የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 Monate her
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 Monate, 2 Wochen her
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 Monate, 2 Wochen her
ታናሽ እህቴ ናት በአስራ ሶስት አመት እበልጣታለሁ ። እሷ ላይ ያለኝ ስልጣን የአለቃ ነው ። 'exercise' የማደረገው ስልጣን ብዙ ነው የአፍሪካ መሪዎች ዜጎቻቸው ላይ ካላቸው ስልጣን አያንስም ። እሷም ስልጣኔ ነው ብዬ 'exercise' የማደርገውን በፀጋ ተቀብላለች ።
ልጄ ትመስለኛለች ምግብ በጋራ ስንበላ ቀድሜ ነው በቃኝ የምለው ። ከሷ ጋር እንዳልሻማ ፍቅሬ እና ሃላፊነቴ ይገታኛል ።
ሁኔታዋን አየዋለሁ ሲዶክካት፣ ስትደሰት እንቅስቃሴዋን አስተውላለሁ ። ከጓደኛዋ እንዳታንሳ 'Invest' አደርግባታለሁ ።
የሆነ ፊልም እያየን መጥፎ ገፀባህሪ ስታይ "ኤፍሬም ፊልም ስለሆነ ነው እንጂ: እንደዚህ አይነት ሰው በትክክለኛ ህይወት የለም አይደል? " ትላለች
ሰው የማርያምን ስም ጠርቶ የሚዋሽ አይመስላትም ፣ ለገንዘብ ብሎ ሰው ጓደኛውን የሚክድ አይመስላትም ፣ የውሸት ለቅሶ ያለ አይመስላትም ። ንፁህነቷ ያስደነግጠኛል ። ብስለት የሚባለውን እውቀት ማጥመቅ ፈልጌ አጠማመቁ ግራ ይገባኛል ።
ስለዓለም ክፋት መንገር እጀምር ና አለምን የምታይበት መነፅር እንዳይንሸዋረር እሰጋለሁ ።
'Feminist ' አደረገችኝ። ትሁቴን እያሰብኩ መደፈር፣ ድብደባ፣ ጭቆና እቃወማለሁ ። ትሁቴን ስለማስብ ሴት አታልሎ ወደ አልጋ መውሰድ አልችልም ። ትሁትን እያሰብኩ ገራገር እንስቶች ላይ 'Advantage ' ለመውሰድ አልሞክርም ።
ትሁቴ የመጀመርያ ልጄ ነች ። በሷ ጉዳይ አልራቀቅም ፣ በሷ ምክንያት ሴቶች ላይ በደል አልሰራም ።
ትሁቴ እንዳትኮርጀኝ ሰክሬ አልንገላወጅም ፣ የማይረባ ጓደኛዬን እቤታችን አላመጣም ፣ ትልቅ ለመሆን እባትላለሁ ።
የአንዳንድ ታናሽ አሻራ እንደ መምህር አይነት ነው !!
© Adhanom Mitiku
🏆 ሁለተኛ ዙር የበጨዋደምብ የግጥም ውድድር እየደረሰ ነው!
በሁለት ሳምንት አንዴ የሚደረገው የግጥም ውድድር እንሆ በፊታችን እሁድ ምሽት ይደረጋል!
አሁኑኑ ይዘጋጁ እና በተሰጠው መወዳደርያ ስራን ማስገቢያ ሰአት ያስገቡ!
ስለህግጋቶቹ እና ተጨማሪ መረጃዎችን በዚህ ሊንክ፡ https://t.me/eyadermoges1/1361 ላይ ማገኘት ይቻላል! እግረመንገድዎን ቻናሉን ጆይን ማድረጎ አይረሳ! ደርሷል 🏃🏃!
`🫦
እስቲ ሳሚኝ
ሳሚኝማ
በያ ሳሚኝ...
{ እሺ ስሚኝ... }
መሳምሽ መሳም አይደለም እኔጋ ፥ ማሳለም ነው ውብ ከንፈርሽን
ለኔም መሳም መሳለም ነው፥ ውስጥሽ ያለ ታቦትሽን።
ታቦትን ጣውላ ነው ለሚል ፥ ለዚህ ትውልድ ባይገባውም
እግዜርን ካንችነትሽ
ታቦትን ከከንፈርሽ ፥ አስበልጬ አላየውም።
ከንፈርሽ...
ያ' ስቴር ልሳኗን
የ'ናቴ ቃሏን
(ይመስለኛል)
ተኝቼ ሳለሁ በህልሜ
አካል አልባ ፤ ፊት አልባ
ከንፈር ብቻ
( ይታየኛል)።
አትሳቂልኝ ግድ የለሽም ፥ ጭንሽም ይቆይ ይከደን
እኔኮ ቤትሽ የመጣሁ ፥ ማር - ዘነብ ከንፈር ለማደን።
ሳሚኝ ቅድም
ሳሚኝ ነገ
ሳሚኝ አሁን...
ከዛ ግን ስትፈልጊ
'ጎረምሳ' ድምፅሽን ልሁን
....
ፀጉርሽ ለፍሬዝ ያንሳል ፥ ሲቀጥል ምላጭ ይሰብራል
ግንባርሽ ሰፊ ሜዳ ነው ፥ አስራ ስንት ሰፈር ያሰራል
አፍንጫሽ ድንበር ይጥሳል
ምላስሽ እግር ይልሳል
አንገትሽ ከቀጭኔ ፊት
እልፍ አ'ላፍ ቅናት ያተርፋል
ቁመትሽ ሲሄዱት ቢያድሩ
ማራቶን ያህል ይተርፋል
የጥርስሽ አደንደሩ
የጥያ ትክል ድንጋይን
ለቅፅበት ያሳውሰኛል
እንዳንቺ ያለን ሴት ታዲያ
ጤነኛ እንዴት ይመኛል ?
ምክንያቱ:-
የማርያም ድንግልናዋን
የክርስቶስ ሰምራ ቅድስናዋን
የአርሴማ ልግስናዋን
በውበት የሚስተካከል፤
እግዜሩ ከንፈር ሰጦሻል
በውርደቶችሽ መካከል።
እኔም ...
" እሷ ትቅር ይቅር
ጌታ ሆይ አደራ ከንፈሯን አትንሳኝ
በዚ አለም ባይሆንም
ኋላ ስትመጣ ከንፈሯ ጋር አንሳኝ ''
እያልኩኝ እፀልያለሁ
ፀሎቴን ከ'ግዜር ደብቄ
አንቺኑ ስሚኝ እላለሁ
(አንቺኑ ሳሚኝ እላለሁ፡፡)
ሳሚኝ እስቲ በ'ናትሽ
:- ግዑዝኤል`
ንዝረቱ ያመጣብኝ መርዶ!
የትናንትናው የመሬት መንቀጥቀጥ ነገር ፈጣሪ አተረፈን እንጂ በጣም አስፈሪ ነበረ።
ይህ ባለሞያዎቹ "አዋሽ ፈንታሌ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥ የፈጠረው ሞገድ በመሬት ውስጥ እዚህ ደርሶ ነው" ያሉት አስፈሪ እና ድንገተኛ የመሬት ንዝረት ሲከሰት እኔ ከሚስቴ ጋ ሀያት በሚገኘው የጋራ መኖሪያ ሶስተኛው ወለል ላይ ያለው መኝታቤታችን ውስጥ አልጋችንን በስሜት እያንቀጠቀጥን ነበረ። በድንገት በከባድ ድምፅ ያለንበት ህንፃ ሲናወጥ እና ህዝቤ ወደመሬት ለመውረድ ሲተራመስ የማትተርፍና በፍርስራሽ የምትቀበር የመሰላት ሚስቴ የበለጠ ጥብቅ ብላብኝ በፍርሀት ተውጣ እያየችኝ ኑዛዜ በሚመስል ሁኔታ "እኔ ላንተ ምገባ ሴት አይደለሁም፤ ፍቅራችንን ረግጬ ፍፁም በማይደረግ መልኩ ከ"........ እያለች ሳለ በቅፅበት ሁሉም ነገር ወደነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ተመለሰ፤ ሚስቴም ምንም እንዳላወራች በሚመስል ወደ ጋለው ጭኗ እያስጠጋችኝ "ውዴ ፍርሀቱ አቃዠኝ እኮ" ብላኝ ይኸው የመሬቱን ንዝረት ተክቼ እኔ እስካሁን እየተንቀጠቀጥኩ እገኛለሁ ምን ተሻለኝ ጎበዝ
✍ጫላ
*' እብድ ነው!' ይሉሻል አይደል ፥ የጠፋው ጨርቁን መጣያ
'ፋንጋ ነው ' ይሉሻል አይደል ፥ ማያፍር - ህሱም - ማስጠያ
'ሞኝ ነው' ይሉሻል አይደል ?
ፍሬ አልባ
እብቅ ገለባ
የአይምሮ ህመም ሰለባ...
ሰው ሁሉ በዚና በዚያ ፥ ከቀን ቀን በብቃት ሲካን
እሱ ግን ምስኪን ገጣሚ ፥ የክብር የዝና መካን
(ይሉሻል አይደል ?)
ሌሊቱ የቅዠት ዓለም ፥ መዓልቱ የጽልመት ጭራቅ
ምኞቱ የቀረቡትን
በሰበቡ አስባቡ መራቅ...
አይምሮው የዲያብሎስ ጋን ፥ ያሉታ ተንኮል ጠማቂ
አይኖቹ የሰማይ ግርዶሽ ፥ ዘወትር ምፅዓት ጠባቂ...
አንደበቱ ማዕበል ጠሪ ፥ የአመፅ ሰልፍ አስተናጋጅ
ለትውልድ መራራ ሐሞት ፥ ለራሱ መርዝ የሚያዘጋጅ
ምላሱ አጥንት ሰባሪ ፥ ልክስክስ ጥምብ አንሳ አሞራ
ዶፍ ሆኖ መዝነብ ሲጀምር ፥ ለቅፅበት የማያባራ
(ይሉሻል አይደል?)
ለጥፋት ማህሌት ቋሚ ፥ ለኃጢያት ደምበኛ አክፋይ
የሰይጣን የክንፉ ቁራጭ ፥ የቃየን የስጋ ክፋይ
ከይሁዳ የክህደት ባህር ፥ ባርባ ቀን የተጠመቀ
በበግ ለምድ በተኩላ ነፍሱ ፥ ከሰዎች የተደበቀ...
የውሽቱን ሁሉን አፍቃሪ ፥ ነገር ግን የጥላቻ ቋት
ቀናቱን ጎባጣ አሮጊት ፥ ሌሊቱን ቆሞ መንቃቃት...
ሀሰት ነው እሱ አይወድሽም
ሌሊት ላይ እንደሚፅፈው ፥ ግጥሙ እንኳ አያይሽም።
( ይሉሻል አይደል?)
እንኳንስ አንቺን ሊወድሽ ፥ ራሱን ጠልቷል አምርሮ
ዝም ብለሽ አትጃጃይ
እሱ እንዶን በቅቶታል ኑሮ ....
( ይሉሻል አይደል ?)
...
..
.
እውነታቸውን ነው!*
፦ ግዑዝኤል
የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::
#Group t.me//Ethio_Jobs2000
#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0
https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk
For promotion 📩 @Share_Home
Last updated 2 Monate her
ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1
Last updated 5 Monate, 2 Wochen her
Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ
Last updated 7 Monate, 2 Wochen her