የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik
ተክለሃይማኖት ጻድቅ ሊሄድ ፈልጎ የጽድቅ መንገድ
መንገዷ ጠባብ ሆናባት በሁለት እግር የማታስኬድ
አንዷን ቆረጠና በአንድ እግር ሄደባት
ባለ ቅኔ
ሰላም ለሰኰናከ ዘተሴረየ በደም።
አመ እግርከ ተሠብረ እምብዝኃ ቀዊም።
ተክለሃይማኖት ኢዮብ ዘትዕግስትከ ፍፁም።
ባርኮሙ ለደቂቅከ እለ ውስተ ኩሉ ዓለም።
ከመ ባረኮሙ ኖኅ ለያፌት ወሴም።
እንኳን ለኢትዮጵያዊው መልአክ ሐዲስ ሐዋርያ ቅዱስ ተክለሃይማኖት እግሩ ለተሰበረችበት (ሰባረ አጽሙ) አደረሳችሁ።
ምስሉ የአቡነ ተክለሃይማኖት የእግራቸው ስባሪ እና የእጅ መስቀላቸው አጼ ኃይለሥላሴ በነጭ ወርቅ ባሰሩት ማኅደር ውስጥ ሆኖ የሚታይ ነው።
በግሸን ደብረ ከርቤ ለብዙ ዓመታት ያገለገሉት አባ መፍቀሬሰብእ ኪዳነወልድ ከዚህ ዓለም ድካም አረፉ!
በግሸን ደብረ ከርቤ ብዙ መንፈሳዊና ልማታዊ ተግባራት ያከናወኑት ታላቁ አባት አባ መፍቀሬሰብእ ኪዳነወልድ በ96 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም ድካም አርፈዋል።
አባ መፍቀሬ ሰብእ የተወለዱት በ1921 ዓ.ም ሰሜን ሸዋ ተጉለት ወርቅጉር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ አለቃ ወርቅ አገኘሁ አገር ገዳምዬ ሚካኤል፣ ድንቡይ ጊዮርጊስ ነው። በልጅነታቸው በገዳምዬ ሚካኤል ለዲቁና የሚያበቃውን ትምህርት ከተማሩ በኋላ ከግብፃዊው ጳጳስ አቡነ ቄርሎስ እጅ ዲቁናን ተቀብለው በአካባቢያቸው ባሉ አብያተ ክርስቲያናት እስከ 14 ዓመታቸው ድረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡
አባ መፍቀሬ በደቡብና በሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከቶች ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ንጹሕ ስንዴን የዘሩ ትጉህ መምህር ፣ ቀናዒ ለሃይማኖታቸው ፣ በርቱዕ አንደበት መምከርን፣ በትጋት ማስተባበርን፣ ከሚዘምሩት ጋር መዘመርን፣ ከሚያመሰግኑት ጋር ማመስገንን፣ ከሚያዝኑትም ጋር ማዘንን ግብር አድርገው፤ እንደ ሕፃን ከሕፃናት ጋር፣ እንደ ወጣት ከወጣቶች ጋር እንደ አበው ደግሞ ከሊቃውንት ጋር ተዋሕደው ቤተ ክርስቲያንን አገልግለዋል።
ከ68 ዓመታት በፊት ግሸን ላይ ከአቡነ ሚካኤል የማስተማር ፈቃድ ተሰጥቷቸው በጎንደርና በወሎ በአብዛኛው ቦታዎች እየተዘዋወሩ አስተምረዋል፡፡ አባ መፍቀሬ ሰብእ ለማስተማር ሲነሱ አንደበተ ርቱዕ ከመሆናቸው ሌላ የትምህርቶቻቸው ይዘትም በአብዛኛው ከአገልግሎታቸው ጋር የተያያዘ ነበር፡፡ አብያተ ክርስቲያናትን ስለ ማነፅ፣ አፀደ አብያተ ክርስቲያናትን ስለ መትከልና መንከባከብ፣ ለቅርሶች መደረግ ስላለበት ጥበቃና እንክብካቤ፣ ስለ መንፈሳዊ በዓላት አከባበርና ወጣቶችን ከመናፍ*ቃን ሴራ ስለመታደግና ከአምልኮ ባዕድ ተግባራት ስለመራቅ በአፅንኦት አስተምረዋል፡፡
ባሕታዊ መፍቀሬ ሰብእ መመስገን ያለበትን ለማመስገንና የተሳሳቱትን ለመውቀስ ወደ ኋላ የማይሉ መሆናቸውን ስሜታቸውን በሽንገላ ለመደበቅ የማይችሉ እንዲሆኑ አድርጓቸዋል፡፡ በተለይም ደስታቸውን በዓውደ ምሕረት ላይ እንደ ሕፃን በመቦረቅ የመግለጻቸውን ያህል በሀዘን ጊዜ እንባቸው ቅርብ የመሆኑ ምስጢር ከብዙዎች ሰባክያንና መምህራን ልዩ የሚያደርጋቸው ባህሪያቸው ነው፡፡
ባሕታዊ መፍቀሬ ከዛሬ 45 ዓመት በፊት በወቅቱ የነበሩትን የደርግ ባለሥልጣናት በማግባባትና በማሳመን የግሸን ደብረ ከርቤ መንገድ እንዲሠራ ማድረግ መቻላቸው የኒህን አባት ጥበብ እና አስተዋይነት የሚያሳይ ተግባር ነው፡፡ ይህ መንገድ ከተሠራበት ከ1972 ዓ.ም. ጀመሮ እስከ አሁን ድረስ በየዓመቱ የየመሥሪያ ቤቱን በር በማንኳኳት በየግለሰቦች ቤት በመሄድ ለመንገዱ ሥራ ከፍተኛ አስተዋጽዖ አድርገዋል፡፡
አባ መፍቀሬ በአገልግሎት ዘመናቸው የራሴ የሚሉት ምንም ነገር የሌላቸው ሲሆኑ ከ1946 ዓ/ም ጀምሮ በወሎ ሀገረ ስብከት ተመድበው አገልግለዋል፡፡
አባ መፍቀሬ በተወለዱ በ96 ዓመታቸው በዛሬው ዕለት ከዚህ ዓለም ድካም ዐርፈዋል።
የደሴ ኤፍ ኤም ሬዲዮ እንደዘገበው ሥርዓተ ቀብራቸውን የሚያስፈጽም ኮሚቴ የተቋቋመ ሲሆን በሚወጣው መርሐ ግብር መሠረት ሽኝታቸው የሚከናወን ይሆናል ።
ዘገባው የተዋሕዶ ሚዲያ ማእከል ነው።
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:
፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot
Channel Created May 3/201
በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።
➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh
ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc
📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik