Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 2 months ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 4 months ago
*In this beauty, calmness and stillness I was thinking of you.
What a relief it is !
It filled my heart with tremendous peace that came from wherever the Almighty God exists. I believe in God when I see you. You're my evidence!... I don't need other philosophical perplexities, YOU ARE MY PROOF!
_ Once the Sufi mystic Jalalu-din Rumi said :"Burn me as much as you want My remains will still smoke of your Love." I feel like that. You're burning me by longing and yearning for you. I'm slowly turning into ashes, but from that ash I resurrect like Phoenix as still your lover.*
*📗 Living on Your Own Terms
( :- Osho ) {ክፍል ፩}``[ የፊደል ግድፈት ስታገኙ አቃንችሁ አንብቡልኝ። የሀሳብ ግድፈት ካለ ግን ከኔ ይልቅ ደራሲውን ብትተይቁ ስል እመክራለሁ ]
`💧*
የኦሾ Life essentials series መካከል አንዱ ነው '' Live In Your Own Terms" ። እንደተለመደው ኦሾ በዚህ መፅሀፍ ውስጥ በርከት ያሉ ጉዳዮችን በድፍረት አንስቷል። እኛም እንደ አቅሚቲ የተወሰነውን ለማብራራት እንሞክራለን ። በተረፈ መጽሐፉን በማንበብ ይተባበሩን ።
....
መፅሀፉ በአጠቃላይ 5 ምዕራፎች አሉት። እኒህም፦
¹.Saying Good-bye to the Past
². Understanding Is Freedom
³. You Are Born with Courage
⁴. Create the Way by Walking
⁵. When All Voices Are Silent
የሚሉ ሲሆኑ በዚህ ፅሁፍ እያንዳንዱ ምዕራፍ ምን ምን እንደያዘ እንቃኛለን ( በወፍ በረር ነው የሚባል ? )
🦅
1.Saying Good-bye to the past
ይህ ምዕራፍ በዋናነት የ Rebellion እና የ revolution ልዩነት ይተነተናል።
revolution የፖለቲካ አብዮትን፣ አንድን ማህበረሰብ ለመቀየር፣ መንግስት ለመገልበጥ የሚደረጉ አመፆችን የሚረገልፅ ሲሆን ። Rebellion ግን ይለያል። Rebellion የውስጥ አመፅ ነው ። አንድ ሰዉ በግሉ ራሱን ለመለወጥ፣ እዉነተኛ ማንነቱን ለማግኘት የሚሄደው የራሱ መንገድ Rebellion ይባላል። Rebellion በይበልጥ መንፈሳዊ መልክ ሲኖረው revolution ግን political ነው።
ኦሾ የሁለቱን ልዩነት ለማሳየት ስለ violence ያነሳል ። revolution is full of violence but rebellion is non violence.
revolution አብዮት የምንለው ነገር ብዙ ጊዜ ከሆነ አካል ነፃ ለመውጣት (freedom from something ) እንጂ ለሆነ ነገር ነፃ ለመውጣት (freedom for something )አይምክርም። በዚህም ምክንያት አለም ላይ የተካሄዱ አብዮቶች በሙሉ ስኬታማ ሊሆኑ አልቻሉም። ለምሳሌ የኢትዮጵያን ኮሚኒስታዊ አብዮት ብናይ ህዝቡን ከሀይለ ስላሴ አገዛዝ ነፃ አወጣ እንጂ የተሻለ መንግሥት መስጠት አልቻለም። በቅድሚያ ማድረግ የጀመረው ነገር ያለፈው አገዛዝ የሰራቸውን በሙሉ ማጠልሸት ነው። revolution የሌሎች (ያልፉት) ድክመትን የራስ ጥንካሬ አድርጎ የማሰብ አባዜ ነው። በዚህም አብዮተኞቹ በዋናነት ካለፈው (ወይም አልፏል ከሚሉት ) ስርዓት ጋር በመጋጨት በዘመናቸው አንድ የራሳቸው መልካም ሳይሰሩ በሌላ ተረኛ አብዮተኛ ይገፈተራሉ። የዚኛውም እጣ ተመሳሳይ ነው።
Rebellion ግን ቀደም ብዬ እንዳልኩት ግለሰባዊ እንጂ ማህበረሰባዊ መሠረት የለውም ። አንድ rebel የሚያምፀዉ በዋናነት በራሱ አዕምሮ ላይ ነው። ይህ አዕምሮ ግን በዚህም አለ በዚያ የማህበረሰቡ ቅጥቅጥ ነው። ስለዚህም ማህበረሰብ ካስቀመጣቸው የእስራት ዘለበቶች ማምለጥ መቻል አንዱ Rebel የሆነ ሰው የሚጠበቅበት መስፈርት ነው ።
🦅
ሌላው የእዉነተኛ Rebel ባህሪ ትናንትን ቻው ማለት መቻል ነው። ትክክለኛ ማንነት የሚገኘው አሁን እዚህ በመኖር ውስጥ ነው። በትናንት ትውስታና በነገ ናፍቆት መሀል ሰዉ ህይወቱን ማጣጣም አይችልም። ህይወት የነፍስ ናት ጊዜ ደግሞ የአዕምሮ። ነፍስ ዘላለማዊ ስትሆን ይህ ዘላለማዊነት የሚገኘው ደግሞ አሁን ላይ ነው። በመሠረቱ Past and future የጭንቅላት ፈጠራዎች እንጂ እውነታ አይደሉም። ለዛ ነው The Rebel Man በየትኛውም ያለፈና የሚመጣ ጊዜ ውስጥ ሟሙቶ የማይጠፋው።
🦅
The Rebel ከየትኛውም የአስተሳሰብ እስር ነፃ ነው። ከዚ በፊት ሰዎች እዉነት ያሏቸውን በሙሉ በግላዊ ሙከራ ካላረጋገጠ አይቀበልም። የትኛውንም የፖለቲካ ideology ፣ የሃይማኖት theory አይቀበልም። እምነቱ ለመሆን አንድ ነገር የስሜት ንኪኪ ሊኖረው ይገባል። አባት እናቱ ስለተከተሉት ብቻ አንድን ሀይማኖት አይከተለም፡፡ የትኛውም ዓይነት ማህበር የማሰብና የመኖር መብቱን እስኪጋፋ ድረስ አይታገስም።
ይህን ሁሉ የሚያደርገው ግን ለመላው ዓለም ካለው ጥልቅ ፍቅር የተነሳ እንጂ እራስን አግዝፎ ከመመልከት አይደለም።
🦅
ማንኛውንም ዶክትሪን የማይቀበልበት ምክንያትም በመጀመሪያ ራሱን እንደ Agnostic ስለሚያይ ነው። አማኞች '' በእግዚአብሄር እናምናለን '' ሲሉ
ኢ-አማኞች ደግሞ '' በእግዚአብሄር አናምንም '' ይላሉ ።
አንድ Agnostic ግን ከእነህ ሁለት ፅንፎች ርቆ በትህትና " እኔ የማውቀው ነገር የለም ። ለማመንም ለአለማመንም የሚሆን መረዳት የለኝም። አሁን ላይ የማወቀው ፍለጋ ላይ መሆኔን ብቻ ነው ይላል። ኦሾ ይህንን ሀሳብ በውብ ቃላት ያስቀምጠዋል
“We do not know yet.We will search, we will see. We cannot say anything before we have looked into every nook and corner of our being.”
ለዚህ ነው The Rebel Violent ሳይሆን እንደ ህፃን ልጅ ንፁህ innocent ነው የሚለን። ከዚህ ጋር በተያያዘ ኦሾ አንዲት ተረት ይነግረናል።
🦅.....
ሁለት ልጆች ለጨዋታ ከቤታቸው ርቀው እየሄዱ ይወያያሉ
" አባቶቻችን ከያዙን ግን ይመቱናል። " ይላል አንዱ ልጅ
" እና ? ''
" እናማ እኛም መልሰን እንመታቸዋለን !"
" ግን እኮ እሱን ማድረግ አንችልም። መፅሀፍ ቅዱስ አባቶቻችሁን አክብሩ ይላል። "
" መልካም: ችግር የለውም በቃ... እኔ ያንተን አባት እመታዋለሁ አንተ ደግሞ የኔን ! "
The Rebel እንደ ልጆቹ ንፁህና የዋህ ነው እንጂ Violent አይደለም ። ምክንያቱም ይለናል ኦሾ
" Through violence you cannot achieve a peaceful, silent, loving humanity. "
The Rebel ደግሞ ሰላማዊ፣ ፀጥታ የነገሰበት፣ በሰብዓዊ ፍቅር የተሞላ ህይወት ነው ያለው ።
🦅
ህይወቱ እንደ revolutionalist በ 'No 'የተሞላ ሳይሆን ለ ' Yes 'የተበረከተ ነው ። The Rebel 'No' ቢልም የሱ 'No' የ 'Yes'ኡ ጥላ እንጂ ሌላ አይደለም። ለሌሌች ሀሳብ እምቢ ማለት ላይ ደርቆ አይቀርም ። ወደ ራሱ ሀሳብ 'እሺ ' ያተኩራል ።
እውነተኛና ትክክለኛ Rebel ስትሆኑ ይላል ኦሾ
" You are transforming their diametric oppositeness into a
complementary, organic unity. "
( ምዕራፍ ሁለት ይቀጥላል.....)`
፦ ግዑዝኤል
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 2 months ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 4 months ago