ከጠቢባን ምድር ツ •[አብዱ ሩሚ]•

Description
°| ✍ከአፍቃሪያን ገጽ በፍቅር ቀለም |°

•[ ከጠቢባን ምድር! ]•
🌴 دار الحكمآء
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

4 months ago

ሒካያ~30

ነብዩላሂ ዒሳ ዘንድ ሶስት የበኒ ዒስራዒል ሰዎች መጡ። " አንተ የአላህ 'ኩን' ቃል ሆይ! የእውነት ነብይ ከሆንክ ይህንን ክምር አሸዋ ወደ ወርቅ ቀይርልን! " ሲሉ ጠየቁት።

ነብዩላሂ ኢሳም ጥያቄያቸውን ተቀብለው  ዱዓ አደረጉ ፡ ዱዓቸውን ካጠናቀቁም ቡኋላ በያዙት በትር ክምሩን አሸዋ መታ ሲያደርጉት ወደ ወርቅ ሳንቲም ክምርነት ተቀየረ። ውስጣቸው በዱንያ ጥማት የተሞላችው ሶስቱ ሰዎች ፡ ወርቁን የግላቸው ለማድረግ ይነታረኩ ጀመር። በጨረሻም ሁለቱ በጋራ በመሆን አንዱን ገድለውት ፡ የቀረውን ለሁለት ሊካፈሉ አሴሩ። የቀረው አንዱ ሰው ደግሞ ፡ ሊያቀርብላቸው እያሰናዳ በነበረው ምግብ ላይ መርዝ ጨምሮ ሙሉ ወርቁን የራሱ ሊያደርግ ፈለገ።

ገድለውት ለሁለት ለመካፈል ያሴሩ ጓደኛሟቾቹ ፣ አንዱን ጓደኛቸውን ምግቡን ካቀራረበላቸው ቡኋላ ተባብረው ገደሉት። ከዚያም ስለሚካፈሉት ክምር ወርቅ እያሰላሰሉ ወደ ማዕዳቸው ቀረቡ። በመርዝ የተበከለውን ምግብም ተመገቡ። ብዙም ሳይቆዩ በስቃይ እያጣጣሩ ፡ ይህችን አለም ተሰናበቱ።

ከቀናት ቡኋላ ኑብዩላሂ ዒሳ(ዐሰ) የሶስቱንም ሰዎች አሟሟት አይተው " እንዲህ ናት ዱንያ ፈላጊዎቿን ምታደርገው! እንዲህ ናት ዱንያ! " በማለት ተናገሩ።

@ktebiban_meder

4 months ago

#ኸሚስ_አመሻሹ_ላይ!

የነቢን የፍቅር ድር እያደሩ፣ እንደ ጥልፍ እየጠለፉ፣ ጥለት እያበጁ፣ ቀለም እያቀለሙ ውለው የሚያድሩ የሙሐባ ሸማኔዎች አሉ። ሐያታቸውን በሸማው ተዘይነው የኖሩ። የወለላው ነብይ ወዳጅ ሰይድ ዩሱፍ ነብሃኒ (ቀ.ሲ) ነቢን ያሏቸውን የሰማን ጊዜ ጉድ ከጉድም በላይ አልን። "ያረሱለሏህ..! ያንቱ የተከበረ እግር መሬትን ባይረግጥ ኖሮ በአፈር ውዱዕ ማድረግ (ተየሙም) ማንንም ባላጠራ ነበር፡" አሉ። መገን! ታቢዒዪ ኡብን ሲሪን ስለ ዘንፋላው ነብዬ አንድ ዘለላ ፀጉር ዋጋ ሲናገሩ ምን አሉ? "የነብዬ አንዲት ቅንጣት ፀጉር እኔ ዘንድ ከብርም ከወርቅም ምድር በውስጧ ከያዘችው ማንኛውም ሃብትም ይበልጥ ውድ ነው!"
ደጋጎቹ የነቢን የኑር ስብስብ ዛት በየዘርፉ ይለብሱታል። እኩሉ ለበረካ፣ ገሚሱ ለውዴታ፣ ታማሚው ለመሻር። እንኳን ዋናውን ጥም ቆራጭ፣ አንጀት አራሽ መጠጥ አግኝተው ቅራሪውንም አያልፉት! ታቢዒዩ ሳቢት አል ቡናን ሰይድ አነስን (ረ.ዓ) ሲያገኙ "እነዚህ’ኮ ነብያችንን ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም ያዩ ዓይኖች ናቸው!" እያሉ ዓይናቸውን ይስሟቸው ነበር። "ነቢን የነኩ እጆች ናቸው!" ብለውም እጆቻቸውን አገላብጠው ይስሙ ነበር።

ሰይድ ጦልሐ የነብዩ ፍቅር ያጠቃቸው የሙሐባ እስረኛ ነበሩ። ታድያ ሰይዳችንን መንገድ ላይ ባገኟቸው ጊዜ አቅፈው ጉንጫቸውን፣ ግንባራቸውን፣ እጅ እግራቸውን ይስሟቸዋል። ነብዬላህ ይህ ፍቅር ያሳሳቸዋል። በአንዱ እለት በመዲና ጎዳናዎች ላይ ሰይድ ጦልሃን ፊት ለፊታቸው አቁመው "የኔ ጦልሐ ትወደኛለህ?" ብለው ጠየቋቸው። "በጣም እንጂ የኔው ነብይ" ብለው መለሱ። ቀጠል አደረጉና "እንዲያው ከአባትህ በላይ ትወደኛለህ?" ብለው ጠየቁ መልሱን በጉጉት እየጠበቁ። አፍቃሪና ተፈቃሪ ልማዱ ይሄው ነው። ከሁሉም በላይ መውደድ፣ ከማንም በላይ መወደድ። ይህንን ሊሰሙ ከጀሉ የኔ በሻሻ። ሰይድ ጦልሐ በአዎንታ ለጥያቄው ማረጋገጫ ሰጡ። ሰይዳችን ይህንን የፍቅር ትኩሳት ይበልጥ ሊያግሉት ከጅለው "አባትህን ሰዋልኝ ብልህስ?" አሏቸው። ሰይድ ጦልሐ መልስ አልሰጡም። ወዲያውኑ "ለበይከ ያረሱለሏህ" ብለው ፈረሳቸው ላይ ተፈናጠጡና ወደ አባታቸው መንገድ ጀመሩ። ይህን ጊዜ ሰይዳችን ወዲያውኑ ጠርተው አስቆሟቸው። በቃ እነሱ ሲያፈቅሩ እንዲህ ነው። የወደዱት ሰው ጥያቄ ትዕዛዝ ነው። የሚሰስቱት አንድም ነገር የለም ገላ ቢሆን ነፍስ። ከጥቂት ቀናት በኋላ ሰይድ ጦልሐ ታመው ተኙ። የኔ ነብይ መታመማቸውን እንደሰሙ ጣደፍ ጣደፍ እያሉ ወደ ወዳጃቸው አቀኑና ጥቂት አጫውተዋቸው ተመለሱ። ይህን ጊዜ ሰይድ ጦልሐ ለእናታቸው "እናቴ እኔ ዛሬ ወደ ጌታዬ ተጓዥ ነኝ። ሞቴ በሌሊት የሆነ እንደሆነ ለነብዬ አትንገሯቸው፣ እኔን ለመቅበር ጎህ ሳይቀድ ሲመጡ አይሁዶች እንዳይጎዷቸው" አሉ። እርሳቸው መጥተው ቢሰግዱባቸው የሚያገኙትን ደረጃ እያወቁት ግና ፍቅር ረታቸው፤ የነቢ ደህንነት ይበልጥ አሳሰባቸው። ወደ ረፋድ አካባቢ አረፉ። ከተቀበሩ በኋላ ሰይዳችን ለለቅሶ የሰይድ ጦልሐ እናት ዘንድ ሄደው ዱዓ አደረጉ። "ጌታዬ ሆይ በጦልሐ ደስተኛ ሆነህ ተቀበለው፣ እርሱም በአንተ ደስተኛ ሆኖ አግኘው" አሉ። እንደ ሚስክ ያለ ኺታም!

#ሶሉ_ዓለል_ሐቢብ!
አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ሰይዲና ወመውላና ሙሐመድ ወዓላ አሊሂ ወሶህቢሂ ወሰለም???

© Atiqa Ahmed Ali?

4 months, 1 week ago

| ምነው እኔን ለኔ ተውከኝ?. . |

@ktebiban_meder

4 months, 1 week ago

ሒካያ~27

< ከዘመናት በፊት አንድ ባለ ሀብት ነበር። ይህ ባለ ፀጋ ድንገት በአንዱ እለት ፡ አንዲትን ውብ ባሪያ ይመለከታል። ባለ ፀጋው በውበቷ ስር ወደቀ። በነጋ በጠባ ቁጥር ምስሏ በምናቡ ይመላለሳል። ትውስታዋ ከልቦናው ሊፋቅ ተሳነው። የፍቅሯ ታሳሪ ሆነ። በፍቅርና በናፍቆት መሀል የምትናወጥ ልቡን ይዞ ወደ አሳዳሪዋ አመራ። ባሪያይቱን ከፍ ባለ ገንዘብ ሊገዛት ጠየቀው። የባሪያዋ አሳዳሪም ፡ ባለ ፀጋው ከባሪያዋ ጋር በፍቅር መውደቁን ከአይኖቹ ተረዳ። አሰብ አደረገና። " አይ በዚህ ዋጋ አትሸጥም! " በማለት ያለውን ሁሉ አስረክቦ ባሪያይቱን እንዲገዛው አደረገ። ባለሀብቱ የለበሰውንም ባርኔጣና ኩታብ ሳይቀር አስረክቦ ተፋቃሪውን ይዞ ተጓዘ። >
   አየህ አይደል የኔ ልጅ! አፍቃሪ ላፈቀረው ነገር ያለውን ሁሉ ይሰዋል። ሚሰዋው ቢጠፋ የቀረችው አንዲትን ነፍስ እንኳን ብትሆን እርሷንም አይሰስትም። የርሱ መሻት የተፈቃሪው ደስታና ውዴታን መጎናፀፍ ነው። ታድያ በፍጡራን መካከል ላለ አላቂ ፍቅር ይህን ያል ቤዛ የሚደረግለት ከሆነና ሀብትና ንብረትን እስከማጣት ካስደረሰ ፡ ስለምን የጌታህን ፍቅር ያለ ምንም ክፍያ ትሻለህ? ክልከላውን ስትዳፈር ፡ ልብህ ላይ ያለው የማፍቀር ሂማ እየሞት እንደሚጠፋ ተሰወረህ? የትዕዛዙን በትር ስትይዝ ፡ የኩራትን ኩታን ከደረብክም በራስህ ላይ የፅልመት ካባን ነው የደረብከው። እኔነትህን ጥለህ ቅረበው። መሻትህን ግደለው። ምንምነትህን ገልጠህ ፡ ከዱንያ ፍቅር ተራቁተህ ቅረበው። ጣላት ይህችን ነፍስ! ተዋድቀህ የእውነት ፡ ሚስኪንና አሳዛኝ ባሪያ ሁንለት። እንዲያ ነው ፍ ቅ ሩ ን የምታገኝ!

@ktebiban_meder

4 months, 1 week ago

| ይሁንታህ ይሁን . . .
ይህ ሙቱ ልቤን ፡ በ'ኩን'ህ አንሳው ፣
ሚስኪን ባሪያህን ፡
ወዳንተ አቅርበህ ነፍሱን አድረሳው ፤ |

@ktebiban_meder

4 months, 2 weeks ago

የከውኑ ንጉስ፣ ጀማሉል‐ዓለም፣ የአላህ ወዳጅ፣ የነቢያት አውራ፣ የአደም ልጆች ዘውድ…
ለቤተሰባቸው ቀለብ ለተበደሩት ብድር ጥሮራቸውን ማስያዣ አድርገው አርፈዋል። ያስያዙት ለአይሁድ አበዳሪያቸው ነው። ህይወታቸውን የሚሰዉላቸው ኃብታም ባልደረቦች ቢኖሩም ለዳዕዋቸው ደመወዝ እንዳይመስል ወይም የግል ጉዳያቸውን በተከታዮቻቸው ጫንቃ ላይ ላለመጣል ከአይሁድ ተበደሩ።
የሚገርመው ገብስ ገዝተውኮ ነው!…
ስንዴማ ውድ ነው። ድኾቹ ሙስሊሞች ሳይበሉት እርሳቸው ቤት እንዲገባ አይፈቅዱም። ከህዝባቸው ቀድመው ለመራብ ከህዝቦቻቸው መጨረሻ ለመጥገብ ወስነው ኖረዋል።
:
ዐይናቸው ቁጥብ ነው፤ አይቅለበለብም። ከሰማይ ይልቅ ወደ መሬት ማየት ያዘወትራሉ። ልባቸው በሐያእ ስለተሞላ ወይም ፍካሬያቸውን ለመሰብሰብ ሊሆን ይችላል።… 
በድንገት ያያቸው በግርማቸው ይደነግጣል። በትውውቅ አብሯቸው የኖረ ይወዳቸዋል።
አብሯቸው የተቀመጠ ሁሉ ከርሱ በላይ የሚወዱትና የሚያከብሩት ሰው እንደሌለ ያምናል። ፈገግታቸውን ከማንም አይደብቁም። ሰዎች በገራገርነታቸው እና በስነምግባራቸው ስፋትና ምጥቀት ተደስተው አፍቅረዋቸው ኖረዋል። ልስላሴያቸው ለሁሉም ይተርፋል። የሁሉም አባት ነበሩ። በሐቅ ጉዳይ ላይ ግን ለርሳቸው ሁሉም ሰው እኩል ነው!
:
ለዚህ ማረፊያቸው፣ ለክቡሩ ዛታቸው…
ነፍሴ ፊዳ ትሁን! እናት፣ አባቴ እና ልጆቼ ቤዛ ይሁኑ!

#ሰሉ_ዐለይሂ_ወሰሊሙ!!?
አላሁመ ሰሊ አላ ሰይዲና ሙሀመዲን አብዲከ ወ ረሱሊከ አ'ነብይል ኡምሚይ ወአላ አሊሂ ወሳህቢሂ ወሰሊም

4 months, 2 weeks ago

| ሒካያ~24 |

መለኩል መውት ወደ ነብዩላህ ሳሊህ(ዐሰ) ዘንድ መጣ። ነብዩላህ ሳሊህም " አንተ መለከል መውት ሆይ ፡ ገና መቶ ሀያ አመት መኖሬ ነው! " ሲሉ የእሜያቸውን ማነስ አይተው ፡ በግርምት ጠየቁት።
መለኩል መውትም መለሰላቸው። " አንተ ሳሊህ ሆይ! ያንተ መቶ ሀያ አመት ብቻ መኖርህ አይግረምህ። እድሜያቸው በስልሳዎቹ ውስጥ የሚሆኑ ህዝቦች ይመጣሉ። "
ነብዩላሂ ሳሊህም እጅግ ተደንቀው " የማን ህዝቦች ናቸው እነዚህ? " በማለት ጠየቁት።
" የመጨራሻዋ ኡመት ፡ የሙሀመድ ሰለላሁ አለይሂ ወሰለም ህዝቦች ናቸው። " ሲል መለኩል መውቱ መለሰላቸው።

ነብዩላሂ ሳሊህም " በአላህ ይሁንብኝ እኔ የዚያ ዘመን ሰው ብሆን ኖሮ ከቀብሬ አጠገብ ድንኳኔን ጥዬ ነበር የምኖረው። " በማለት ተናገሩ።

@ktebiban_meder

4 months, 3 weeks ago

ያጣሁ ኹሉን ሲያጣ፣ ያገኘሁ ምን ኣጣ…!?

4 months, 3 weeks ago

ሒካያ~23

ይሄ ታሪክ ፡ ከኪታብ አልያም ከመሻዒኾች አንደበት የሰማሁት አይደለም። ይልቅ ከእናቴ አንደበት እናቴ ደግሞ ከእናቷ አላህ ያቆያቸውና ( ያው ሰነድ መሆኑ  ) የሰማችው የቅርብ ጊዜ ኸበር ነው።

ገጠር አካባቢ ላይ የሚኖሩ አንዲት ምስኪን ሴት ነበሩ። ከኢባዳ የማይሰንፉ። ታድያ ይህች እንስት ሁለቱንም አይኖቿን በጠና ታመመች። ከሀኪም ቤት ደጃፍ ተመላለሰች። ግና ችግሩ ስር የሰደደ ነበርና ሁለቱንም አይኖቿን አጣች። ዳግም መዳን ፡ እማይችልና ሙሉ ለሙሉ የአይኖቿ ስሮች ከአገልግሎት ውጪ እንደሆኑ ይነገራታል። የመጣባትን ሙሲባ ተቀብላ ፡ የአይኖቿ ብርሀን የፅልመት መጋረጃውን ለብሶ ወደ ቤቷ ተመለሰች። የአይኖቿን ብርሀን አጥታለች። የልቧ ግን እንደ ንጋት ጠዋት ያበራል።
ምንም እንኳን አይኖቿን ማጣቷ ክፉኛ ልቧን ቢያደማትም ፡ ከጌታዋ ደጃፍ አላስቀራትም። በስባራቷ ውስጥ ወደርሱ ትዋደቃለች። ምርኩዝህን ስትል ትማፀነዋለች።
    ሁሌም በትሯን ይዛ መንገዱን በበትሯ እያሰሰች ወደ መስጂድ ትመላለሳለች። በሶላት ወቅት ከሁሉ በፊት የምትገኝ ነበረች። ከእለታት በአንዱ ዕለት ግን ከባድ ዝናብ ዘነበ። ዝናቡ ትንሽ ረጋ ፡ ሲልና ማካፋት ሲጀምር ወደ ሰላት ትጓዝ ጀመር። በመንገዷ ላይ ግን ከባድ ጎርፍ አጋጠማት። ጎርፉ ወደ ጌታዋ ቤት ከመሄድ አቀባት። ወደ ቤት መመለስ አልፈለገችም። መሀል ላይ ቆማ የጎርፉ ሀይል እስኪቀንስ ትጠባበቅ ጀመር። በዚህ አሳዛኝ ሁነት ላይ ሆና አላህ(ሱወ) የአይኖቿን ብርሀን መለሰላት። አንደበቷ በምስጋና እና በእልልታ ተሞላ። በብርሀን የተሞሉ አይኖቿ የደስታን እምባ አረገፉ።
___
ወዱዱ ከእኛ ሚፈልገው ፡ የምንኩራራበትን አምልኮ አይደለም። የምንመፃደቅበትንም ደግነት እንዲሁ። ሚፈልገው...የሀቂቃ ባሪያው እንድንሆን ነው። ምንምነትን ፣ አቅመቢስነትን ተላብሰን እንድንዋደቅለት።
የጥፋት ጎርፊ ፊታችን ላይ ኬላ ሆኖብናል ፣ ወስዶ ከማናውቀው ጨለማ ሊዶለን ተሰናድቶዋል። ወደ እርሱ ምናደርገውን መንገድ ሊያሰናክለን። የታውረ ልባችን በብርሀን ይሞላ ዘንድ ፣ ተናንሰን እንዋደቅ። ከእርሱ ምንሰትረው አንዳች ነገር የለምና ፡ እኛነታችንን በአንደበታችን ገልጠን እንለምነው።  ከሪም ነውና።

@ktebiban_meder

7 months, 2 weeks ago

| ሀሳቦቻችሁን በውስጥ መስመር ላደረሳችሁኝ ፡ ወንድምና እህቶቼን ልባዊ ምስጋናዬን አደርሳለሁ። ሀሳቦቻችሁ የሞተ ሂማን የሚያድስ ፡ የሚያበረታም ፡ ነበር። ጀዛኩሙላሁ ኸይራ!
ሀሳብ የሰሰታችሁም መስጠትን ይስጣችሁ እላለሁ።  :)   |

እንደ አላህ ፍቃድ በሌሎች ስራዎች( ምናልባትም ለየት ባለ ይዘት ) እንገናኝ ይሆናል። ኢኽላስና ተቅዋን ይለግሰንና።

እስከዛው ግን..ላልተወሰነ ጊዜ እዚህ መንደር ላይ ዝምታ ይነግሳል  ፡ ባላችሁበት አማን ቆዩልኝ! የልባችሁ ሰላም አይደፍርስ።

በዱዓችሁም መሀል አስቡኝ??

አላሁመ ሰሊ ወሰሊም ወባሪክ አለይህ!?
•ወሰላም•

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago