዲያቃምሱ ጋበዝንዎ። "ዘመኑን እየዋጃችሁ፥በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።"ቆላ.፬፥ የዩቲዩብ ቻናል ***👇*** https://youtube.com/channel/UCH5c3LZnu5c-cVbPT0ZI-rg

[#ስለምንታገልለት\_ዕውቀት\_ይኑረን](?q=%23%E1%88%B5%E1%88%88%E1%88%9D%E1%8A%95%E1%89%B3%E1%8C%88%E1%88%8D%E1%88%88%E1%89%B5_%E1%8B%95%E1%8B%8D%E1%89%80%E1%89%B5_%E1%8B%AD%E1%8A%91%E1%88%A8%E1%8A%95)
1 year, 3 months ago

☝️☝️☝️☝️
አበው አቶ ሳይባሉ የተሠራ መሆኑን አስባችሁ አዳምጡት። ድንቅ ሥራ ነው👏👏

1 year, 3 months ago

https://youtu.be/A0vAHZEBgEs

YouTube

ዘማሪ ዳንኤል ጥበበ ሥላሴ - "ምነው አበው ምነው?" || አዲስ ወቅታዊ ዘለሰኛ መዝሙር

ዘማሪ ዳንኤል ጥበበ ሥላሴ በወቅታዊው የቤተክርስቲያናችን ጉዳይ የዘመረው ዘለሰኛ መዝሙር ነው፡፡ ይህ ዝማሬ ሦስቱ ሿሚ አባቶች ሥልጣነ ክህነታቸው በውግዘት ተገፎ አቶ አካለ ወልድ ከበደ ፣ አቶ አሰፋና አቶ አራርሳ ከመባላቸው በፊት የተዘጋጀ ሥራ እንደሆነ ማስገንዘብ እንወዳለን። #orthodoxmezmur #eotc #abunemathias የዘማሪ ዳንኤል ጥበበ ሥላሴ ሕጋዊ የዩቲዩብ ቻናል ሲሆን ዝማሬዎቹን…

1 year, 4 months ago

Watch ""ትጉኃን የአምኑ ልደቶ - ትጉኃን ልደቱን ያምኑታል" - ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት" on YouTube
https://youtu.be/z-d4xuntJBE

YouTube

"ትጉኃን የአምኑ ልደቶ - ትጉኃን ልደቱን ያምኑታል" - ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት

ድንቅ ሊደመጥ የሚገባው የልደት መልእክት መምህር ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገብረኢየሱስ (ዶ/ር) New Ethiopian Orthodox Sibket by deacon doctor kesatebirhan Gebreyesus #eotc #newmezmur #sibket

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago