ሱመያ-ስርሞላ(Sumi-ser)

Description
እየሞከርኩ ነው!
We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 8 months, 2 weeks ago

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo

1 month, 2 weeks ago

ረመዳን ሙባረክ!
.
ጨረቃ ታይታለች። ረመዳንም ነገ 1 ሆኗል። የረመዳን ፆም የተራውሂ ሰላት ደግሞ ዛሬ ጁሙዓ ከኢሻ ሰላት በኋላ ይጀመራል።

አህለን ቢከ ያ ረመዳን😍

.

1 month, 3 weeks ago
"ምን አጋፋሽ?

"ምን አጋፋሽ?
በገዛ እጅሽ ምን አስከፋሽ?
እንደ ሁሉም
በተሰራ መንገድ መሀል
ሽዉታ ሆኖ እንደመዋል
ለአዲስ ቅያስ ስትባዝኚ
እድፍ ወሮሽ ምትገኚ?"

እንደማንም
በተሰራ መንገድ ቁልቁል
መረማመድ ባይቸግረኝ
እዉስጤ ላይ የሚቀበር
ፀፀት ሚሉት ጠላት አለኝ...
"ባደረግኩት ኖሮ..." እያለ
በየ እርምጃ የሚጥለኝ!

1 month, 3 weeks ago
የሚመጣዉ

የሚመጣዉ
ዙሪያ ገባ አንከዋላይ
ስክነት ሰርቆ አተርፍ ባይ
ወይ ያልረጋ
ስንዝር ስትርቅ
ክንዱን ሊያሸሽ የዘረጋ
የምትሻዉ
ትንሽ እረፍት
ትከሻ ትደገፍበት
እቅፉን ትሸሸግበት
እማይፈርድ
እማይበርድ
ትነግረዉ እማትሸሽበት
እራሷን የምትሆንበት!!

የሚመጣዉ
መንከላወስ ያልደከመዉ
ነፍሷን ከነፍሷ ሚያጣላ
ግብሩ ከምላስ የላላ
ወይ ያልረጋ
ክንፉን ላገኘዉ የዘረጋ
እኔነቱን ያገዘፈ
እሷነቷን የነቀፈ
በሸዉራራ እይታዉ ልክ
ሚዛኑ የተሻንፈፈ
እንደመጣለት ሚያስካካ
ፍርዷን በ ፍርዱ ሚለካ
ይደንቃል
እሷ አለሟ ከሱ ይርቃል
የምትሻዉ
ትንሽ እረፍት
ትከሻ ትደገፍበት
እቅፉን ትሸሸግበት
እማይፈርድ
እማይበርድ
ብታጠፋ ብታለማ
ልትነግረዉ ማታቅማማ
ትለብስ ዘንድ የማይበርዳት
የእዉነትነት የሷን ሸማ
..
የልቧን ሰሚ ጀሊሉ
ነበርና ጥንትም ቅሉ
ካመሻሹ
የተስፋዋ ጠብታ ላይ
ቻይነቱን በሷ ሊያሳይ
ደሞ አመጣዉ
ያን ደግ ሰዉ
ያን የነፍሷን ፍንጣቂ
የሆነችዉ ክፋይ ወርቁ
ያካሉ ላይ ፍልቃቂ
ትደገፍበት ትከሻዉ
ትስቅበት የምትሻዉ
እማይፈርድ
እማይበርድ
ነፍሷን ከነፍሱ ሚያስታርቅ
ልጅነቷን የሚያስቦርቅ
ለሷ ይሄ
አተኩሮ ላስተዋለዉ...
ከሙሴ በትር የሚልቅ
ከፀሀይ ወግ የሚተልቅ
ተአምር ነዉ!!

ቅ ዳ ሜ ፡

3 months ago
የጠዘጠዘኝ ኑሮን ጎርሼ

የጠዘጠዘኝ ኑሮን ጎርሼ
እንባ የጨረሸኝ ዉስጥዉስጥ አልቅሼ
የሸረሸረኝ
የምድር ርብራብ
እንደ ቅልብልብ
ከወዲያ ወዲህ ያነጣጠረኝ
ሞት ሞት ሲሸተኝ
ማር ነዉ እያለ
እሬት ሲያግተኝ
ከዚህ ምስቅልቅል
ግማሽ ፈገግታህ የሚነርተኝ!!
ግማሽ ፈገግታ
ኑሮ አደካክሞት የማይረታ!!
እንኳን አልሞላህ
እንኳን ለ ሙሉ አለም አልደላህ
በሳቅህ ወጀብ
በጥርስህ መደብ
በክፋይ ብቻ
ለጋ ነፍሴ ላይ ሳቅህ ሲደንስ
ዱንያ ስትለጋኝ
በሰራችዉ ጎርፍ
ድል ቷንኳ ሰርቶ ሀሴት ሲደግስ
አስበኀዋል ሳቅህ ቢሞላ?!
ሩሄ ችላ??
እንኳን ልትችል
ከኑሮ ቀድማ በሳቅህ ፍንግል!!
አንተዬዋ...
በፈጠረህ አንተን ረቂቅ
ሞልተህ እንዳትስቅ!!
እንዳይታይ ጥርስህ ሙሉ
ለጭንቀቴ ሀሳብ ሁሉ
ክፋይህ አስማት አለበት
ደሞ
እንዲህ አለም በጀሽ ሲርቃት
ነፍሴን ጭንቀት ሲያስጨንቃት
መሞላትህ ያስፈራኛል
እንደ ሀበሻ መድሀኒት
ሲቃ ሀሴቴ
በዝቶ ሚገድል ይመስለኛል!
ብቻ ብቻ
መቆም ከብዶኝ ስንገዳገድ
በከንፈርህ ቀጭን ገመድ
ነፍሴ እንዳትነድ
ሳትሞላዉ
ግማሽ ሳቅን ወዲህ ስደድ!!
(ሳቅህ እና ይሄ አበባ)

3 months, 1 week ago

There are days that i say

"ኦ አላህ !
እነዚያን የለመንኩህን ሁሉ ሰጥተኸኝ ቢሆን ኖሮስ ?
What would my life look like?
አልሀምዱሊላህ ።"

3 months, 1 week ago

"ትወጂዉ የለ?"
"እና?" አልኳቸዉ።ደነገጡ።"እሱማ..." ብዬ እንደልማዴ ምቅለሰለስ መስሏቸዉ ነበር።

"እና?? እና ምን ማለት ነዉ? በቃ ልትፈቺዉ ነዉ? ምን ነካሽ ልጄ!
ልጅሽስ?
በይ ተማርኩ ተማርኩ ስትዪ አጉል ዘመናዊነት አያጥቃሽ።ደሞ
ባልን እንዳመሉ እየሸመገሉ መኖር ነዉ የ ሴት ወግ!
እንደዉ ገና ለ ገና መታኝ ብለሽ ቤትሽን ልትበትኚ???"

እንደ ሁልጊዜዉ ጎረቤቶቻችንን ሰብስቦ ሽምግልና ልኮ መቀመጣቸዉ ነዉ።ያኔ እንደዛ ሲሰድበኝ ፤ አንዴ ስራዬን ፣ አንዴ ቤቴን ፣ አንዴ ልጄን ፣ ብዙ ጊዜ ስድቡን እና ዱላዉን ሽሽት እየተክለፈለፍኩ ስውል የቀጠቀጠኝ ማግስት ተሰብስበዉ መጥተዉ

" 'እንደ ድሮ አትዘንጥም' አለን እኮ!
'ስመጣ በተቀደደዉ ሺቲዋ ነዉ ማገኛት' አለ ስናወራዉ..... እንደዉ ልጄ ወንድም አይደል? ቤቱን ሊሞላ አይደል ሚለፋዉ? አይኑ ብዙ ቀላዉጦ ስለሚመጣ እንደምንም ታጥበሽ ልብስ ቀይረሽ ብጠብቂዉ እኮ ደስ ይለዋል...ጎሽ!....እንደ ሴት እንደ ጥበብሽ ያዝ አርጊዉ እስቲ..." ያሉኝ። ሲደበድበኝ ያገላገሉኝ።

እጄን በ አፌ ጭኜ ያቺን አስቤዛ እና የቤት-ኪራይ መክፈል ለዚህ ሁሉ ነገሩ መሸፈኛ መሆን መቻሉን ሳይ ግርምም ድንግጥም ያረገኛል።እንደዉ ረብጣዉን ቢያዘንበዉ እራሱ የዚህን በደል ይሸፍነዋል? አረ እንዴት ማባበል ቻሉበት?

በእርግጥ አልዘንጥም!!
ሳያገባኝ በፊት የነበረኝ ሊፒስቲክ ሲያልቅ ጠይቄዉ 'አሁን ያለሁበትን ወጪ እያየሽ!" ሲለኝ ከሱ አይበልጥም ብዬ ትቻለዉ።ደግሜም አላነሳዉ።ልብስም ቢሆን ቤተሰቦቼ ጋር ቤተሰቦቹ ጋር ስሄድ እንዳላሳጣዉ እያልኩ ከሽንኩርት ከ ቲማቲም እየለቀምኩ በሰበሰብኩት ቦንዳ ልቃርም እንጂ አልጠይቅም።ሁሉንም ማድረጌ ለ ፍቅሩ ነበር።አጥቼ እንኳን ማስበዉ የሱን አለመዋረድ ነበር። ሲመታኝ መታገሴ የነገ ይቅርታዉን አምኜ ነበር።

ጭቅጭቁን ፣ ስድቡን ባስክ ሲልም ዱላዉን መቀበል ሲሰለቸኝ እንደመከሩኝ ለመዘነጥ ልጄን ይዤ ወጣሁ።"ምን ጎደለሽ?" ሲለኝ ብዘረዝር ለማይገባዉ ችግሮቼ... ትቼዉ ስራዬን ቀጠልኩ።ተፍ ተፍ ብዬ ሊፒስቲኩንም ፤ ልብሱንም ሸማመትኩ።ትንሽ መለስ አልኩ።የድሮ እኔን በ ትንሽ በ ትንሹ መሰልኩ።ከዛ ጎረምሳ ያዝሽብኝ ብሎ ዱላዉን ዘረጋዉ።
ደከመኝ
ሰለቸኝ
ቆረጠልኝ!!!

ለ እዉር መፅሃፍ አይሰጡትም። ለ አይናማም ብሬል አይገባዉም።ቋንቋችን ለየቅል ፤ ሀሳባችንም በየፊናችን ሲሆን የገጠመ እስኪገኝ መታገስ እያለ ካልገጠምነዉ ካልገጠምን ሙግት ትርፉ መሰበር ነዉ።

አይሆኑ አሰባበር ፤ አይሆኑ አወዳደቅ ከሚሆን ደሞ በጊዜ መሸኛኘት እንዴት እንደሚያድን!

በጊዜ አልሄድኩም።ቆይቼም ግን አልቀርም።ስብርባሪዬን ለቅሜ ተነሳሁ።በተረፈዉ ለ ልጄ ልኑር። ከምንም በላይ ደሞ ለራሴ ልቅር!

"ታግሶ በትዳሯ ተከብራ እንደመኖር! ልጇን አባት አልባ ልታረገዉ፤ አይ የሴት ወጉ እንዲህም አልነበር! ተነካዉ ተብሎ ፍቺ??!!..."
የ ሴቶቹ ጩኀት ከጀርባ እየገፋኝ ተነሳሁ

We recommend to visit

● Welcome to Ethio music Channel

➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !

Last updated 8 months, 2 weeks ago

🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹

#ካሮት_ሙዚክ✋


ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo