Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ምክረ አበው

Description
ትክክለኛው ቻናላችን ይሄ ብቻ ነው። በዚ ብቻ ትምህርተ ሃይማኖትንና የኢትዮጵያ ምስጢራትን የአባቶቻችን ምክር በጥልቀት እንዳስሳለን። ሌሎቹ ቻናሎች የእኛ አይደሉም።
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her

2 months, 2 weeks ago

📜ዘፍጥረት 2፥15-18📜
------------------------------
15.“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።”

#ያበጃት_ይጠብቃትም_ዘንድ ፦ ስለዚህ ክፍለ ምንባብ ሰቨርያን እንዲህ ይላል «ይሰራና ይጠብቃትም ዘንድ የሚለው ሌባ ሳይኖር አላፊ መንገደኛም ሳይኖር ወይም ሆን ብሎ ክፉ የሚያደርግ ሰውም ሳይኖር ከማን ነው የሚጠብቃት? ከራሱ ነው የሚጠብቃት።ትእዛዙን ካልተላለፈ ገነትን አያጣትም፥ትእዛዙን መጠበቅ ለሰውልጅ ስራ ነው በዚህ ስራም ራሱን ይጠብቃል የተሰጠችውን ገነትንም ይጠብቃል»
ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው ከፈጠረው በኋላ በኤደን ወደ አዘጋጀለት ልዩ የአትክልት ስፍራ አስገባው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
16.“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
17.ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”

የታዛዥነቱ መለኪያ ቀዳሚው ትእዛዝ ይህ ነው ዛፉ መርዛማ ሆኖ ወይም የሆነ ልዩ የዕውቀት ሃይል ኖሮት ሳይሆን ቁጥር 9 እንደተብራራው መልካምና ክፉ የተባሉት የመኖር ሁኔታዎች የሰው ልጅ ለተሰጠው ትእዛዝ ባለው ግብረ መልስ የሚወሰን ነው።ምክንያቱም መልካም ብቻ ነው የሚያውቀው ዛፏን አትንካት ተብሏል ካልነካትም በዚህ መልካምነት ብቻ ይኖራል፥ትእዛዙን ከተላለፈና ዛፏን ቢበላ ግን ክፉን ያውቃል ማለትም በሞት(ከእግዚአብሔር መለየት፥የስጋና የነፍስ መለያየት) መቀጣት መጎስቆልን ያውቃል።ክፉና መልካም የሚያስታውቅ መባሉ ስለዚህ ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
18.“እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።”

#የሚመቸውን_ረዳት ፦ ረዳት ባርያ ወይም ተገዢ ሳይሆን በባህርይ በሙላት እርሱን የምታክል ሆና ለዓይኑ ደስ የምታሰኝ ከእርሱ ጋር በደስታ የምትነጋገር በሁሉም ከእርሱ ጋር የምትስማማ ለሁኔታውና ለፍላጎቱ በሙሉ መልስ የምትሰጥ...

#እንፍጠርለት ፦ በምዕራፍ 1፥26 እንዳለው ትንታኔ በተመሳሳይ እዚህ ምንባብም እንጠቀመዋለን። እግዚአብሔር ሌሎች ፍጡራንን እያማከረ ሳይሆን፥ የመፍጠር ውሳኔ ምክረ-ሐሳብ ከራሱ ጋር ብቻ እንጂ ሌሎችን አላማከረምና በራሱ ከራሱጋር ማሰቡንና መወሰኑን የሚያሳይ ነው፥ ልክ እኛ እስኪ ዛሬ ይሄን ላድርግ ይሄን ልስራ ብለን በህሊናችን ከራሳችን ጋር እንደምንመክረው ነው።

2 months, 3 weeks ago

📜ኦሪት ዘፍጥረት 2፥11-15📜
_____
#ማስታወሻ ፦ የተለያዩ ትናንሽ ምንጮች በተለያየና ዝቅተኛ ወደሆነ ቦታ በመፍሰስ እየተቀላቀሉ #መጋቢ_ወንዝን ይፈጥራሉ፤እነዚህ የተፈጠሩት መጋቢ ወንዞችም እየተቀላቀሉ አንድ ትልቅ ወንዝ ይፈጥራሉ።ትላልቅ የተባሉት ወንዞችም ወደሌላ ቦታ እንደፈሰሱ ከነርሱ ለሚበልጥ ወንዝ መጋቢ ሊሆኑ ይችላሉ።ይህ በዘመናችን ያለ የወንዝ አፈጣጠር ሂደት ነው። የመጀመርያው ግን የተለየ ነበረ ከኤደን የሚፈልቀው ትልቁ ወንዝ ወደ አትክልቱ ስፍራ(ገነት) ገብቶ እንዳጠጣ ሌላ አራት ወንዞችን ፈጥሮ ይወጣል።እዚህጋ መጋቢው ትልቁ ወንዝ ነው።
🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊🌊
11.“የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤”

#ኤውላጥ(ሐዊላ) ፦ በኩሽ ልጅ (ዘፍ10፥7) የተሰየመ በሲና አከባቢ ያለ አገር(ዓረቢያ) ነው።ከገነት የወጣው የወንዙ አንደኛው ክፍል(ፊሶን) በዚህ አካባቢ ይፈስ የነበረ።
------------------------------------
13.“የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።”

#ኢትዮጵያ ፦ ይህ በዕብራይስጡ የኩሽ ምድር ብሎ ነቢዩ ሙሴ የፃፈውን  ”ኢትዮጵያ” ተብሎ በግሪክኛ ሰባ ሊቃናት(septuagint) የተተረጎመ ነው።ፀሓፊው (ነቢይ ሙሴ) ቦታውን በቀጥታ ሲገልጥ፥የሰባ ሊቃናት ትርጉም ግን የፊትን ቀለም ስለሚገልፅ አሻሚ እሳቤ እንዲፈጠር አድርጓል።ምክንያቱም በግሪክኛ «ኢትዮጵያ» #ጥቁር ማለት ስለሆነ። ብዙ ሊቃውንት ደግሞ ወንዙ ከቪክቶሪያ ሃይቅ የሚነሳውና ዓባይን ጨምሮ ብዙ የብዙ ሃገራት ወንዞች እየመገቡት ወደ ግብፅ የሚፈሰው «የናይል-ወንዝ» ነው ብለው ተርጉመውታል።ነገር ግን ናይል ከጥፋት ውሃ በኋላ ባለው የመልክአ ምድር አቀማመጥ የተፈጠረ ወንዝ ስለሆነ ትርጓሜው አያስኬድም አመጣጡ ከኤደን እንደመሆኑ።ዞሮ ዞሮ ግዮን ወደ የአሁኑ አፍሪካ ይፈስ የነበረ ወንዝ ነው።
--------------------------
14.“የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው።”

#አሦር ፦ በሴም ልጅ ዘፍ10፥11 የተሰየመና ነነዌ መናገሻውን ያደረገ የአሁኖቹ ኢራቅ፣ቱርክ፣ኢራን ወዘተ የሚያጠቃልል ግዛት ነው።ጤግሮስ(tigris,hiddekel) በዚህ ግዛት በስተምስራቅ የሚፈስ ወንዝ ነው።
---------------------------
15.አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።”
ኤፍራጥስ ከአሶር በስተምዕራብ የሚፈስ ወንዝ ነው።እግዚአብሔር ለአብርሃም የሚሰጠው ርስት ድንበሩ እስከዚህ ወንዝ እንደሆነ ተጠቅሷል።👇👇

“በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ #ኤፍራጥስ_ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤”— ዘፍጥረት 15፥18

3 months, 3 weeks ago

ሰይጣን ክፉ ሰው ሊያደርግህ ሞክሮ ካልሆነለት መልካም ተግባራትን ያስተውሀል የማትፀልይ፣መፅሐፍ ቅዱስ የማታነብ፣ቅዳሴ ላይ የማትሳተፍ ወዘተ በማድረግ ለሌሎች ስጋዊ ተግባራት ለመዝናናት ምናምን ግን ግዜ ያለህ እንድትሆን ያደርግሀል ስለዚህ ስንፍናን ተዋጋ ከሰይጣን ነው!!

3 months, 4 weeks ago

ከ2016 ዓመታት በመላእክት የተሰበከው የምስራች “በመድሐኒትነቱ ለሕዝቡ ሁሉ ደስታ የሆነ ክርስቶስ ጌታ ተወልዶላችኋል” የሚል ነው።የተወለደው መድሓኒት፥የሰው ልጅ እርሱን በማመን እንዲድን አብ ለዓለም የሰጠው የፍቅር ስጦታ ነው።ስለዚህ ስጦታ በልዕልና(አርያም) ምስጋና ለእግዚአብሔር ይሁን፥በምድርም ይህን ስጦታ ተቀብሎ የሚኖርበት የህሊና ሰላም ለሰውልጅ ይሁን አሜን!! እንኳን አደረሰን 😇😇

የሉቃስ ወንጌል 2:10 - 11
“መልአኩ ግን እንዲህ አላቸው፦ “እነሆ፥ ለሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ደስታ የሚሆን የምሥራች እነግራችኋለሁና አትፍሩ፤ እነሆ! አዳኝ እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ዛሬ በዳዊት ከተማ ተወልዶላችኋልና።”

የዮሐንስ ወንጌል 3:16
“በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘለዓለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር ዓለምን እጅግ ስለ ወደደው አንድያ ልጁን ሰጠ።”

8 months, 2 weeks ago

ሐሳብ የስሜት ሕዋሶች ውጤት ነው...በልብህ የሚመላለሰውና የምታሰላስለው ነገር ከምትሰማው ከምታየው ከምትዳስሰው ወዘተ የተነሳ ነው። በልብህ ሲመላለስ ልማድ ከልማድ ቀጥሎ ፀባይህ(የስብእናህ መገለጫ) ወደ መሆን ያድጋል።ማንነትህ መንፈሳዊ እንዲሆን ሕዋሳትህ የእግዚአብሔርን መንፈስ(ፈቃድ) ይፈልጉ።

1 year, 1 month ago

ክርስቶስን በማመን መዳን የተባለው የዘላለም ህይወት እንዲሁም ጽድቅንና ቅድስናን በነፃ ከተሰጡት፤ አማኙ እነዚህን ለመጠበቅ እንደየ አቅሙ በቻለው መጠን #መጋደል ይጠበቅበታል። ስጦታ እንደመሆኑ እኛም ለስጦታው ግብረመልስ መስጠት ያስፈልገናል። ተጋድሎአችንም ከስጋችንና ከሰይጣን ጋር ነው።

🧠ስጋችን ከዚህ የእምነት ስጦታ እንዳይጎድል ክፉ መሻቱን በመግታት በጸሎት በመልካም ስራዎችንና እንደ ቃሉ ለመኖር ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ማድረግን እናለማምደዋለን እያለማመድንም ህብረቱ ን እናሳድገዋለን።

👹 ሰይጣንን ደግሞ በስጋ ዝለን ደክመን ይህን ስጦታ እንድንጥል ስለሆነ የሚዋጋን በአግዚአብሔር ቃል እየተቃወምነው እንዋጋዋለን።

ይህን ስጦታ ለመጠበቅ እየወደቅክም እየተነሳህም ከስጋዊ ድካም እስክታርፍ (እስክትሞት) ድረስ ተጋድሎው ይቀጥላል።ተጋድሎው መገዛት ነው መገዛትም ፍቃዱን ማገልገል ነው። መልካምና ክፉ አገልጋይ የሚያስብለንም የጸጋ ስጦታውን ለመጠበቅ ለራሳችን ምን ሰራን የሚል ነው።

1 year, 1 month ago
እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ሰው በተፈጥሮ …

እያንዳንዱ በምድር ላይ ያለ ሰው በተፈጥሮ ያገኘው ስጦታ አለው።ይህም ስጦታ በዓለም ላለው የሰው ልጅ አንዱ ለአንዱ የሚያገለግልበት ነው።ይህ ስጦታ እያንዳንዳችን እንደየአቅማችን መስራት የምንችለውና የተለያየም ነው።በዚህች ምድር ላይ ያለው የሰው ልጅ ለሚገጥሙት እያንዳንዳቸው ችግሮች መፍትሔው በሌላው ሰው እጅ ላይ ነው ስለዚህ እርሱ ባደለን ተፈጥሯዊ ስጦታ አማካይነት ፍላጎቱንና ፈቃዱን ስለምንፈፅም ሰውን ማገልገል ፈጣሪን ማገልገል ነው።

ባለስልጣን ብንሆን ሐኪም፥መሃንዲስ ብንሆን ነጋዴ፥መምህር ብንሆን አማካሪ፥መንፈሳዊ አገልጋይ ብንሆን ፈላስፋ፥ዳኛ ብንሆን የፀጥታ አስከባሪ፥ገበሬ ብንሆን ተቀጣሪ ሰራተኞች፥ወላጆች ብንሆን የሃገር ሽማግሌዎች...ወዘተ ነገ ስጦታ በሚያድለው አምላክ ፊት ምን ሰራህበት ሌሎችን በማገልገል ምን አተረፍክበት ተብለን እንጠየቅበታለን!!ለሰው ልጅ ህይወት መቃናት በሞያችንና በአቅማችን መስራታችን ለእግዚአብሔር ክብር ነው።

ስጦታ + ሐላፊነት =ተጠያቂነት
ተፈጥሯዊ ስጦታ ሐላፊነት ነው ሐላፊነት ደግሞ የሚያሸልም ወይም የሚያስቀጣ ተጠያቂነት አለው። ሰውን በታማኝነት ማገልገል "አንተ የታመንክ አገልጋይ በትንሽ ታምነሀልና በብዙ እሾምሀለሁ ወደ ጌታህ ደስታ ግባ" የሚል የዘላለም የህይወት ቃል እንሰማበታለን።በአግባቡ የማያገለግል ግን አንተ ክፉ ሐኬተኛ የማይጠቅም አገልጋይ ተብሎ ወደ ጨለማ ይጣላል ስጦታውም ተቀምቶ ለሌላ በቅንነት ለሚያገለግል ትጨመርለታለች!!
በዚህ ሳምንት ስለ ስጦታና አገልጋይነት ይሄንን ነው የምንማረው።

1 year, 1 month ago
ምክረ አበው
1 year, 1 month ago
ምክረ አበው
1 year, 1 month ago
ምክረ አበው
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 2 Wochen, 2 Tage her

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 Tag, 13 Stunden her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 Monate, 2 Wochen her