Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ሱመያ-ስርሞላ(Sumi-ser)

Description
እየሞከርኩ ነው!
Advertising
We recommend to visit

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹
ሁለተኛው ቻናላችን👇
https://t.me/+TmHVOxLVNmVIaTa3


For promotion and Advertisements
👉 @Mussegirma

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን🤝
Admin
@Aymu_xo

OLDIES_MUSIC_BAND የድሮ እና የቆዩ ዘፈኖችን ብቻ በመልቀቅ አባላቶቹን ፈታ እያረገ የሚገኝ የመጀመሪያው አንጋፋ የሃገራችን ቀደምት እና ብቸኛው ቻናል ይህ ነው

አስተያየታችሁን በዚህ ላኩልን
@NATI_Z_LAST_KING

3 months ago
ያላወቁትን መንገድ መጓዝ ክብደቱ እግር ላይ …

ያላወቁትን መንገድ መጓዝ ክብደቱ እግር ላይ ሳይሆን ጭንቅላት ላይ ነዉ።"እደርስ ይሆን?" "ልክ ባይሆንስ?" "መጨረሻዉ እሾህ ቢገጥመኝስ?"....ስንል ስንል ለስንት ዳገት እና ቁልቁለት ነሽጦ የሚዘረጋዉን እግር ገና በ ኮረብታዉ አይምሮዋችን ላይ በተበተብነዉ የፍርሀት ድር ጠቅልለን እንይዘዋለን።ግድ የለም...ኮረብታዉ ላይ ተቀምጦ ከ ማላዘን ከ ተራራዉ ጫፍ ቆሞ ቀጣዩ መንገድ እሾህ እንደሆነ ማየት ይሻላል።ቢያንስ ያ መንገድ እንደማያስቀጥለን አዉቀን አቅጣጫ እንድንቀይር........

በጠራራ ፀሀይ በእኩለ ቀን
ቀኔን ሳጨልም በሀሳብ ሰቀቀን
በፍርሀት ካብ እግሬን አዝዬ
ፀሀይ እያለች  'ባይነጋስ?' ብዬ
በርቆብኝ ቀረ መዳረሻዬ!

ልነሳ ደሞ
እግሬን ልበጥስ ከታሰርኩበት
ሰበብ እስካለኝ
ይደርሳል እና መድረስ ካለበት!

4 months, 1 week ago
ወጣቱ ተጨንቆ በዝግታ ወደ ሸሁ ወንበር …

ወጣቱ ተጨንቆ በዝግታ ወደ ሸሁ ወንበር ተጠጋ።

"ምን ገጠመህ ልጄ?"

"ያ ሸይኽ ምን መሰልዎት... አሏህን ለረጅም ጊዜ ስለምነው የነበረ አንድ ዱዓ ነበር።ግን እስካሁን ምላሽ አላገኘሁም። ምን ላድርግ?"

"በድብቅ ለራስህ የምታደርገውን ዱዓ፤በተመሳሳይ ለ ቅርብ ወዳጅህ አድርግለት።"

"ምን ነካዎት ያ ሸይኽ?"

"ምነዉ?"

" ኢክራምን እሱ እንዲያገባት ነው እንዴ ፍላጎቶ🙄?"

4 months, 3 weeks ago
በገሃድ የምንስቀው ሳቅ ፤ ተሸሽገን የምናነባው …

በገሃድ የምንስቀው ሳቅ ፤ ተሸሽገን የምናነባው እምባ ነው የሚያጠነክረን።

የሳቀ ... የፈካ እና ጥርሱን ያሳየ ሁሉ ህመም የለውም ማለት አይደለም ። ሁሉም በአቅሙ የሚያለቅስበት ጉድለት አለው።

ዝም ያለ ... ያልተፍነከነከ እና ያልሳቀ ደግሞ ሁሉም ነገር አልጎደለበትም። በራሱ ልክ ልቡ የምትደሳበት ነገር አለው።

ትልቁ ጉድለት የተሰጠንንም የተነጠቅነውንም ለምን እንደ እከሌ አልሆነም ማለት መጀመር ነው።

እንስቃለን። እናለቅሳለን። የተሰጠንን በተሰጠን ልክ እንኖረዋለን። ሳቃችንም ለቅሷችንም የኛ ነው!

Muna Abduselam Mu

4 months, 3 weeks ago
በ ብዙ መዋከብ ዉስጥ ስላጣናቸዉ ማንነቶች …

በ ብዙ መዋከብ ዉስጥ ስላጣናቸዉ ማንነቶች ፣ ለአንዳንድ ሰዎች ስንል ስለሰበርናቸዉ የግል መስመሮች ፤ ለ ጥቂት ሁኔታዎች ስንል በጭንቀት ስላጣበቅናቸዉ ነፍሶች..... እራሳችንን ተጠራጥረን ስላኮራመትናቸዉ ህልሞች ፣ ተስፋ ስለቆረጥንባቸዉ ለሊቶች...... ብቻ ብቻ ስለሁሉም

"رفعت الأقلام وجفت الصحف ".
እንደሚሉት ማበርቻ ቃል አይገኝም።በእርግጥ ብእሩ ስለተነሳ ቀለሙም ስለደረቀ መጨረሻ ስለምን ትቆዝማለህ? ስላለፈዉ እራስህን ይቅር በለዉ....ስለ ሚመጣዉ አቻ በማይገኝለት ፀሀፊ ተከትቧል እና ግድየለም እመነዉ።ለምትፈልገዉ ነገር እስከ መጨረሻዉ ታገል።አትስነፍ።የተፃፈዉ አንተን ላያጣህ ግን አትጨነቅ።

ህይወት በሁለቱም balance ስታረግ ነዉ መሀል የምትረግጠዉ

እናልህ በዱአክ አደራ......

5 months ago
ሂንድ የዑበይዲላህ ባለቤት ነበረች። በሞተ ወቅት …

ሂንድ የዑበይዲላህ ባለቤት ነበረች። በሞተ ወቅት “የርሱን ፊት ለማየት ቂያማ ይናፍቀኛል” አለች።
ኢብኑ ዐሳኪር  [ሙኽተሰር ታሪኽ ዲመሽቅ] መፅሀፍ ላይ እንዲህ ብለው አስከተሉ« ስለ ናፍቆት ከተባሉት ሁሉ ጫፍ የደረሰው ይህ ነው።»

እ'ልቤ ላይ
ለ አይኖቼ እሩብ ጉዳይ
ተስለህበት ብትታይ
ላትመጣ ብትናፍቀኝ....
ቀፈፈኝ!

ይህ አለም ኩታንኩት አዝሎ
ያላንተ ዳኢም ላይሞላ..
ፍርዱ ቀን አይደርስም ቶሎ?!

የፍቅር ጥግ

6 months, 3 weeks ago

' አይደለም አንቺን የመሰለች ልእልት ይቅርና እኛም ከዛሬ ነገ አንዱ ይወስደናል በሚል ተስፋ እየኖርን ነዉ።" ካልኳት በኃላ ለረጅም ሰአት ተክዛ ነበር።
"ባክሽ አንዳንዴ ቆንጆ መሆን ደስ አይልም።"
አለቺኝ ከትካዜዋ ተመልሳ።ልእልት ስል ባሳንስ እንጂ አላጋነንኳትም።እያንዳንዱን ሰዉነቷን ለቅሞ ነዉ የሰራት።አስተሳሰቧም ኪሷም ሙሉ ነዉ።ያያት ካለፋት ወይ ተወስዳለች ብሎ አሊያ ፈርቷት ነዉ እንጂ በጭራሽ!

'አየሽ! ህይወትሽ ዉጥንቅጡ የወጣ እና የደበዘዘ መልክ ቢኖርሽ ወዳንቺ የመጣዉ ሰዉ አፍቅሮሽ እንደሆነ እርግጠኛ ነሽ። "ቢያፈቅር እንጂ ከኔ ሌላ ምን ይተርፈዋል? " ብለሽ አምነሽ ልብሽን ታስረክቢያለሽ።መሰበር አያስጨንቅሽም።ብዙ ነገር ሲኖርሽ እና የብዙ አይን ማረፊያ ስትሆኚ ግን ሀሳብሽ እልፍ ነዉ።'አፍቅሮኝ ይሆን?'....' ወይስ ከኔ የተሻለ እንደማያገኝ አስቦ?'....' በ ጭንቅላት ካልኩሌሽን ተመኘኝ ወይስ የእዉነትም ከነፍሱ ስር ከትሚያለዉ?'.....ብቻ ብዙ ያስብልሻል።እና.....እሄኛዉም ወዶኝ አልመስልሽ አለኝ።ልቡ ዉስጥ ስለቀበራት ሴት እሱ ባይነግረኝም አይኑ እየዋሸኝ አይመስለኝም።ከልቡ ጋር ስለገጠመዉ ሙግት፣እኔ ዉስጥ እሷን ስለፈለገበት ቅስፈት....አይነግረኝ ነገር "እቺን የመሰለች አጊኝተህ?"በሚሉት ሰዎች አፍ ታስሮ ላይተወኝ ይጋጋጥ ይዟል።አይኖቹን አይቻቸዋለዉ' አለቺኝ የቀረረ እንባዋን እየጠረገች።

ለካ የጎደለበት ባይመስለዉም መሙላት እራሱ ፈተና ነዉ።እቺ ዉጥንቅጥ አለም🙇

10 months ago
ከቀናት መሀል...እንደ ቀልድ "ተወከልቱ አለላህ!" ብላችሁ …

ከቀናት መሀል...እንደ ቀልድ "ተወከልቱ አለላህ!" ብላችሁ የነካካቹት ነገር... ተዓምር በሚመስል አህዋል አብቦ ፍሬዉን ስታዩት.... ከቀልብ ላልደረሰ የምላስ ተወኩል.......ምላሹ እልፍ ሲሆን

"ሱብሀነክ" ተብሎ በራስ ይታፈራል እንጂ ምን ይባላል!

ጉዳዩ አንድ ጊዜ ደጋ ላይ ረሀብ የሸቀሸቃቸዉ ሸሁ
"በድርቅ ለተራቆተዉ ህዝብ ቆላ ላይ ዳቦ እየታደለ ነዉ" ቢባሉ ጊዜ ደረሳቸዉን አስከትለዉ ቆላ እንደተመሙት ነዉ።ታያ መንገዱ ጉልበቱን የፈተነዉ ደረሳ "ያሸህ ግን ይሄ ዳቦ ባይኖርስ?" እያለ ልቡን ቢያሸብር.. አላህን በመመካት ልባቸዉ የደነደነዉ ሸህ ዘወር ብለዉ" ልጄዋ...ነፍስህን አታስጨንቃት። ከሰበቡ አይጉደል እንጂ ከሰጪዉ አያጠያይቀንም!" አሉት እና ልቡን ሞልተዉት ቀጠሉ ይባላል።እና ምን ልል ነዉ... በአላህዋ ይሁንብኝ!... ተላኪዉ ማንም ይሁን ማን ላኪዉ ላይ የተመካ ሰዉ ስለ ሰጪዉ አያጠያይቀዉም !

10 months, 2 weeks ago

ምናልባት ጥቅመ ቢስ እንደሆንሽ እየተሰማሽ ይሆናል።ምናልባትም ጠዋት ከ እንቅልፍሽ እንደነቃሽ "what the hell i am doing ቆይ? " ከሚያስብል ህይወት ዉስጥ እየዋኘሽ ነዉ። ቆም ብለሽ ግን "ምንሆኜ ነዉ እንዲህ ማስበዉ?" ብለሽ ታዉቂ ይሆን?

መልስሽን ስሚልኝ።በ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር 1971 ነዉ አሉ።ስታንፎርድ ዩኒቨርስቲ ጥናት ሊያረግባቸዉ የመለመላቸውን ሰዎች ይዞ ወደ እስር ቤት ወሰዳቸዉና ለተወሰነ ጊዜ ግማሹን እንደ እስረኛ ቀሪዉን ደሞ እንደ ጠባቂ እንዲያስመስሉ አድርጎ አስቀመጣቸዉ።ቀናት በነጎዱ ቁጥር ግን "አ'ጃኢብ! " ከማስባል አልፎ "አረ በቃ!" ብለዉ ጥናቱን እርግፍ አርገዉ እንዲተዉት ያስገደዳቸዉ ዉጤት ተፈጠረ።ምን ይመስልሻል? ቀን ቀንን በተካ ቁጥር አስመስል ያሉት ዘበኛ የምርም ቁጡ እና ሀይለኛ የሆኑ በሀሪዎችን ከማሳየት አልፎ የማይሆን እንቅስቃሴ ማሳየት ሲጀምር እስረኛ ያስመሰሉት ታሳሪ ደሞ በተራዉ ጠባቂዉ ለሚለዉ ነገር ሁሉ ከልቡ አምኖ መገዛት አልፎ የጭንቀት ምልክቶችን ማሳየት ስለጀመረ ነበር።
እና ምን ብሎ ጥናቱ ተደመደመ?አካባቢያችን ላይ ያለዉ አየር ይዋል ይደር እንጂ በልቦቻችን ላይ ከፍተኛ ለዉጥ ማስከሰቱ አይቀርም።እኛ እንደዛ ባንሆን እንኳ።በ አንቺኛ ሲገለፅ ደሞ ሁሌ እንደማትረቢ የምታስቢበት env't ዉስጥ እስከጠለቅሽ ድረስ ጠዋት በደስተኛ መንፈስ ነቅቶ መቀጠል ዘበት ነዉ።

ግድየለሽም! አንዴ ቁሚ እና ያለሽበትን ቃኘት ቃኘት አርጊ.....ማንበብ ስትጀምሪ "ኡኡቴ ከመቼ ጀምሮ ሚገባሽን! ፊደሎቹ አልጠፉብሽም እንዴ?" ብላ ሞራልሽን.. እስቲ ልስተካከል ብለሽ ስትሰግጂ ደሞ "ቂያማ ልትቆም ነዉ አሉ እንዴ!" ብላ ቅስምሽን የምታጋድም ጓደኛ ትታይሻለች? አምልጫት! ስንት ነገር እንዳላደረግሽለት ከሚገባሽ እሩብ ቦታ እንኳ የማይሰጥሽ መስሪያ ቤት ዉስጥ ነሽ?ከቦታዉ ጥርግ በይ! እሚመጥንሽን ቦታ ገንቢ። አካባቢሽን ሳታፀጂ አላህዬ ምናለ ብትቀይረኝ እያልሽ አታማሪ።

" ለእርሱ (ለሰው) ከስተፊቱም ከኋላውም በአላህ ትዕዛዝ (ከክፉ) የሚጠብቁት ተተካኪዎች (መላእክት) አሉት፡፡ አላህ በሕዝቦች ዘንድ ያለውን ጸጋ በነፍሶቻቸው ያለውን (ኹኔታ) እስከሚለውጡ ድረስ አይለውጥም፡፡ አላህም በሰዎች ላይ ክፉን በሻ ጊዜ ለእርሱ መመለስ የለውም፡፡ ለእነርሱም ከእርሱ ሌላ ምንም ተከላካይ የላቸውም፡፡" አር-ረዕድ (13: 11)

እና ተለወጪ።መለወጥሽኝ በሚመጥንሽ ቦታ ከመገኘት አስጀምሪዉ።እርግጥ አንዳንድ ቦታዎች ለመፀዳት ይከብዳሉ።እነሱን በዱአሽ በደንብ አጅቢያቸዉ።ቀና ስትዪ የሚኮረኩም ማንኛዉም area ካየሽ እና ምትችዪ ከሆነ ጊዜ ሳታጠፊ ጥለሽዉ ዉልቅ በይ! እመኚኝ መጥፎ ሀሳቦችሽም ያለ እነሱ ከ ዱአሽ ጋር ከልብሽም ከህይወትሽም ዉልቅ ይላሉ!

11 months, 1 week ago

"ምንድን ነበር ህልምሽ?"

አለቺኝ ልትጋብዘኝ ቃል የገባችልኝን የናና ሻይ ወደ ጠረፔዛዉ እያቀረበች።
"ቆንጆ የ ቢዝነስ ሰዉ መሆን!" ደግሜ ማሰብ አላስፈለገኝም።ፊትለፊቴ የምኞቷን እኔ ካሁኗ እኔ ጋር እያወዳደርኩ ከንፈሬን መጠጥኩ።

ሰሙ የ እህቴ ጓደኛ እና የ የሳይኮሎጂ ምሩቅ ናት።ሰበቡን በማልደራደርበት የ ናና ሻይ አርጋ ጠራቺነኝ እንጂ እህትየዉ "እስቲ አንቺ መላ በያት...እኔስ አቃተቺኝ!" ብላት እንደጠራቺኝ ገብቶኛል።

"አሁን ምን ይሰማሻል?"

አለቺኝ ወንበሯን አስተካክላ ከተቀመጠች በኃላ

"የባከነ እድሜ፣ከሁሉም ወደኃላ የመቅረት ድባዜ..." አይምሮዬ ላይ የተከመሩ ቃላቶቼን ማዉጣት አቃተኝ።

"የተሰማሽን ሁሉ ተናገሪ...እስትጨርሺ ድረስ እሰማሻለሁ"

እንዳነቀኝ የገባዉ አይኗን ሳትነቅል አይዞሽ በሚል አስተያየት ገረመመቺኝ።

"ምኑን ላስረዳሽ ሰሙ? አብረዉኝ ቢዝነስ የተማሩ ጓደኞቼ በሙሉ አሁን የሆነ ነገር እየሰሩበት ነዉ።ሀይስኩል 'ዉይ እቺንስ ከየት ነዉ ያበቀሏት!' እምንላት ያቺ ፀባይም መልክም ጣል ያላረገባት ልጅ እንኳን ቆንጆ ባል አግብታ ሁለት እሱን አፍርታለች። ሁሉም ህይወቱ ላይ የሆነ መሰረት ገንብቶ እየለሰነ ነዉ።ያኔ አብረዉኝ ካፌ ሚሰለፉት እንዳለ ተሰልፈዉ ዉጪ ሄደዋል።ቅዳሜ እና እሁድ ፌስቡኬ እና ኢንስታግራሜ አለምን በኔ መስኮት ነዉ ሚቃኘዉ።ሁሉም ትሪፕ ላይ ነዉ።ሁሉም የሀያዎቹን adventure እያሟሟቀ ነዉ።"

በረጅሙ ተነፈስኩ።አንድ ቁምነገር ሳልሰራ ሀያዎቼን አጋምሻቸዋለዉ።

"በዲግሪሽ ስራ አገኘሽ?"
"ለምን አታገቢም?"
"ያቺ ጓደኛሽ ምን ሆነች?"
"ለምን ማስተርስ አትቀጥዪም?"
"እንዴት እስከዛሬ ከ አዲስአበባ ሳትወጪ?"
...
...
..

እነዚህ ጥያቄዎች ታክተዉኛል።እነሱን ላለመጋፈጥ ስል ከክፍሌ ሳልወጣ ዉሎ ማንጋት ደክሞኛል።ያኔ የሰለቸኝ ትምህርት እራሱ ናፍቆኛል።የተሰጠኝን አንብቤ በተቀረፀልኝ መንገድ ተጉዤ ስኬት ላይ መቆም የለመደዉ እግሬ ካርታዉ በጠፋበት ዉጥንቅጥ አለም ላይ መጓዝ አቅቶታል።

"ለምን የጀመርሽዉን ስራ አቆምሽ?"

"ፀሀፊነቱን?" ሳስበዉ ገና ሳቄ መጣ።

"የእድሜዬን ሶስት አመት ቡና ለመቅዳት ስላልተማርኩ!እኩል ተምረን ቢሮዋቸዉ ላይ ፀሀፊ ቀጥረዉ የሚሰሩ ሰዎች ፊት ቆሜ' ምንድነዉ ስራሽ ሲሉኝ 'ፀሀፊ ነኝ" ማለት ስለደከመኝ። are you getting what i said ግን?" አልኳት።ስለፈልፍ በተመስጦ እያዳመጠቺኝ መሆኑ ገርሞኝ።በአንገቷ አዎንታዋን መልሳ የቀረኝ ሀሳብ እንዳለ ሁሉ አፈጠጠችብኘኝ።

"ዉቅያኖስ ላይ እየዋኘዉ ይመስለኛል...አለ አይደል መድረሻዉዐየማይታወቅ ከንቱ ድካም።"

"የምኞቷ የ25 አመት አንቺ ምን ትመስላለች?" አለቺኝ ከረጅም ዝምታ በኃላ

"ዲኗ ላይ ጠንካራ፣ የራሷን ቢዝነስ የምትመራ፣ቆንጆ ኦፊስ እና ፀሀፊ ያላት፣በ የሀገሩ እየዞረች ድንቅ ተፈጥሮን የምታደንቅ ፣ ቆንጆ እና ወንዳወንድ ባል እና ደሞ አንድ ድንቡሽቡሽ ልጅ ያላት.."

"እያወራን ያለነዉ ስለ 25 ነዋ?" አለቺኝ ፈገግ እያለች።"ሀያዎቹ ላንቺ ምን አይነት እድሜ ነዉ?"

"አለምን ማጣጣሚያ፣ህይወትን መስመር ማስያዣ...በቃ! ገንዘብ መሰብሰብ፣የምወደዉን ማግባት፣ቤት መግዛት ፣ መዉለድ ፣ቤተሰቤን መርዳት...እንደዛ አይደል? "

" አይደለም!

ሀያዎቹ እዉቀት እና ልምድ መሰብሰቢያ ጊዜ ነዉ።የመንገድሽን ጥግ ሳታቂ በድፍረት የምትጓዢበት፤ የምትፈልጊዉን ስራ ለማግኘት የማትፈልጊዉን ስራ የምትጋፈጪበት ፤ የምትወጂዉን ሳይሆን የምትስማሚዉን የምታገቢበት ፤ ገንዘብሽን እና ጊዜሽን የሰጠሽዉን ስራ የምትከስሪበት፤እንክት ብለሽ የምትወድቂበት፤ከዉድቀትሽ የምትማሪበት፤ተመልሰሽ የምትነሺበት ነዉ። belive me ዛሬ የዘራሽዉ እያንዳንዱ ስንዴን ነገ ማሳ ሆኖ ታጭጂዋለሽ።"

"እና ምን ላድርግ?ካርታ የሌለዉ ቦታ እንዴት ነዉ ሚጎበኘዉ?"

"ቱሪስት ነዉ የመጣዉ እነዛን ቦታዎች ለመቃኘት ብቻ ስለሆነ ሚጎበኘዉ።መንገደኛ እያንዳንዱን እርምጃ explore ነዉ ሚያረገዉ።በእያንዳንዱ እርምጃ የነከሰችዉን ጉንዳን አክሞ ፣ ሲጠማዉ ያጠጡትን እጅ ስሞ ዉድቀቱንም ከፍታዉንም እያጣጣመ ነዉ ሚጓዘዉ።አንቺ መንገደኛ እንጂ ቱሪስት አይደለሽም። "

"ግን ከምን እንደምጀምር እራሱ እኮ አላቅም ሰሙ።የቱ ጋር ነዉ የቆምኩት? ምንድነዉ ማድረግ ያለብኝ?"

"ማወቅ አይጠበቅብሽም እያልኩሽ ነዉ።ሁሉም ለመታየት እያስመሰለ እንጂ ህይወቱ 100% የገባዉ የለም።ይሄ የራስሽ መንገድ ነዉ።ወደ ስራሽ ተመለሺ።ወደ ማርኬቱ ምታድጊበትን መንገዶች ፈልጊ።አዲስ ሰዉ ተዋወቂ።የምታዉቂያቸዉን ሰዎች ለእርዳታ እጅሽን ለመዘርጋት አትፈሪ።አሁን የማፈሪያ እና የመፍሪያ እድሜሽ ላይ አይደለሽም።ብዙ ስራ ሞክሪ።ዉደቂ።በእርምጃዎችሽ ተማሪበት።ስትሞክሪዉ ነዉ ሚሳካልሽ።ያልሞከርሻቸዉን እድሎች 100% አጥተሻቸዋል።ሌላዉ ቢቀር የ ሀያዎችሽ ማብቂያ ላይ ቆንጆ ባል እና ስራ እንደ መና እንዲወርድላት እየጠበቀች ከጨረሰችዉ ልጅ ይልቅ የህይወቷን ጥሪ ለመሙላት እየተጋች ብዙ ልምዶችን የተካፈለች ሴት ትሆኛለሽ።ሰላሳዎችሽ ላይ የምትነግሪዉ የራስሽ ታሪክ ይኖርሻል።ህይወት ላይ ደሞ ወድቆ መነሳት ካለመዉደቅ በላይ ጠአም አለዉ።"

ለመጀመሪያ ጊዜ የሆነ ነገር ብልጭ አለልኝ።መንገዴን ሳላዉቅ መጓዝ እንደምችል...ለመራመድ እግር እንጂ ካርታ ግዴታ እንዳልሆነ

"ነገ እደዉልና ካላባረሩኝ እመለሳለሁ።" አልኳት።

1 year, 5 months ago
ምን ልልህ ነዉ?

ምን ልልህ ነዉ?
ትላንትና. . . . . . . .
ተወግቼ ስለቆሰልኩ
ከማጡ ስር ስለጣልከኝ
ተገልዬ ስላለቀስኩ
አደናቅፈህ ስላቆምከኝ
እግሬን ሰብረህ ስላዳከኝ

ደግ አረከኝ!
እንዴት አልከኝ?

ባትጥለኝ
በቀላሉ ሚዝል ክንዴ
በምን ሀይል ሊገሰግስ?

ባልቆም ኖሮ
ያልሄድኩትን አዲስ መንገድ
በምን ጉልበት ልጠነስስ?

ባታነክተኝ
በመዳህ ዉስጥ ያለን መጓዝ
ማን ሊነግረኝ በለሆሳስ?

We recommend to visit

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹
ሁለተኛው ቻናላችን👇
https://t.me/+TmHVOxLVNmVIaTa3


For promotion and Advertisements
👉 @Mussegirma

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን🤝
Admin
@Aymu_xo

OLDIES_MUSIC_BAND የድሮ እና የቆዩ ዘፈኖችን ብቻ በመልቀቅ አባላቶቹን ፈታ እያረገ የሚገኝ የመጀመሪያው አንጋፋ የሃገራችን ቀደምት እና ብቸኛው ቻናል ይህ ነው

አስተያየታችሁን በዚህ ላኩልን
@NATI_Z_LAST_KING