የስብዕና ልህቀት

Description
በዚህ ቻናል
⚡ህይወትን የሚያንፁ የስነ-ልቦና ምክሮች
⚡መሳጭ የፍቅር ታሪኮች እና ወጎች
⚡ጥልቅ ማህበራዊ እና ፍልስፍናዊ እይታዎች
⚡ውብ የጥበብ ስራዎች
በፅሁፍ እና በድምፅ/Audio ይቀርባሉ።

#ሼር በማድረግ ወዶጅዎን የዚህ የእውቀት እና የጥበብ ድግስ ታዳሚ እንዲሆኑ ይጋብዙ።
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 year, 7 months ago

ለቡሄ ያበደ ሆ ሲል ይኖራል!!

ከዕለታት የሆነው ቀን፣ አንድ ስኮትላንዳዊ እና እንግሊዛዊ ዱር ውሥጥ ሲንሸራሸሩ ሳለ አንበሳ መጣባቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ስኮትላንዳዊው ያጠለቀውን ትልቅ ቦቲ ጫማ አውልቆ ሸራ ሲቀይር እንግሊዛዊው በመገረም "አሁን ጫማ መቀየር ምን ያደርጋል? አንበሳውን ሮጠህ ልታመልጠው ነው? ይለዋል፡፡

"አንበሳውንማ እንደማልቀድመው የታወቀ ነው፤ ሸራውን ግን የምቀይረው አንተን ለመቅደም ነው" አለው....

አንተን እስኪበላህ እኔ ጊዜ አገኛለሁ አይነት...

ይህችን ጨዋታ ሃገሪቱ ላይ የምትጫወቱ፣ ነገር አቀጣጥላችሁ ሸራ ጫማችሁን አጥልቃችሁ ለመሮጥ የተዘጋጃችሁ ሰዎች ሆይ... አንበሳው እኛን እስኪበላ ጊዜ ታገኙ ይሆናል፤ ነገር ግን... አንደኛ አንበሳ ብቻውን አይመጣም፣ሁለተኛ ቀጣዩ ታዳኝ እናንተ መሆናችሁን በልባችሁ ፃፏት...ለዚህ እኮ ነው የወሎዋ አልቃሽ

አሁን ምን ያደርጋል የሴት ወየው ባይ
ወሎ የመጣው ሞት ሸዋ የለም ወይ?
ያለችው...
አገር አለን ለማለት እየከበደን ነው፤ ነፃነቱ እና ልቅነቱማ ተደበላልቆብናል፡፡

፨፨፨

አንዳንድ ሰው ግን..."መብራት ጠፋብን" እያለ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል ቆይቶ፣ ለእሱ ሲበራ ሌላው ሰፈር ግን ሲጠፋ ፍትሃዊ የሚመስለው ለምንድነው?

ሌሊሳ ግርማ እንዳለው የሰው እግር ቆርጦ ከራስ እኩል እንደማድረግ ያለ ‹ፍትህ›

አንዳንድ ተምሬያለሁ የሚል ሰውስ የተማረ ሳይሆን በዩኒቨርሲቲ የፊት በር ገብቶ በኋላ በር የወጣ የሚመስለውስ?

ሃገሪቱ ላይ ያለው ህዝብ ይህን ይመስላል፡፡ እንዲህ ያለህዝብ ያላትን ሃገር ደግሞ ጤነኛ ትሆናለች ብሎ ማሰብ ራሱ ህመም ነው... ዝም ብሎ እጅና እግሯን ጥፍር አድርጎ ሁለት ሰባት ማስጠመቅ ይሻላል፡፡

አሁን በቀደም የመብራት ኃይል ኃላፊው መብራት በተደጋጋሚ የሚያጠፉበትን ምክንያት ጋዜጠኛው ሲጠይቃቸው "አሁን እንደድሮው አይደለም፤ መብራት መጥፋቱ ባይቀርም ምክንያቱ ግን ተቀይሯል" ካሉ በኋላ... "ዘንድሮ መብራት የሚጠፋው አሁን በተያያዝነው የብልፅግና ጎዳና የደም ግፊታቸው የሚጨምር ሰዎች በንዴት ኮረንቲ መያዛቸው አይቀርም፤ እናም መንግስት የእነዚህን ሰዎች ደህንነት ለመጠበቅ ነው መብራት የሚያጠፋው"

ቀጠሉ... 'ይህ በእንዲህ እንዳለ አንዳንድ የኮንዶሚኒየም ነዋሪዎች ልብስ አጥበው የሚያሰጡበት ቦታ ስለሚያጥራቸው ቀን ቀን የኤሌክትሪክ ገመዶቹን እንደልብስ ማስጫ እንዲጠቀሙ መንግስት መብራት በማጥፋት ይተባበራቸዋል"

ጋዜጠኛው ችኮ ነው ጥያቄውን ቀጠለ "እሺ ራሳቸውን በኮረንቲ ማጥፋት የሚፈልጉ ዜጎችን መብት መጨቆን እንዳይሆን... መንግስት ምን ያመቻቸው ነገር አለ? ብሎ ጠየቀው

ማለዳን መናፈቅ
መምህርት ዕጸገነት ከበደ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 7 months ago

*ጊዜ እንዳለኝ እያሰብኩ ነበር — እንደምኖር።

በመጻሕፍት መደርደሪያዬ እኔን መጠበቅ ያደከማቸው ያልተነበቡ መጻሕፍት ተገጥግጠዋል።

አንድ ቀን እንደማነባቸው ተስፋ ሳደርግ ምጽዓት ደረሰ —ሀገሬ። በሲዖል ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ አይቻልም። አንደኛ ሀገሩ የእሳት ነው። በእሳት ሀገር ወረቀት ቀለም ይዞ አይቆይም። ይነዳል፥ አመድ ይሆናል። ብዙ ጩኸት አለ —ሰቆቃ። እና አይመችም። ዙሪያው ገደል ነው። ልብ ዝቅ ያደርጋል።

ቀን በቀን መጻሕፍቴን እየተሰናበትኩ ነበር። ምን ትርጉም አለው? ሳልፈልግ አእምሮዬ እንደተረበሸ ከተማ ሐሳብ ይጎሎጉላል።  በሥነ ሥርዓት ላጠነጥን እሞክራለሁ —መሥመር ላስይዝ። ግን አልችልም ይሳከርብኛል። አንጎሌ፥ ሰውነቴ ይሰንፋል። 

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው።  አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? ዳሩ ብትነቃስ ምን ታደርጋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ብትተኛ አይከፋም፥ ብትማር፥ ብትቆጥብ፥ ብታገባ፥ ብትወልድ።

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት  ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ።  ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ማንንም መርዳት አትችልም። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ግን ተራው ያንተ ከሆነ ያንተ ነው። ትከሻህን ማስፋት፥ መቻል፥ መቀበል ይጠበቅብሃል። እውነት አይመስልም አይደል? ትላንት በእቅፍህ የነበረ ሰው እንደወጣ ሲቀር? ደብዛው ሲጠፋ?? ግን ይህ የብቻህ እውነት ነው። ይህ የብቻህ ሕመም ነው —ጽና።

እ. . .

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በሌላ አውድ የጻፈው አንድ ግጥም አለ። ያለ ዐውዱ እዚህ ጋር እንድጠቀመው ይፈቀድልኝ፦

“...ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተዉኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?! . . . .
ተስፋ አድርገህስ ምን ልትሆን ፡ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ ?
እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ።”*

እሱባለው አበራ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 7 months ago

[ተስፋ በመቁረጥ ተስፋ መቀጠል] እንዳለ ገጣሚው መዘክር ግርማ...!

-/ ተስፋ በተስፋ ይተካል:: በማይቀየር  እና ከቁጥጥራችን ውጭ በሆነ ነገር ላይ ተስፋ መቁረጥ... ሊቀየር በሚችልና በቁጥጥራችን ውስጥ በሆነ ጉዳይ ተስፋ ለመቀጠል/ለማድረግ ያግዛል:: [ አዲስ ተስፋ ለመቀጠል በአሮጌው ተስፋ መቁረጥ ያስፈልጋል::]... ትውልድ ያለ ዕዳው እየተቀጣ ነው:: አባቶቹ ባለራዕይና ንቁ አልነበሩም:: ለሃያላን ስሁት ህልም የተገበረ የመስዋእት በግ ሆኑዋል:: ይህን ለመቀየር ረፍድዋልና ተስፋ መቁረጥ አለበት... ይህን የሚነግሩት ደፋር ብእርና አንደበት ያላቸው ቀንዲሎችም ያስፈልጉታል:: አዎ! ተስፋ መቁረጥ ከባድ ነው: ዙሪያን ጨለማ: መንገድን ግራ ያስመስላል ያኔ ግን የራስ ህልም ይወለዳል: አዲስ ተስፋ ይቀጠላል:: መጀመሪያ ተስፋ እንቁረጥ! አባቶቻችን አያቶቻችንን አይመስሉም:: ቅዠት እንጂ ህልም አልነበራቸውም::

[ናትናኤል ዳኛው]
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 7 months ago

ቅደም ተከተልን የማወቅ ጥበብ“የሚያጣድፍ ነገር ሁሉ አስፈላጊ ነገር አይደለም” - Stephen Covey

አንድ ቀን አንድ የማኔጅመንት ሳይንስ ሊቅ ለተማሪዎቹ ንግግር በማድረግ ላይ ነበር፡፡ ይህ ሰው ለእነዚህ በጣም ለተነሳሱና ብሩህ አእምሮ ላላቸው ተማሪዎች በመናገር ላይ እያለ አንድን ነገር አደረገ፡፡ አንድ ባሊ አመጣና ጠረጴዛው ላይ ካስቀመጠ በኋላ ድንጋዮችን በማምጣት ባሊውን አፉ ድረስ ጢም አድርጎ በድንጋይ ሞላው፡፡ ይህንን ካደረገ በኋላ፣ “ይህ ባሊ ሙሉ ነው የሚል እጁን ያውጣ” አለ፡፡

በክፍሉ ያሉ ተማሪዎች በሙሉ እጃቸውን አወጡ፡፡ “እርግጠኛ ናችሁ?” አላቸው፡፡ “አዎን” በማለት እርግጠኝነታቸውን አረጋገጡለት፡፡ ከዚያም ከጠረጴዛው ስር አስቀምጦት ወደነበረው ሌላ ባሊ አጁን ዘርግቶ አነሳውና በውስጡ ያለውን ጠጠር ወደዚያ ድንጋይ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ ጠጠሮቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡

“አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አለ መልሶ፡፡ አሁን አሰልጣኙ ምን ሊል እንደፈለገ በመጠኑ እየገባቸው ስለመጣ በማንገራገር የተደባለቀ ምላሽ ሰጡት፡፡ አንዳንዶቹ፣ “አሁን ሙሉ ነው” ሲሉ፤ ሌሎቹ ደግሞ፣ “አሁንም አልሞላም” አሉ፡፡ አሁንም በመቀጠል እጁን ወደ ጠረጴዛው ስር ሰደድ በማድረግ ሌላ ባሊ አነሳ፡፡
ይህኛው ባሊ በአሸዋ የተሞላ ነው፡፡ ወዲያውኑ አሸዋውን ወደዚያ ድንጋይና ጠጠር ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰው፡፡ አሸዋዎቹ ሹልክልክ እያሉ ባገኙት ቀዳዳ ሁሉ ገቡ፡፡ ለሶስተኛ ጊዜ፣ “አሁንስ ባሊው ሙሉ ነው የምትሉ ስንት ናችሁ?” አሁን ተማሪዎቹ በሙሉ በአንድ ቃል፣ “ባሊው አሁንም አልሞላም” ብለው መለሱለት፣ አካሄዱ ገብቷቸው፡፡ አሰልጣኙ እንደገና ሌላ ውኃ የሞላበት ባሊ ከጠረጴዛው ስር በማንሳት ድንጋይ፣ ጠጠርና አሸዋ ሞልቶበት ወደነበረው ባሊ አፈሰሰውና በባሊው ውስጥ ሌላ ምንም ነገር መጨመር እስከማይቻል ድረስ ሞላው፡፡

የመጨረሻው ትምህርታዊ ጥያቄ እንዲህ የሚል ነበር፡፡ “ከዚህ ምሳሌ የምናገኘው ዋና ቁምነገር ምንድን ነው?” አላቸው፡፡ አንዱ ሰልጣኝ አጁን አውጥቶ፣ “ምንም እንኳ ጊዜህ በብዙ ነገር ቢጨናነቅ፣ አሁንም ሌላ ነገርን አጨናንቀህ ማድረግ እንደምትች ነው” አለው፡፡

አሰልጣኙም፣ “ተሳስተሃል! የዚህ ምሳሌ ዋነኛ ትምህርት በመጀመሪያ ትልልቆቹን ድንጋዮች ባሊው ውስጥ ባትጨምር ኖሮ ትንንሾቹን ጠጠሮች፣ አሸዋውንና ውሃውን መጨመር አትችልም ነበር፡፡ ትልልቆቹ ድንጋዮች የሚወክሉት በሕይወትህ ያሉትን ዋና ዋና የሕይወት አላማዎችና ግቦች ነው፡፡

ቤተሰብህ፣ ጤንነትህ፣ የትምህርትህ አቅጣጫ፣ ዋነኛ ሕልሞችህና የመሳሰሉት … ዋና ዋና ከሚባሉት “ድንጋዮች” መካከል ይገኛሉ፡፡ በመጀመሪያ በእነዚህ ነገር ካልተደላደልክና የሕይወትህን አቅጣጫ ካልሞላኸው፣ በጥቃቅን ነገሮች ተጨናንቀህ ሕይወትህን ታባክናለህ፡፡

አንዳንድ ሰዎች ጊዜን በአግባቡ የመጠቀምን ጥበብ ማዳበር በራሱ እጅግ አድካሚ ስራ ነው  ብለው  ያስባሉ፡፡ ነገር ግን ሁኔታው የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ ዛሬ የሕይወቴን ዋና ዓላማ በመለየትና ቅድሚያን ለእርሱ በመስጠት መልክ የያዘ ሕይወት ለመኖር ማቀድ ካልቻልኩ ነገ በዚህና በዚያ የባከነውን ጊዜዬን መለስ ብዬ ከማየትና ከመቆጨት ውጪ ምንም ነገር ለማድረግ ያስቸግረኛል፡፡

“የጊዜ አጠቃቀም ጥበብ” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ መጽሐፍ የተቀነጨበ፡፡

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 7 months ago

በዋናው ነገር ላይ ማተኮር!(“ትኩረት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ)

አንድን እጅግ በጥበብ የላቀን ሰው አገኘሁትና ባለችኝ የጋዜጠኝነት ሙያ ተጠቅሜ መጠየቅ የምችለውን ያህል ለመጠየቅ ሞከርኩ፡፡

ጠቢቡ - “ና ጠጋ በል … ጥያቄ ልትጠይቀኝ እንደፈለግህ ታስታውቃለህ” አለኝ፣ የልቤን ፍላጎት ገምቶ፡፡

እኔ - “ጊዜ ካለህ” አልኩት፡፡

ጠቢቡ (ልብን በሚሰርቅ ፈገግታ) - “ለማወቅ ለሚፈልጉ ሰዎች ሁሉ ጊዜ አለኝ” ብሎ መለሰልኝ፡፡

ይህ ጥበበኛ እንዴት ለሰው ሁሉ ጊዜ ሊኖረው ቻለ? እያልኩ ሳወጣና ሳወርድ በፈገግታና በትእግስት ይጠብቀኝ ነበር፡፡

እኔ፡- “ስለ ሰው ፍጥረት ከሚያስገርሙህ ነገሮች መካከል ጥቂቱን ንገረኝ” አልኩት፡፡

ጠቢቡ -

•  “ልጆች ሳሉ መሰልቸታቸውና ትልቅ ለመሆን መሮጣቸው … ካደጉ በኋላ ደግሞ ልጅ መስሎ ለመታየት መሯሯጣቸው ያስገርመኛል …

•  ገንዘብ ለማካበት ጤንነታቸውን ማጣታቸው … ጤናቸውን ለመመለስ ደግሞ እንደገና ያንኑ ገንዘብ ማፍሰሳቸው ያስደንቀኛል …

•  ስለ ነገ በመጨነቅ ዛሬን ለመኖር አለመቻላቸውና ከዛሬም ሆነ ከነገ ሳይሆኑ መንከራተታቸው ያስገርመኛል …

•  ልክ እንደማይሞት ሰው መኖራቸውና ልክ እንዳልኖረ ሰው ተጽእኖ ቢስ ሆነው መሞታቸው ያስገርመኛል፡፡

**ይህን ጠቢብ ዝም ብለው ሌሎች ሃሳቦች እንደሚጨምር እየተሰማኝ በማቋረጥ፣ “ሌላ ጥያቄ ልጠይቅህ?” አልኩት፡፡

ጠቢቡ፡-** ደስ በሚያሰኝ ፈገግታ ፈቃደኝነቱን ገለጠልኝ፡፡

እኔ፡- “የሰው ልጅ ሁሉ አባት ብትሆን ለሰው ልጆች እንዲያደርጉ ከምትመክራቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹን ንገረኝ” አልኩት፡፡ 

ጠቢቡ (ረዥም ጺሙን ዳበስ ዳበስ በማድረግ ካሰበ በኋላ)፡-•  ማንም ሰው እንዲወዳቸው ማስገደድ እንደማይችሉ፣ ነገር ግን ማድረግ የሚችሉት የሚወደድ ማንነትን ማሳደግ ብቻ እንደሆነ እንዲያወቁ እመክራቸው ነበር፡፡

•  መልካም ማንነትንና የተመሰከረለት ማህበራዊ ሕይወት ለመገንባት አመታት እንደሚፈጅ፣ ለማፍረስ ግን አንድ ደቂቃ እንደሚፈጅ እንዲያውቁ አስተምራቸው ነበር፡፡

•  የሕይወታችቸውን አቅጣጫ የሚወስነው ያላቸው ንብረትና ሃብት ሳይሆን በሕይወታቸው ያስጠጓቸው የወዳጆች አይነት እንደሆነ እንዲገነዘቡ አሳስባቸው ነበር፡፡

•  ታላላቅ ሕልሞችን ለማለምና ከግባቸው ለማድረስ የሚያስፈልገው ታላቅ ሰው መሆን ሳይሆን ከግብ ለመድረስ የቆረጠ ማንነት እንደሆነ እንዲያውቁ የተቻለኝን አደርግ ነበር፡፡

•  ሃብታም ሰው ብዙ ገንዘብና ቁሳቁስ ያለው ሰው ሳይሆን የሚያስፈልገውን ነገር ያወቀ ሰው እንደሆነ እንዲያውቁልኝ እጥር ነበር፡፡

•  ራሳቸውን ከሌላው ጋር ማነጻጸርና ማወዳደር እንደማይገባቸውና ከእነርሱ የሚያንስ ሰው እንዳለ ሁሉ የሚበልጥም ሰው የመኖሩን እውነታ እንዲቀበሉት አስረዳቸው ነበር፡፡

•  አመለካከታቸውን መቆጣጠር እንዳለባቸው አለዚያ አመለካከታቸው እነሱን እንደሚቆጣጠራቸው እንዲማሩ እሞክር ነበር፡፡

•  እጅግ በጣም የሚወዷቸውና የሚያከብሯቸው ነገር ግን ያንን በቅጡ ለመግለጽ የማይሆንላቸው ብዙ ወዳጆች እንዳሏቸው አስረዳቸው ነበር፡፡ 

•  እውነተኛ ጓደኛ ማግኘት እጅግ ከባድ እንደሆነ፣ ያንን ያገኘ ግን የሕይወቱን አብዛኛውን ችግሩን እንዳቃለለ እንዲያውቁ እመክራቸው ነበር፡፡

•  የቅርብ ወዳጆቻቸውን ለማቁሰል ሰከንድ እንደሚበቃ ለመፈወስ ግን አመታት እንደሚፈጅ እንዲገባቸው እጣጣር ነበር፡፡

•  ሰዎችን ለመቆጣጠር በመሞከር እንደሚያጧቸው፣ ምርጫቸውን በማክበር ነጻነታቸውን በመስጠት ግን ለዘለቄታው ወዳጆች እንደሚያደርጓቸው እንዲገነዘቡ ለማድረግ እሞክር ነበር፡፡

•  የውስጥ ሰላም ለማግኘት ከሰዎች ይቅርታን ማግኘት ብቻ ሳይሆን ራሳቸውንም ይቅር ማለት እንደሚገባቸው እንዲያስታውሱ አሳስባቸው ነበር፡፡

•  ከመናገር በሚቆጠቡበት ነገር ላይ ጌታ፣ በልቅነት ለሚናገሩት ንግግር ደግሞ ባሪያ ሆነው እንደሚኖሩ አሳውቃቸው ነበር፡፡

•  እውነተኛ ደስታ የውሳኔ ጉዳይ እንደሆነ፣ በማንነታቸውና ባላቸው ነገር ደስተኛ መሆን፣ አለዚያ በቅንአትና በፉክክር ወጥመድ ውስጥ እንደሚገቡ አስገነዝባቸው ነበር፡፡

•  በአጭሩ በዋናው የሕይወት ነገር ላይ ያተኮረ ዝንባሌ ቢኖራቸው እመክራቸዋለሁ፡፡
@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 7 months ago

**ሶፋ ወይስ አልጋ?

አስፈላጊው ነገር ላይ የማተኮር ምስጢር**!

“ወሳኙና ትኩረታችንን ልንጥልበት የሚገባው ነገር ሰው የሚያይልንና የሚያደንቅልን ነገር ላይ ሳይሆን ለሕልውናችንና ለእድገታችን አስፈላጊ የሆነው ጉዳይ ላይ ሊሆን ይገባዋል”

የትኩረት አስፈላጊነት የገባቸው ሰዎች የሰዎችን አድናቆት ከማግኘት የዘለለ የሕይወት ዘይቤ ያዳበሩ ሰዎች ናቸው፡፡ ሰዎች አይተውላቸው “ደስ ይላል” ብለው የሚያደንቁላቸውን ነገራቸውን የማስዋብን አስፈላጊነት ባይክዱም ከዚያ የበለጠ ትኩረት የሚገባው ነገር ግን ለእድገታቸውና ለሕልውናቸው ወሳኝ የሆነው ነገር እንደሆነ ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ትኩረታቸውም በዚያ ላይ ነው፡፡  

አንድ ሰው በሚኖርበት ማሕበረሰብ አካባቢ አንድን ጥናት ማድረግ ፈለገ፡፡ ከጥናቱ ሊያገኝ የፈለገው እውነታ ይህንን ይመስላል፡፡  በአንድ በኩል ትኩረታቸው ከላይ ለሰዎች የሚታየውን ብቻ ቀባ ቀባ ማድረግ የሆነና ለታይታ ብቻ የሚኖሩ ሰዎችን የሕይወት ሁኔታ ማወቅ ፈለገ፡፡ በሌላ ጎኑ ደግሞ ለታይታ ብቻ ሳይሆን በትክክለኛውና በሕይወት ላይ ለውጥ በሚያመጣው ነገር ላይ የሚያተኩሩ ሰዎችን ሁኔታ መገንዘብ ተመኘ፡፡ ይህንን ሁኔታ በቀላሉ ለማወቅ የሚችልበትን ዘይቤ ሲፈልግ አንድ ነገር ብልጭ አለለት፡፡

በየሰፈሩ እየተዘዋወረ ፈቃድን ባገኘበት ቤት ሁሉ እየገባ አንድን ጥያቄ መጠየቅ ጀመረ፡፡ ጥያቄው አጭርና ግልጽ ነበር፡- “በቤትዎት ካለው ሶፋ እና አልጋ በዋጋ የትኛው ይበልጣል? እነዚህንስ እቃዎች ሲገዙ ብዙ ትኩረት የሰጡበት የትኛውን ነው? ብዙ ዋጋ ላወጡበት እቃስ ያንን ያህል ዋጋ እንዲያወጡ ያነሳሳዎት ምንድን ነው?” የሚል ነበር፡፡ እነዚህን ሶስት ጥያቄዎች ከጠየቀ በኋላ የሰዎቹን የአኗኗር ሁኔታ በቀስታ ያጤን ነበር፡፡ በመቶ የሚቆጠሩ ቤቶችን በመጎብኘት ይህንን መጠይቅ ለማቅረብና መረጃ ለመሰብሰብ ወደ አንድ አመት ፈጅቶበታል፡፡ በመጨረሻ ያገኘው መልስ ሲጨመቅ አስገራሚ ስእል አመላከተው፡፡

በዚህ ጥናታዊ መጠይቅ ላይ ከተሳተፉት ሰዎች አብዛኛዎቹ ለገዙት አልጋ ካወጡት ዋጋ ይልቅ በብዙ እጥፍ የከፈሉት ለሶፋቸው ነበር፡፡ ከዚህ በላይ ግዢውን ሲፈጽሙ ብዙ አማራጭ ለማግኘት ጊዜን የወሰዱትና ብዙ ሰው ያማከሩበት እቃ ሶፎውነበር፡፡ አልጋ ለመግዛት ካወጡት ገንዘብና ለምርጫ ካሳለፉት ጊዜ ይልቅ በሶፋ ላይ የበለጠ ገንዘብና ጊዜ የማውጣታቸውን ምክንያት ሲጠየቁ የሰጡት መልስ ሲጨመቅ፣ “ሰዎች ሲገቡ የሚያዩት ሶፋውን ስለሆነ ነው፣ አልጋውንማ ማን ያየዋል?” የሚል ነበር፡፡

ግኝቱ ይህ ነው፡- አንድ ሰው በቀን ውስጥ በአማካኝ ሰባት ወይም ስምንት ሰዓታትን በአልጋው ላይ ያሳልፋል፡፡ በቀን በሶፋው ላይ ተቀምጦ የሚያሳልፈው ጊዜ ግን በአማካኝ ከሶስትና ከአራት ሰዓት በላይ አይሆንም፡፡ ስምንት ሰዓታት ሰውነቱን ጥሎበት የሚያሳልፈው ይህ አልጋ የተሰኘው ነገር በአካላዊ ጤንነቱ ላይ ይህ ነው የማይባል ስፍራ አለው፡፡ በተጨማሪም ከማይመች አልጋ የሚመጣ የእንቅልፍ ማጣት ችግር ለቀን ተግባር ስኬታማነት ወሳኝ መሆኑም እሙን ነው፡፡

አስፈላጊ ከሆኑት  በሕልውናችንና በስኬታማነታችን ላይ ዘላቂ ተጽእኖ ከሚያመጡት የሕይወታችን ጉዳዮች ላይ ትኩረታችንን ማንሳት ብዙ አሉታዊ ተጽእኖዎች አሉት፡፡ እንዲህ አይነቱ አካሄድ ከታይታ ወደማያልፉ ነገሮች እንድንዞርና ብዙ ውድ ነገሮቻችንን እንድናባክን አሳልፎ ይሰጠናል፡፡ ለምሳሌ ጊዜአችንን፣ ገንዘባችንንና ሃሳባችን በተለያዩ ጊዜአዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የመበታተን የሕይወት ዘይቤ ውስጥ እንገባለን፡፡ ትኩረቱን ከጊዜአዊውና ለታይታ ከሆነው ነገር ላይ በማንሳት ወደ አስፈላጊውና ወደ ዘላቂው ነገር ያዞረ ሰው ለጊዜው ሰዎች አይተው የሚያደንቁለት ነገር ባይኖረውም እንኳ ለነገ እንደሚሰራ ያውቀዋል፡፡

የሚታየውንና ጥቅሙ ውስን የሆነውን የኑሮአችንን ሁኔታ ከማይታየውና ጥቅሙ እጅግ የላቀ እንዲሁም ደግሞ ዘላቂ ከሆነው ሁኔታ ለመለየት ልናስታውሳቸው የምንችላቸው እውነታዎች አሉን፡፡ ምናልባት ለረጅም አመታት ከለመድነው የኑሮ ዘይቤ ለመላቀቅ ከባድ ቢሆንም እንኳ የማይቻል አይደለምና ዛሬውኑ ጉዞውን መጀመር እንችላለን፡፡

1.  ከስውር የዝቅተኝነት ስሜት ተላቀቅ:- ለታይታ ለመኖር የመጣጣር አንዱ ምንጭ የዝቅተኝነት ስሜት ነው፡፡ ከሌሎች በታች የሆንን ሲመስለንና በዚህ ስሜት በስውር ስንጠቃ አውቀነውም ሆነ ሳናውቀው ራሳችንን ከሌላው ለማስተካከል ወይም የበለጥን እንደሆንን ለማሳየት ስንጣጣር እንታያለን፡፡

2.  የትርጉም ማስተካከያ አድርግ:- ትክክለኛ ኑሮ ማለት እኛ ሲመቸን እንጂ በእኛ ሁኔታ ሌላው ሲገረም ማለት አይደለም፡፡ ዘላቂ ስኬት ማለት እኛ ተመችቶን ለሌላው ስንተርፍ እንጂ ኑሮአችን ወድቆ በውጫዊው “ውበታችን” ሌላው ሲገረም ማለት አይደለም፡፡

3.  የእቅድ ሰው ሁን:- ከሰው ጋር መወዳደርን አቁምና ለራስህና ለቤተሰብህ መሻሻል ካወጣኸው እቅድ አንጻር መሮጥ ጀምር፡፡ ትክክለኛ ስኬት ማለት የት መድረስ እንደሚፈልጉ ማወቅና በዚያ አቅጣጫ በመገስገስ፣ በሂደቱም መርካት ማለት ነው፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ

1 year, 8 months ago

የአቶሚክ ልማድ አስደናቂ ሀይል

ውጤቶችህ የልማዶችህ ቀሪ መለኪያዎች ናቸው፡፡ ያለህ ገንዘብ የፋይናንስ አጠቃቀምህ ውጤት ነው፤ እውቀትህም የመማር ልማድህ ቀሪ መለኪያ ነው።
በሕይወትህ ውስጥ ያሉት ምስቅልቅሎችም ነገሮችን የማጽዳት ልማዶችህ  ድምር ውጤቶች ነው።የምታገኘው የምትደጋግመውን ነው፡፡

የሕይወትህን መዳረሻ ለመገመት ከፈለግህ ማድረግ ያለብህ ነገር ቢኖር የምታገኛቸውንና የምታጣቸውን ጥቃቅን ለውጦች ተከትለህ ማየትና ይህ የለውጥ መስመር በሃያ - በሰላሳ ዓመታት የት እንደሚያደርስህ መረዳት ነው፡፡ የወር ወጪህ ከገቢህ ያነሰ ነው? በየሳምንቱ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ትሰራለህ? በየቀኑ አዳዲስ ነገሮችን ታውቃለህ? መጽሐፍ
በጥቂቱም ቢሆን ታነባለህ? የወደፊት ሕይወትህን ሙሉ የሚወስኑት እንደነዚህ ያሉ ጥቃቅን የጦር ግንባሮች ናቸው፡፡

በሙሉ ጊዜ በውድቀትና በስኬት መካከል ያለውን ልዩነት ያሰላል፡፡ ጊዜ የሚያደርገው ነገር ቢኖር የምትሰጠውን ነገር ማባዛት ነው፡፡ ጥሩ ልማዶች ጊዜን አጋርህ ሲያደርጉት፣ መጥፎ ልማዶች ግን ጠላትህ ያደርጉታል፡፡

ልማዶች በሁለቱም በኩል የተሳሉ ሰይፎች ናቸው፡፡ መልካም ልማዶች ሊስሉህና ሊያሳድጉህ የሚችሉትን ያህል መጥፎ ልማዶች ደግሞ ቆራርጠው ሊጥሉህ የሚችሉበት እድል በዚያው መጠን ነው፡፡
ለዚህም ነው ዝርዝሩን መረዳት ጠቃሚ የሚሆነው፡፡ ልማዶች እንዴት እንደሚሰሩና እንዴት ወደ ውጤት እንዲወስዱህ ማድረግ እንደምትችል መማር አለብህ፡፡ በዚህ መንገድ የሰይፉን ቆራጭ ስለት የማስወገድ እድል ታገኛለህ፡፡

ብዙውን ጊዜ ሁኔታ ቀያሪ ቅጽበቶች ቀደም ብለው የተሰሩ የብዙ ተግባራት ድምር ውጤቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ተደራራቢ ቅድመ ተግባራት ዋናውን ለውጥ ለማምጣት የሚያስፈልገውን አቅም ይገነባሉ፡፡ ይህ ሁኔታ በሁሉም ቦታዎች የሚታይ ነገር ነው፡፡ ካንሰር የሕይወት ዘመኑን 80 በመቶ የሚያሳልፈው የማይታይ ሆኖ ነው፡፡ ከዚያ የሰውነትን አካል የሚቆጣጠረው ግን በወራት ውስጥ ነው፡፡ ሸምበቆም መሬት ለመሬት ስሮቹን በሚዘረጋባቸው አምስት ዓመታት ውስጥ ብዙም አይታይም፡፡ ከዚያ ነው በስድስት ሳምንታት ውስጥ በአየር ላይ እስከ 90 ጫማ ድረስ ማደግ የሚችለው፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ ልማዶችም የሆነ ወሳኝ ምዕራፍን አልፈን አዲስ ሁኔታ ውስጥ ገብተን እስክንገኝ ድረስ ምንም ለውጥ የሚፈጥሩ አይመስሉንም፡፡ በየትኛውም ሁኔታ መጀመሪያ እና መካከለኛ ዘመን ውስጥ ብዙውን ጊዜ የመከፋት ሸለቆ ይኖራል፡፡ ለውጥ ለማምጣት ስትነሳ የእድገት ደረጃዎችህን በማይቆራረጥ እና ወጥ በሆነ መልኩ ማየት እንደምትችል
ታስባለህ፡፡ ግን አታይም፡፡ በመጀመሪያዎቹ ቀናት፣ ሳምንታትና ምናልባትም ወራት አካባቢ ለውጥ የማይመጣ መስሎ መታየቱ በጣም የሚያበሳጭ ነው፡፡ የትም የምትሄድ መስሎ አይሰማህም፡፡ ይህ የየትኛውም የድርርቦሽ ድል መገለጫ ባህሪ ነው - ሁልጊዜም ትላልቅ ውጤቶች የሚመጡት ዘግይተው ነው፡፡

ዘላቂነት ያላቸውን ልማዶች መገንባትን ከባድ ከሚያደርጉት መሰረታዊ ምክንያቶች መካከል አንደኛው ይህ ነው፡፡ ሰዎች ትናንሽ ለውጦችን ለማምጣት ይሞክሩና ውጤቱ ግን አልታይ ይላቸዋል፡፡ ከዚያም ለማቆም ይወስናሉ። “ለአንድ ወር ያህል በየቀኑ እሮጥኩ፤ እና ለምንድነው ሰውነቴ ላይ ለውጥ ያላየሁት?” ብለህ ልታስብ ትችላለህ፡፡ እንደዚህ አይነት አስተሳሰብ አንድ ጊዜ ከተቆጣጠረህ ጥሩ ልማዶችን እየተውክ ለመሄድ ትመቻቻለህ። ትርጉም ያለው ለውጥ ለማሳየት ግን ልማዶችን ለረዥም ጊዜ ማቆየትና ጉብታውን ለማለፍ የሚያስችላቸው አቅም ማጠራቀም አለባቸው፡፡ እኔም የተዳፈነ ችሎታ ጉብታ (The plateau of atent potential) የምለው ይሄንን ነው፡፡

ጥሩ ልማድ ለመገንባት ወይም መጥፎ ልማድ ለመተው ስትታገል ራስህን ብታገኘው የመሻሻል አቅም አጥተህ እንዳይመስልህ፡፡ ይልቁንም እንደዚህ የሚሆነው ገና የተዳፈነው ችሎታህን ጉብታ ስላለፍክ ብቻ ነው፡፡ “ጠንክሬ ብሰራም ውጤት አላመጣሁም አይነት አቤቱታ “በረዶው ለምን በ26፣ በ27 ወይ በ28 ዲግሪ አልቀለጠም?” ብሎ ቅሬታ እንደማቅረብ ያለ ነው፡፡ ድካምህ አልባከነም፣ እየተጠራቀመ ነው እንጂ፡፡ ሁሉም ድካሞችህ ተደማምረው 32 ዲግሪ ላይ ውጤት ማሳየት ይጀምራሉና፡፡

በስተመጨረሻ የእምቅ ችሎታ ጉብታህን ስታልፍ ሰዎች ስኬትህን የአንድ ቀን ስኬት ብለው ይጠሩታል፡፡ የውጪው ዓለም ሁሉንም የለውጥ ደረጃዎችህን አያይም፡፡ ሰዎች ማየት የሚችሉት ድራማዊ የሆነውን የለውጡን ፍሬ መገለጫ ብቻ ነው፡፡ አንተ ግን ለዚህ ያበቁህ ምንም ለውጥ እያሳየህ በማይመስል ሰዓት ሁሉ የሰራሀቸው ጠንካራ ስራዎች መሆናቸውን ታውቃለህ፡፡

ሁሉም ትላልቅ ነገሮች የሚነሱት ከትናንሽ ጅማሮዎች ነው፡፡ የእያንዳንዷ ልማድ ዘር አንዲት ትንሽ ውሳኔ ነች፡፡ ይህች ውሳኔ ስትደጋገም ግን ልማድ እያደገና እየጠነከረ ይሄዳል፡ ስሮቿ እየተስፋፉ ይሄዱና ቅርንጫፍ ማውጣትም ትጀምራለች፡፡
የእምቅ ችሎታ ጉብታን አልፎ ለመሄድና በሌላው ጎን ለመገኘት የሚያስችለንን የጥንካሬ ትግል ቆይታ የሚወስነው ምንድን ነው? አንዳንድ ሰዎች የመልካም ልማድን ድርርቦሽ ትርፍ ሲያጣጥሙ አንዳንዶች ግን የመጥፎ ልማዶቻቸው ምርኮኛ ሆነው የሚቀሩትስ ለምንድን ነው?

ይቀጥላል

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 8 months ago

ትናንሽ ልማዶች ትልቅ ልዩነት ይፈጥራሉ።
Atomic Habit
ደራሲ- ጄምስ ክሊር
ትርጉም-ድረስ ጋሻነህ

የአንድን ወሳኝ ቅጽበት ሚና ከፍ አድርጎ ማየትና በየቀኑ የሚደረጉ የጥቃቅን መሻሻሎችን ሚና ዝቅ አድርጎ ማየት ይቀለናል ፡፡ ብዙውን ጊዜ ትልቅ ስኬት ትልቅ አድርገን ራሳችንን ተግባርን እንደሚፈልግ እናሳምነዋለን፡፡ ክብደት መቀነስም ይሁን ትልቅ ቢዝነስን መገንባት፣ መጽሐፍ መፃፍም ይሁን ውድድርን ማሸነፍ ወይም የትኛውንም ሌላ ግብ ለማሳካት ሁሉም ሰው የሚያወራለት አይነት መሬት የሚያንቀጠቅጥ ትልቅ ነገርን መስራት እንዳለብን በማመን ራሳችንን እናጨናንቃለን፡፡

ጥቃቅን ነገሮችን በአንድ በመቶ ማሻሻል ግን የማንመኘው ለእይታም የማይገባ ነገር ነው፡፡ ይሄኛው አይነት የመሻሻል መንገድ ግን ከፍተኛ ውጤት የማምጣት አቅም አለው - በተለይ በረዥም ጊዜ፡፡ ትንሽ ለውጥ በጊዜ ሂደት የምታመጣው ልዩነት አስደናቂ ነው፡፡ ሂሳባዊ ስሌቱ ይሄን ይመስላል፡፡ ለአንድ ዓመት ሙሉ በቀን 1 በመቶ እያሻሻልን ብንሄድ በአመቱ መጨረሻ መጀመሪያ ከነበርንበት በ37 በመቶ እንሻሻላለን፡፡ በተቃራኒው ደግሞ በቀን በአንድ በመቶ ወደታች እየሄድን ለአንድ ዓመት ከቆየን ወደ ዜሮ አካባቢ እንደርሳለን፡፡ በጥቂት ጅማሮ የተጀመረች ቀጣይነት ያላት ትንሽ መሻሻል ተጠራቅማ ታሪክ ትሰራለች፡፡

ልማዶች ራስን የማሻሻል ድርብርብ ድርብርብ ወለዶች (compound interests) ናቸው፡፡ በድርብርብ ወለድ ራሱን በሚያበዛበት ልክ ገንዘብ መጠን የልማዶች ውጤትም በደጋገምናቸው መጠን ይባዛል። በየቀኑ ተነጥለው ሲታዩ የሚፈጥሩት ለውጥ በጣም ጥቂት መስሎ ቢታይም በወራት ወይም በዓመታት ቆይታ የሚያመጡት ለውጥ ግን አስደናቂ ነው፡፡ የመልካም ልማዶች ጠቀሜታዎች እና የመጥፎ ልማዶች ጉዳቶች ግልጽ ብለው የሚታዩት ከአምስት ወይም ከአስር ዓመታት በኋላ ወደኋላ ዞር ብለን ስንመለከታቸው መሆኑን ልብ ይሏል፡፡

ይህንን ነገር በየቀኑ ሕይወታችን አንጥረን ለማየት ከባድ ነገር ሊሆን ይችላል። በዚህም የተነሳ እነዚህን አይነት ለውጦች መተውና መናቅ ይቀናናል፡፡ ዛሬ ላይ ጥቂት ገንዘብ መቆጠብ ብትችል አሁኑኑም ሚሊየነር አትሆንም፡፡ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ጂም ብትሰራ በአካል ቅርፅህ ላይ ምንም ለውጥ አታይም፡፡ ዛሬ ምሽት ፈረንሳይኛ ቋንቋን ለሶስት ሰዓታት ብታጠና የቋንቋው ተናጋሪ አትሆንም፡፡ ጥቃቅን ለውጦችን ለማምጣት እንሞክራለን፡፡ የለውጡን ውጤት ቶሎ ማየት ስለማንችል ግን ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለሳለን፡፡

መጥፎው ነገር ደግሞ ይህ የለውጡ ውጤት የሚታይበት ፍጥነት እጅግ ዘገምተኛ መሆን ለመጥፎ ልማዶች እንድንመቻች የሚያደርገን መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ ምሽት ቤተሰቦችህን ተወት አድርገህ ስራ ላይ ብታሳልፍ ይረዱሃል፡፡ ሥራህን የምትጨርስበት ሰዓት ለነገ ብለህ ብታሳድረው ለዚህ የሚሆን ጊዜ “ነገ ላይ አይጠፋም፡፡ በዚህ መንገድ አንዲትን ውሳኔ መተው ብዙም ከባድ ነገር አይደለም፡፡

መጥፎ ውሳኔዎችን በየቀኑ ችግሮቻችንን በ1% እያባባስን፣ እየደጋገምን፣ ትንንሽ ስህተቶችን እየሰራን እና ጥቃቅን ምክንያቶችን እያበጀን ከሄድን ግን ድምር ውጤታቸው እጅግ የገዘፈ እና የከፋ ይሆናል፡፡ ችግር የሚዳርጉንም እዚህም  እዚያም የምንስራቸው ችግሮቻችንን በ1% የማባባስ ስራዎቻችን ድምር ውጤቶች ናቸው

በልማዶቻችን ላይ በምናመጣቸው ጥቃቅን ለውጦች የምናመጣው ጠቅላላ . ውጤት የአውሮፕላንን የበረራ መስመር በጣም በትንሽ ዲግሪ በመቀየር እንደሚመጣው ለውጥ ያለ ለውጥ ነው፡፡ ለምሳሌ ከሎስ አንጀለስ ወደ ኒው ዮርክ እየበረርክ ነው እንበል፡፡ ከላክስ አየር ማረፊያ የተነሳውን
አውሮፕላን ፓይለቱ በ 3.5 ዲግሪ ወደ ደቡብ ቢቀይረው መዳረሻህ የሚሆነው ኒው ዮርክ ሳይሆን ዋሽንግተን ዲሲ ነው፡፡ እንዲህ አይነት ትንሽ ለውጥ ስትነሳ አካባቢ አይታወቅህም፡፡ የአውሮፕላኑ አፍንጫም አቅጣጫውን የሚቀይረው በጣም በትንሽ ጫማዎች ናቸው፡፡ ጉዞው መላው አሜሪካን ሲያካልል ግን መዳረሻህ መጀመሪያ ካሰብከው ቦታ በመቶዎች በሚቆጠሩ ማይሎች ርቀት ላይ ይሆናል፡፡

በተመሳሳይ ሁኔታ በየቀኑ በልማዳችን ላይ የምናሳያቸው ጥቃቅን ለውጦች ሕይወታችንን ፍፁም የተለየ መዳረሻ ይስጡታል። በ1% የተሻለ ወይም በ1% የወረደ ውሳኔን መስጠት ትርጉም ሊኖረው የሚችል ለውጥ አይመስለንም፡፡ በጊዜ ሂደት ግን አሁን አንተ በሆንከው እና አንተ ትሆን በነበረው ማንነት መካከል ያለውን ልዩነት የሚፈጥሩት እነዚህ ጥቃቅን ልዩነቶች ናቸው፡፡ ስኬት የ በየቀኑ ልማዶች ድምር ውጤት ነው፡፡ ወሳኙ ነገር ልማዶችህ ወደ ስኬት የሚወስዱህ ናቸው ወይስ አይደሉም? የሚለው ነው፡፡

ስለሆነም አብዝተህ መጨነቅ ያለብህ ዛሬ ላይ ስላመጣኸው ውጤት ሳይሆን የዛሬው ጉዞህ አቅጣጫ ላይ ነው፡፡ የወጪ አወጣጥ ልማድህ ካልተቀየረ ጥሩ ነገር አትጠብቅ፡፡ በተቃራኒው ዛሬ ላይ ደሃ ብትሆንም ሽርፍራፊ ሳንቲሞችን የምትቆጥብ ከሆነ ግን ወደ የፋይናንስ ነፃነት የሚወስደው መንገድ ላይ ነህ - ከምታስበው በላይ በዝግታ ብትጓዝም፡፡

ይቀጥላል

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

1 year, 8 months ago

ይቀመጣል እንደ አደራ
ሰው ክፉም ሰራ
ደግም ሰራ

ሁሉም የእጁን ያገኘዋል፤
ቢቆይ እንጂ መች ይቀራል!!

?ወንድሙ ጅራ

የስብዕና ልህቀት
@Human_Intelligence

1 year, 8 months ago

ድንቅ አባባሎች

‹ልምድ ንድፈሃሳብ ከሌለው እውር ነው፡፡ ነገር ግን ንድፈሃሣብ ራሱ ልምድ ከጎደለው እንደው ዝምብሎ የምሁር ጨዋታ ነው የሚሆነው፡፡››
ኢማኑኤል ካንት

‹‹ደስታ ከምክንያታዊነት ጋር የሚስማማ ሳይሆን ከምናብ ጋር የሚዋሃድ ነው፡፡››
  ኢማኑኤል ካንት

‹‹ሌላ ሠው ማፍቀር የፈጣሪን ሌላኛውን ፊቱን ማየት ነው፡፡››
  ቪክቶር ሂጎ

"አእምሮ አስደናቂ አገልጋይ ነው ፣ ግን አስፈሪ ጌታ ነው።"
  ሮቢን ሻርማ

"አንድን ነገር መቼም ላላውቀው አልችልም በሚል ስሜት ተማረው፤ስታውቅ ደግሞ መቼም ላጣው እችላለሁ በሚል ስሜት አጥብቀህ ያዘው!!"
  ኮንፊሽየስ

"ሁለት የሞኝነት መንገድ አለ ። አንደኛው እውነት ያልሆነውን ማመን ሲሆን ሌላኛው እውነት የሆነውን አለማመን ነው ።"
      ሶረን ኪድጋርድ

‹በህግ አንድ ሠው የሌላን ሠው መብት ከተጋፋ ወንጀለኛ ነው፡፡ በስነምግባር ግን አንድ ሠው ሌላ ሠው ላይ ክፉ ማሠቡ ብቻ ወንጀለኛ ያደርገዋል፡፡››
  ኢማኑኤል ካንት

"ትንሽ ኪሳራ ፈርተን ትልቅ ጥቅም የሚገኝበትን ነገር አለመሞከር ሞኝነት ነው።"

"ቅናት ከፍቅር ጋር አብሮት ይኖራል ነገር ግን አብሮት አይሞትም።"
ያልታወቀ

"ስለራስዎ ጥሩ ስሜት እስኪሰማዎት ድረስ አንድ ሰው ስለራሱ ጥሩ ስሜት እንዲሰማው ማድረግ አይችሉም ፡፡"
  ሮቢን ሻርማ

‹‹ሠዎች ጥንካሬ አላጠራቸውም፡፡ ያጠራቸው ፈቃድ ወይም ፍላጎት ብቻ ነው፡፡››
  ቪክቶር ሁጎ

‹‹ዝናህን ለመገንባት ሃያ ዓመት ይወስድብሃል፡፡ ዝናህን ለማበላሸት ግን ሃያ ደቂቃ በቂህ ነው፡፡ ይሄን ጉዳይ ካሰብክ ነገሮችን በተለያየ መንገድ ታከናውናቸዋለህ፡፡››
  ዋረን በፌት

"ከኑሮህ ለመማር የምትከፍለው ትልቁ ዋጋ ትዕግስት ነው።"
ካቴና

"የበለጠ ለመስራት እና የበለጠ ለመሞከር ጥረት ያድርጉ። ህልሞችዎን ለመጀመር ሀይልዎን ይጠቀሙ ፡፡ ህልሞችዎን ያስፋፉ። በአእምሮዎ ምሽግ ውስጥ ማለቂያ የሌለው አቅም ሲኖርዎት የመለስተኛነት ሕይወት አይቀበሉ ፡፡ ታላቅነትዎን ለመጠቀም ደፉሩ"

ሮቢን ሻርማ

@Human_Intelligence
@Human_Intelligence

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago