★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 4 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago
[💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
✝ጊዜ ለምን? || ጾመ ነነዌ✝
Size:-82.9MB
Length:-1:29:33
በርእሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
@mezigebehayimanot
"ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው" ስምዖን አረጋዊ
#የካቲት_8 ፤ የጌታችን ከከበርች ልደት በኋላ ወደ ቤተመቅደስ የገባበት ዕለት ኾነ ፡፡ በዓሉ ከጌታችን ንዑስ በዓሎች መኻከል አንዱ ነው ፡፡
++++
የካቲት 8 ፤ ልደተ ስምዖን አረጋዊው ፣ ካህን ፣ ጻድቅ ፣ ነቢይ ፡፡
++++
ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ የኦሪትን ሕግ ለመፈጸም ወደ ቤተ መቅደስ ገባ ። ይህም ሕግን ሊፈጽም እንጂ ሊያፈርስ አለመምጣቱን በቃልም ፣ በግብርም የገለጠበት በዓል መኾኑን ያስረዳናል። ሥርዓቱን ለመፈጸም እናቱ ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ጌታቸውን ይዘው፣ የርግብ ግልገሎችና ዋኖስ ጨምረው ወደ ቤተ መቅደስ ሔዱ ።
++++
የስምዖን አረጋዊ ነገርም እንዲኽ ነው ..
ዓለም በተፈጠረ በ5,200 ዓመታት በጥሊሞስ የተባለ ንጉሥ በግሪክ ነግሦ ነበር። ዓለሙን እንደ ሰም አቅልጦ፣ እንደ ገል ቀጥቅጦ የገዛው መሆኑን ገልጦ፣ የቀረው ነገር አለመኖሩን ሲናገር ባለሟሎቹ በእሥራኤል ጥበብ የመላባቸው 46 መጻሕፍት ስላሉ እነርሱን አላስተረጎምክም አሉት። እስራኤልን አስገብሮ ስለነበር 46ቱን የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከ72 የአይሁድ ሊቃውንት ጋር አስመጣ። አይሁድ ተንኮለኛ መኾናቸውን ስለሚያውቅ 36 ድንኳን እንዲዘጋጅ አድርጎ ኹለት ኹለቱን መድቦ፣ የየድንኳኑን ሊቃውንት የሚቆጣጠሯቸው አንዳንድ ጠባቂዎች ጨምሮ እንዲተረጕሙ አዘዛቸው።
በዚህ ምክንያት በ284 ዓመት ከክርስቶስ ልደት በፊት 46ቱ የብሉይ ኪዳን መጻሕፍት ከዕብራይስጥ ወደ ልሳነ ጽርዕ (ግሪክ) በ70ው ሊቃናት ተተረጐሙ። ከ70 ሊቃናት በመኻከል አንዱ የነበረው #ስምዖን ምሁረ ኦሪት ነበር። ይተረጕም ዘንድ መጽሐፈ ኢሳይያስ ደረሰው። ታዲያ ይህ ሊቅ የትንቢቱን መጽሐፍ እየተረጎመ ሳለ ምዕራፍ ፯ ላይ ሲደርስ የሕይወቱን አቅጣጫ ወደ ዘላለማዊ በረከት የሚያሳድግ ልዩ ገጸ ንባብ ገጠመው ። እርሱም
“ ስለዚኽ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነኾ ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።” ኢሳ 7፥14 የሚል ነበር።
ስምዖንም "እንዴት ድንግል ትፀንሳለች?" ብሎ "ድንግል" የሚለውን "ሴት" ብሎ ቀይሮ " ሴት ትፀንሳለች " ብሎ ለማረም ይሞክርና አመሻሽ ላይ ስለነበር እንቅልፍ ሸለብ አድርጎት ሲነቃ የቀየረው ተቀይሮበት " ድንግል ትጸንሳለች" የሚል ሁኖ ያገኘዋል። ተሳስቼ ነው ብሎ አሁንም ሊያበላሽ ሲሞክር መልአኩ ሦስት ጊዜ አርሞበት በሦስተኛው መልአኩ ራሱ ተገልጦለት "ይህችን ድንግል ሳታይና ልጇንም ታቅፈህ ሳትባረክ አትሞትም"
( የተጠራጠርከውን ሳታይ አትሞትም ብሎ ብሎ ነግሮት ) ተሰወረ። አረጋዊ ስምዖንም ከዚያች ዕለት ጀምሮ መድኅን ክርስቶስ እስከሚወለድ ለ284 ዓመታት ከአልጋ ጋር ተጣብቆ ኖረ።
አምላካችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም በተወለደ በ40 ቀኑ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያምና አረጋዊው ቅዱስ ዮሴፍ ወደ ቤተ መቅደስ ይዘውት ወጡ ። በዕለቱም መልአከ እግዚአብሔር አረጋዊ ስምዖንን ቀስቅሶ ተስፋ የሚያደርገው አዳኝ ክርስቶስ መምጣቱን ነገረው። በዚህ ጊዜ አረጋዊ ስምዖን አካሉ ታድሶ፣ እንደ 30 ዓመት ወጣት እምር ብሎ ከአልጋው ተነሣ። በፍጥነትም ወደ መቅደስ ገባ። መድኀኔዓለምን ከድንግል ማርያም ተቀብሎ በመታቀፍ "ይእዜ ትስዕሮ ለገብርከ በሰላም እግዚኦ በከመ አዘዝከ፡-አቤቱ ባሪያህን እንደ ቃልህ በሰላም አሰናብተው"
(" ጌታ ሆይ፥ አን እንደ ቃልህ ባሪያህን በሰላም ታሰናብተዋለህ ፤ ዓይኖቼ በሰዎች ሁሉ ፊት ያዘጋጀኸውን ማዳንህን አይተዋልና፤
ይኽም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን ለሕዝብህም ፳ኤል ክብር ነው።" (ሉቃ 2÷29-32) )
በማለት ጸለየ።
አምላኩም ጸሎቱን ሰምቶት በዛሬው ዕለት ዐረፈ። ከበዓሉ በረከት ይክፈለን። አሜን!!
የሊቁ ስምዖን አረጋዊ በረከት እና ምልጃ አይለየን !
በዓለ ስምዖን በዐይቢይነት ሜላት ደብረ ገነተ ኢየሱስ ይከብራል ፡፡
ጐንደር -- › አንዳቤቴ ወረደ -- › ገነተ ኢየሱስ
በ13ኛ መቶ ክፍለ ዘመን በአጼ ሰይፈ አርዕድ ዘመነ መንግስት
ልዕልት ሜላተ ወርቅ ያሰተከለችው ደብር ነው ፡፡
+++
በዓሉ በኢየሱስ ስም የተሰየሙ አድባራትና ገዳማት ላይ ይከበራል !
የበዓለ ዕረፍቱ ክብረ በዓል የሚከበርባቸው
#ደብረ_ጽባሕ_ጸዶየ_መርቆሬዎስ_፤ (በዐፄ ይኵኖ አምላክ ዘመን የተመሠረተ፡፡)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ አኵሱም ከተማ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ጸዶየ፡፡
#ርዕሰ_አድባራት_ወገዳማት_ደረስጌ_ደብረ_ጽዮን_ማርያም_፡፡
አድራሻ፤ ሰሜን ጎንደር ሃገረ ስብከት፥ ስሜን፥ ጃናሞራ ወረዳ፥ መካነ ሰላም ከተማ (ራስ ደጀን ተራራ አናት አጠገብ)፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. መርካቶ አውቶቡስ ተራ → ጎንደር → ደባርቅ → ጃናሞራ፡፡
#ጎንደር_ደብረ_ፀሐይ_ቊስቋም_ማርያም_ቤ/ክ፤ጎንደር ሀገረ ስብከት፤
#ጎንደር ደብረ መድኀኒት ዐቢየ እግዚእ ኪዳነ ምሕረት፤
አድራሻው፤ ማዕከላዊ ጎንደር ሀገረ ስብከት፤
#ጋሹ_አምባ_አርማንያ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤ (ስዕሉ በበዓለ መርቆሬዎስ ቀን የሚያሸበሽበው)
አድራሻ፤ ሰሜን ሸዋ ሃገረ ስብከት፥ ደብረ ሲና፥ ጣርማበር ወረዳ፥ አርማንያ ቀበሌ፤
ትራንስፖርት፤ ከአ.አ. ጉርድ ሾላ አውቶቡስ ተራ → ደብረ ሲና → አርማንያ(ጋሹ አምባ)፡፡
.#ደሴ_ደብረ_መዊዕ_ኪዳነ_ምሕረትና_መርቆሬዎስ_፤ ደሴ፤
#ናዝሬት_ደብረ_ሰማዕት_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤
ናዝሬት(አዳማ)፤
፡፡
#አማን_ጎሪቃ_ቅዱስ_መርቆሬዎስ_፤
አድራሻ፤ ደቡብ ምዕራብ ሃገረ ስብከት፥
#ደብረ ሲና ቅዱስ እግዚአብሔር አብ ቤ.ክ በድርብነት
❤️“ ንዑ ንትመሀር ልሳነ ግእዝ ”
?ኑ የግእዝ ቋንቋ እንማር?
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 2 weeks ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 7 months, 4 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago