★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 19 hours ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
የጓደኛው ቤት ደጃፍ እንደቆመ ሲፈራ ሲቸር እያመነታ በሩን በቀስታ አንኳኳ። ተከፈተለት። አይኑን ከመሬቱ እንደተከለ ለጓደኛው እንዲህ አለው፡-
"ብዙ ጊዜ የሆነው ዕዳ አለብኝ። ጧት ማታ አበዳሪዬ ሲጠይቀኝ የምከፍለው ገንዘብ ስላጣሁ ሰላሜን ነሳኝ። የማደርገው ግራ ቢገባኝ ችግሬን ላካፍልህ ብዬ ወዳንተ መጣሁ።" አለው።
ጓደኛውም ምንም ሳይናገር ወደ ውስጥ ገባና የሚፈልገውን ያክል ገንዘብ አምጥቶ ቆጥሮ ሰጠው። ጓደኛው ለብድሩ የሚመልሰው ገንዘብ ስላገኘ በደስታ እየተፍለቀለቀ ተሰናብቶት ሲሄድ ሰጭው ግን እያለቀሰ ወደቤት ዘለቀ።
ይህን ሁሉ ተደብቃ ስትከታተል የነበረችው ሚስት የባሏን ለቅሶ ስታይ "ለምን ታለቅሳለህ? ብሩን መስጠት ከብዶህ ከሆነ ይቅርታ የለኝም ብለህ ምክኒያት ፈጥረህ አትመልሰውም ነበር?" አለችው።
"ያስለቀሰኝስ ገንዘቡን መስጠቴ ሳይሆን ይህን ያክል እስኪጨነቅ ድረስ ያለበትን ሁኔታ ሳልከታተል መቅረቴና ተቸግሮ እስኪጠይቀኝ ድረስ ቸልተኛ መሆኔ ነው" አላት።
ለሁላችሁም እንዲህ ያለ ጭንቀታችሁ ጭንቀቱ የሆነ የቁርጥ ቀን ወዳጅ ይስጣችሁ!
ሀቅ እና ድንቅ
Black man ነኝ ሼር በማረግ ተባበሩኝ
በBlack manየተዘጋጀ
በገዳይዋ ፊት ጥሏት የሄደው የጎስቋላዋ ህፃን ነፍስ ለወራት እንቅልፍ ነሳው፡፡
ካርተር ራሱን ወነጀለ፡፡ የፎቶግራፍ ሽልማቱን ባሸነፈ በሦስት ወሩ በልጅነቱ
ሲቦርቅ ባደገባት "ፓርክሞር በተባለች ለምለም መንደር ሀምሌ/19/1986
በ33 ዓመቱ እራሱን ገድሎ ተገኘ፡፡ ራሱን የሞት ፍርድ ፈረደበት ፡፡
በሞቱ ዋዜማ ላይ ሆኖ ለወዳጅ ዘመዶቹ ባስቀረው ማስታወሻ የሚከተለውን
ፀፀት አሰፈረ፡፡
"ካለኝ ነገር ቀንሼ አልሰጠሁም፡፡ እኔን ለማኖር ስራየን ብቻ ሰራሁ፡፡ ሚጡ
ከርሀብ ጋር ስትታገል ጥንብ አንሳው በእሷ ጠግቦ ይሆናል፡፡ ሚጡዋ፣ የአሞራው
እራት ስትሆን፣ በሚጡ ርሀብ እኔ ተሸለምኩ፡፡ ይህም እኔን ሚጡ ወዳለችበት
የሞት ጎዳና እንዲሄድ ፀፀቱ አስገደደኝ፡፡ ደህና ሁኑ ዘመዶቸ፡፡ ሰው ሲራብ፣
ሲቸገር አትዩ፡፡ ካያችሁም ከሌላችሁ ቀንሳችሁም ቢሆን እርዱ፡፡
የህሌና ቁስል መፈወሻ የለውም፡፡ ራሳችሁን ከህሌና ቁስለት ታደጉ፡፡"
መልካምነት ዋጋ አለው።
═════════❁✿❁ ════════
ወዳጆቼ ሼር በማረግ ተባበሩን
Black man ነኝ አዘጋጅቼ ማቀርብላቹ
ቀጣዮ ክፍል
አሁን ይህን ልብ ብለን እናስብ!
ለምን ቁሳዊ ህይወትን አብልጠን እንወዳለን?
በዚህ አለም ትልቅ የምንሮጥለት ነገር ምንድን ነዉ?
ለምን በመንጋ አስበን በመንጋ ኑረን በመንጋ እንሞታለን ?
ሕይወታችን የሚነዳዉ ሀሳባችንን በመለወጥ ነዉ ወይስ ልብስና መልካችንን በመለወጥ ?
በሕይወት ትልቁ ነገር ደስታ ፣ ሰላም እና ባለን ነገር እርካታ ነዉ ፡፡ ስለዚህ ገንዘብ ማካበት ደስታ አያመጣም ባለን ነገር መርካት ግን ደስታን ያመጣል ፡፡ ሰላም በወሬና በምኞት አይመጣም ነገር ግን ባለን ነገር ተረጋግተን ማሰብ ስንጀምር ይመጣል፡፡ ሞት አይቀርምና ባለን እድሜ ጥሩ ነገር ሰርተን እንለፍ።
black man ነኝ ያቀረብኩላቹ ሼር እና ኮመንት እንጠብቃለን
አንድ ቀን ቅዳሜ ደውዬላት ቤቴ መጥታ ሰፊ አልጋዬ ላይ እንደተቃቀፍን ....በስሜት እየቃተተች
በደንብ አባልገኝ አለችኝ" ቃሉ ቀፈፈኝ ...
አባልገኘሰ!... ፈፅሞ ከእሷ አንደበት የወጣ አይመሰሰለኝም ፤። የእሷ ቃላት ጠያይሞች ናቸው። ይሄኛው የተቃጠለ የመኪና ዘይት የመሰለ ጥቁር የከተማ ቃል ነበር።
"እንደዛ አትበይ ማሂ" አልኳት
"ለምን?"
" ይደብራል!"
"ይደብራል! አባልገኝ
ዝም አልኳት ። ከብዙ ግርምት ጋር
።
በአራት አመት ቆይታ አልጋ ላይ ከስሬ ተኝታ ከሚቆራረጥ ትንፋሽ ውጭ አንድ ቃል ስትተነፍስ ሰምቻት አላውቅም ነበር፣ የዛን ቀን ግን ምርር ባለ ድምፅ ብዙ ብዙ ነገር አለች አልሰማም ብል እንኳን አስገድዶ ጆሮዬ የሚፈስ ነገር ...
" አሰንደማታገባኝ እያወቅሁ አብሬህ መተኛት ብልግና ነው... ለመባለግ፣ ለመርካስ ፈቅጄነው... ይሄ ፍቅር አይደለመሰ፤አባልገኝ! ሳሎን ውስጥ አባልገኝ ፣ ሶፋ ላይ አባልገኝ፣ ምንጣፍ ላይ አባልገኝ ፣። ኩሽናህ ውስጥ አባልገኝ..."
ከእኔ ጋር መተኛት እርኩሰቷ ነው። ግን እርኩሰቷን በሚቆራረጠሰ ትንፋሽ ውስጥ ባለው ፍቅር አጠበችው።
ታፈቅረኛለች ግን አላገባትም። እንደተሳሳተች ታውቃለች ግን ፍቅር አስሯታል
Happy New Year !! In the name of God, I wish to you and your family peace, prosperity and to be successfull in all phases of life.
🌼🌼 መልካም አዲስ አመት 🌼🌼 🌼🌼 🌼
@Blakman21
ኒቼ የፈጠረው ገፀባህሪ የዚህ ዓለምን የስብዕና ልሽቀት የሚያሳይ ጥሩ ምሳሌ ነው፡፡ እብድ የተባለው ሰው ይሟገት የነበረው ስለእውነት ነበር፡፡ ሃይማኖት ቢዝነስ ሲሆን፣ ፍትህ ሲጠፋ፣ እኩልነት ሲርቅ፣ አድልኦ ሲበዛ፣ ደሃ-አደጉ ሲበደል፣ ምስኪኑ ሀብት ንብረቱ ተቀምቶ ሲሰደድ፤ ንጹሃን በፖለቲከኞች ቁማርና ሴራ ደማቸው ደመ-ከልብ ሲሆን ሲያይ እንዴት እግዚአብሔር ሞቷል አይል፡፡ የሐገራችን ገበሬም እኮ በ77ቱ ድርቅ ወገን ዘመዶቹን በርሃብ ሲያጣ፣ ከብቶቹ መንምነው ሲሞቱ አይቶ የሚደርስለት ቢያጣ፡-
‹‹አንጋጥጬ ባየው ሰማዩ ቀለለኝ፣
አላህንም ሰፈራ ወሰዱት መሰለኝ፡፡›› ......... ብሏል እኮ፡፡
በርግጥ ይሄ ዘመን ስለእውነት ስትሟገት እብድ የምትባልበት ዘመን ነው፡፡ መታመን፣ ለህሊና መቆም፣ ለምን እንዴት ብሎ መጠየቅ እብድ ያስብላል፡፡
እውነት ያበደው ግን ማነው? ስለእውነት የተሟገተው? ማነው ህሊና ቢስ የሆነው? በጠራራ ፀሐይ ፋኖስ አብርቶ እግዚአብሔርን የፈለገው? አይደለም! እሱማ ጤነኛ ነው፡፡ ነገር ግን እብዶች በነገሱበት ሐገር ጤነኛው እንደቀውስ ይቆጠራል፡፡፡ ዘንድሮ መሪው እብድ፣ ተከታዩ እብድ፣ ጳጳሱ እብድ፣ ፓስተሩ እብድ! ኡስታዙ እብድ! ምሁር ተብዬው እብድ! ምዕመኑ እብድ፣ ፖለቲከኛው ቀውስ! ካድሬው ንክ ነው፡፡ ላመነበት የቆመ፣ ለእውነት የወገነ፣ ለሐገር የሚያስብ፤ ለተበደሉ የሚሟገት፣ ለምስኪኖች የሚጮህ ጤነኛ ሰው ማግኘት ብርቅ ነው፡፡ የሃይማኖት ድርጅት የበዛበት፤ እምነትና ምግባር ያነሰበት ሐገር ሆነናል
?↗️Share ማድረግ እንዳይረሳ
Join us here??
?Channel @ppofpps ?Group @ppofpps1 . ?Robot # በቅርብ ቀን
Comment
___
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 19 hours ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 2 weeks ago