በረካ☺️☺️☕️

Description
በረካ 😊😊☕

እዚህ Channel ላይ ያስተምራሉ ያዝናናሉ ብለን የምናስባቸውን
🎯 መፅሀፎች
🎯ተከታታይ ልቦለድ
🎯ግጥም
🎯ፍልስፍና
🎯ምክር
የተለያዩ PDF መፅሐፍት እንደፍላጎቶ አሉ
https://t.me/abolbere
We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik

1 year, 7 months ago

.... ሆድ ሲብስ ሲከፋን
መሄጃ ሲጠፋን....
እንደ ወጀብ ሆኖ ሰው ሁሉ ሲገፋን....

ከአበቦች ማሳ ፅጌሬዳ ቀጥፎ
አይዟቹ የሚለን እንደ እናት አቅፎ...

ግን አንድ ሰው አለ.......
እሱን ሰው ናፈኩት አምጡልኝ የት አለ??

ቸኮ

1 year, 7 months ago

...you're going to make it😊

...God in on ur side🥹

1 year, 7 months ago

... Best way of save money😃..
leave ur wallet at home😌

1 year, 10 months ago

.......ልጠጣ አንድ ቢራ ሀሳብ እንዲቀለኝ
ሶስት ልድገምበት ስምህ እንዲጠፋኝ
ልድገም ሰባተኛ መልክህ ትዝ እንዳይለኝ
አስር ይሙላ እንደውም ጭራሽእንድረሳህ
12ስደርስ በሌላ እንድተካህ
ይምጣ 15ቱ እንደጠፋህብኝ ደውዬ እንድነግርህ
ሌላ ልጠጣበት
አለማንሳትህን እንዳስብበት
ይጨመር ይጨመር ተተኪህን ልሳም
ሽታህን ብረሳው አብሬው ልጋደም
እሰይ ተመስገን ነው ደሞ እስኪነጋ አላስታውስክም

ስማግጥ ሰክሬ?

ቸኮ

1 year, 10 months ago
...ለረከሰው ቆዳ ቆዳ እያዋደደ

...ለረከሰው ቆዳ ቆዳ እያዋደደ
ሚዛን አፍ ሆነና ስንቱ ተነገደ.....

ይሸጣል......

ይገዛል......

እርባኑ ሳይለይ ቀርቦ ለገበያ
ካለው በቂ ሆኗል ደና ማስታወቂያ...!!!

1 year, 10 months ago
....አብሽር ያስረሳሻል ...

....አብሽር ያስረሳሻል ...
......በሌላ ይክስሻል
ሲሉኝ ተስፋ ሰነኩ ፤ሌላ አንተን ጥበቃ

ከፍለጋም ገባኝ.....

የሰው ፍላጎቴ ባንተ እንዳበቃ!!

ቸኮ

1 year, 10 months ago
ግማሽ ህይወት አትኑሩ ።

ግማሽ ህይወት አትኑሩ ።
  ግማሽ ሞት አትሙቱ  ።
  ዝምታን ከመረጣችሁ ዝም በሉ ።
   ከተናገራችሁ ጨርሳችሁ ተናገሩ ።
የተስማማችሁበትን ሀሳብ በልበሙሉነት እንደተቀበላችሁት ተናገሩ አትሸፋፍኑ  ።
የማትቀበሉትን ሀሳብ በድፍረትም እምቢ በሉ ። አሻሚ እምቢታ ደካማ መቀበል ነውና ።
ግማሽ መፍትሔ አትቀበሉ ።
ግማሽ እውነትን አትመኑ ።
ግማሽ ህልም አታልሙ ።
ስለ ግማሽ ተስፋዎች አታስቡ ።
ግማሽ መንገድ የትም አያደርስም ።
በግማሽ ሳይሆን ህይወትን በምሉዕ ኑሯት

https://t.me/abolbere

1 year, 10 months ago
ትንሽ ስለተስፋ በሆነች moment ከተረዳሁት ልንገራችሁ …

ትንሽ ስለተስፋ በሆነች moment ከተረዳሁት ልንገራችሁ በጣም ስለገረመኝ ነው!
        ከምሽቱ  ወደ አራት ሰአት አካባቢ ካመሻሸሁበት ወደ ቤት እየሆድኩ ሳለ ጎዳና ላይ የመንገድ ጠርዝን በፌስታል ሸፍነው የሚያድሩ ብዙ ወጣቶች ተሰብስበው እየጠበቁት ያለ አንድ ጓደኛቸው በፌስታል የያዘውን ምግብ ይዞ ዜብራ ለመሻገር እየመጣ ያለውን ታክሲ በመቅደም መሮጥ ጀመረ የልጆቹ ስብስብ ላይ ለመድረስ የሶስት ወይም የአራት እርምጃ ርቀት ሲቀረው እንደ ድንገት በሽቦ ያስያዛት የሲሊባር ጫፍ ተበጥሳ በሚሮጥበት ፍጥነት ልጁን በቀኝ ፌስታል ውስጥ ያለው ምግብ በግራ በታተነቻቸው።የሚጠብቁት በድንጋጤና በኋላ ምን አለኝ በሚል የቅራኔ ፊት ተነስተው ጭንቅላታቸው ሲይዙ እኔ ደግሞ የልጁ ወድቆ የደማበት ቁስልን ሳያስታግስ ድጋሚ የተበተነውን ምግብ እጁ ላይ ያለውን አቧራ አራግፎ ለመሰብሰብ ከአስፓልቱ ላይ ሲጠርግ ሳይ የነሱን ያህል ደንግጬ እኩል ከልጆቹ ጋር ጭንቅላቴን ያዝኩኝ ያው የወንድምነት እንዲሁም እኔ በዛች ቅፅበት ውስጥ እዚህ ህይወት ውስጥ አስቢያት ይበልጥ ለልጁ እኔ ከፋኝ። እራሷችሁን በዚህ ልጅ የጭንቅ ምሽት ላይ አድርጋችሁት አስብት ተስፋ ያረጋችሁት ነገርና በአንድ ጊዜ ከእጃችሁ ያጣችሁትን ነገር አስብና ተስፋ የቆረጣችሁበትን ጌዜ አስታውሱ?

ተስፋ ነገ ናት ዛሬን የምትኖርላት ነገን የምትክስህ!
1. እንደ ልጁ ዛሬ ላይ የወደቀብህን ነገር ሰብስበህ አንስተህ እራስህን ለማስቀጠል ትጥራለህ ቆራጥ ከሆንክ!
2. እንደ ልጆቹ የመጣው ይምጣ ብለህ ዛሬ ላይ የግድ መደረግ ያለበትን ታደርጋለህ  ለራስህ ሀላፊነት ወስደህ!
ካልሆነ ግን የተበተነውን እያየህ እያለቀስክ የግድ መጋፈጥ ያለብህን ችግር እያባበልክ ነገ ትሞታለህ። እግዚአብሄር የዛሬን ይሰጥሀል የዛሬን ትጋትህን አይቶ ደግሞ ነገህን ያሳምርልሀል። አምላክ ነገን ተስፋ አድርገው ከሚተጉ ጎን ነው!
“ሰነፍ እጆች ሰውን ያደኸያሉ፤ ትጉ እጆች ግን ብልጽግናን ያመጣሉ።”

https://t.me/abolbere

1 year, 11 months ago
***?***በህይወትህ ውስጥ የተለያዩ ነገሮች ተፈጠሩ ማለት …

?በህይወትህ ውስጥ የተለያዩ ነገሮች ተፈጠሩ ማለት ህይወት አለቀ ማለት አይደለም

❤️የምትወደውን ሰው ስታጣ? ህይወት አያልቅም
??ያቀደከው ሳይሳካ ሲቀር ህይወት አያልቅም
??መጥፎ ውጤት ሲመጣ ህይወት አያልቅም
??ፍቅረኛህ ብትከዳህ ህይወት አያልቅም

??‍♀ብቸኛ ስትሆን ህይወት አያልቅም

??ስትወደቅ እና ፈተና ውስጥ ስትገባ ህይወት አያልቅም

?ከላይ የተጠቀሱት ነገሮች በአንተ/ቺ ላይ ቢፈጠሩ ህይወት አለቀ ማለት አይደለም ፤ አንድ ሰው ህይወቱ አለቀ የሚባለው ፦

?በሁሉም ነገር ላይ ተስፋ?? መቁረጥ ሲጀምር ነው።

ምንም ከባድ ሁኔታ ውስጥ ብትሆኑ ተስፋችሁን እንዳታጡ እስከመጨረሻው ድረስ ተጓዙ  ፤ ተስፋ ያለው ሰው ከምንም ተነስቶ ትልቅ ደረጃ ላይ መድረስ ይችላል
# Share  ??Family ?
https://t.me/abolbere
https://t.me/abolbere

1 year, 11 months ago

.......ከለሊቱ 6 ሰዐት ሆኗል ....እንቅልፍ እንቢ ብሎኝ እገላበጣለው.....ድንገት የሰው የእግር ኮቴ ስሰማ ታላቅ ወንድሜ ነው ብዬ ስላሰብኩ አንገቴን ቀና አድርጌ በጨለማ የተሞላው መኝታ ክፈላችን ውስጥ ወደ ወንድሜ አልጋ አይኔን አጥበቤ ተመለከትኩ ...... በሰላም ተኝቷል ግን አሁንም የምሰማው የእግር ኮቴ እየቀረበ ነበር የመጣው......ከተኛሁበት ተነሳው.... መብራት ለማብራት ማብሪያ ማጥፊያ ወዳለበት የክፍሉ በር አካባቢ ለመሄድ ከተደራራቢው አልጋዬ ላይ ወረድኩ ..... እየተሰማኝ ያለው ኮቴ ቀፋፊ ሳቅም ተጨመረበት.......ካለወትሮው በሩ ራቀኝ ....ባለሁበት ቆምኩ.....ፍርሀት ወርሶኛል.....ልቤ እየመታ ነው ............በቆምኩበት ከኃላዬ የሰው ትንፋሽ ነገር ተሰማኝ .....
ስዞር ነጭ ልብሱና አፉ በደም የተለወሰ ...ፀጉሩ የተንጨባረረ.... በእጁ ስል ቢላ ይዞ ...ቀጥ ብሎ እኔን አፍጥጦ እየተመከተኝ አየሁት......
ደነገጥኩ ...... ፈገግ ብሎ ስሜን እየጠራ ቢላውን ወደ እኔ ቀስሮ እየተንደረደረ መጣ .......

ከመግደሉ በፊት ታግዬ ተቀብዬ ስምንቴ ወግቼ ገደልኩት........

እውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተ!!

" ይህን የተናገረው ወንድሙን ስምንት ጊዜ በስለት ወግቶ የገደለው አይምሮ ታማሚ ግለሰብ ነው"

መልካም ምሽት
ቸኮ

We recommend to visit

የኢትዮጵያ የመጀመሪያው አልበሞች እንደወጡ መገኛ ቻናል ነው ይቀላቀሉን የሚገራርሙ አልበሞች እንደወጡ እንዲሁም ቆየት ያሉ የድሮ አልበሞች እና የሳምንቱ አሪፍ ነጠላ ዜማ ያገኛሉ
........................
Buy ads:

፨ለማንኛውም ሀሳብ አስተያየት እና ፕሮሞሽን
👉👉 @ethioalbumsbot

Channel Created May 3/201

በዚህ ቻናል ላይ የተለያዩ ተከታታይ ፊልሞች በትርጉም ማግኘት ይችላሉ 😍 ።

➲ቻናላችንን ሼር ያርጉ @Series_Amhh

ለማስታወቂያ ስራ 👉 @Abusheymc

📥ምርት እና አገልግሎቶን ማስተዋወቅ ከፈለጉ ያናግሩን
FOR ANY PROMOTION 📩 @Abemallik