አርጋኖን መጻሕፍት መደብር ARGANON BOOK STORE

Description
#የኅብርቱዋናዓላማ

፩.መንፈሳዊ መጻሕፍትን በዓላማ፤በእቅድ እንድናነባቸው፤እንድናስነብባቸው በሕይወታችን ትርጉም እንዲኖራቸው ማድረግ።

፪.ከቤተሰቦቻችን፤ዘመዶቻችን፤ወዳጆቻችን ስላነበብናቸው መጻሕፍት እነሱም ስላነበቡት መጻሕፍት ውይይት የማድረግ ልምድን ማዳበር።
፫.አንባቢ ትውልድ መፍጠር። ለአስተያየትዎ @orthokiha ይጻፉ።
https://t.me/BetMetsahfte
Cross @dawitfikr
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 4 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month, 3 weeks ago

በዲን ዮሐንስ ጌታቸው
#ዐይነ_ልቡና_የተሰኘ_አዲስ_መጽሐፍ_በቅርብ_ይጠብቁን

#በእግዚአብሔር_ፈቃድ_የትምህርተ_ጽድቅ_ቅጽ_ኹለት_ዐይነ_ልቡና_የተሰኘ_መጽሐፍ_በቅርቡ_በእጃችሁ_ይገባል

በዚህ መጽሐፍ ውስጥ አራት ክፍሎች አሉት። የመጀመሪያው ክፍል ነገረ ሥጋዌን ይመለከታል። በዚህ ክፍል ውስጥ በነገረ ሥጋዌ ውስጥ የተወሰኑ የአገላለጽ ውዝግቦችን በተመለከተ እንዴት መረዳት እንዳለብን ተዳስሷል። እንደ መነሻ ይኾን ዘንድ ታስቦ ነገረ ሥጋዌን የተመለከተ መጠነኛ ገለጻ ከማድረግ ጀምሮ በነገረ ሥጋዌ ውስጥ ልንጠነቀቃቸው የሚገቡ አገላለጾችን በተመለከተ ማብራሪያ ቀርቧል። ነገረ ሥጋዌ እጅግ መሠረታዊ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ስለ ኾነ በጥንቃቄ ሊታይ እንደሚገባ ከማሳሰብ ጋር ውዝግብ ያሥነሱ ጉዳዮችን ለማጥራትና ወጥ አረዳድ እንዲኖረን ለማገዝ ጥረት የተደረገበት ክፍል ነው። ይህን ክፍል በጥንቃቄ ያነቡት ዘንድ በትሕትና እጠይቃለሁኝ።

የመጽሐፉ ኹለተኛው ክፍል ምሥጢረ ጥምቀትን ይመለከታል። በዚህ ክፍል ውስጥ መናፍቃን ምሥጢረ ጥምቀትን በተመለከተ የሚያነሷቸውን ጥያቄዎች በቅደም ተከተል የተመለሰበት ክፍል ነው። ይህም ጉዳይ እጅግ በጣም መሠረታዊ ጉዳይ ነው። ምሥጢረ ጥምቀት ላይ የተዛባ አረዳድ ካለን ወደ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መግባት አንችልም። ወደ ቤተ ክርስቲያን መግቢያ በሩ ምሥጢረ ጥምቀት ነውና። ምእመናን በዚህ መሠረታዊ የክርስትና የምሥጢር ትምህርት ላይ የጠራ መረዳት እንዲኖራቸውና ከመናፍቃን ክሕደት ልቡናቸው እንዲጠበቅ ደጋግሞ መልስ መስጠቱ ተገቢ ነው። በመኾኑም በዚህ መጽሐፍ ኹለተኛ ክፍል ውስጥ "ያመነ የተጠመቀ ይድናል፣ ሐዋርያት ተጠምቀዋልን?፣ ጥምቀት በማን ስም ሊኾን ይገባዋል፣ የውኃ ጥምቀት አያስፈልግምን? ... የሕፃናት ጥምቀት አስፈላጊ ነውን?"  የሚሉ እና መሰል ጥያቄዎች ተመልሰውበታል። የዚህ ክፍል መደምደሚያ የሐሰተኛ አጥማቂዎችን መለያ በማብራራት ያበቃል።

ክፍል ሦስት ደግሞ የክህነት የመጀመሪያ ደረጃ የኾነውን ዲቍናን የሚመለከት ነው። በዚህ ዘመን ሰይጣን በክፉዎች እያደረ እንዲቃለል እያደረገ ካላቸው ዐበይት ነገሮች ውስጥ አንዱ ክህነት ነው ማለት ይቻላል። ክህነት እጅግ በጣም ሊከበር የሚገባው ታላቅ ምሥጢር ነው። በብዙዎቻችን ዘንድ በተለያዩ ምክንያቶች መነሻነት ክህነት ተገቢውን ክብር እያጣ ያለ ይመስላል። ይህ በእርግጥ በአንድ በኲል የክህነት አገልግሎትን ከሚፈጽሙ አካላት ችግር የተነሣ የመጣ ሲኾን በሌላ በኲል ደግሞ እኛ ምእመናንም ስለ ክህነት ካለን የግንዛቤ እጥረት የተነሣ ነው። ከዚህ በተጨማሪ ከውጭም ያሉ አካላት ክህነት እንዲጠላ በተለያዩ መንገዶች ብዙ ጥረቶችን አድርገዋል። ክህነትና የክህነት አገልግሎትን የሚፈጽሙ ካህናት በአግባቡ እስካልተከበሩ ድረስ ክርስቶስ አምላካችን የሠራልንን የድኅነት መንገድ በአግባቡ ማግኘት አንችልም። ክህነት ከተጠላ ምሥጢራትን በየት በኲል አግኝተን ወደ ድኅነት ልንገባ እንችላለን? ስለዚህ ከምንም በላይ ክብረ ክህነት እንዲጠበቅና ካህናትም አርአያ ክህነታቸውን ጠብቀው እንዲያገለግሉ ኹላችንም የበኩላችንን አስተዋጽኦ ልናበረክት ይገባል። በዚህ መሠረታዊ ምክንያት በዚህ መጽሐፍ በሦስተኛው ክፍል የዲቍናን ክብርና እንዴት ሊሰጥ እንደሚገባው ማብራሪያዎች ቀርበውበታል። ዲቍና ከተስተካከለ ሌሎቹ የክህነት ደረጃዎች የመስተካከል ዕድላቸው በእጅጉ ከፍ ያለ ይኾናል። ዲቍና ከተበላሸ ቅስናም ያን ተከትሎ የሚመጣ ነውና የመበላሸት ዕድሉ ሰፊ ይኾናል።

የዚህ መጽሐፍ የመጨረሻው እና አራተኛው ክፍል የተለያዩ ጉዳዮችን የያዘ ነው። በዋነኛነት በእናታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ንጽሕና ጉዳይ የሚያትት ነው። አንዳንድ ሰዎች የእመቤታችንን ንጽሕናና ከማኅፀን ጀምሮ የመጠበቋን ጉዳይ ላለመቀበል ብዙ ምክንያቶችን ሲያነሡ ይታያል። የቅድስት ድንግል ማርያም ሰውነት ከማኅፀን ጀምሮ በመንፈስ ቅዱስ የተጠበቀ እና ለወልድ ሥጋዌ ተለይቶ የተዘጋጀ መኾኑን በተለያዩ መረጃዎች ያቀርባል። እርሷ መርገመ ሥጋ መርገመ ነፍስ የሌለባት በረከተ ሥጋን በረከተ ነፍስን ከልጇ ዘንድ እያማለደች የምታሰጥ፣ የጎሠቆለ የአዳም ባሕርይ ያልደረሰባት፣ ንጹሕ ዘር መኾኗንና አካላዊ ቃል በሥጋዌውም ከእርሷ የነሣው ሰውነት ቅዱስና ከመርገም የተጠበቀ መኾኑን በዝርዝር ለማስረዳት የተሞከረበት ክፍል ነው። በዚህ ክፍል የመስቀልን ክብር በተመለከተ፣ የቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊን መጨረሻ በተመለከተ አርፏል ወይስ ተሰውሯል? የሚለውን በተመለከተና ለአብርሃም የተገለጡት ሦስቱ ሰዎች እነማን ናቸው የሚለውን በአበው አረዳድ ለማቅረብ ተሞክሯል።

#እባክዎትን_ለብዙዎች_እንዲዳረስ_በማድረግ_ሓላፊነትዎን_ይወጡ🙏🙏🙏

1 month, 3 weeks ago

#የምሕረት_በር_የመጽሐፍ_ዳሰሳ በወንድማችን Fitsum A Abraham

የመጽሐፍ ዳሰሳ/ Book review
     "የምሕረት በር- አንቀጸ ምሕረት"

በቤተ ክርስቲያን አገልግሎታቸውና በ"ፍካሬ ሞት ወሕይወት" በ "ጾምና ምጽዋት" መጽሐፋቸው በምናውቃቸው መምህር ቃኘው ወልዴ የተጻፈው   "የምሕረት በር" ወይም "አንቀጸ ምሕረት" የተሰኘው መጽሐፍ ርእሰ ጉዳዩን በትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ያደረገ ሥራ  ነው። "የምሕረት በር" በ 533 ገጾች የተከተበ ድርሳን ሲሆን በውስጡም ስድስት ምዕራፎችን ይዟል።  በምክንያተ ጽሑፍነት የቀረበው #የዲያቆን #ብርሃኑ_አድማስ "ከገጠመን ችግር ለመውጣት በፍጥነት ልናደርገው የሚገባን ምንድን ነው?" በሚል ርእስ ከሦስት ዓመት በፊት በወርኃ መስከረም ማኅበራዊ ትሥሥር ገጽ #Facebook ላይ የቀረበ ጽሑፍ ነው።

መምህር ቃኘው ወልዴ ይህ የመምህር ብርሃኑ አድማስ ጽሑፍ ከልባቸው እንደገባና በትንቢተ ዮናስ ላይ በእነ ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ፣ በቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ በቅዱስ ሄሮኒመስን (ጄሮም)፣ በቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያ እና መሰል ጸሐፊያን የተጻፉ የትርጓሜ ድርሳናትንና ጥናታዊ ሥራዎችን አሳድደው በጥልቀት እንዲያነቡ እንዳነሣሣቸው፣ በመጨረሻም በዚህ ሒደት ውስጥ "የምሕረት በር" የተሰኘው መጽሐፋቸው ተፀንሶ ለመወለድ እንደበቃ ይገልጻሉ።

እኔ ከዚህ በታች ለማስቀመጥ የምሞክረውን ዳሰሳ ብፁዕ አቡነ ኤርምያስ የመጽሐፉ ሽፋን ላይ በአጭሩ በዕውቀትና በጥበብ በጥቂት ቃላቶች ለደራሲው የሚገባ አጭር አስተያየት (blurb) አስቀምጠዋል። መምህር ያረጋል አበጋዝ ደግሞ ከአሥር ገፅ በላይ ወስዶ መቅድሙን ድንቅ አድርጎ ጽፎታል። "የምሕረት በር" መታሰቢያነቱን ያደረገው ለብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቄርሎስ ስድስተኛና ለቅርብ ወዳጃቸው ለሰማዕቱ ቅዱስ ሚናስ ነው።

"የምሕረት በር" የመጀመሪያው ምዕራፍ ስለ ትንቢተ ዮናስ መጽሐፍና በአሕዛብ ስላለች ቤተ ክርስቲያን፣ ስለ ነብዩ ዮናስ ማንነት፣ ስለ ነነዌ የደም ከተማነት፣ በመጽሐፉ ጸሐፊ ላይ ስለሚነሡ ውዥንብሮች፣ ስለ ትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ አጠቃላይ ይዘትና የአጻጻፍ ባሕርይ ይዳስሳል። ምዕራፍ ሁለት ትኩረቱን በነቢዩ ዮናስ ላይ አድርጎ ከእግዚአብሔር ስለተላለፈለት ትዕዛዝ፣ ወደ ተርሴስ በምታመራ መርከብ ስለመኮብለሉ፣ ስለተነሣው ታላቅ ነፋስ፣ የመርከቡ አለቃ በውስጠኛው የመርከቢቱ ክፍል ተኝቶ ወደነበረው ነቢዩ ዮናስ ቀርቦ፣ ከእርሱ ጋር  ስለ ተለዋወጣቸው ቃላት፣ ስለ ወጣበት ዕጣ፣ ወደ ባሕር ስለ መጣሉ ነገር ያለውን አንድምታ ገልጦ ያስረዳል።

ምዕራፍ ሦስት ነቢዩ ዮናስ በባሕር ውስጥ እያለ ስላቀረበው መሥዋዕት ይተርካል። እግዚአብሔር ታላቅ ዓሣ አንበሪን ስለ ማዘዙ፣ በአንበሪ ከርሥ ውስጥ ስለ ጸለየው ጸሎት ውስጠ ምሥጢር ያትታል። ምዕራፍ አራት ዓሣ አንበሪው በደረቅ የብስ ላይ ነቢዩን ከተፋው በኋላ ከእግዚአብሔር ዘንድ ዳግመኛ ወደዮናስ ስላመጣው መልእክት ያስተምራል።

ከዚያም ነቢዩ ዮናስ ወደ ኃጢአተኛዋ ከተማ ገብቶ "ነነዌ በሦስት ቀን ውስጥ ትገለበጣለች" በማለት በአደባባይ አሰምቶ ስለሰበከው  አስጨናቂና አስፈሪ ስብከት፣ ነነዌ የነቢዩን ቃል ሰምታ ከንስሓ ጋር ስላወጀችው ጾም፣ ስለንጉሡ ዐዋጅ፣ ስለለበሰችው ማቅ፣ በላይዋ ላይ ስለነሰነሰችው አመድና ትቢያ፣ ስለተቀበለችው ምሕረት፣ በወለተ ያዕቆብ ላይ ስለፈረደችው ፍርድ፣ እኛም እንደሀገር፣ እንደሕዝብ፣ እንደግለሰብ ልንሸሸው ስለሚገባ ቀቢጸ ተስፋ በስፋት ይነግረናል።

ምዕራፍ አምስት ነነዌ ባገኘችው ምሕረት ስለተከፋው ነቢዩ ዮናስ፣ ስለገጠመው ኀዘን፣ ወደ እግዚአብሔር ስላቀረበው አቤቱታ አዘል ጸሎት፣ እግዚአብሔርም ስለሰጠው ምላሽ በምልዓት ያትታል። ምዕራፍ ስድስት የነነዌን ታሪክ ይዞ ወደ ኢትዮጵያና ሕዝቦቿ ይመጣል። የሰብአ ነነዌን ንስሐና በእነርሱ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖችን በንጽጽር እያመለከተ ገንዘባችን ልናደርገው የሚገባንን የንስሓ ፍሬ ያመላክተናል።

በነቢዩ ዮናስ አንደበት ተገብቶም በቅድሚያ በትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ለሚነሡ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት መንገድ ይጠርጋል። ከዚያም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባቶች እስከ ምዕመናን በሀገረ ኢትዮጵያ ከመጣው የመከራ ዘመን እንደነነዌ ብሔራዊ ምሕረትን አግኝተን እንድን ዘንድ እያንዳንዳችን ልንፈጽመው የሚገባውን የንስሐ ተጋድሎ፣ ከመንፈሳዊ ምክረ ሀሳቦች ጋር ያስረዳናል።

በአጠቃላይ አንቀጸ ምሕረት (የምሕረት በር) ርእሰ ጉዳዩን በትንቢተ ዮናስ ላይ ያድርግ እንጂ ከነነዌ ጾም ባሻገር ለጥፋት ለተቃረበች ለየትኛዋም ሀገርና ሕዝቦች ታላቅ ትምህርትን የሚያስጨብጥ ድርሳን ነው። እንደ እኔ በኃጢአት ፍላጻ ለቆሰለች ነፍስም በመራራ ስብከቱ የሚያሽራት ፍቱን መድኃኒቷ ነው።

መጽሐፉ በቅዱሳን ሐዋርያነ አበውና በቤተ ክርስቲያናችን ሊቃውንት የተጻፉ አያሌ መጻሕፍትን በማጣቀሻነት ተገልግሏል። ስለዚህም በትንቢተ ዮናስ መጽሐፍ ላይ ተበታትነው፣ በብዙ የንባብ ድካም የሚገኙ መጻሕፍትንና መጣጥፎች በአንድ ገበታ ላይ እንድናገኝ ዕድል የሚሰጥ ነው። ይህም የመምህር ቃኘው ወልዴን "የምሕረት በር" መጽሐፍ በትንቢተ ዮናስ ዙሪያ ከተጻፉ ውብ ድርሳናት መካከል በሀሳብ ጥልቀቱ ተጠቃሽ የትንቢተ ዮናስ አንድምታ (commentary) ሥራ እንዲሆን ያደርገዋል።

"የምሕረት በርን" ገዝተን ስናነብ ሰሜን ወሎ የሚገኘውን የዳውንት ሁለገብ ጉባዔ ቤት ግንባታን እየረዳንም ነውና፣ የምሕረት በርን ለራሳችንም ለወዳጆቻችንም በስጦታ መልክ ስንሰጥ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እየመታን መሆኑ ልብ ይላል።

መምህር ቃኘው ይሄን የመሰለ ብዙ የደከምክበትን ልጅህን ገፀ በረከት አድርገህ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን እንደሠጠህ በዘመንህ ሁሉ ክፉ አይንካህ። እናመሰግናለን ስለ መልካምነትህ ሁሉ። መልካም ንባብ!

#የምሕረት_በር_መጽሐፍ ዘወትር በመደብራችን በቅናሽ ዋጋ ያገኙታል።ይምጡ ይሸምቱ።

ለበለጠ @dawitfikr ይዘዙ።

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_4ኪሎ_ቱሪስትሆቴል_80ሜትር_ወረድብሎ_የቀድሞ_ሪፍትቫሊ_ዪኒቨርስቲ_ሕንፃ_ከኦሮሚያ_ሕብረት_ሥራ_ባንክ_አጠገብ_0954838117_0912044752_ይደውሉ

2 months, 2 weeks ago

መልካም ዜና!

ቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ በአዲስ መጽሐፍ ሊመጡልን ነው።

ቅዳሴ
ወደ ጌታ ደስታ የመግብያ ምሥጢር
!

የሚል ርዕስ ሰጠውታል። ከዚህ በፊት #አኰቴተ_ቊርባን የሚል መጽሐፍ ጽፈውልና።በብዝዎቻችሁ ተወዳጅ የሆነው ባለፈው ፮ኛ እትሙ አሳትመን ጥቂት ኮፒዎች እጃችን ይገኛሉ።ያላነበባችሁ አንብቡ።

ቅዳሴ ምንድነው? Linkን ተጭናችሁ 32 ገጽ በነፃ ታነቡ ዘንድ ጋብዘናል።ካነበባችሁ በኃላ ለሌሎች ማጋራት አትርሱ!!

👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
ቅዳሴ ምንድነው?
https://acrobat.adobe.com/id/urn:aaid:sc:VA6C2:890bc83d-dd0a-4e36-98f0-afc953221abb
🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏 https://t.me/BetMetsahfte

3 months, 3 weeks ago
[#እያከፋፈልን\_ነው](?q=%23%E1%8A%A5%E1%8B%AB%E1%8A%A8%E1%8D%8B%E1%8D%88%E1%88%8D%E1%8A%95_%E1%8A%90%E1%8B%8D)!

#እያከፋፈልን_ነው!
በብዙ ምዕመናን ጥያቄ በመምህር Henok Haile ፍቃድ ተወዳጅዎ #ቃና_ዘገሊላ መጽሐፍ 11ኛ ዕትም ለኅትመት በቅታለች።

በቃና ዘገሊላ መጽሐፍ ውስጥ ቅዱሳት መጻሕፍትን መሪ አድርገን በቃና ዘገሊላ ሰርግ ቤት ውስጥ እንመላለሳለን፡፡ ከጌታችንና ከሐዋርያቱ ጋር ወደ ሰርግ ቤቱ እንገባለን፡፡ ወደ ጓዳ ዘልቀን የወይኑን ማለቅ አስበን እንጨነቃለን ፣ እመቤታችን ስታማልድ ልጇም ሲማለድ እናያለን ፣ ከአገልጋዮቹ ጋር ውኃ ልንቀዳ ወንዝ እንወርዳለን፡፡ አብረን ውኃውን እስከአፉ ሞልተን ጌታችን የሚያደርገውን እንጠብቃለን፡፡ ከታዳሚዎች ጋር ወይን የሆነውን ውኃ ቀምሰን እናደንቃለን፡፡ መልካሙ የወይን ጠጅ ምነው እስካሁን ቆየ? ብለን ከአሳዳሪው ጋር አብረን እንቆጫለን፡፡ ከዚያም ከሐዋርያቱ ጋር በስሙ አምነን ከሰርግ ቤቱ እንወጣለን፡፡ ከምድራዊው ሰርግ ቤት ወጥተንም ወደ የቤታችን ሳንገባ ወደ ሌላ ሰማያዊ ሰርግ በዚሁ መጽሐፍ ውስጥ እንታደማለን፡፡

የሽፋን ዋጋ 250ብር

ዋና አከፋፋይ
አርጋኖን መጻሕፍት መደብር Areganon Book Store
0954838117/0925421700

ለማዘዝ @dawitfikr ያነጋግሩ።

አድራሻ፡

#አርጋኖን_መጻሕፍት_መደብር_4ኪሎ_ቱሪስትሆቴል_80ሜትር_ወረድብሎ_የቀድሞ_ሪፍትቫሊ_ዪኒቨርስቲ_ሕንፃ_ከኦሮሚያ_ህብረት_ሥራ_ባንክ_አጠገብ_0954838117_0912044752_ይደውሉ

4 months ago
6 months, 3 weeks ago

በመምህር ያረጋል አበጋዝ የተዘጋጀ።

6 months, 4 weeks ago
7 months ago
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 7 months, 4 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 3 weeks ago