★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 3 weeks ago
እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።
መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77
#ፋኖነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ፋኖነት /አማራነት /ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏
Last updated 6 days, 14 hours ago
"የወላእ ( መረዳዳት ወይም መዋደድ ) እና የበራእ ( መራራቅ እና መቆራረጥ ) ክፍል ''
በሚል ርዕስ በዚሁ ቻናል በተከታታይ አምስት ክፍሎች ሲቀርብ የነበረዉ፣ በሸይኽ ሷሊሕ ዓብዱላህ አል ፈውዛን ተዘጋጅቶ በኡስታዝ ዩሱፍ አሕመድ የተተረጐመው ፅሁፍ በአላህ ፈቃድ ለንባብ በሚመች መልኩ በPDF ተዘጋጅቶ ቀረቦልዎታል ።
ለሌሎችም እንዲደርስ ሼር በማድረግ የአጅሩ ተካፋይ እንሁን!!
አላህ አንብበው ከሚጠቀሙት ያድርገን!
የባህር ዳር አህለሱና መሻይኾች ገፅ
كن على بصيرة
የታላቁ ሸይኽ #ዐብዱልሐሚድ_ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ #ቁርዓን ተፍሲር
#ክፍል_አራት (4⃣)
ለሞባይል በሚመች መልኩ ቁርዓን እየታየ እንዲቀራ ተስተካክሎ የቀረበ
ከሱረቱል ሷድ እስከ ሱረቱ አን-ናስ
ለኡማው እንዲዳረስ በየቻናላችሁ ሼር አድርጉት
@Abdul_halim_ibnu_shayk
የታላቁ ሸይኽ ዐብዱል ሐሚድ ለተሚይ ሀፊዘሁሏህ የቁርዓን ተፍሲር!
ክፍል ሶስት (3⃣**)
ለሞባይል በሚመች መልኩ እየታየ እንዲቀራ ተስተካክሎ የቀረበ
ከሱረቱል #መርየም እስከ ሱረቱ #አስ-**#ሷፋት
@Abdul_halim_ibnu_shayk
ትኩረት የሚሰጣቸው ጉዳዮች
የሚከተለውን የአላህ ቃል አስመልክቶ
“ከእነዚያ በሃይማኖት ካልተጋደሏችሁ ከአገሮቻችሁም ካላጧችሁ (ከሀዲዎች) መልካም ብትውሉላቸውና ወደእነርሱ ብታስተካክሉ አላህ አይከለክላችሁም፡፡ አላህ ትክክለኞችን ይወዳልና፡፡”
(ሙምተሂና ፡ 8)
የዚህ ቁርዓን ትርጉም ፡ ከከሀዲዎች ሁከታቸውን ያቀቡ ፣ ሙስሊሞችን ያልተጋደሉ ፣ ከአገሮቻቸው ያላስወጡ ከሆነ ፣ ሙስሊሞች ለዚህ ውለታቸው በጎ መዋል ፣ አለማዊ በሆኑ ግንኙነታቸው ፍትሀዊ መሆን ይገባቸዋል፡፡ ይህን ሲፈጽሙ ግን በልቦቻቸው አይወዷቸውም፡፡
ምክንያቱም አላህ የሚከተለውን ተናግሯልና
“መልካም ብትውሉላቸው ወደነርሱ ብታስተካከሉ”
ተወዳጁዋቸው አፍቅሯቸው አላለም፡፡
የዚህ ቢጤ ካፊር ስለሆኑ ሁለቱ ወላጆች የተናገረው ነው፡
“ለአንተ በእርሱ እውቀት የሌለህን ነገር በእኔ እንድታጋራ ቢታገሉህም አትታዘዛቸው፡፡ በቅርቢቱም ዓለም ፤ በመልካም ስራ ተወዳጃቸው፡፡ ወደእኔም የተመለሰን ሰው መንገድ ተከተል፡፡”
(ሉቅማን ፡ 15)
የአስማእ - ረዲዬሏሁ ዓንሃ - እናት ካፊር ከመሆኗ ጋር ዝምድናን ለመቀጠል መጣች፡፡ አስማ በዚህ ጉዳይ ረሱልን - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - አስፈቀደች፡፡ “የእናትሽን ዝምድና ቀጥይ” በማለት ለእርሷ ነገሯት፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል
“በአላህና በመጨረሻው ቀን የሚያምኑትን ሕዝቦች አላህንና መልክተኛውን የሚከራከሩትን ሰዎች ፤ አባቶቻቸው ፣ ወይም ልጆቻቸው ወይም ወንድሞቻቸው ወይም ዘመዶቻቸው ቢሆንም እንኳ የሚወዳጁ ሆነው አታገኝም ።”(ሙጃደላ፡ 22)
አለማዊ የሆነው ውለታን መመለስና ዝምድናን መቀጠል አንድ ነገር ሲሆን ውዴታ ደግሞ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ዝምድናን መቀጠልና መልካም ውለታ ከሐዲዎችን ወደእስልምና ለመሳብ ያነሳሳል፡፡ እነዚህ ሁለቱ (ዝምድና መቀጠልና መልካም ውለታ) በውዴታና በወዳጅነት ተቃራኒ የዳእዋ መንገዶች ናቸው፡፡ ሁለቱ ደግሞ (መውደድና ወዳጅነት) ካፊር ያለበትን መጥፎ ተግባር ማጽደቅና ከእነርሱ ዘንድ ያለውን (የክህደት ተግባር) መውደድ ይሆናል፡፡ ይህ ደግሞ ወደኢስላም ዳእዋ ላለማድረግ ምክንያት ይሆናል፡፡
ካፊርን ወዳጅ አድርጎ መያዝ ሀራም ነው ሲባል ከእነርሱ ጋር በተፈቀዱ ንግዶች አብሮ መስራት ፣ ሸቀጥ እና ጠቃሚ ምርቶችን ከእነርሱ ማስገባትና በእውቀታቸው እና በፈጠራቸው መጠቀምን ይከለክላል ማለት አይደለም፡፡ ነብዩ - ዓለይሂሶላቱ ወሰላም - ኢብን ኡረይቂጥ አልለይሲ የተባለውን ካፊር መንገድ እንዲጠቁማቸው ቀጥረውታል፡፡ ከአንዳንድ አይሁዶች ብድር ተበድረዋል፡፡
ሙስሊሞች እስካሁን ድረስ ሸቀጥ ፣ የተለያዩ ምርቶችን ከካፊሮች ከማስገባት አልተወገዱም፡፡ ይህ ከእነርሱ በዋጋ ከመግዛት አንዱ ክፍል ነው፡፡ በዚህ ጉዳይ እነርሱ በእኛ ላይ አንድም የሚመጻደቁበት ነገር አይደለም፡፡ ለውዴታም ፣ ለመወዳጀትም ምክንያት አይሆንም፡፡ አላህ ሙእሚኖችን መውደድ እና መወዳጀት ፣ ከሐዲዎችን መጥላትና መጣላት ግዴታ አድርጓል፡፡
አላህ የሚከተለውን ተናግሯል
“እነዚያ ያመኑና የተሰደዱ፡፡ በአላህም መንገድ ላይ በገንዘቦቻቸውና በነፍሶቻቸው የታገሉ፡፡ እነዚያም (ስደተኞቹን) ያስጠጉና የረዱ፡፡ እነዚያ ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ እነዚያም ያመኑና ያልተሰደዱ እስከሚሰደዱ ድረስ ከነሱ ምንም ዝምድና የላችሁም፡፡ በሃይማኖትም እርዳታን ቢፈልጉባችሁ በእናንተና በነሱ መካከል ቃል ኪዳን ባላችሁ ህዝቦች ለይ ካልሆነ በስተቀር በናንተ ላይ መርዳት አለባችሁ፡፡ አላህም የምትሰሩትን ሁሉ ተመልካች ነው፡፡ እነዚያም የካዱት ከፊሎቻቸው ለከፊሉ ረዳቶች ናቸው፡፡ (ከምእምናን መረዳዳትን ከከሐዲያን መቆራረጥን) ባትሰሩት በምድር ላይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይሆናል፡፡”
(አንፋል ፡ 72-73)
ሀፊዝ ብን ከሲር የሚከተለውን ተናግረ ፡
“ባትሰሩት በምድር ለይ ሁከትና ታላቅ ጥፋት ይሆናል” (አንፋል ፡ 73)
የሚለው የቁርዓን ትርጉም ሙሽሪኮችን (ጣኦት አምላኪያን) ባትርቁ ፣ ሙእሚኖችን ወዳጅ አድርጋችሁ ባትይዙ በሰው ውስጥ ፊትና (ሁከት) ይከሰታል፡፡ እርሱም ነገሩ ይደበላለቃል ፣ ሙእሚን በካፊር ይቀላቀላል፡፡ በሰዎች መካከል ፈሳድ (ብልሹነት) ይከሰታል ፣ በርዝመትም በስፋትም ፈተና ይሰራጫል…”
كن على بصيرة
ይህን ያውቃሉን?!
"“"""""""
በአንድ ረከ'ዐ ብቻ ቁርኣንን ሙሉበሙሉ (ከሱረቱል "በቀራ" እስከ ሱረቱ "አን-ናስ" ያነበቡ ሰዎች 4 ናቸው። የስም ዝርዝራቸውም እንደሚከተለው ነው:
*📗 [تبيض الصحيفة، صفات: ٩٤-٩٥]*
Translated by: Abu Hafsah
@semirEnglish
https://t.me/semirEnglish
"ዝሙትን ፈርቼ ሰገራ ተለቀለኩ!"
"""""""""""
አቡበክር አል-ሚስኪ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) እንዲህ የሚል ጥያቄ ተጠየቀ: "ሁልጊዜም ካንተ ጥሩ መዓዛ ያለው ጠረን ይፈነጥቃል (ይወጣል) ይህ የሆነው ለምንድነው? አኳሃኑስ?"
አቡበክር አል-ሚስኪ (ረሂመሁላሁ ተዓላ) የሚከተለውን ምላሽ ሰጠ፡ "በጌታዬ በአላህ ይሁንብኝ! ለአመታት ያክል ሽቶ ሚባል ነገር ተጠቅሜ አላውቅም፤ይሁንእንጂ የዚህ ጥሩ ጠረን ምክንያቱ እንደሚከተለው ነው፡ ከእለታት አንድቀን የሆነች ሴት ሸውዳ እቤቷ ውስጥ አስገባችኝ።
ከዚያም በሩን ዘጋግታ ቆላለፈችው፤እኔን ማማለል ጀመረች፣በጊዜው ምን እንደማደርግ ግራገባኝ ምክንያቱም ምንም አይነት አማራጭ አንነበረኝምና። ለጊዜው እንዲህ ብዬ አልኳት፡
"መታጠብ (እራሴን ማፅዳት) እፈልጋለሁ።"
ከዚያም ባሪያዋን ወደ ሻውር (መታጠቢያ ክፍል) እንዲወስደኝ አዘዘችው። እኔም ከሷ አገልጋይ ጋር ወደ መታጠቢያ ክፍል ሄድኩ፣ ወደ መታጠቢያ ክፍል ከገባው በኃላ፣በእጄ ሰገራ ይዤ መላው ሰውነቴን ለቀለኩት።
ከዚያም በዚህ ሁኔታው ሳለሁ ወደሷ ሄድኩ፤ ሁናታዬን ካየች በኃላ በእጅጉን ተደናገጠች፤ ሴትየዋ ከቤት እንደወጣ ትዕዛዝ አስተላለፈች።እኔም ቤቱን ለቅቄ ወጣሁ፣ ወዲያውኑ ሻውር ወሰደኩ። የዛን ሌሊት ህልም ተመለከትኩ። የተመለከትኩት ህልም እንደሚከተለው ነበር፡
እንዲህ ተባልኩ፦ "ከዚህ በፊት ያልተሰራውን ስራ ነው የሰራኸው፤በዚች በቅርቢቷ ዓለምና በመጪውም አለም ጥሩ መዓዛ (ጠረን) እንዲኖርህ፣ንፁህ አእንድትሆን አደርግሃለሁ።"
ከእንቅልፌ ስነቃ ከሰወነቴ እጅግ በጣም ጥሩ መዓዛ ያለው ከሰውነቴ ይፈልቃል (ይወጣል)። ከዛን እለት ጀምሮ እስካሁንም ድረሥ ይህ ጠረን ቀጥሏል።"'
📗 አል-መዋዒዝ ወል-መጃሊስ (ገፅ:224)
Translated by: Abu Hafsah@semirEnglish
https://t.me/semirEnglish
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 1 month, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 3 months, 3 weeks ago
እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።
መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77
#ፋኖነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ፋኖነት /አማራነት /ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏
Last updated 6 days, 14 hours ago