ነጋሪት ሚዲያ Negarit Media

Description
" ኢትዮጲያ ለዘላለም ትኑር "
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 years, 7 months ago

"የተሳሳተ አካሄድ እንጂ የተሳሳተ መንገድ የለም"

ሁለት ወጣቶች ወደ ቤታቸው ለመሄድ የታክሲ ሰልፍ ላይ ቆመዋል፡፡ ታክሲው መጣና ሁለቱም ተሳፈሩ፡፡ ከ30 ደቂቃ ጉዞ በኀላ "መጨረሻ" በማለት ረዳቱ ሲናገር ሁሉም ከታክሲው ወረዱ፡፡ በዚህ ወቅት አንደኛው ወጣት በትክክል ሰፈሩ ሲደርስ ሌላኛው ግን በስተት ካለሰፈሩ ነበር የመጣው፡፡

በስተት ሌላ ሰፈር የሄደው ወጣት 'የተሳሳተ መንገድ ነው የመጣውት" ብሎ ማማረር ጀመረ፡፡
ነገር ግን የተሳሳተው መንገዱ ነው ወይስ ወጣቱ?

መንገዱማ ትክክለኛ ስለሆነ ሌላኛውን ወጣት በትክክል ሰፈሩ አድርሶታል፡፡ ነገር ግን መንገዱ ሳይሆን ተሳፋሪው የተሳሳተ በመሆኑ አንዱን ደሞ የማይፈልገው ሰፈር አምጥቶታል፡፡

የአብዛኞቻችን ህይወትም ተመሳሳይ ነው፡፡ መሆን የምንፈልገው ዶክተር ነው፡፡ ነገር ግን የምንማረው ያሬድ ሙዚቃ ቤት ነው፡፡ መሆን የምንፈልገው ታዋቂ ዘፋኝ ነው ነገር ግን የተሳፈርነው በኢንጅነሮች ታክሲ ነው፡፡ በህይወታችን ደስተኛ መሆን ከፈለግን ወደ ምንፈልገው ቦታ የሚያደርሰንን ትክክለኛ መንገድ ፈልገን መጓዝ ይጠበቅብናል፡፡ ነገር ግን ወደ እኛ ፍላጎት በማይወስድ መንገድ በመገኘታችን ብቻ ያ መንገድ ተሳስቷል ማለት አንችልም፤ ምክንያቱም በዛ መንገድ ተጉዘው ካሰቡበት የሚደርሱ ብዙ አሉና፡፡

'ምሽታችንን ባሰብነው መልኩ የተሳካና ቀና ይሁንልን"

መልካም ምሽት !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1

3 years, 7 months ago

ጓደኛሞች ነን። አራት ነን። አብረን ብዙ ግዜ አሳልፈናል። ስንሰባሰብ እንቧልታለን
እንቀመቅማለን ፤እንጨቃጨቃለን ፤ ስሜት የተቀላቀለበት ሃሳብ ይነሳል።
አንዱ ከአማራ ፤አንዱ ከኦሮሞ ፤አንዱ ከትግሬ ብሄረሰብ የመጡ ኢትዮጵያዊ ናቸው ።
የቡዙ ግዜ ሙግታቸው ሲብላላ ፤ሲቧካ ሲጋገር እንዲ ነው
.
.
.

#ኦሮሞው
ያኔ ወለጋ ላይ ከላይ የጦር አውሮፕላን ሲያርደን ። አገር በኮሮና ሲታመስ ህዝቧቻችን ናቸው
ስለወረርሺኙ መረጃ ይድረሳቸው ኢንተርኔት ይለቀቅ ብላችኾል ወይ....?????? እልቂታቸው
እልቂታችን ነው ማን አለ????
የራሳቹ ጉዳይ!!!

#አማራው

በየጊዜው፤ በየቧታው ፤በየጥጋጥጉ እልፍ አማራ በገፍ እና በግፍ ሲፈጅ ፤የቀስት እራት
ሲሆን የት ነበርክ? ሃዘኔታክ ከወዴት ነበር???
የራሳቹ ጉዳይ!!!!!

#ትግሬው

ስልክ ፤ መብራት፤ መንገድ ፤ባንክ ተዘግቶ እርሃብ ሲንጠን ፤የመዳኒት እጦት ሲፈጀን ፤
የኤርትራ ወታደር ሲዘረፍን የት ነበራቹ???? የሉአላዊነት ጥያቄ ማን አነሳ ???
የራሳቹ ጉዳይ !!!!

#ማስታወሻ
ጓደኞቼ ሃሳብ ውስጥ አገር የምትባል ምህዋር ትታየኛለች ሊያውም ኢትዮጵያ!

ሰላም?ለሀገራችን !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© አድሀኖም

@Negarit_media1

3 years, 7 months ago

.
ለምትወዳቸውና ለምታፈቅራቸው
ሰዎች መልካም ነገር ሰርተህላቸው
ቢደክምህ ምንም ደከመኝ
ብለህ አትሰላች ምክንያቱም
ለነሱ መልካም ሰርተህ መድከምህ
እረፍት ነውና፡፡

መልካም ምሽት ለሁላችን፡፡?

ቃለአብ ? ነኝ

❤️#በያላችሁበት_ፍቅር_ይኑራቹ፡፡❤️
#ፍቅር_ያሸንፋል

@Negarit_media1

3 years, 8 months ago

Live stream finished (8 days)

3 years, 8 months ago

#ነጋሪት
ከልብስህ ይልቅ ልብህ እንዳይቆሽሽ ጥንቃቄ አድር
.
ልብስህን ከአቧራ እና ቆሻሻ እንደምትጠብቅ ሁሉ ልብህንም ከተንኮል፣ ከክፋት፣ ከትዕቢት፣ ከሃሜት፣ ከቅናት እና ከምቀኝነት ጠብቃት
.
ልክ እንደ ልብስ ልብም ሲቆሽሽ ጠረን ያመጣል ።

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1

3 years, 8 months ago

ሰላም እንደምን አመሻችሁ የነጋሪት ቤተሰቦች !

"ደስተኛ መሆን ከፈለክ ሲፈልጉህ ከሚያገኙህ ስትፈልጋቸው ከምታጣቸው ሰዎች ሙሉ በሙሉ ዕራቅ"

የሰው ልጅ ሀዘን 99 በመቶ የሚሆነው የሚፈጠረው በእራሱ በሰው ልጅ ድርጊት ነው፡፡ ከእዚህ ውስጥ ደሞ ከፍተኛውን ድርሻ የሚወስዱት የእኔ የምንላቸው ሰዎች ናቸው፡፡ ለዛም ነው "በጣም የሚጎዳህ በጣም የምትወደው ሰው ነው" የሚባለው፡፡

አንዳንድ ሰዎች ልክ እንደ ወባ ትንኝ ናቸው፤ እነሱ ሲፈልጉና ደስ ሲላቸው ብቻ አንተ ጋር ይጣበቃሉ፡፡ አንተ ስትፈልጋቸው ግን ርቀው ሂደዋል፡፡ እናም ሁሌ እንዳሳዘኑክና እንዳስከፉክ ይኖራሉ፡፡ እናም እንደዚህ አይነት ሰዎችን መራቁ ትልቁ መፍትሄ ነው፡፡

ፈጣሪ ስንፈልገው የምናገኘው መልካም ጓደኛና ወዳጅ ይስጠን፡፡

መልካም ምሽት

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1

3 years, 8 months ago

ለውብ ቀን !

"ንፅፅር የደስታ ጠላት ነው" ።

#አብዛኞቻችን እየተሰቃየንበት ያለው በሽታ ይመስለኛል "ንፅፅር" አሁን ያለንበትን ቦታ (የሆነውን) መሆን ከምንፈልገው ቦታ ጋር #ንፅፅር ውስጥ እየከተትን ምን ያህሎቻችን ተሰቃየን ፣ ደስታ ከእኛ ራቁ አሁንም በዚህ መንገድ ውስጥ ያሉ ሰዎች አሉ በዙሪያችን ጓደኞቻችን ፣ ቤተሰቦቻችን ፣ የስራ ባልደረቦቻችንም ጭምር.....እንደዚህ ብሆን ኖሮ እኮ እንደዚህ አልሆንም ነበር የምንል ብዙዎች አይደለንም..? ማህበራዊ ሚዲያዎችን ስንጠቀም እንደ ቲክ ቶክ የመሳሰሉትን በተለይ ከሌሎች ጋር ራሳችንን እያነፃፀርን ስንቶቻችን ያለንበትን ሁኔታ ጠላነው #ደስታዎቻችን ተነጠቅን...?

አንድ ወዳጅ አለኝ ሁሉም #ለራሱ እንዲህ ይለዋል......<< የምፈልግበት ቦታ አልደረስኩም ግን ደሞ የነበርኩበትም ቦታ ላይ አልቆምኩም >>

#እስቲ እናውራበት የሚሰማቹ ስሜት ካለ በዚህ ሀሳብ ዙሪያ የናንተንም አስተያየት እንፈልገዋለንና ከስር ባለው ሊንክ ምልከታዎን ያጋሩን

ውብ የስራ ቀን..! "ፈገግ በሉ ሳቁ ያን ጊዜ ውብ ናቹ!?

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© ነጋሪት ሚዲያ

@Negarit_media1

3 years, 8 months ago

ጠላቶችህን አትነካካቸው የእባብ መርዝ ማክሸፊያ መድሀኒት ሳይኖርህ ከእባብ ጋር አትጣላ አትተናኮላቸው። ክፏ አስተሳሰብ ባለቤቶችን ለማሸነፍ ዝምታ እና ምስጋናን ተጠቀም እንጂ በክፋት አትመልስ። ሰነፍ ሰው ገንዘቡን ይቆጥባል ብልህ ሰው ደግሞ ከአንደበቱ ይቆጠባል። ገንዘብ ቢወጣም ይተካል። ከአንደበት የሚወጡ መርዛማ ቃላቶች ግን ምንም መልካም ሰው ብትሆንም ለጠላቶችህ ጥሩ አጋጣሚን ይፈጥራል። ስለዚህ ትሸነፋለህ። አሸናፊነትህ በገንዘብህ አቅም ሳይሆን በአንደበትህ ቃላቶች ይወሰናል። ዘመንህን ለመጠበቅ መልካም ንግግርን ተጠቀም። ጠላቶችህን ለማሸነፍ ዝምታን ስንቅህ ምስጋናን ቃልህ አድርግ። ያኔ የመልካሞች አባት ይከፍልሀል። ገንዘብ አይደለም ክፍያው። በገንዘብ የማይገዛ ፀጋን ያላብስሀል። ያ ፀጋ ደግሞ ዘመንህን ይመራል።

መልካም ቀን !

━━━━━━━━━━━━━━━━━━━━
© ራውኤል

@Negarit_media1

3 years, 8 months ago

???????#ነጋሪት ???????

?? እንደምን አደርሽ ኢትዮጵያ ??
?እንደምን አደራቹ የሀገሬ ልጆች?

"ቃልን መወጣት ከ መስዕዋትነት ይበልጣል፡፡ ለገባኸው ቃል ታመኝ ሁን ፤ ማድረግ ለማትችለው ነገር ቃል አትግባ! ቃል የገባኸውን ነገር ከመፈፀም ወደ ሁዋላ እንዳትመለስ! 'ያሉት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ' ነውና ነገሩ፡፡"

? #መልካም_ቀን ?

???????
?? #ኢትዮጵያ_ለዘለዓለም_ትኑር! ??
#ፍቅር_ያሸንፋል

@Negarit_media1

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago