Infinite Entertainment, Zero Cost: Get Your Free Books, Music, and Videos Today!

ኪነት በዮዳኒ

Description
በዚህ የጥበብ ቤት▼▼▼

🎨ስዕል

📔ወግ

📖የመጽሐፍ ጥቆማ

📚መጽሐፍት

🗒ግጥም

🗣ትረካ

🎭ኪነጥበባዊ መረጃና ትምህርት

📑ወቅታዊ ፅሁፍ ያገኛሉ።
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her

2 месяца, 2 недели назад

በዚህም መሰረት አንደኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ አሸናፊ አንድ ሚልየን ብር የገንዘብ ሽልማት እና ሁለት ሚሊየን ብር የሚያወጣ አልበም እንደሚሰራለት በጥቅሉ የሦስት ሚሊዮን ብር አሸናፊ የሚሆን ሲሆን
ሁለተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ ደግሞ 500,000 ብር ሽልማት እና አንድ ሚልየን አምስት መቶ ሺህ ብር የሚያወጣ የሙዚቃ አልበም እንደሚሰራለት በአጠቃላይ የሁለት ሚሊዮን ብር አሸናፊ እንደሚሆኑ ተገልጿል።
ሶስተኛ ለሚወጣ/ለምትወጣ ተወዳዳሪ 250 ሺህ ብር ሽልማት እና ሰባት መቶ ሃምሳ ሺህ ብር የሚያወጡ ዘፈኖች በጥቅሉ የ አንድ ሚሊዮን ብር ሽልማት ያገኛል ነው የተባለው።
በእለቱ ልዩ ተወዳዳሪዎች የተዘጋጁባቸውን የሙዚቃ ስራዎች በማቅረብ ሽልማት እንደሚበረከትላቸው ታውቋል።
ለውድድሩ የተመደበውን ሽልማት ሶስት አገር በቀል ድርጅቶች የሸፈኑ ሲሆን አንደኛ ለሚወጣው/ለምትወጣው ተወዳዳሪ ጊፍት ሪል ስቴት ፣ሁለተኛ ለሚወጣው/ ለምትወጣው ታፍ ኢነርጂስ እንዲሁም ሶስተኛ ለሚወጣው/ለምትወጣው ተስፋዬ የኦቾሎኒ ቅቤ ማምረቻ ድርጅት በመሸፈን ለፍጻሜ ውድድሩ ስኬት ከፍተኛውን ሚና ተወጥተዋል።
የፍጻሜ ውድድሩ በባላገሩ ቴሌቪዥን፣በባላገሩ የዩቲዩብና በሁሉም የማህበራዊ ሚዲያ ቻናሎቹ በኩል በቀጥታ በአገር ውስጥና በመላው አለም ለሚገኙ ተመልካቾች እሁድ የካቲት 17 ከ8 ሰአት ጀምሮ ለእይታ ይበቃል ።
እንደ ዳዊት ፅጌ እንደ ኢሳያስ ታምራትንና ሌሎችም በባላገሩ ውድድር ስኬት ያገኙትን ተወዳዳሪዎች አይነት ተተኪዎች ለማዋለድ በሚደረገው ዝግጅት የፊታችን እሁድ ሚሊኒየም አዳራሽ በመገኘት የአይን እማኝ እንዲሆኑም ለህዝቡ ጥሪ ቀርቧል።

በአይነቱ ልዩ በሆነ መንገድ በእለቱ በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም አንድ ሰው የፈለገውን ያህል የገንዘብ መጠን መክፈል የሚችል ሲሆን ከመግቢያው የሚሰበሰበውም ገንዘብ ሙሉ ለሙሉ ለመቄዶንያ የአእምሮ ህሙማንና አረጋውያን መርጃ ተቋም ይውላል ተብሏል።

በመጨረሻም 😮😮😮 የካቲት 17!!!

@balageru_miert
@gbw_dan 💃

2 месяца, 2 недели назад
2 месяца, 2 недели назад
2 месяца, 2 недели назад

ከሞተች ቆይቷል
[ ገብረክርስቶስ ደስታ ]

ከሞተች ቀይቷል
ብዙ ዘመን ሆኗል
ብዙ ነበር ጊዜው
ግን ፎቶግራፏ አለ
ደብዳቤዋም አለ
በጠጉሯ ጉንጉን የጠቀለለችው
ምን ቀን ቀጠሮ ነው
ቀን የቀን ጎደሎ
የቀን ጥቁር መጥፎ
አበባ ሄድኩ ይዤ
እዛ አበባ አልጠፋም
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ስሜቴ ፈነዳ ገላዬን በተነው
ነፍሴን ነቀነቃት ገላዬን በተነው፡፡
ነፍሴን ነቀነቃት
እንባዬ ወረደ ጉንጬን አረጠበው
ለተረሳ ነገር እንዴት ያለቅሳል ሰው!
ለተረሳ ነገር
ምን ጊዜው ቢረዝም
የዚህ ዓለም ጣጣ እያንከራተተኝ
የዚህ ዓለም ስቃይ እየቦረቦረኝ
ሲጨንቀኝ ሰውነት
ፍቅሬ ይሁን ያንቺ የኔ መቃብር ቤት
ህይወት ነዶ ጠፍቶ
ሞት ፍሙን ሲያዳፍን
ያን ጨለማ ጓዳ ሄጄ ልተኛበት።

ይመስላል ዘላለም
ሰው ሰውን ሲወዱት
አይኑን አይኑን ሲያዩት
ይመስላል ዘላለም
አድማስ አልፎ አድማስ
ምጥቀት አልፎ ምጥቀት
ጠፈር አልፎ ጠፈር
ይመስላል ዘላለም
ሰው ባካል የሚኖር
ድሮ አውቀዋለው
ተረድቼዋለው
ፀሀይ ጥቁር ስትሆን
ቀን ቀንን ሲያጠላው
ሌት ሌትን ሲሸፍን
እረስቸው እንደሁ፡፡
እንዴት አንቺን ልርሳ
ነፍሴ አብሯት የሚኖር
የፍቅርሽ ጠባሳ፡፡
˝ፍቅርሽና ፍቅሬ የተወሳሰበው
አልበጠስ አለኝ ብስበው ባስበው˝
ማን ነበር ማ ነበር
ማ ነበር እንደዚህ ብሎ የገጠመው?

ይመስላል ዘላለም
አንቺ የኔ እመቤት ብያት የነበረ
አንተ የኔ ጌታ
አንተ የኔ ጌታ ብላኝ የነበረ
አንቺ የኔ እመቤት

ይመስላል ዘላለም፡፡
እንባዬ ወረደ ልቤን አቃጠለው
ልቤ ተነደለ
የሰቀቀን እሳት አካሌን ሲያነደው
ደሜ ገነፈለ
የደም ጥቁር እንባ
ቆዳ የሚያሳስር መንፈስ የሚያባባ
አለቀሰቅሳትም
ቡዳ እሷን አይበላም
ቢስ አሷን አያይም
አልቀሰቅሳትም በነብሴ ተጉዤ እጠይቃታለው
አውቃለው አውቃለው
በመቃብሯ ውስጥ
ጢስ እንጨት ይጨሳል
ከርቤ ብርጉድ እጣን
መቃብሯ ሽቱ
ጣፋጭ መኣዛ አለው አጥንቷ ታቦቱ
መቅደስ ቤተልሄም ቅኔ ማህሌቷ
እጣኑ ይጨሳል ይታጠናል ቤቷ
ፍቅሬ ሙሽራዬ
እመቤቴ ፍቅሬ ያለም አለኝታዬ
አቴቴዋ ይታጠናል
ልዩ መዓዛ አላት
በመቃብሯ ውስጥ ጢስ እንጨት ይጨሳል
በመቃብሯ ውስጥ አበባ ተኝቷል፡፡
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ፤
ፍቅሬ ፍቅሬ ፍቅሬ
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ፤
እመቤቴ ፍቅሬ እመቤቴ ፍቅሬ
ፍቅሬ አለኝታዬ ፍቅሬ አለኝታዬ፤
ፍቅሬ አለኝታዬፍቅሬ አለኝታዬ
እንባዬ ወረደ…………………..
እንግዲህ ይበቃል ይቅር ይቅር ይብቃ
በድካም መድከም ባሳብ ሀሳብ አለ
ባዘን………….. ሃዘን……….ሃዘን

@gbw_dan

2 месяца, 3 недели назад

ማዛሮት

✍️ በመጋቤ ሐዲስ ሮዳስ ታደሰ

@gbw_dan

2 месяца, 3 недели назад

የጥበብ መንገድ

ደራሲ ካህሊል ጂብራን

@gbw_dan

3 месяца назад

የጋሽ ስብሐትለአብ ገብረእግዚአብሔር የፊልም ግብዣ

፱,The Silence (director: Ingman Bergman)

@gbw_dan

3 месяца назад

ጠብቄሽ ነበረ!

መንፈሴን አንጽቼ
ገላዬን አጥርቼ
አበባ አሳብቤ
አዱኛ ሰብስቤ
ጠብቄሽ ነበረ፤
ብትቀሪ ጊዜ፣
መንፈሴን አሳደፍኩ
ገላዬን አጎደፍኩ

አበባው ደረቀ
አዱኛው አለቀ
ብትቀሪ ጊዜ፣
የጣልኩብሽ ተስፋ
እኔን ይዞኝ ጠፋ።

✍️ደበበ ሰይፉ

@gbw_dan

3 месяца назад

የጋሽ ስብሐትለአብ ገብረእግዚአብሔር የፊልም ግብዣ

፰, All Charlie Chaplin films

@gbw_dan

5 месяцев назад

ሩሚ ማነው? ላላችሁ

ጀላል አል ዲን ሩሚ (1207-1273 እ.ኤ.አ)

ጀላል አድ ዲን ሙሀመድ ኢብኑ ሙሀመድ ኢብኑ ሁሴን አል ሩሚ ከሂጅራ በኋላ በ640 (1207/8) ባልክ (የዛሬዋ አፍጋኒስታን) ነው የተወለደው፡፡ አባቱ በሃአ ዲን እጅግ የታወቁ የሃይማኖት ምሁር ናቸው፡፡ በሱ የቅርብ ክትትል ሥር ሆኖ በልጅነቱ ትምህርቱን ከሰይድ ቡርሃን አል ዲን ቀሠመ፡፡ እድሜው 18 አካባቢ ሲደርስ ከቤተሰቡ ጋር የተሠደደ ሲሆን ከረጅም ጊዜ የስደት ህይወት በኋላም በኮኛ ሰፈሩ፡፡ እድሜው ሀያ አምስት ሲሆን ሩሚ ለተጨማሪ ትምህርት መጀመሪያ ወደ አሌፖ ቀጥሎም ወደ ዳማስቆ ተላከ፡፡

ሩሚ እስከ 40 አመት እድሜው ድረስ በትምህርት ፍለጋው የቀጠለ ሲሆን አባቱ በሞተ ጊዜም እርሣቸውን በመተካት በሀያ አራት አመቱ ኮኛ በሚገኘው ታዋቂ መድረሣ በፕሮፌሰርነት አገልግሏል፡፡ ቀልብን በሚያረቁ መንፈስን በሚያፀዱ ነገሮች ዙሪያ መጀመሪያ በሰይድ ቡርሃን አል ዲን ኋላ ላይ ደግሞ በሸምሰዲን ታብሪዚ እጅ ሰልጠና ወስዷል፡፡ አል ሩሚ በመንፈሣዊ አመለካከቱና ሃይማኖታዊ እውቀቱ እንዲሁም በፐርሺያ ግጥሞች ከፍተኛ እውቅና ነበረው፡፡ በመድረሣው በርካታ ተማሪዎችንም ያስተምር የነበረ ሲሆን እውቅ የሆነውን በተሰውፍ የማሉቪ ሥርኣትንም መሥርቷል፡፡ የሞተውም በ672 (1237) በኮኛ ሲሆን ይህም ቦታ ኋላ ላይ በማሉዲ ሥርኣት የተቀደሰ የውዝዋዜ ቦታ ሊሆን ችሏል፡፡

ዋና ዋና አስተዋፅኦዎቹም በፍልስፍና እና ተሰውፍ ዙሪያ ያተኮሩ ናቸው፡፡ ይህም በዋናነት በግጥሞቹ ውስጥ በተለይም ማትናዊ በተሠኘው መፅሃፉ ውስጥ ተካቷል፡፡ ይህ መፅሃፍ ረቂቅ መንፈሣዊ ግጥሞችን በማካተት ትልቁ ሲሆን በሜታፊዚክስ፣ በሃይማኖት፣ በሥነምግባር፣ በመንፈሣዊነት እና በመሣሰሉት ውስጥ ያሉ ጉዳዮችን የሚዳስስና ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ መፍትሄዎችን ለመጠቆም የሚያስችል ነው፡፡ ማትማዊ በዋናነት ድብቅ የሆኑ በርካታ የሱፊያ ጎኖችንና ከዓለማዊ ህይወት ጋር ያላቸውን ግንኙነት በጨረፍታ የሚቃኝ ነው፡፡ ሩሚ በርካታ ጉዳዮችን የነካካ ሲሆን ከያንዳንዱ የእለት ተእለት ህይወት ውስጥም በርካታ ምሳሌዎችን መዟል፡፡ አቢይ አጀንዳውም በአንድ በኩል በሰው ልጅ እና በአምላክ መካከል ያለውን ግንኙነት በሌላ በኩል ደግሞ በሰው እና በሰው መካከል ጥሩ ግንኙነት እንዲፈጠር ነው፡፡

ሩሚ ከማትናዊ በተጨማሪ ዲዋን የሚባል (የግጥም መድብል) እና ፊሂ ማ ፊሂ የሚባል (ረቂቃዊና ጥበባዊ ንግግሮችን) የያዘ መፅሃፍ ፅፏል፡፡ የሩሚን መልእክቶች ያስተላለፈው በዋናነት ማትናዊ ነው፡፡ ማትናዊ ከተጠናቀቀ በኋላ ሌሎች ምሁራን በተሰውፍ፣ በሜታፊዚክስ እና ሥነምግባር የተሻለና ጠቃሚ ትርጉሞችን ለማስገኘት በማሰብ ዝርዝር ማብራሪያዎች በሱ ዙሪያ ፅፈዋል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮም በተለያዩ ቋንቋዎች በርካታ ማብራሪያዎች ተፅፈዋል፡፡

በፍልስፍና፣ በሥነፅሁፍ፣ በረቂቅ መንፈሣዊ ህይወትና እና በባህል ላይ በመካከለኛው ኢስያ እና በአብዛኛው ሙስሊም ሀገራት ውስጥ የነበረው ተፅእኖ ሰፊና ጥልቅ ሲሆን ምሁራን፣ ፈላስፋዎች፣ የሥነ ልቦና አዋቂዎች በአጠቃላይ ሁሉም ለማለት በሚያስችል መልኩ በነኚህ ምእተ አመታት ወቅት እስከ እለተ ሞቱ ድረስ ከአንቀፆቹ ማጣቀሻ ወስደዋል፡፡ መልእክቶቹ በመካከለኛው ኢስያ እና ዙሪያውን ባሉ አካባቢዎች የሚገኙ በርካታ ምሁራንን መስጠዋል፡፡ ኢቅባልን የመሣሰሉ ትላልቅ ምሁራን ደግሞ ፅንሠ ሀሳቡን በተሻለ መልኩ አዳብረውታል፡፡ ማትናዊ በፐህላቪ ቋንቋ የቁርኣን ትርጉም እንደሆነ ተደርጎ ሊታወቅ ችሏል፡፡ ሩሚ ላቅ ባለ እይታው በዓለም አመለካከትና በአብዛኛው የሙስሊሙ ዓለም ላይ በከፍተኛ ሁኔታ ተፅእኖ ካሳደሩ በቁጥር ጥቂት ከሆኑ ምሁራን መካከል አንዱ ነው፡፡

በተጨማሪም የበረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ " የግጥም መድብል ይበልጥ ገልጾታል።

SHARE THIS ሼር ያድርጉት☞☞

@gbw_dan

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her