Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

Miki market and poem

Description
Ⓙⓞⓘⓝ በሉ
@satsun273
@Satsun273_bot
@mikiendialem
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 1 day ago
3 weeks, 1 day ago

እዚ ላይ ገብታቹ vote አድርጉኝ🙏🙏🙏

1 month ago

እንደ አንድነታችን
አንድ ነው ምክንያቱ ለአብሮነታችን
ለመለያየት ግን ለሆድና ጀርባ
እልፍ ሰበብ አለን ለልዩነት ካባ
...........

በሌት ፍቅር ቀጥፎ ቀን መጾም ማስቀደስ
በተላጠ ቁስል ሚጥሚጣ መነስነስ
በዝምታ ውሎ በበደል መከሰስ

ቢሆንም.....
ስብራቴን ስውር ጉዳትህን እብስ
ውዴ አንጠለል ዝናብ ላይ እናልቅስ።

  ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

3 months ago

የዛሬ ሶስት አመት ቀጥሬሽ ነበረ
በንፁህ አፍቃሪ ልብ ስላንቺ በኖረ
ትመጣለች እያልኩ መንገድ መንገድ አየሁ
አርፍዳ ነው ብዬ ራሴን አፅናናሁ ስጦታ ገበየሁ
ነገሩ ወዲህ ነዉ ለካ አንቺ ቀርተሻል
ፍቅር እየራበኝ ጥጋብ ወጥሮሻል
ቆይ እኔ የምለው
ያዙኝ ልቀቁኝ ነው ምንድነው መንቀልቀል
ይዤ ለቅሻለው ከንግድባንክ ህንፃ እኔም የከፋኝ ቀን
ብዬ
አምርሬ ዝቼብሽ እንድትመጪ አልሻም
ፍቅር በውድ እንጂ በግድ አያረካም
ደግሞ ይሄን መልክ ይዘሽ ልትኮሪ ያምርሻል
እስኪለመድ ድረስ ስንቴ ፌንት ያስበላል
ስንት መስታወቶች ፊትሽን ሲያዩ ደንግጠው ደቀዋል
ፀጉርሽን አይተሻል
በሽምግልና እንጂ መች በሻጤ ይያዛል
የመሸሹስ ነገር አይወራ ከቶ
ግንባርሽ ወቶ ነው ወይስ ፀጉርሽ ገብቶ
ደሞ ካንቺም ብሶ ቆንጆ ቆንጆ ልጆች መውለድ አስበሻል
ቆይ እስኪ በዚ ፊት ቆንጆ ይወለዳል
ቀጥሬሽ ከቀረሽ
ሸራፋ ሚስት ሁኚ ሸራፋ ባል ይስጥሽ
የምቶልጂውን ልጅ የፊት ጥርስ ይንሳልሽ
እያልኩኝ መራገም አንደበቴ አይፈቅድም
ጨዋ የጨዋ ልጅ ነኝ ስድብ እኔ አላውቅም
ደግሞ
ከ15 ቀን በፊት አዲስ ጉድ ነገርሽኝ
ላገባ ነው አልሽኝ
ከፊል አዘንኩልሽ ከፊልም ጨከንኩኝ
ብርታት እዲሆነኝ በፍቅሬ እንድቶድቂ መመኘት ቀጠልኩኝ

ፍቅሬን ከድተሽዋል ጴጥሮስ ክርስቶስን ሶስቴ እንደከዳው
አለመፈቀሬን እንደምን ልረዳው
እንዴት እሺ ልበል
እንዴትስ ልቀበል
በቀል አያስቡ ሞኝ ያደርጋል ማፍቀር

ይቅር መወሻሸት ይቅር መነቃቀፍ
ይቅር መተቃቀፍ
ይቅር የውሸት እንባ ይቅር መነፋረቅ
አንቺን ደስ ካለሽ ይቅር መነፋፈቅ
አላስገድድሽም
በከፋ ጭካኔ ቆዪም አልልሽም
እኔ ግን ፈራሁኝ
የመጨረሻችን ሊሆን ነው መሰለኝ
ከማግባትሽ በፊት የምልሽ ቃል አለኝ

ከኔ ከበለጠ የወደድሽው ምርጫሽ
ለመታማት እንኳን አይመች አፍንጫሽ
ይደፍጠጥ ይቀበር
ቅልጥምሽ ይሰበር
ልክ እንደ ሽንብራ የተጠቀለለው ከርዳዳ ፀጉርሽ
መላጣ ይሁንልሽ
ጊሽጣ ልጅ ውለጂ
በሰውዬሽ ምክንያት በቶሎ እበጂ
ግን ስለማፈቅርሽ ብዙ እንዳትጎጂ።

  ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ&
            ፀጋው

3 months ago

ከየት ነኝ? ምንድነኝ? ጥያቄ
በማንነት ቀውስ ወድቄ
ከመልስ አልባ ባህር ስቀዝፍ ስንሳፈፍ
ቆሽሼ ስፀዳ እየፀዳው ሳድፍ
አንድ እውነት አገኘው
ለጥያቄ ሁሉ መልስ እንደማይኖረው
ሌላኛውም አለ
በጊዜ ወረቀት የተጠቀለለ
ሶስተኛውም ገባኝ
ነገር ግን አሳጣኝ
መድሀኒት ቀምሞ ፈውስ ባይነሳቹም
አንዳንድ እውነታዎች ለልብ አይመቹም።

✍️ ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

3 months, 2 weeks ago

የሚያውቁሽን ሁሉ ሰዎች ጠይቃለው
እንዴት ነች እላለው
ፈክታለች ይሉኛል አበባ መስላለች
ነጭ ጥለት መስላ ደምቃ ትውላለች
ሳቅ አይጠፋ ከሷ መከፋት የት አውቋት
ግሩም ድንቅ ፍጥረት ህይወት የቀናቻት

ብለው አወጉልኝ አላውቅሽ ይመስል
ምን ብዬ ላስረዳ የህይወትሽን ምስል
የሳቅሽን ትርጉም የጀርባሽን ቁስል
በረጋ ሳቅሽ ውስጥ ያለውን ረብሻ
ቁርጥ የሚመስለው የእብድ ውሻ ንክሻ

ደግሞም ሰምቻለው
እንዴት ነው ትያለሽ
ሰው ትጠይቂያለሽ
እንዴት ነኝ ይሉሻል
ምን ያጫውቱሻል

ከስቶ አዝኖ ጠቁሮ
ህልሙ ተበትኖ አንገት አቀርቅሮ
ተስፋ ይሉት ነገር እንደ ጉም እርቆት
ለነፍሱ ሲታገል የጠጣው ውሀ አንቆት

ወይንስ
ፏ ብሎ ዘንጦ በጌጥ ተሽቀርቅሮ
ለሰው ሰላምታ አይሰጥ ኮርቶ ተጀንኖ
አቤት አረማመድ መራመድ እንደሱ
ምቹ ናት መኝታው ስኬት ናት ትራሱ
ይነግሩሻል አይደል
ሲሉት እንዴት አይቀል
ግን አንቺ አይጠፋሽም
ለሰው ብመሰጥር ከራሴ አልሸሽም

ያው እነሱ እንዳሉት
ልክ እንደተረዱት
አንቺማ ደህና ነሽ እኔም አልከፋኝም
ህመምሽ ህመሜን ፈዋሽ አናገኝም

ውዴ
ሰው በጠፋ ጊዜ ከሰው ከምትሸሺ
እንባሽን አታውጪ ወደ ውስጥ አልቅሺ።

      ተጻፈ በአብዱ የእሙዬ ልጅ

7 months ago

ከእለታት አንድ ማታ!
(በእውቀቱ ስዩም)

ነግቶ፥ ተነሳሁኝ ካልጋየ
ከሰገባው የሚመዘዝ ፤ የንጉስ ሰይፍ መስየ
የሚያብረቀርቅ ፊቴን
የተትረፈረፈ ጉልበቴን
ያዝኩና ከቤቴ ወጣሁ
ቡናየን በደስታ ጠጣሁ፤

የማለዳ ቡናየ ጢስ
እንደ ንግስት እሌኒ ደመራ
ወደ ምኞቴ አቅጣጫ ፥ ልቦናየን ሲመራ
ሺህ እቅዶች ነድፌ
ለሺህ ትግል ተሰልፌ

እምነት ኖሮኝ ፤ ቁና ሙሉ ሰናፍጭ ያክል
ከስጋጃ ልቆጥረው፥ የመንገዴን መሰናክል
ለድል ተሰናድቼ
ደረቴን ለመዳልያ፥ ኪሴን ላዱኛ አጭቼ
ጅንን እንዳልኩ፥ እንደኮራሁ
ወደ ኑሮ ተሰማራሁ፥

ከዚያ ትንሽ ቆይቶ
የሰከነው ጎዳና፤ በትርምስ ጨቅይቶ
እንቅፋት ከየቤቱ ፥ እንደ ጥራጊ ወጥቶ
አሳር እና አሳርኛ ፥ በየርምጃው ተሰጥቶ
ሳፊው አየር ተበርዞ
የኑሮ ሰልፍ ረዝሞ፤
ወረፋው ተበውዞ
ደረስሁ ስል እየጀመርሁ
በርምጃየ ጣልቃ መሀል፥ የምቧይ ጡቤን እየከመርሁ
የምችለው ባይሳካ፥ የማልችለውን ሞከርሁ::

ከዚያ መሼ
የተረፈ ተስፋየን ፤ እየቀበርሁ አፈር ምሼ
ድምጤን አጥፍቼ አነባሁ፤
እንደ ሰይፍ ተመዝዤ ፥ እንደ ቀንዳውጣ ገባሁ ::

Join us

7 months, 1 week ago
Miki market and poem
7 months, 1 week ago
Miki market and poem
7 months, 1 week ago
Miki market and poem
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago