የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc
?▬▱▬▱▬?▬▱▬▱▬?
ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር
መጋቢት ፪, ፳፻፲፮ ዓ.ም
ሰላም ለእናንተ ይኹን!
የተከበራችኹ ዕጩ የ፲፫ኛ ዙር የግእዝን
በርቀት ተማሪዎች እንኳን ለጌታችንና
ለመድኀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የጥምቀት በዓልና ለመልአኩ ለቅዱስ ሚካኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳችኹ።
ከዚኽ ቀደም እንደገለጽኹላችኹ በ፲፫ኛ
ዙር በቍጥር በርከት ያሉ ተማሪዎችን
ለማስተማር ያሰብኹ ቢኾንም እስካኹን
በኹለት ወራት ውስጥ 6000 የሚጠጋ
ተማሪዎች ብቻ ገብታችዃል።
የቀረው ቍጥር እስኪሞላ እንጠብቅ ብንል
ከዚኽ በኋላ ከዐሥር ወራት በላይ ልንጠብቅ እንችላለን። ይኽ ደግሞ አስቀድማችኹ የገባችኹትን ሊያሰለች /የመማር ፍላጎት ሊቀንስ/ ይችላል ብዬ ስላሰብኹ ትምህርቱን ባለው
ተማሪ መጀመር የተሻለ እንደሚኾን ተረድቻለኹ።
ዛሬውኑ ትምህርቱን ለመጀመር በኔ በኩል ዝግጁ ብኾንም ያለንበት ወቅት ክብረ በዓላት የሚበዙበት ፣ ሰርግና ሌሎች ማኅበራዊ ጉዳዮችም የሚበዙበት ነውና ተረጋግተን ለመማር ልንቸገር እንችላለን። የግእዝ ትምህርት ደግሞ የጥሞና ጊዜ ፣ የተረጋጋ ጊዜ ይፈልጋልና አብዛዎቻችን በሚባል ደረጃ የተረጋጋ ጊዜ የሚኖረን በዐቢይ ጾም በመኾኑ ትምህርታችን በጾሙ ወቅት ቢኾን ብዬ ዐሰብኹ።
በመኾኑም እግዚአብሔር ቢፈቅድና
ብንኖር የ፲፫ኛ ዙር የግእዝን በርቀት
ትምህርት የሚጀመረው ሰኞ መጋቢት
፪, ፳፻፲፮ ዓ.ም ይኾናል።
ከዚኽ ቀን ኹለት ሳምንት ቀደም ብዬ የምዝገባው ጊዜ የሚጠናቀቅበትን፣ ስለትምህርቱ ዘርዘር ያለ ማብራሪያ ፣ ከእናንተ በፊት የተማሩ ተማሪዎች ለእናንተ የሚያስተላልፉትን መልእክት አቀርብላችዃለኹ።
እስከዚያው መማር የሚፈልጉ ተማሪዎች
ካሉ የመግቢያ ሊንኩን ላኩላቸው። ቢያንስ
ኹለት ኹለት ሰው ብታስገቡ የታሰበውን
ግማሽ ያኽል ተማሪዎች ይገኛልና እንዲማሩ ሳትሰለቹ በመጋበዝ በጋራ የግእዝ ቋንቋን እንማማር ስል በትሕትና እጠይቃለኹ።
@Geezdistance13 ወይምhttps://t.me/Geezdistance13
?▬▱▬▱▬?▬▱▬▱▬?
Telegram
ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር [33,300]
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰ ሰላም ለእናንተ ይኹን! የተከበራችኹ የግእዝን በርቀት የ፲፫ኛ ዙር ዕጩ ተማሪዎች ግእዝን በርቀት በቴሌግራም፣ ባላችኹበት አገርና ቦታ ኾናችኹ መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋን ለኹለት ወራት ለመማር በፈቃዳችኹ ወደዚኽ ቡድን ተሰባስባችዃል። ይኽንን በማድረጋችኹም ለእናንተ ክብርና አድናቆት አለኝ። እስከ ፲፪ኛ ዙር ድረስ የተማሪው ቍጥር ትንሽ በመኾኑ እና ለእኔ ቍጥሩ ቢጨምርም ድካሙ…
?▰▱?▰▱?▰▱?▰▱?
**ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር
ለጀማሪ ተማሪዎች ታስቦ የተዘጋጀ፣
መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋ ትምህርትን በቴሌግራም፣ ለኹለት ወራት፣ በነጻ መማር ለምትፈልጉ ኹሉ በሚከተለው ሊንክ አማካኝነት የትምህርት መስጫውን ቡድን ትቀላቀሉ ዘንድ በታላቅ አክብሮት ተጋብዛችዃል። @Geezdistance13 ወይምhttps://t.me/Geezdistance13 ግእዝን በርቀት ፲፫ኛ ዙር
?▰▱?▰▱?▰▱?▰▱?**
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
ሰላም ለእናንተ ይኹን!
የተከበራችኹ የግእዝን በርቀት የ፲፫ኛ ዙር ዕጩ ተማሪዎች
ግእዝን በርቀት በቴሌግራም፣ ባላችኹበት አገርና ቦታ ኾናችኹ መሠረታዊ የግእዝ ቋንቋን ለኹለት ወራት ለመማር በፈቃዳችኹ ወደዚኽ ቡድን ተሰባስባችዃል። ይኽንን በማድረጋችኹም ለእናንተ ክብርና አድናቆት አለኝ።
እስከ ፲፪ኛ ዙር ድረስ የተማሪው ቍጥር ትንሽ በመኾኑ እና ለእኔ ቍጥሩ ቢጨምርም ድካሙ ተመሳሳይ በመኾኑ ከደከምኹ አይቀር በዛ ያሉ ተማሪዎችን ማስተማሩ የተሻለ ኾኖ ስላገኘኹት በ ፲፫ኛ ዙር 33,300 ተማሪዎችን በአንድ ጊዜ ለማስተማር አስቤአለኹ። ነገር ግን እንደምታዩት በአንድ ወር ውስጥ የገባችኹት ተማሪዎች 1/10 ያኽል ናችኹ። በዚኽ አካኼድ ትምህርቱ የሚጀመርበት ወቅት ሊዘገይ ይችላል።
በመኾኑም በ፲፫ኛ ዙር ለመማር የወደዳችኹ እናንተ ትምህርቱ የተማሪው ቍጥር በሞላ ጊዜ እንዲጀመር ወይንም በዐጭር ጊዜ እንዲጀመር ከፈለጋችኹ መፍትሔው በእጃችኹ ነው።
ይኸውም እያንዳንዳችኹ ዐሥር ዐሥር ተማሪዎችን በተለያዩ ማኅበራዊ መገናኛዎች ቀጣዩን መልእክት ወይም በራሳችኹ መንገድ በማዘጋጀት በመጋበዝ በዐጭር ጊዜ ቍጥሩን በመሙላት ማስጀመር ትችላላችኹ።
አኹን ያላችኹት 3562 ተማሪዎች እያንዳንዳችኹ ዐሥር ዐሥር ተማሪ ብትጋብዙ የሚፈለገው ቍጥር ይገኛል። የተማሪው ቍጥር በሞላ ማግስት ትምህርቱ ይጀመራል።
እኔ ትምህርቱን ለመጀመር ኹልጊዜም ዝግጁ ነኝ። እናንተ ተማሪን በመጋበዝ ድርሻችኹን ተወጡ።
ግዛቸው ደጀኑ
(የትምህርቱ አስተባባሪ)
ታኅሣሥ ፲፪ ፥ ፳፻፲፮ ዓ.ም
▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰▱▰
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads: https://telega.io/c/ethioalbums
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ 👉 @Abusheymc