Abdul Halim Al Letemiy

Description
``በድምፅ ብልጫ ሳይሆን በእውነት ላይ የተመረኮዘ አካሄድ ተጓዝ፤ብቻህንም ቢሆን በሐቅ ላይ ፅና!!``
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

3 weeks, 3 days ago

ብለውን ነበረ!

ብለውን ነበረ ትላንት እየጮሁ አሀባሽን እንራቅ
አንሰፍስፎ መጥቶዋል ከቤትህ ሊገባ እምነትህን ሊነጥቅ
መስጂድህ እንደይፈርስ እምነትህ ተንዶ ጎዳና አንዳቶድቅ

==============================
   ክተት  ውጣ ሆሆሆሆ  በል መብት ኢንዲከበር
ሰልፍ ተጠርቷል ተነስ እንሰለፍ በአንድነት እንዘምር

በፉፁም አትቅረብ ከአህባሾች መንደር እሳትነው እያሉ
ብለውን  ነበረ  ትለነት እየጮሁ  ዘሬ ግን ዬት አሉ?
=============================
አሀባሽ ሲጨልም ሱናን እነያለን ብርሃኑ ገኖ
ብለውን ነበረ ውሸት እያሳዩን እውነታው ተከድኖ
ግርዶሹ ሲገለጥ ውጤቱን አየነው ያልጠበቅነው ሆኖ

ተሰልፈን ነበር ትለንት እውነት መስሎን አንዋር አዋልያ
      መንነቱን ሳነውቅ እያውለበለበን የኢኽዋን  ማለያ
ተሰልፈን ነበር ሰልፉ እውነት መስሎን ይዘን ጥሩ ንያ
==============================
    ባዳ አደረጉን በመደመር ወሬ ዱላቸውን መዘው
ተቀቅፈው መጡልን ካወገዙት ጋራ እጅ ተያይዘው!

ለካስ ለካስ አነበረም ያ ሁሉ መከራ ያ ሁሉ ሰቆቃ
ለእምነቱ ስኬት ለኡመው ተጨንቀው ህዝቡ እንዲነቃ
ፋራ አደረጉን.....
ወደ ወንበር መንደር ወደ ስልጣን መንደር መወጠጫ እቃ
አማኝ በአንድ ገደል ሁለቴ አይወድቅም ህዝቤ ዛሬም ንቃ
=====================

አብዱል በር አል-ለተሚይ

https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk

3 weeks, 3 days ago

ለሙሪዱና መሰልቹ!!

እንዳንተ አይነቱ አቅለ ደካማ አእምሮ ለጋ
ትላንት እንዳልነበረ በጤነኛ አቋም ከሰለፍዮችጋ
ዛሬ ተከርብቶ ሀቅን ሊያስገርፍ በእስር አለንጋ
በጭፍን ጥለቻ ምኞቱን ቢገልፅም ከመሰሎቹጋ  
ቦታ አንሰጠውም የእኽዋን ጥገኛ ኮተት ነዉ እኛጋ

አብዱል በር  አል ለተሚይ አሏህ ይጠብቀው!!

https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk/760

Telegram

Abdul Halim Al Letemiy

ለሙሪዱና መሰሎቹ == ▬▱== ▬▱=^> ➽ አጭበርባሪዎች ሆይ! ከሀቅ ሰዎች ተስፋ ቁረጡ ሰለፍዮችን የመጉዳት 0.1% ድርሻ የላችሁም። እናንተ በባጢል ባህር ስለምትዋኙ ሀቀኞችን እንደሀሰተኛ ማድረግ ጀብድ ይመስላችኋል። "አወቅሽ አወቅሽ ቢሏት መፅሃፏን አጠበች" እንደሚባለው አብሽር ባይ ሲበዛ ጭንቅላታችሁ ማገናዘብ ተሳነው። ለማንኛውም እዛው ከፖለቲካው ጋር የሚግማማ ለባጢል ሰዎች ጠበቃ የሆነ ሰው በሀቅ…

3 weeks, 5 days ago

ጉደኛው ሙሪድ ሲለፈልፍ
▬▱▬▱▬▱▬▱▬

~> አንዳንድ ጊዜ ሰዎች ማንነታቸውን የሚገልፁበት አጋጣሚዎች አሉ። ታዋቂው ሙሪድ ዛሬ በሞጫጨረው ፅሁፉ ማንነቱን ገልጿል።

እንዲህ ይላል፦ "እኔ እነዚህን ፌክ ሰለፊያ ነው የምላቸው። እነዚህ ትክክለኛውን የሰለፎች ጎዳና እና ትክክለኛ ሰለፊዮችን የሚያሰድቡና መንገዱን ሌሎች እንዲጠሉት የሚያደርጉ፣ የሚያወሩትንና የሚተገብሩትን የማያውቁ ጉዶች እንጂ ሰለፊይ ናቸው ማለት ይከብደኛል።"

መልስ፦ ተመልከቱ ጀርህ መሆኑ ነው። እኔኮ የማዝነው ራሳቸውን እንዲህ ተቺ አድርገው ኡለሞችን ማጣጣላቸው ነው። ፌክ ሰለፍያ ማለት ምን ማለት ነው? ሸይኽ ሀሰን ገላው ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ አብዱልከሪም ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ ሙሐመድ ሀያት ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ አብዱልሃሚድ ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ ዩሱፍ አህመድ ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ ሁሰይን አስልጢ ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ሸይኽ ጦሃ ኸድር ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? ወይስ ማን? ሰለፍይ ማለት ይከብደኛል ብለህ ከባድ ቃል ትናገራለህ! ምን ናቸው ታዲያ ሀዳዲይ ወይስ ሱፍይ ወይስ ምን? በእርግጥ ከነቀላችሁ ቆይታችኋል። እናውቃለን ሸይኽ ኘ
አብዱልሃሚድ ሱፍይ ነው ስለ አቂዳ አያስተምርም እያሉ የሚጮሁ መሪዶች እንዳሉ በደንብ እናውቃለን።

እንዲህ ይላል፦
"መውሊድ" የሚለውን መጽሐፍ መውሊድ አክባሪ የሆኑ አሕባሾችና መሰል ቡድኖች እንኳ አቃጥለው ጀብዱ እንደሠራ ሰው አላሳዩንም።

መልስ፦ አንተ ደደብ አህባሾች ዘንድ ይህ መፅሐፍ ምን ይሰራል!? ታወርክ እንዴ ወላሂ አንዳንዴ በጥላቻ ስሜት ህፃን የሚያስቅ ንግግር ታወራላችሁ! ጓደኞችህ የአህባሽ መፅሃፍ አታቃጥሉም ነበርን ይላሉ ሲመጀር የአህባሽ መፅሐፍ ምን ሊያደርግ ከሰለፍዮች ጓዳ ይገባል!? ሲቀጥል መንዙማ መፅሃፍን በተመለከተ ስህተት አለበት እያሉ የሚጨፍሩት የምትሞርድላቸው የነሲሃ አመራሮች ናቸው።
በአንድ ወቅት ወደ ኬሚሴ ከተማ በመሄድ በዳዕዋ ጉዳይ ከኡስታዝ ኸድር ከሚሴ ጋር ተገናኝተን ነበር። በወሬዎቻችን መሃል የሚከተለውን አካቶ ነገረን። "ገና ከውጭ እንደመጣሁ በነሳዳት እና በኢብኑ መስዑዶች መካከል ልዩነት እንዳለ ሰማሁ። ለማስተካከል ብዬ ወደ አዲስ አበባ ሄድኩ እነሳዳትን ሳናግር አግኛቸው አሉኝና ወደ መርከዙ ሰዎች ሄድኩ ሳላህ እህመድን አገኘሁት። ገና እንዳገኘሁ ከየት ነው አለኝ። ከከሚሴ አልኩ። ማሻአላህ ከሚሴ እነ አብዱልፈታህ ጋር ነው? ጥሩ ነው ከነሱ ጋር አብረን ነው የምንሰራው" አብዱል ፈታህ ማለት በወቅቱ ኸድር ከሚሴን አዛ የሚያደርግ የለየለት ኢኽዋኒ ነው ሸዋሮቢት ስለሚመጣ በደንብ እናውቀዋለን አንዳንደም በአፍሪካ ቲቪ ይቀርባል። "ከዚህ ኢኽዋንይ ጋር እንደሚሰሩ ሲነግረኝ 'እኔ ኸድር ከሚሴ ነኝ' ለማለት አፈርኩ። ለማንኛውም በወንድሞቻችሁ በነሳዳት በኩል ያለውን ልዩነት ለማስተካከል አይቻልምን? አልኩት በጣም ተቆጥቶ ከነሱ አንድ አይደለንም። ብዙ ርቀው ሄደዋል። የሳዳት መንዙማ መፅሐፍ ራሱ ብዙ ስህተት አለበት አለኝ በጣም ተገርሜ ተመለስኩ" በማለት ለኔና አብረውን ለነበሩ ወንድሞች ነግሮናል። ሙሪዱ ሆይ! ታዲያ የመርከዙ መሪ ሳላህ አህመድ መንዙማ መፅሐፍ ብዙ ስህተት አለበት ስላለ ፌክ ሰለፊ ነውን?

እንዲህ ይላል፦ "እኔ እንዲህ አይነት ሰለፊይ ነኝ ባይ ሰምቼም አይቼም አላውቅም።"

መልስ፦ የሰለፎችን መንሃጅ የት ሰምተህ የት አውቀህ ነው? ሰለፍይን ለማወቅ ሰለፎችን ማወቅ ያስፈልጋል። አንተኮ በትምህርት በፖለቲካ በተምይዕና በኢኽዋኖች ኮተት የተሞህ ነህ እንደት ሰለፍዮችን ታውቃለህ!? አታውቅም! እንዲህ አይነት ሰለፊ ለማወቅ ወይም ለመስማት እንዲህ አይነት ሰለፍን ማወቅ አለብህ አንተ ግን ጃሂል ግብዳ መሃይም ነህና አታውቅም።

እንዲህ ይላል፦ "አላህ ይምራቸው። ምክንያቱም ባቃጠሏቸው መጽሐፍቶች ውስጥ ያለን ሐዲሥና ቁርኣን አቃጥለዋል።"

መልስ፦ ተመልከቱ ይህንን ፍርደ-ገምዲል ግለሰብ! የሚናገረው ምን በተባለ ጉዳይ እንደሆነ ራሱ አያውቅም። በማያውቀው ገብቶ ነው እያቦካ የሚገኘው። ከመተቸቱ በፊት አዳምጦ ቢሆንማ ቁርኣንና ሀዲስ ቢኖርም እንደሚቃጠል በርካታ መረጃ ተጠቅሶ ነበር። ሰሃቦች ቁርኣንን አቃጥለዋል ታዲያ ይወቀሱ? ፌክ ይባሉ? ሸይኽ ኢብኑ ዑሰይሚንና መሰሎቻቸው የሙብተዲዕን ኪታብ ይቃጠል ብለዋል። ታዲያ ፌክ ሰለፍይ ናቸውን? እነዚህ አቅለ-ደካማ ሙሪዶች ቢያንስ የሚናገሩት የሚያስከትለውን መዘዝ መገምገም አይችሉም ባዶ ናቸዋ?

ሌላኛው ከአራት አመት በፊት በሳዳት ላይ ውርጅብኝ ስታዘንብ ፌክ ሰለፍይ ነበርክን???
እንዲህ ብለኸዋል፦ «እንደ መፍትሄ እየወሰድከው ያለው ነገር ግን ሌላ የባሰ ችግርም እየፈጠረ ነው። ጥበብና ሪፍቅ ይጎድለዋል።»

እንዲህም ብለኸዋል፦ «አካሄድህን አስተካክል። ታላላቆችህን አክብር፤ እነርሱን አስቀድም። የማይመጥኑህን ርዕሶችም በማንሳት ራስህን አታጨናንቅ። ለሁሉም ሰው አለው።»

እንዲህም ብለኸዋል፦ «የሚገርምህ ወንድም ሳዳት፤ አንተ እየሄድከው ያለው አካሄድ እየጎዳ ያለው አንተን ብቻ አይደለም። ሁሉንም ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ዱዓቶችን ነው።»

እንዲህም ብለኸዋል፦ «አብዛሃኛው ሙስሊም ወደ ተውሒድ የሚጣሩ ዱዓቶች ሁሉ አንተን አንተን ይመስሉታል። የሚገርምህ እኔ እንኳ ባቅሜ የተለያዬ አመለካከት ካላቸው ሙስሊሞች ጋር ሳወራ፤ ዘለው የሚያነሱብኝ አንተንና መሰሎችህን ነው። አንተ ስምህ በመጥፎ ስለተሰራጨ፤
ሌላውን ተውሒድ ብሎ የሚጣራውን ዳዒያህ ሁሉ እያስጎዳኸው ነው።»

እንዲህም ብለኸዋል፦ «በአንተና በመሰሎችህ የተነሳ፤ የተውሒድ ዳዕዋን ከሰፊው የእስልምና ዳዕዋ ነጥለውና ጠባብ አድርገው የሚያስቡ አሉ።

⁉️ እና ይህን ሁሉ ስትናገረው ፌክ ስለፍይ ስለነበርክ ነውን!?

⁉️ ያኔ ይህን ያልከው ትክክለኛውን የሰለፎች ጎዳና እና ትክክለኛ ሰለፊዮችን የምታሰድብ መንገዱን ሌሎች እንዲጠሉት የምታደርግ፣ የምታወራውንና የምትተገብረውንን የማታውቅ ጉደኛ እንጂ ሰለፊይ ነህ ማለት ይከብድ ነበርን!?

⁉️ ስሜትህን ያላሸነፍክ በእውር ድንበር የምትጓዝ ያልተገራ አንደበት ያለህ ነበርክን?

https://t.me/AbuImranAselefy/8614

1 month ago

#እንመካከር!!
*
#ቢስሚላህ
*!!

ይህ ዲን መመካከር፣ እስከሆነ ድረስ፣
ያለው ሃላፊነት፣ እንዲወርድ ከ~~እ~~ራስ፣
ከዲን ወገኖቼ፣ ወደድኩ መተዋወስ፣
ቀጥታ ልሻገር፣ ያለብኝን ላድርስ!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▱
በል ስማኝ ወገኔ፣ ያለህ በእስልምና፣
ዲንህን ተማረው፣ ስሜቱን ተውና፣
የተዓሱብ ዝገት፣ አጣጥበህ በሱና፣
የዲን ዘበኛ ሁን፣ ለሀቅ ታጋይ ጀግና፣
ወረተኛ አትሁን፣ ሞላጫ ሳሙና፣
ለባጢል አራማጅ፣ አትቁም ጥብቅና!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭▱
ዲን ሲጣስ ይመምህ፣ ለኢስላም ተቆሮቆር፣
ችልታን አስወግድ፣ ሱና እንዲህ ሲደፈር፣
ለይተህም እወቅ፣ ቃላትና ተግባር፣
እንደ እቃ አትገፋ፣ ሰምተህ አውርቶ አደር!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▱▭▱
ጠላት ተሰልፎ፤ በዲኑ ላይ ዘምቷል፤
ተውሒድን ለማክሰም፣ ተሳስሮ ተነስቷል፣
በአልከሶ ሀላባ፣ ምሳሌ ይሆናል፣
ከጼንጤ ጀምሮ፣ እስከታች ተጋምዷል፣
በፊት የጠበቅነው፣ የፈራነው ሆኗል፣
ይህ ጉደኛ መጅሊስ ዲን ማሞት ቀጥሏል!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭
ጅብሪል የለፋለት፣ ይህ ትልቅ ሃይማኖት፣
ነቢ የከፈሉት፣ ያ ሁሉ መስዕዋት፣
የሰሀቦች ህይወት፣ በዱር የቀረለት፣
አኢማዎች ሁሉ፣ ፍዳቸው ያዩለት፣
ዛሬ ደርሰህ አንተ፣ ድርድር ያዝክበት፣
ለስሜት ለጥቅምህ፣ ንግድ አተረፍክበት፣
ለቀረበህ ምቹ፣ የራቀን በመውጋት፣
የእልህ ዲን አረከው፣ የጨዋታ ልኬት!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭
በመጣው በሽታ፣ ከሆነ ተለክፈህ፣
የእነገሌ ቡድን፣ የሚል ጭነውብህ፣
ዲን ተጣሰ! እንርዳ፣ ተነስ ዝመት ሲሉህ፣
መሰለፉ ቀርቶ፣ ትዝ ሲልህ "እልህ"!፣
ይሄ ነው መቀበር፣ የቁም ሞት የሚሉህ!!
▭▱▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭▱▭
ይልቁን ልንገርህ፣ ከልብህ ተቀበል፣
ይህ አያዋጣህም፣ የዛሬው መታለል፣
በእልህ በፉክክር፣ መቋመጥ ለባጢል፣
ቁጭትን ያወርሳል፣ ጣትን ያስነክሳል፣
ባልታወቀ አኳኋን፣ ባልታወቀ ጊዜ፣ በተራ እንሞታል፣
ሁሉም በስራችን፣ እንቀሰቀሳል!!
#የዛኔ፦ ለባጢል ላገዘው፣ ለሀቅ ለደከመው፣
ጀሊል ይመነዳል፣ ሁሉም በከሰበው፣
ያን ቀን እያሰብክ ሁን፣ አሁን ለምትሰራው፣
እልህና ስሜት፣ አይቀርቡም በጊዜው፣
ጭብጫቦ,ውም ጥቅሙም፣ ዱንያ ላይ ቀሪ ነው፣
አላህ ሁሉን መክሯል፣ ደርሶናል ግሳጼው፣
ተቀብለን መስራት፣ መመካከር ድርሻው፣
የኛ ነው ምርጫችን፣ ከዛ ሚቀጥለው!!
#ጨርሻለሁ وَالْحَمْدُ لِلَّهِ رَبِّ الْعَالَمِينَ

አብዱረህማን ዑመር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://t.me/Abdurhman_oumer

1 month ago

⭕️የዘቀጡ እለት ⭕️****

ዘግይቶ የመጣው  ሀዳድይ ይባላል  ሱኒይ ሰለፊዩ
ዱዓት ወመሻኢኽ  ተብሎ ይጠራል  ኢኽዋን አታላዩ
የዘቀጡ እለት!
===========
የሱፊይ ጥርቅም የመጅሊስ አመራር እየታየው ገዝፎ
የሱን-ናውን ዓሊም ዱርዬው ይለዋል ክብሩን አጉድፎ
የዘቀጡ እለት!
===========
ጥላቻን ተግተው የተመዩዕ ልክፍት አናት ላይ ሲወጣ
ምላስ ተጥወልውላ መርዟን ትረጫለች በንዴት በቁጣ
የዘቀጡ እለት!
===========
ያስጎመጃል መሰል የሱና ሰዎችን ዘሎ ዘሎ መንከስ
ከድሮ ጀምሮ መች አደብ ኣለው ሉጋም አልባ ፈረስ

እንዲያ ባይሆንማ እራሱን የማያውቅ የተምዪዕ ጡሩንባ
ሙስጠፋ እና ሸይኹን ወደማነፃፀር ራሱን ባላስገባ

ገመዱን አርዝሞ ያዝ ብሎ ከላከው ውሻን ባለቤቱ
ብዙም አትገረም ይታወቅ የለም ወይ ይሄ ነው ውጤቱ
የዘቀጡ እለት!
===========
ሸይኽ ዩሱፍ አህመድን በወራዳ ነገር በኒፍቅ ጠርጥሮ
አህባሽ ኢኽዋንዩን በሳል ናቸው ይላል ወደ ኋላ ዞሮ
ስሜትን መከተል ለረዕይ መወገን የሀቅን ሰው መጥላት
ዓሊም ማጣጣሉም እጅጉን ይቀላል የዘቀጡ እለት

አቡ ያሲር አብዱል ፈታህ
https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk/743

የተለያዩ ኢስላማዊ ግጥሞች የሚለቀቁበት ቻናል ነው ይቀላቀሉ
👇👇👇👇👇
https://t.me/abdul_fettah

Telegram

Abdul Halim Al Letemiy

***👆******👆******👆******👆******👆******👆******👆******👆******👆*** ***📖******📖*** ገመድ አርዝሞለት ያዝ ብሎ ከላከው ውሻን ባለቤቱ ብዙም አትገረም ይታወቅ የለም ወይ ይሄ ነው ውጤቱ ***📖******📖*** https://t.me/abdul\_fettah https://t.me/abdul\_fettah

***⭕️*****የዘቀጡ እለት ***⭕️*****
1 month ago

የአለከሶው ከሳሽ ያጣው ክስ
★★★★★★★★★★★&

የአልከሶ ተፍጨርጫሪው ቡድን ያሰራቸውን ልጆች ከሳሽ አተው ቀጠሮ እያረዘሙ እስካሁንም መፍቴ አለማግኘታቸው በጣም ያሳዝናል ።
የአልከሶው መረጃ አልባው ብዱን ያሳሰሰራቸውን ለምን እንዳሳሰረ ስጠየቅ ትክክለኛ ምክያት ማቅረብ ስኖርበት ገና ለገና በየ ቀኑ የሙጉት ፊብረካውን እየጨመረ እየታየ ነው ።
የባጢል ሙጉት እንደዚህ ነው ያዋርዳል ።
ብርን፣ሀብትን መከታ ማድረግ በምንም ልጠቅም አይችልም ።የአልከሶው በብርና በጉልበት ያመነው ብዱን እስከመቼ ሰለፍዮችን እንደምያንከራትት እናያለን ።
እሄ ለግዜው እንጂ አይን ያወጣ ደባ ነው ትንሽም አያራምድም ።ለቀጠሮ በቀረቡ ቁጥር ሁላ ቀጠሮን ማራዘሙ ከምንም ፍትህ አይደለም ።
በጉዳዩ ላይ ትኩረት አለመስጠት እንጂ በአንድ ቀን ምጣራ ጉዳይ ነው ።
በውስጡ ጭስ ከሌለበት በዝህ ልክ ምንም ከሳሽ ሳይኖር የምን ማጣራት ነው ከዚህች እዚ አጣርቶ ወደ ዳኛ መቅረብ እንዴትስ ያቅታል ።
ነገሩ ግልፅ ነው ወዴትም መቆልመምና ማጠምዘዝ ነገርን አያጠራም ።ይልቅ ነገሩን ከመስመሩና በትክክለኛው አካሄድ ብፈለግ ነው ምሻለው አሁንም የታሰሩበት ጉዳይ የሀይማኖት እንጂ የግል ጉዳይ አይደለም። እሄ ሆኖስ ሳለ ይዘቱ ተቀይሮ የሀይማኖት፣ የመንሀጅ አይደለም የግል ከሳሽ ኣለ እያሉ በሰማይ ላም ኣለኝ ከሳሽ ስያስፈራሩዋቸው ቆይተዋል ።አሁንም መፈታታቸውን ሳይሆ ምንጠይቀው ነፃነታቸው ይረጋጋጥ። እንደ ማንኛውም አማኝ መብታቸው ተከብሮ ትክክለኛውን እምነት እና ዐቂዳ መስበክ ኣለባቸው መፍታቱ ወደዱም ጠሉ ይፈቱዋቸዋል ። የመስጂድ፣ የመድረሳ ቦታ ልሰጣቸው ይገባል።
ቤንጤ በነፃነት ፣ኦርቶዶክስ በነፃነት ምሰብክበት ሀገር ላይ ሰለፍዮችን ማገድ ከምንም ከፍትህ አይቆጠርም ።
📌የቴሌግራም ቻናል👇👇
https://t.me/ibnujemilchannel

1 month, 1 week ago

የሸዋል ወር ፆምን የተመለከቱ ጥቂት ፈትዋዎች‼️*================================
▪️*የአሏህ መልዕክተኛﷺ እንዲህ ብለዋል ፦ "ረመዳንን ፆሞ የሸዋልን ስድስት ቀናት ፆምን ያስከተለ አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠራል።"

📚[አቡ ዳውድ (2433) ዘግበውታል አልባኒ ሷሒሕ ብውታል]

▪️ከረመዷን ቡኃለ የሸዋል ስድስት ቃናትን የመፆም ፈድሉ ምንድ ነው?

◻️"ከረመዷን ቡኃለ የሸዋል ስድስት ቀናት መፆም አመቱን ሙሉ ከመፆም ይስተካከላል!"📚[ኢብኑ ዑሰይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (17/20) ]

▪️ከሸዋል ስድስት ቃናት መፆም ሚለው ወንዶችንም ሴቶችንም ያካትታልን?

◻️"ሴቶችም ወንዶችም ያካትታል!"

📚[ኢብኑ ዑሰይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (17/20)]

▪️ኣንድ አካል የረመዷን ቀዷዕ ያለበት ሆኖ እሱን ሳይጨርስ ከሸዋል ወር  ስድስት ቃናት ቢፆም "አመቱን ሙሉ እንደፆመ ይቆጠርለታል" የሚለው ፈድል ይገኝለታል?

◻️"የሸዋል ስድስት ቀናትን የመፆም ምንዳ ረመዷንን ጨርሶ እስካልፆመ አይገኝለትም!"

***📚***[ኢብኑ ዑሰይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (18/20)]

🔹ኢብኑ ባዝ እንዲህ ይላሉ "የሸዋል ወር ፆም እንደሚያመልጠው እያወቀ ቢሆንም እንኳን ፈርዱን ነው ቀድሞ መፆም የሚገባው"📚[መጅሙዕ አል_ፈታዋ (393/15) ]

▪️የሸዋል ስድስት ቀናት እንዴት ነው ሚፆሙት?

◻️"ኣንድ አካል በሸዋል ወር በፈለገው ግዜ የመፆም ምርጫ ኣለው። በመጀመሪያወ ፣ በመሃሉ ፣ በመጨረሻው ሲፈልግ በታትኖ መፆም ይችላል"📚[ኢብኑ ባዝ መጅሙዕ አል_ፈታዋ (390/15)]

▪️የሸዋል ወር ፆም'ን በተመለከተ የተኛው አፇፇም ነው የተሻለ ሚኾነው?

◻️"ከሸዋል ወር መጀመሪያ አካታትሎ ቢፆም የተመረጠ ነው"

📚[ኢብኑ ባዝ መጅሙዕ አል_ፈታዋ (390/15)]

◻️"የተሻለው ከዒዱ ቀን ቀጥሎ በተከታታይ መፆሙ ነው!"

📚[ኢቡኑ ዑስይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (20/20)]

▪️የሸዋል ወር ፆም'ን የግድ አከታትሎ መፆም ኣለበት?

◻️"አከታትሎም ለያይቶም መፆም ይቻላል"

📚[ኢብኑ ባዝ መጅሙዕ አል_ፈታዋ (391/15)]

▪️ኣንድ አካል የሆነ አመት ላይ የሸዋል ስድስት ቀናት'ን ከፆም በተቀሩት አመታታ ፆሙ ዋጂብ (ግዴታ) ይሆንበታል?

◻️" የሆነ አመት ላይ ፁሙ የሆነ አመት ላይ ቢተወው ምንም ችግር የለበትም ምክንያቱም በቅንነት የሚደረገ እንጂ ግዴታ ፆም አይደለም"

📚[ኢቡኑ ዑስይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (21/20)]

▪️በሸዋል ወር ፆምን ለመፆም የግድ ለሊት መነየት ግድ ይላል?

◻️"ሙሉ አጅር እንዲገኝለት ሲባል ነይቶ ማደር ኣለበት!"

📚[ኢቡኑ ዑስይሚን መጅሙዕ አል_ፈታዋ (184/19)]

🟦ኣንድ ሰው በሆነ ምክንያት ሳይፆም የሸዋል ወር ቢያመልጠው ቀዳዕ ማውጣቱ ይቻላልን?

◻️ " ሱና ፆም ስለሆነች በመክንያትም ሆነ ያለምክንያት የሸዋል ወር ያመለጠው ሰው ግዜዋ አልፎዋልና ቀዳዕ ማውጣቱ አልተደነገገም።"

📚[ኢብኑ ባዝ መጅሙዕ አል_ፈታዋ (389/15)]

Translation: IBNU AS_SHAYKH

https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk

1 month, 1 week ago

#የሸዋል ዒድ ተብሎ
ስለሚከበረው ብይኑ

▬▬▬▬▬▬
— ነቢዩን መቃረንና መከተል በ 6 (ስድሥት )ነገራቶች ይካተታል

🗓 ሸዋል 8/10/1443 ዓመተ ሒጅራ የተደረገ ሙሓዶራ

🇸🇦 በሳዑዲ ዓረቢያ በጂዳ ከተማ የተደረገ አንገብጋቢና ወሳኝ የሆነ ሙሓዶራ።

— በተለይ በደቡብ እና በሐረር ክልል ይህ የሸዋል ዒድ ተብሎ ከዒድ አል-ፊጥር በበለጠ ሁኔታ ይከበራል። አላህን ልትፈሩ ይገባል ይላሉ ሸይኹ...

*🎤 #በሸይኽ *ዐብዱልሐሚድ አል-ለተሚ (ሀፊዘሁሏህ)
https://t.me/abdulham/1904

1 month, 1 week ago

የዒድ መኻለፋቶች!!

- በሕብረት ተክቢራ ማለት
-ሴቶች እና ወንዶች መቀላቀል
-የዒዱን ለታ ሙታንን ለመዘየር መለየት
-ሴቶች የዒድ ሷላት'ን ሽቶ ተቀባብተው እና ፈታኝ አለባበስ ለብሰው መጣድ
-በዕድ የሆኑ ሴቶችን መጨበጥ
-ደስታን ለመግለፅ በሚል ዘፈን እና የመሳሰሉ ሙንከራትን ማስማት
-ሕፃናት ሰዎችን አዛ የሚያደርጉ ርችቶችን መተኮስ
-በመጨረሻም የዒባዳና የመልካም ተግባራት ወር የነበረው ረመዷን በማለቁ ከላያቸው ላይ ትልቅ ችግር እንዳቀለሉ አድርገው ረመዷን በመገባደዱ መደሰት (ከዒባዳ ሽሽት)!!

https://t.me/Abdul_halim_ibnu_shayk/720

Telegram

Abdul Halim Al Letemiy

ዒድ እና ተያያዥ ነጥቦች!! =================== በእስልምና ሁለት ዒዶች ይገኛሉ አንደኛው የረመዳን ፆም መጠናቀቅን አስመልክቶ የሚደረግ የኢደል ፈጥር በዓል ሲሆን ሁለተኛው የዙልሒጃ አስር ቀናት መጠናቀቅን በማስመልከት የሚደረግ የዒደል አድሃ በዓል ነው፡፡ በዚህ ርዕስ ስር በርካታ ነጥቦች ተካተዋ። ሸሪዓዊ ብይኑና ማስረጃው:- የዒድ ሰላት ከታላላቅ የኢስላም መገለጫዎች አንዱ በመሆኑ የተወሰኑ…

1 month, 2 weeks ago
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago