የመንፈሳዊ መጻሕፍት ንባብ ቤተሰብ

Description
#የኅብርቱዋናዓላማ

፩.መንፈሳዊ መጻሕፍትን በዓላማ፤በእቅድ እንድናነባቸው፤እንድናስነብባቸው በሕይወታችን ትርጉም እንዲኖራቸው ማድረግ።

፪.ከቤተሰቦቻችን፤ዘመዶቻችን፤ወዳጆቻችን ስላነበብናቸው መጻሕፍት እነሱም ስላነበቡት መጻሕፍት ውይይት የማድረግ ልምድን ማዳበር።
፫.አንባቢ ትውልድ መፍጠር። ለአስተያየትዎ @orthokiha ይጻፉ።
https://t.me/BetMetsahfte
Cross @selam1981
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago

1 Monat, 2 Wochen her
ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በስካይ ላይት …

ዛሬ የመጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር በስካይ ላይት ሆቴል ላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ዕሴቶቻችንን በህዝባችን ሕይወት ላይ እናስርጽ በሚል መሪ ቃል ያዘጋጀው የመንፈሳዊ መጻሕፍት ዓውደ ርዕይ /ባዛር ኤግዚቢሽን/እኛንም ያሉንን መንፈሳዊ ምርቶቻችንን ይዘን በድካይ ላይት ሆቴል አባይ አዳራሽ ተገኝተናል እየመጣችሁ እንድትጎበኙን እናሳስባለን።
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ
https://t.me/BetMetsahfte

1 Monat, 2 Wochen her
**ኑ መጥታችሁ ጎብኙን!

**ኑ መጥታችሁ ጎብኙን!

እቁብተኞች እንዲሁም አባሎቻችን ይዘንላችሁ እንድንመጣ ምትፈልጉትን መጻሕፍት ቀድማችሁ @dawitfikr እዙዙ!#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ!**https://t.me/BetMetsahfte

1 Monat, 3 Wochen her
[#ከአዲሱ](?q=%23%E1%8A%A8%E1%8A%A0%E1%8B%B2%E1%88%B1) የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ትርጉም …

#ከአዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ መጽሐፍ ትርጉም በጨረፍታ እናስቃኛችሁ።

እውነትም አፈወርቅ ጥዑም ዘይጥዕም እም መዓር ወሦከር።

#10_የነፍስ_ምግብ_ጉርሻዎች

#የነፍስ_ምግብ አዲስ መጽሐፍ በገበያ ላይ

አዲሱ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ #የነፍስ_ምግብ የተሰኘው መጽሐፍ በገበያ ላይ መዋሉን ምክንያት በማድረግ 10 የነፍስ ምግብ ጉርሻዎችን ከነፍስ ምግብ መጽሐፍ ጋብዘናል፦

#1
"ቃላቶችህ ምንም ያህል ትክክል ቢሆኑም በቁጣ ስትናገር ሁሉንም ነገር ታበላሻለህ።"

#2
"ብል ልብስን እንደሚበላው ሰውንም ቅናት ይበዋል።"

#3
"እግዚአብሔር የሚጠይቀው ጥቂት፣ የሚሰጠው ብዙ ነው"

#4
"እያንዳንዱ ሰው የህይወቱ ሠዓሊ እና ቀራፂ ነው።"

#5
"ባለጠጋ ብዙ ያለው ሳይሆን ብዙ የሚሰጥ ነው።"

#6
“ምሕረት አምላክን ይመስላል ሰይጣንንም ያሳዝነዋል።"

#7
" ኃጢአት ስትሠራ እንጂ ንስሐ ስትገባ አትፈር"

#8
"ለምን በትንንሽ ነገሮች መደሰትን አትማርም - በጣም ብዙ ናቸው።"

#9
"ጸሎት የጭንቀት ሁሉ መሸሸጊያ፣የደስታ መሠረት፣ ከሐዘን መከለያ ናት። "

#10
"ክርስቶስን በቤተ ክርስቲያን ደጃፍ ላይ ባለው ነዳይ ውስጥ ማግኘት ካልቻላችሁ፣ በቤተመቅደስ ውስጥ አታገኙትም።"

እውነትም #የነፍስ_ምግብ የሚያሰኘው ይህ ድንቅ መጽሐፍ ከእንጀራ በፊት አንድ አንድ ጉርሻ ጎረስ ጎረስ እያረጋችሁ እንድትመገቡ ጋብዘናችኋል።

#የመጽሐፉ ርእስ #የነፍስ ምግብ
የጀርባው ዋጋ=450
አርጋኖናዊ ቅናሽ እንደተጠበቀ ነው ይጎብኙን።

ለበለጠ @dawitfikr ይዘዙን። https://t.me/BetMetsahfte
#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_5ኪሎ_ቅድስት_ማርያም_ዋናው_በር_ፊትለፊት_ሽዋ_ዳቦ_መነጽር_ቤቶቹ_ውስጥ_ወይም_0912044752_0925421700_ይደውሉ

3 Monate, 2 Wochen her

ሰኞ - ጥር 13 2016 ዓ.ም

ዘፍጥረት 1-5

በዛሬው እለት ኦሪት ዘፍጥረት ምዕራፍ 1 እስከ 5 ድረስ እናነባለን። በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ እግዚአብሔር በስድስት ቀናት ውስጥ ፍጥረታትን እንዴት እንደፈጠረ፥ በስድስተኛው ቀን አዳምና ሔዋንን ፈጥሮ በሰባተኛው ቀን እንዳረፈ እናነባለን። በገነት ውስጥ አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን እንዳልታዘዙ፥ በዚህም ምክንያት ከገነት እንደተባረሩም ተጽፎ ይገኛል። በተጨማሪም በልጆቻቸው በአቤል እና በቃየን መካከል ችግር ተፈጥሮ፥ ቃየን ወንድሙ አቤልን እንደገደለው የምናነበውም በእነዚህ ምዕራፎች ውስጥ ነው። በምዕራፍ አምስት ላይ ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ያለውን የዘር ግንድ የምናገኝ ሲሆን፥ ይህም ቀጣይ ለምናነባቸው ታሪኮች ያዘጋጀናል። 

የክለሳ ጥያቄዎች

1) እግዚአብሔር በመጀመሪያው ቀን ምን ፈጠረ?

2) እግዚአብሔር የሰው ልጅን የፈጠረው በስንተኛው ቀን ነው?

3) በዘፍጥረት 2 መሠረት፥ አዳም የተፈጠረው እንዴት ነው?

4) እግዚአብሔር በገነት ውስጥ ለአዳም እና ሔዋን የሰጠው ኃላፊነት ምን ነበር?

5) አዳም እና ሔዋን እግዚአብሔርን ባለመታዘዝ የበሉት ምን ነበር?

6) የአዳም እና ሔዋን አለመታዘዝ ምን ውጤት አስከተለ?

7) በዘፍጥረት 4 ላይ የተጠቀሱት የአዳም እና የሔዋን ልጆች እነማን ናቸው?

8) በአቤልና ቃየን መካከል የነበረው ግጭት በምን ተነሳ? ፍጻሜውስ ምን ሆነ?

9) በዘፍጥረት 5 ያለው የዘር ግንድ ዓላማው ምንድር ነው?

10) በዘፍጥረት 5 መጨረሻ ላይ የተጠቀሰው ሰው ማን ነው?

ለውይይት እና ክትትል እንዲመች ከዚህ በኃላ ንባቡን ለመቀጠል የሚከተለውን join አድርጉ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://t.me/+3kpzSPDfiVMzYzQ0 https://t.me/BetMetsahfte

3 Monate, 2 Wochen her

**ሰላም! በየእለቱ የሚከተለውን ቅድመ ተከተል ይከተሉ፦

1 - ለማንበብ አመቺ ቦታ ተቀምጠው አሳብዎትን ይሰብስቡ።

2 - እግዚአብሔር የቃሉን ምስጢር እንዲገልጥልዎት አጭር ጸሎት ይጸልዩ። ከዚህ ሥር የሠፈረውን የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ጸሎት መጸለይ ይችላሉ፦

“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፤ የአንተን ቃላት እሰማ እና እረዳ ዘንድ፥ እንዲያውም ፈቃድህን ለመፈጸም እበቃ ዘንድ የልቤን ጆሮዎች እና ዓይኖች ክፈትልኝ።”

3 - በእለቱ ስለሚነበበው ክፍል የቀረበውን አጭር መግለጫ ያንብቡ።

4 - በእለቱ የሚነበበውን ክፍል በተመስጦ ሆነው ያንብቡ።

5 - ያነበቡትን በሚገባ እንደተገነዘቡት ለማረጋገጥ የቀረቡትን ጥያቄዎች ይሞክሩ።**

3 Monate, 2 Wochen her
  • የትውውቅ መርሐ ግብር + (ቻሌንጅ/ሞክረኛ)

ከውሃ የወጣ ዓሳ፥ ከአፈር የተነቀለ ተክል፥ ከአየር የተለየ ሰው ሙት መሆኑ እርግጥ ነው። ለክርስቲያን ደግሞ ሞቱ ከእግዚአብሔር መለየት ነው። አንድ ክርስቲያን ከእግዚአብሔር ቃል ጋር ያለው ግንኙነት ከተቋረጠ፥ በጸሎትም አምላኩን ማነጋገሩን ከተወ የሞቱ ዋዜማ ላይ መሆኑን እንረዳለን። የቫይታሚን እጥረት የሰውነት መቀንጨርን እንደሚያስከትል ሁሉ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ስንለይ መንፈሳዊ ሕይወታችን ይቀነጭራል። ይህ እንዳይሆን መጸለይ፥ የእግዚአብሔርም ቃል በውስጣችን እንዲያድር ቅዱስ መጽሐፉን በርትተን በጸሎት መንፈስ ማንበብ ይኖርብናል።

ብዙ ጊዜ “ሰው ከእግዚአብሔር ቃል አልገናኝ አለ! ሰው የአምላኩን ቃል አያውቅም!” ወዘተ እየተባለ አስተያየት ሲሰጥ ይስተዋላል። በእርግጥ እውነት ሊሆን ይችላል። ሆኖም ግን ችግሩን እያገዘፉ ከመኖር፥ መፍትሔው ላይ ማተኮሩ ብልህነት ነው። ጨለማውን እያማረሩ መኖር ይቻላል፤ ወይም ደግሞ እንደ አቅማችን ሻማ መለኮስ። ምርጫው እንግዲህ የእኛው ነው።

ይህንን ታሳቢ በማድረግ አንድ ቻሌንጅ/ሞክረኛ አዘጋጅቻለሁ። ይህም ቻሌንጅ መጽሐፍ ቅዱስን ከኦሪት ዘፍጥረት አንስቶ እስከ ዮሐንስ ራእይ ድረስ በስድስት ወር ውስጥ አንብቦ ማጠናቀቅ ነው። በአጭሩ ከመጽሐፍ ቅዱስ ጋር የሚደረግ የትውውቅ መርሐ ግብር ብሎ ማሰብ ይቻላል። መጽሐፍ ቅዱስ ሁሌም አዲስ እንደመሆኑ፥ ሁሌም ትውውቅ ይፈልጋል። “አውቄዋለሁ። ጨርሼዋለሁ።” የሚል ቃል ለመጽሐፍ ቅዱስ አይሠራም። ቤተ-ክርስቲያንንም ለመረዳት ትልቁ ቁልፍ መጽሐፍ ቅዱስ መሆኑ እሙን ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ እና ብንኖር፥ በዓመት ሁለት ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስን ከጫፍ እስከ ጫፍ ማንበብ እንችላለን ማለት ነው። ንባቡን ሳያውቁ ምስጢሩን መጠየቅ የማይሆን ነውና፥ አስቀድመን ንባቡን ማወቅ ይገባል። ጥልቅ የሆነው የእውቀት ጉዞም የሚነሳው ማንበብ ከመጀመር ነው።

ክርስትና የኅብረት ጉዞ እንደመሆኑ መጠን፥ ይኽም ጉዞ የኅብረት ቢሆን ጥቅሙ ብዙ ነው። እግዚአብሔር ቢፈቅድ ይህ ጉዞ በነገው እለት ጥር 13 2016 ይጀምርና ሐምሌ 16 2016 ይጠናቀቃል። ይኽንን ጉዞ አብራችሁ ከእኔ ጋር ለመጓዝ ፈቃደኛ የሆናችሁ ሁሉ፥ በኮሜንት ላይ አሳውቁኝ። የፌስቡክ ቻት ግሩፕ ከፍተን አብረን ጉዞውን እንጀምራለን።

ኑ፥ ከእግዚአብሔር ቃል ጋር አብረን እንጓዝ!!
#ለማንበብ_ፍቃደኛ_የሆናችሁ_ፍላጎታችሁ_በ❤️👏👍 ግለጹ።

🖋 Fresenbet G.Y Adhanom

5 Monate, 2 Wochen her

ስለ ኾነ የኾነ ጉደይ ነው እንዲሁም እኛም ወደዚህ ጊዜያዊ ሕይወት የገባነው ከዚያ በላይ ስለ ኾነ ጉዳይ ነው፤ ይኸውም ዘላለማዊ ሕይወት ነው። ወታደር ወደ ቤቱ መመለስን በደስታ እንደሚያስብ ኹሉ፤ ክርስቲያኖችም የሕይወታቸውን መጨረሻና ወደ አባታቸው ዓለም ወደ መንግሥተ ሰማያት መመለሳቸውን ሳያቋርጡ ያስባሉ።" ብሎ በምሳሌ ጥሩ አድርጎ በሕሊናችን ውስጥ የሕይወትን ዓላም በሥዕል መልክ ይቀርጽብናል።
(St. Nicholas of Serbia, Thoughts on Good and Evil)።

ሌላው የሕይወት ዓላማ ምስጋና ነው። ምስጋና ቅዱሳን መላእክትን የምንመስልበት፣ የእግዚአብሔርን ቸርነት የምናደንቅበት፣ ፍቅሩን እያሰብን የምንመሰጥበት የሕይወት ዓላማ ነው። ታላቁ ምስጋና በእያንዳንዳችን ገቢራዊ ሕይወት እግዚአብሔር እንዲታይ የምናደርግበት የየዕለት ሕይወት ያልተቋረጠ ምስጋና ነው። በሰማይ ላይ ፀሐይ እንደሚወጣ በእውነተኛ ክርስቲያን ሰውነትም ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስ ይወጣል። በብዙ አለማስተዋልና ተስፋ መቍረጥ ተቀጥቅጠው ሊወድቁ ያሉትንም እግዚአብሔር በእውነተኛ ምስጋናችን በኩል ኾኖ ወደ ራሱ ይጠራቸዋል። እውነተኛ የክርስትና ሕይወት ያልተቋረጠ የምስጋና ሕይወት ነው። ስለዚህ በዚህ ውስጥ ያለ ሰው በራሱ ሕይወት ተስፋ የመቍረጥ በሽታን አያኖርም። እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ይክፈትልን ከክፉ ኹሉም ይጠብቀን አሜን። https://t.me/BetMetsahfte

5 Monate, 2 Wochen her

++++++++#ለምን_ተፈጠርኹኝ?++++++++

የተፈጠርንበትን መሠረታዊ ዓላማ በአግባቡ መረዳት። ቢያንስ በመሠረታዊነት የተፈጠርነው ስለ ሦስት ጒዳዮች ነው ማለት ይቻላል። እኒህም፦ ፍቅር፣ ቅድስናና ምስጋና ናቸው። የእግዚአብሔር አንድነቱ ከሦስትነቱ የተስማማው በእርሱ ዘንድ ባለ ዘላለማዊ (Eternal) በኾነ ፍቅር ነው። እኛንም የፈጠረን አንዳች የኾነ ነገር ከእኛ ለማግኘት ብሎ አይደለም። ይልቅስ ለእኛ ካለው ጥልቅ የኾነ ፍቅር የተነሣ በቸርነቱ ፈጠረን። አዳምን ሲፈጥር በጎኑ ሔዋንን የተከለው ስለ ፍቅር ነው። ኋላም ከአዳም ጎን ሔዋንን ያስገኘው ዓለም እግዚአብሔር በሰጠን ፍቅር ተጠቅሎ በአንድነት ይኖር ዘንድ ለማድረግ ነው። አዳም ሔዋንን ይህቺ አጥንቷ አጥንቴ፣ ሥጋዋ ሥጋዬ ነው፤ ከወንድ ተገኝታለችና ሴት ትባል ማለቱ የፍቅርን ትርጒም ሲገልጥ ነው። ፍቅር ማለት ራስን በሌላ ውስጥ ማግኘት ወይም ራስን ለሌላ መሥዋዕት አድርጎ ማቅረብ ነውና። በዚህም መሠረታዊ ምክንያት የሕይወት አንዱ ዓላማ ፍቅር ነው። ራስን መጥላት፣ በራስ ላይ ያልተገባ ውሳኔን መወሰን ይህን የፍቅር እውነተኛና ተፈጥሮአዊ መንገድ የሚጻረር አጋንንታዊ ነው። ሶሎሞን በመኃልየው "የውዴ ዓላማ በእኔ ላይ ፍቅር ነው" መኃ 2፥10 እንዳለው፤ ከዚህ ውጭ ኾነን መኖርን መምረጥ የለብንም። የሕይወት ትርጒም ወደ ምሬት የሚገለበጥብን ይህን ጉዳይ ሳንረዳ እንዲሁ ዝም ብለን በሥጋዊ ሐሳብ ተወጥረን ስለምንኖ ነው። በሕይወታችን ፍቅር ምን ያህል እንደ ተገፋችና ጥላቻ እንደ ሠለጠነች የምንረዳው ራሳችንን ለማጥፋት እንኳን ድፍረት እስከማግኘት መድረሳችንን ልብ ስንል ነው። ውድ ወንድም እኅቶቻችን ሆይ! አምላክ ሰው ኾኖ በግርግም መወለድን ስለምን የፈቀደ ይምሳላችኋል? ከፍቅር ወጥተን በጥላቻ መኖር የጀመርነውን እኛን ወደ ቀደመው የፍቅር አኗኗር ለማምጣት አይደለምን? በቃና ዘገሊላ ውኃውንስ ወይን ያደረገው በሕይወታችን የጠፋውን ወይን የተባለ ፍቅርን ሊሰጠን የመጣ መኾኑን እንድንረዳ አይደለምን? እንግዲያውስ ጥላቻን ተውትና ወደ ፍቅር ተነጠቁ።

ትክክለኛ በኾነ መንገድ የሕይወትን ዓላማ መረዳት ራስን ከማጥፋት ይልቅ ራስን ወደ መጠበቅ ይመራናል። የሞስኮው ፊላሬት የሕይወትን ዓላማ አስመልክቶ፦ "እያንዳንዱ ክርስቲያን ለራሱ ቅዱስ ለመኾን አስፈላጊና አበረታችን ነገር መፈለግ አለበት። ያለ ተጋድሎና ቅዱስ የመኾን ተስፋ የምትኖር ከኾነ፤ አንተ ክርስቲያን የኾንኸው በስም ብቻ ነው እንጂ በባሕርይው አይደለም። ነገር ግን ከቅዱስነት ውጭ ኾኖ ማንም ሰው ጌታን ሊያየው አይችልም፤ ይኸውም ማለት ዘለዓለማዊ ክብር ሊያገኙ አይችሉም ማለት ነው። ኢየሱስ ክርስቶስ የመጣው ኃጥአንን ሊያድን ነው ማለት ተገቢ ነው 1ጢሞ 1፥15። ነገር ግን ኃጢአተኛ ኾነን ሳለ የዳንን እንደ ኾነ አድርገን ካሰብን ራሳችንን እናታልላለን። ኢየሱስ ክርስቶስ ኃጥአንን ያደነው ቅዱሳን የመኾኛ መንገዱን በመስጠት ነውና።" ይላል። (St. Philaret of Moscow, Sermon of September 23, 1847)። ይህ የሊቁ አገላለጽ መኖር የሚገባን ቅዱሳንን ለመኾን መኾኑን በአጽንዖት የሚያሳስብ ነው። ክርስቶስ አምላካችን ሰው ኾኖ የተገለጠበት መሠረታዊ ምክንያትም እኛን ከኃጢአት አውጥቶ ወደ ቅድስና ለማስገባት ነውና። "ከእኔ ተማሩ" ብሎ መናገሩ በወንጌል መዘገቡ የእርሱን የአርአያነት ሥራ መሠረት አድርገን እንድንቀደስ ሲጋብዘን ነው። ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ፦ "ክፉ አኗኗርህን የምትተውና ወደ እግዚአብሔር የምትመለሰው ቅጣትን ከመፍራት የተነሣና ከቅጣት ለማምለጥ ብቻ ስትል ካልኾነ፣ ወይም ደግሞ የመልካምን ነገር ዋጋ ለማግኘት ብቻ ስትል (እንደ ምንደኛ) ከማድረግና የመልካም ምግባር ሕይወትን በሒሳባዊ ስሌትና ጥቅምን በሚያብሰለስል ራስ ወዳድ ሕሊና የምትለውጥና የምትነግድ ከመኾን ነጻ መውጣት እውነተኛ ፍጹምነት ይህ ነው። ኹሉም ነገር ለኛ የተዘጋጀና የተጠበቀልን ስለ መኾኑ የተነገረንን ተስፋ አምነህና ተማምነህ የሚያጨንቅህና የሚያሳስብህ ነገር ኹሉ ከእግዚአብሔር ፍቅር እንዳትለይ ብቻ ሊኾን ይገባል፤ የሕይወት ታላቁ መዳረሻና የዳርቻ ፍጻሜ ከኾነው በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ ከመኖርና በእርሱ የተወደደ ከመኾን የሚበልጥ አንዳችም ነገር የሌለ መኾኑን አስተውለህና ተረድተህ ብትኖር ታላቁ ፍጹምነት ማለት ይህ ነው።" እያለ እንዴት መኖር እንዳለብን ይመክረናል። (ያረጋል አበጋዝ (ዲ/ን)፣ መድሎተ ጽድቅ ቅጽ አንድ፣ 2007 ዓ.ም፣ ገጽ 116-117)። የሕይወት መዳረሻ ሊኾን የሚገባው ቅዱስ ጎርጎርዮስ እንዳለው በእግዚአብሔር ፍቅር ውስጥ መኖር ነው። የተፈጠርነው ስለ ፍቅር እንደ ኾነ ኹሉ ልንኖርም የሚገባን ስለ ፍቅርና በፍቅር ነው። ክርስቶስን እኛን እስከ መስቀል ሞት የወደደን እኛ እርስ በእርሳችን በፍጹም እንዋደድ ዘንድ ነው።

ሰማዕቱ ኦንፊራይ ጋጋሉክ ቅድስና ኹላችንም የተጠራንለት የሕይወት ዓላማ መኾኑን ሲገልጽ፦ "ቅድስነት ማግኘት አንዳንድ ሰዎች እንደሚያስቡት የመነኮሳት ጒዳይ ብቻ አይደለም። ቤተሰብ ያሏቸው በዚህ ዓለም በተለያዩ ሞያዎች የሚኖሩ ሰዎች በሙሉ ለቅድስና ተጠርተዋል። ስለ ፍጽምናና ቅድስና የተሰጡ ትእዛዛት የተሰጡት ለመነክሳት ብቻ ሳይኾን ለሕዝብ ኹሉ ነውና።" ይላሎ። (Hieromartyr Onuphry Gagaluk)። ስለዚህ ኹላችንም የተጠራነው ለቅድስና መኾኑን ልናስተውል ይገባል። ውድ ወንድሜ ሆይ አንተ የተጠራኸው ለቅድስና መኾኑን አስተውል። ወጥረው የያዙህ እና ራስህን ወደ ማጥፋት ገፍተው የሚወስዱ ጒዳዮች ላይ ከምታተኩር ይልቅስ ስለ ሕይወትህ መቀደስ አስብ። በዚህ ዓለም ምንም ነገር አሌተሳካልኝም አትበል፤ የሕይወት ዋና ዓላማው መቀደስ ነውና፥ አኹን ከዚህ ሰዓት ጀምረህ ወደ ቅድስና መግባት እንደምትችል አስተውል። እኔ ረክሻለሁኝ ክፉን ነገር ማቆም አልችልም አትበል ይልቅስ በመስቀል ላይ በሕይወት መጨረሻ ላይ ወደ በጎነት የተቀየረው የቀኙኝ ሽፍታ አስበው። በመጨረሻዋ ሰዓት ወደ መልካምነት ሲመጣ ጌታም በፍቅር እንደ ተቀበለው አስተውል። አንተም እንዲህ መኾን የምትችል መኾንህን ከልብህ አምነህ አሐዱ ብለህ ጀምር።

ቴኦፋን እንዲህ ይላል፦ "የሕይወታችን ሥሙር መጨረሻው ከእግዚአብሔር ጋር በአንድነት መኖር ነው። የእግዚአብሔር ልጅ ሥግው የኾነው በኃጢአት ምክንያት ውድቀን ያጣናትን ከእግዚአብሔር ጋር የነበረችንን አንድነት ሊመልስል ነው። የእግዚአብሔር ልጅ በኾነው በኢየሱስ ክርስቶስ ከአብ ጋር ኅብረት ወደማድረግ እንገባል፤ ስለዚህም የሕይወትን ዓላማ እናገኛለን።" ይላል። (St. Theophan the Recluse, Letters to various people, 24)። እንግዲህ ይህ ሊቅ ደግሞ የሕይወት ዓላማው ከእግዚአብሔር ጋር የሚኖረንን ኅብረት ማግኘት ነው። ከእግዚአብሔር ከተለየን ከእውነተኛ የሕይወት ዓላማ ውጭ ኾነናል ማለት ነው። በምንም መንገድ ቢኾን ከእርሱ እቅፍ ልንወጣ አይገባንም። እግዚአብሔር ኹል ጊዜም አብረነው እንድንኾን ይፈልጋል። ኃጢአተኛ ነኝና እንዴት ከእርሱ ጋር መኖር እንችላለሁኝ አትበል፤ ይልቅስ ከእርሱ ጋር መኾንን ከውስጥህ ፈልጋት ያሌ እርሱ ራሱ ከኃጢአትህ አንጽቶ ካንተ ጋር መኾኑን ይገልጽልሃል። የሰርቢያው ኒቆላስ ደግሞ "ሰዎች ወደ ጦርነት የሚገቡት በጦርነቱ ለመደሰት ሳይኾን ከጦርነቱ ለመዳን እንደ ኾነ ኹሉ እኛም ወደዚህ ዓለም የገባነው በዚህ ዓለም ለመደሰት ሳይኾን ከዚህ ዓለም ለመዳን ነው። ሰዎች ወደ ጦርነት የሚገቡት ከጦርነቱ በላይ

5 Monate, 2 Wochen her

#ስለ_ቅዱስ_ሚናስ **አዲስ ዝማሬ " ማር ሚና " ዘማሪት ሲሰተር ሕይወት ተፈሪ mar mina

Video ውን ከፈለጋችሁ
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇**https://youtu.be/IZc9_v6IxFU?si=-EAZm_XflLD1OlIGhttps://t.me/BetMetsahfte

5 Monate, 3 Wochen her

♦️ራሴን እንዳላጠፋ 📍ያገኘሁት መፍትሄ📍ክፍል ኹለት♦️
https://youtube.com/watch?v=sCnyBDKLhMg&si=z5oZGpg4ZQGu4cyi https://t.me/BetMetsahfte

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 4 days, 3 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 days, 2 hours ago

በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።

Last updated 10 months, 1 week ago