Ethio zodiac/ ዞዳይክ

Description
ኮኮብዎን መዋቅ ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ይሄን ቻናል ይቀላቀሉን ይወዱታል አይቆጩበትም ♥♣♦





ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 መጠየቅ ትችላላቹ
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 years, 7 months ago

ውድ የኢትዮ ዞዳይክ ቤተሰቦች፣ #የወላጆችን ዞዳይክ ሚገልፀው ምዕራፍ፣ እዚጋ አብቅቷል፣ በሌላ ፕሮግራም በቅርብ እንገናኛለን፣ እስከዛ ባላቹበት ሰላም ሁኑልን?

@zodiac_zodiac

3 years, 7 months ago

#ፓይሰስ_ወላጆች

»» ፓይሰስ ወላጆች ፈጠራዊ ችሎታ አላቸው፣ ትምህርትም ክፍል ገብተው ብቻ ሳይሆን አለምን በተለያየ አቅጣጫ በመመልከትና በመመርመር ማግኘት አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ። ልጆቻቸው ጥሩ እውቀት እንዲያገኙና እንዲማሩ የተቻላቸውን እንዳለ ያደርጋሉ። ልጆቻቸው ድጋፍ ሲፈልጉም እንዴት ድጋፍ ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ፣ ጎበዝ ናቸው፣ ጥግ ይዘው አይቀመጡም፣ ሁሌም የተሻሉ ወላጅ መሆንን ይፈልጋሉ፣ እንደዛም ቢሆን ግን ስሜታቸው ዝቅ ሲልና ደስታቸው ሲጠፋ፣ ቁጡና ብሶተኛ ይሆናሉ።

»» ልጆቻቹ እያወቋቹ ሲመጡ አድቫንቴጅ እንዳይወስዱባቹ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቹ፣ እንደ ወላጅ መስመር መስጠት ግዴታ ነው። ደግና ዝም የሚል ወላጅ ከምቶኑ፣ ትኩረት ምትሰጡ ወላጅ ብትሆኑ ነው ሚሻለው። ፓይሰስ ወላጆች ሁኔታዎችን ሚያዩበት ጥልቀት አስገራሚ ነው፣ እንደ ወላጅም ትልቅ አሴት ነው።  ልጆቻቹ እናንተን ሲየዩ፣ ደና የመሆን ስሜት ይሰማቹዋል፣ ልጆቻቹን የማሸማቀቅ እፍረት እንዲሰማቹ አታደርጓቸውም፣ ያለውን ተቀብለው ቀስ ብለው መስተካከያ ያደርጋሉ። ሰውን መረዳት ትልቁ የፓይሰስ ወላጆች ኳሊቲ ነው።

»» በእያንዳንዷ ተፈጥሯዊ ሂደት ውስጥ ውበትን መመልከት ትችላላቹ፣ ተፈጥሯዊ አርቲስት ናቹ፣ በጥበብ ውስጥ ሙሉ ስሜታቹን የመግለፅ ብቃት አላቹ። በሙዚቃ፣ በስዕል፣ በግጥም፣ በማስታወሻና ቪዡዋል አርት ራሳቸውን ይገልፃሉ። ላላቸው ጥበባዊ ችሎታ ግዜ ስጡት፣ ህልመኞቹ ፓይሰስ ወላጆች፣ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ፣ ልጆቻቸው ያላቸውን ተፈጥሯዊ ክህሎት እንዲያወጡ እገዛ ያደርጋሉ። ፓይሰሶች ለሁሉም ነገር መስፈርታቸው ደግነት ነው።

»» አሳዎቹ ፓይሰሶች ቁጡ ሚሆኑበት አጋጣሚ አለ፣ ሻርክም የአሳ ዘር ነው፣ ፓይሰሶችም በልጆቻቸውና በሚወዱት ነገር ከመጡባቸው እንደ ሻርክ ተናካሽ ይሆናሉ። ለአከባቢያቸው ሲበዛ ስሜታዊ ናቸው፣ ልጆቻቸው ህፃን እያሉ ላደርጉት እያንዳንዷ አስቂኝም ሆነ አዛዛኝ ድርጊት ትዝታ አላቸው። ለራሳቸው ረፍት መስጠት፣ ስላለፈውና ስልወደፊቱ ብቻ ሳይሆን ስለ አሁንም ማሰብ ያስፈልጋል። ፓይሰሶች አለምን የመውደድ ተምሳሌት ናቸው፣ ለልጆቻቸውም አለምን ነው ሚሰጡት።

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

3 years, 7 months ago

#አኳሪየስ_ወላጆች

»» አኳሪየስ ወላጆች ቤተሰባዊነት ላይ ሙጥኝ የሚሉ ወላጆች አይደሉም፣ ጥብቅ በሆነ አስተዳደግና ህግም አያምኑም። ምክንየቱም ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ የተለያየ ፍላጎት አለው ብለው ያምናሉ። በዚህም ልጆቻቸውን ጨምሮ የራሱ የሆነ ክህሎት ማዳበር እንዳለበትና ለሰው ሳይሆን ለራሳቸው ተማኝ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ። በቅንነትና ሌላውንም ሰው የማከለ ድርጊት እስካደረጉ ድረስ ልጆቻቸው የፈለጋቸውን መስራት ይፋቅዱላቸዋል። ለክህሎት ክፍት የሆነ አስተሳሰብ ነው ያላቸው። ማድረግ ያለባቸውን ምክንያታዊ ድርጊት በማድረግም፣ እንዴት መስራት እንዳለባቸው አቅጣጫ ይሰጧቸዋል። 

»» አኳሪየስ ወላጆች ለልጆቻቹ ስሜታቹን መግለፅና መናገር ያስፈልጋል። ካማንም ጋ መቀራረብ ማይከብዳቸው አኳሪየሶች፣ ለልጆቻቸው ቅርብና ቀልደኛ ወላጆች ናቸው፣  ከልጆች ጋ መጫወትም ደስታን ይሰጣቸዋል። አዳዲስ ነገር ለመፍጠርም ሆነ አዳዲስ ቦታ ልጆቻቸውን ለመውሰድ ችግር የለባቸውም፣ ትንሽ አደግ ማለት ሲጀምሩ ሙዚየም፣ ፓርክና ጥንታዊ ቦታዎች ይወስዷቸዋል። ነገር ግን ማድረግ ሚፈልጉትንና እቅዳቸውን ሚያሳኩበት የብቻቸው ግዜ ያስፈልጋቸዋል።

»» በአስቸጋሪ ግዜያት ወቅት ብቻቸውን መሆንን ይፈልጋሉ። ሁሌም ከፊት ለሚማጣው ወቅትና ግዜ ጥርት ያሉ እቅዶችን ያቅዳሉ፣ ትክክለኛ አቅጣጫውንም ይገነዘባሉ፣ ረጅም ግዜን ሚፈልጉ እቅዶች ሊሆንም ይችላሉ። አኳሪየስ ወላጆች አዲስ ምንም ያልተሰማ ሀሳቦችን ያለመቀብል ችግር የለባቸውም፣ ይሰማሉ፣ ልጆቻቸውንም እንደ ቅርብ ጓደኛ ይቀርባሉ። ለሚጠይቋቹ ስሜታዊ ንግግር ግን ልብ ሊሏቸው ያስፈልጋል።

»» ተፈጥሯዊ ሆነው ለመጡ ሰዎች ተፈጥሯዊና እውነተኛ ፍቅራቸውን ይሰጣሉ። ቤታቸውም ለማንም ክፍት ነው፣ በተለይ ለህፃነት፣ እነሱም ደስተኞች ይሆናሉ፣ ጥሩ አስተማሪም ናቸው። ሲበዛ ገለልተኛና የራሳቸውን ግዜ ሚፈልጉት አኳሪየሶች፣ አንድ አንዴ ከሌሎች ሰዎች ጋ አንድ ሚያደርጋቸውን የጋራ ሁኔታዎችን ሳይቀር ፈልገው ያጣሉ። 

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

3 years, 7 months ago

#ካፕሪኮርን_ወላጆች

»» ካፕሪኮርን ወላጆች ዋንኛ ፍላጎታቸው ምርጥ ሚባል ልጆች እንዲኖራቸው ነው፣ ለዚህም ነው አጥብቀው ልጆቻቸውን ሚቀጡት፣ በእርግጥ ካፕሪኮርን ወላጆች እነሱ ያሳለፉትን ስተት ላለመድገም ጭምር ነው ሚቀጧቸው፣ ቢሆንም ልጆችም የራሳቸው ፍላጎት እንዳላቸውና ስተት መስራት የልጆች ባህሪ መሆኑን መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ነገሮችንም ማክረርና ማጥበቅ ምክንያታዊና ስልታዊ መሆን እንዳለበት መገንዘብ አስፈላጊ ነው። ልጆችን ከተጠያቂነት እንዲሸሹ በር ይከፍትላቸዋል።

»» ካፔዎች ለቤተሰባቸው ቅድሚያ ሚሰጡ ወላጆች ናቸው፣ ብዙ ግዜያቸውንም ከቤተሰብ ጋ ያሳልፋሉ፣ ቤት ውስጥም ሰለምና መረጋጋትን ይፈልጋሉ፣ ጥድፊያ የበዛበት ኑሮ አይመቻቸውም። የራሳቸው ውስጣዊ ካላንደር አላቸው፣ እንዴት ቤተሰቡ መጓዝ እንዳለበት መስመር ያበጃሉ፣ ተግባር ላይ ሚያተኩረው የካፕሪኮርኖች አዕምሮ፣ እንዴት ቤተሰብ ማስተዳደር እንዳለባቸው ይረዳቸዋል። ተጫዎች የሆነውን የህፃነትን አዕምሮን ለመረዳት ግን በነሱ ቦታ ላይ የተወሰነ መምጣት ይኖርባቸዋል፣ አለምን በነሱ አዕምሮ ለመመልከት መሞከር ይጠቅማል።

»» የካፔዎች ማንኛውም ድርጊት ቤተሰባቸውን ኣሳታፊ ያድርገ ነው፣ ሁሌም ትልቁን ምስል ያያሉ፣ ለልጆቻቸው፣ ለልጅ ልጆቻው ሚሆን ሌጋሲን ማስቀጠል ይፈልጋሉ። ልጆቻቸውን ግን እንደ ቤት ውስጥ መሽን ሳይሆን እንደ አንድ ገለልተኛ ራሱን የቻለ ሰው መመልከት ይኖርባቸዋል። ካፔዎች ለማንም ወላጅ ተመስሌት ሚሆኑ ጠንካራ ሰራተኛ ወላጆች ናቸው፣ ቤተሰብ ውስጥም የነሱ መኖርና አለመኖር ትልቅ ተፅኖ ያመጣል። ማንኛውም ምክር አዘል ንግግራቸው በምሳሌ የታገዘ ነው። እንደ መፃፍና አስተማሪ መጫዎቻዎችን ለልጆቻቸው ይገዛሉ። ማድረግ ካልፈለጉም አይሆንም የማለት ችግር የለባቸውም፣ አይሆንም ካሉ አሉ ነው።

»» ዋና አላማቸው ተጠያዊና ትልቅ ግብ ያለው ልጅ እንዲኖራቸው ነው፣ ከልጆቻቸውም ብዙ ይጠብቃሉ። ለባህላዊ ትሩፋቶች ካላቸው ትልቅ ተነሳሽነት የተነሳ፣ እነሱ እያሉ ሲበለሻሽ ማየትን አይፈልጉም፣ በተቻላቸውም መጠን በአከባቢያቸው ያለውም ሰው እንዲያከብር ይፈልጋሉ። ካፔ ወላጆች ሁሌም ራሳቸው ላይ ይበረታሉ፣ ምርጥ ሚባለውን ስራ እየሰሩ መሆኑን ማሰብ ያስፈልጋል። በወሩና ሳምንቱ መጨረሻ ላይ ራሳቸውን ለቀቅ፣ እቅዳቸውንም ላላ ማድረግ ያስፈልጋል፣ የተለያየ ጫዎታዎችን፣ ትሪፖችን መጓዝና መለማመድ ይጠቅማቸዋል።

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

3 years, 7 months ago

#ሳጁታሪያስ_ወላጆች

»» ሳጁታሪየስ ወላጆች ትልቁ ፍራቻቸው፣ ለአለም ዝግ የሆነ አዕምሮ ያላቸው ልጆች እንዳይኖራቸው ነው። ስለዚህ በተለያየ መንገድ ስለ ህይወት የተለያየ ትምህርትን ያስተምሯቸዋል፣ ሀገር አቀፍ ጉዞዎች ይኖራቸዋል፣ እውነተኛ ገጠመኞቻቸውን ይነግሯቸዋል፣ እንዲሁም የከተማ ውስጥ ሽርሽር ያደርጋሉ፣ በዚህም ለትሪፕ ባላቸው ትልቅ ፍላጎት፣ የልጆቻቸው አዕምሮ አድማስ ሰፊ እንዲሆን ያደርጋል፣ ውጤታማና ለምንም ነገር አዲስ ማይሆንበት ልጆች ይኖራቸዋል።

»» ሳጁታሪየስ ወላጆች አበረታችና ድጋፍ ሚሰጡ ኩል ወላጆች ናቸው፣ ማንኛውንም ስራ ይስሩ ልጆቻቸው ከጎናቸው መሆናቸውን ማረጋገጥ ይፈልጋሉ። ሳጁተሪየስ ወላጆች፣ ልጆቻቸው ወጣት እያሉ፣ በነሱ ግልፅነትና ታማኝነት የተሞላበት ንግግር ይበሳጩ ይሆናል፣ እያደጉና እየበሰሉ ሲመጡ ግን በወላጆቻቸው መኩራራትን መደነቅ ይጀምራሉ። ሳጁታሪየስ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋ ባላቸው ግንኙነት እንደ ጓደኛ ብቻ ሳይሆን እንደ ወላጅም አክት ማድረግ አለባቸው።

»» ሳጁ ወላጆች ሁሌም በትልቅ ተነሳሽነት ላይ ናቸው፣ ቤታቸው ውስጥ ቀልድ፣ ጨዎታ፣ ጩወትና ቁጣ አይጠፋም፣ ለመናገር ነፃ ናቸው፣ የማንንም ሰው ፍቃድ አይጠብቁም፣ ልጆቻቸው ፊት ለሚናገሩት ከባድ ንግገር ግን ጥንቀቄ ማድረግ ያስፈልጋቸዋል። ለእውቀት ያላቸው ቦታ በጣም ትልቅ ነው። ለትላልቅ እንጂ ለትናንሽ ነገሮች ቦታ የላቸውም። ሁሌም ጉዳይ ስለሚበዛባቸው ለቤተሰቦቻቸው ሚሰጡትን ግዜ ማመጣጠን አለባቸው። እንዴት መረጋጋትና መስከን እንዳለባቸውም እንደዛው።

»» ሳጁ ወላጆች፣ ልጆቻቸው ህብረተሰብ ውስጥ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይፈልጋሉ፣ በጎ አድራጎት ስራዎችም ላይ ጉልህ ሚና እንዲኖራቸው ይሻሉ። ከክብረ በዓልና ፌስቲቫል ጭምር እንዲነጠሉ አይፈልጉም።

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

3 years, 7 months ago

#ስኮርፒዮ_ወላጆች

»» ስኮርፒዮ ወላጆች የልጆቻቸው ተከላካይ፣ ጠባቂና ተቆጣጣሪ ወላጆች ናቸው፣ ሁሌም ቢሆን ከልጆቻቸው ጎን እንደሆኑ እርግጠኛ መሆንን ይፈልጋሉ፣ በዚህም በተደጋጋሚ የልጆቻቸውን መስመር በማለፍ አስጨናቂ ወላጆች ይሆናሉ፣ ስለ አለም አስደናቂ  ግንዛቤና ጥልቅ እውቀት እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ፣ በዚህም የራሳቸውን ጥላ እንኳን እንዳያምኑ ተፅኖ ውስጥ እንዳይከቷቸው ያሰጋል።  የልጆቻቸው ክፍል ለመግባት የማንንም ፍቃድ አይጠይቁም፣ ይሄም ቤት ውስጥ ምንም አይነት ሚስጥር እንዳይኖር ከመፈለግ አንፃር ነው።

»» ሁሉም ሰው የራሱ የሆነ ብቸኝነት ግዜን እንደሚፈልግ ማዎቅ ተገቢ ነው፣ ልጆችም ቢሆኑ። ስኮርፒዮ ወላጆች በጣም የተነሳሱና ለልጆቻቸው ያላቸው ፍቅር ጥልቅና ገደብ የለሽ ነው፣ የመጠራጠር ስሜት ከተሰማቸው ግን ያሰቡትን እንዳለ ከማድረግ አይመለሱም። ስኮርፒዮዎች ሁሌም አሪፍ ጓደኞች ናቸው፣ ለልጆቻቸው ሆነ ለቤተሰባቸው ታማኝ ሲሆኑ፣ ቤተሰባቸውም ቢሆን ከናንተ ቀድሞ አስፈላጊ ነው ብለው ሚየስቡት ሰው አይኖርም፣ ጥራት ያላቸው ወላጆች ናቸው።

»» የስኮዎች ትልቁ ቁምነገር፣ ከልጆቻቸው ጋ ያላቸው አብሮነት ነው፣ ፍልስፍናቸውም ጭምር ነው። ሁኔታዎች በጣም ሲካረሩና በተወሳሰቡ ግዜ፣ ፍቱን የማረጋጋትና መፍትሄ አመንጪ ናቸው። በዚህም ልጆቻቹ የናንተ ላባ ምን ያህል ጠንካራና ማይነቀል እንደሆነ ይረዳሉ። ስኮርፒዮ ወላጆች፣ ለልጆቻቸው በተመሳሳይ ቀን፣ ቋሚ የሆነ ሚሰሩበትና ሚያስተካክሉበት ግዜና ቦታ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ።  ለምሳሌ ሰውነታቸውን ሚታጠቡበት ቀን፣ ልብስ ሚያጥቡበትና ሚያስተካክሉበት ተመሳሳይ ቀናቶችን እንዲለማመዱ ይፈልጋሉ።

»» ቤተሰባቸው የተረጋጋና ተመጣጣኝ የሆነ ሕይወት እንዲኖራቸው ፍላጎት አላቸው፣ ጤናማ የሆነ የአመጋገብ ሁኔታ፣ ጤናማ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ፣ ሰለማዊ የሆነ እንቅልፍ እንዲኖራቸው ይሻሉ። ለቤተሰብ በሚሰጥ ግዜና ፍቅር ያምናሉ፣ ከሁሉም ጋ መልካም ቀረቤታ ቢኖራቸው ደስተኛ ናቸው፣ ነገር ግን እነዚን ለማምጣት በሚያደርጉት ሁኔታ ውስጥ ጦርነትና ሽኩቻ ውስጥ ይገባሉ።

»» ስኮርፒዮ ወላጆች ልጆቻቹ እያደጉ በመጡ ቁጥር፣ ከሌሎች ጓደኞቻቸውና ልጆች ጋ ማሰለፍና ሌሎች ጓደኞችን መያዝ እንደ ኖርማል መቁጠር ይኖርባቸዋል፣ እሱም ብቻ ሳይሆን የተወሰነ ነፃነት መስጠት፣ የተገነነ ውጤት ከነሱ አለመጠበቅና ዘና እንዲሉ ማድረግ አስፈላጊ ነው። ስኮርፒዮ ወላጆች ለልጆቻቸው ትልቅ ፍቅር ቢኖራቸውም አካላዊ ንክኪ ላይ እንብዛም ናቸው፣ በደንብ ማቀፍ ያስፈልጋል፣ ልጆችን ማሽሞንሞንና ማሞላቀቅ አይሆንላቸውም። ጠንካራ እንዲሆኑ ስለሚያግዟቸው፣ በራስ መተማመን ያለው ልጅ ይኖራቸዋል፣ ነገር ጣልቀ ገብ የስኮርፒዮ ባህሪ ልጆቻቸው እየጎረመሱ ሲመጡ ከልጆቻቸው ጋ ችግር ውስጥ መግባት ይጀምራሉ። 

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

3 years, 9 months ago

#ሊብራ_ወላጆች

»» ሊብራዎች ቀጠይነት ያለውና ተከታታይ ማህበረሰባዊነትን ይፈልጋሉ፣ እንደ ወላጅ ደግሞ፣ ልጆቻቸውን እንደ ጓደኛ ያያሉ እንጂ ቤት ውስጥ እንዳለ የአለቃና፣ ታዛዥነት ቅድመ ሁኔታ እንዲኖር አይፈልጉም። በቤት ውስጥ ምንም አይነት ሚስጥርም ሆነ መደባበቅ አይፈልጉም፣ አደጋም ሆነ ደስታ፣ መሰናክልም ሆነ ስኬት አንድ ላይ መጋራትን ነው ሚፈልጉት። ሊብራ ወላጆች ለቤተሰባዊነት ያላቸው አመለካከት ምርጥ ወላጆች እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል።

»» ልጆቻቸውን ሚያስጨንቁ አይነት ወላጆች አይደሉም፣ ነገር ግን አንድ አንዴ ከንቱ የመሆን ስሜት ይሰማቸዋል፣ ይሄንንም ስሜት ልጆቻቸው ላይ ያንፀባርቃሉ። የማህበረሰብና አከባቢ ቢራቢሮ የሆኑት ሊብራዎች፣ በተለያየ ግሩፕ ውስጥ ተሳትፎ አላቸው፣ መሳተፍ ብቻ ሳይሆን መሪም ጭምር ሲሆኑ ይታያል። የሊብራ ወላጆች ሞቶ "የሆነ ነገር ማድረግ ከፈለክ/ሽ ትክክለኛውን ነገር በራስህ/ሽ አድርግ/ጊ" የሚል ነው። ሆኖም ይሄ ሞቶ ልጆቻቸው ወጣት በሚሆኑበት ግዜ ልጆቻቸውን ቢዚ ሊያደርጋቸው ይችላል፣ ቢሆንም ግን ያን ያህል መረን ሚለቁ ወላጆች አይደሉም።

»» የሊብራዎች ፖዘቲቭ እነርጂ፣ ለቤተሰቡ ብርሀንና ተስፋን ይሰጣል። ለልጆቻቹ ስሜት መጨነቅ አለባቹ፣ ሁኔታዎችን ወደ ቀልድ ሚወሰድና ቀለል ማድረግ ሁሌም አስፈላጊ ነው ብሎ ማሰብ አስፈላጊ አይደለም፣ ያለ ምንም ተፅኖ ትክክለኛ የልጆችን ስሜት መገንዘብ ይኖርባቹዋል። የሊብራ ወላጆች አዕምሮ ውስጥ ንፅፅር ሁሌም በአዕምሯቸው ውስጥ ያለ ነገር ነው። ጥሩ ነገርን ይፈልጋሉ፣ በትልቁ ያልማሉ፣ ሁሉም ግን ለቤተሰባቸው እንዲሆን ነው ምኞታቸው። 

»» ልጆች ሚፈልጉትን በቶሎ ያውቃሉ፣ ልጆቻቸውም ግልፅ ነው ሚሆኑላቸው፣ ምንም አይደብቋቸውም። በቬነስ ሚመሩት እነዚ ወላጆች፣ ለገፅታ ካላቸው ትልቅ ፍላጎት የተነሳ፣ ቤታቸው በተለያየ ጌጣጌጥ ያሸበረቀና የተዋበ እንዲሆን ምኞታቸው ነው። ልጆቻቸውንም የአርት ጋላሪዎችና ሙዚየሞች ይወስዷቸዋል። ልጆቻቸውም ጎበዝና ታዛዥ እንዲሆኑ ይጠብቃሉ። ሰለማዊ ህይወትን መምራት ቢፈልጉም ከሙግትና ፀብ አይድኑም፣ ከልጆቻቸውም ጋ ንትርክ ውስጥ ይገባሉ፣ ይሄም ሁለቱንም ያደክማል። እንደ ወላጅም እውነተኛ ስሜታቸውን ለልጆች ማሳየት አለባቸው። 

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 
? 
@zodiac_zodiac

3 years, 9 months ago

#ቪርጎ_ወላጆች

»» ቪርጎ ወላጆች ያላቸው ልጆች እድለኞች ናቸው፣ ለተሻለ እውቀትም ሆነ ስራ ብቁ እንዲሆኑ ያደርጓቸዋል። በተፈጥሯቸው ልጆቻቸው እንዲማሩ ትልቅ ፍላጎት አላቸው፣ የቤት ስራቸውን እንዲሰሩ፣ ያልገባቸውን እንዲጠይቁ ያበረታቷቸዋል፣ ጎበዝ እንዲሆኑም ያደርጓቸዋል። ትልቅ የማሰብ ችሎታ ያላቸው ቪርጎ ወላጆች፣ ጎበዝና ታታሪ ልጆችን የመፍጠር ኳሊቲ አላቸው፣ ከልጆቻቸውም ቢሆን ትልቅ ውጤትን ይጠብቃሉ።

»» ሁሌም ቢሆን ሀላፊነት ሚሰማው ወላጅ መሆንን ነው ሚፈልጉት፣ ምርጥ ወላጅ መሆንን ይፈልጋሉ። ምንግዜም የልጆቻቸውን ሁኔታ እስከመጨረሻ ድረስ ይከታተላሉ፣ ማስተካከልም ያለባቸውንም እያስተካከሉ ያሳድጓቸዋል። ቪርጎ ወላጆች፣ ልጆቻቹን በግልፅ መናገርም ሆነ መስማት፣ ለልጆቻቸውም እድል መስጠት አስፈላጊ ነው፣ ያለ ምንም ክልከላ ስራዎችን እንዲሰሩ፣ ፍቀዱላቸው ቢበላሽም ይበላሽ፣ እንዲገሩ ያደርጋቸዋል።

»» ቤት ውስጥ ማንም ሰው ቆሻሻ እንዲጥልም ሆነ ቤቱን እንዲያቆሽሽ አይፈቀድለትም፣ ያለዚያ ጦርነት መፈጠሩ ነው። ለእያንዳንዱ ክንውን ጥንቁቅ ናቸው፣ ከራሳቸው በለይ ለቤተሰባቸውና ልጆቻቸው ሚጨነቁ ናቸው። ትልቅ ስታንዳርድ ያላቸው ቪርጎ ወላጆች፣ ማንም ሰው ከነሱ ብዙ ቁምነገር መውሰድ ይችላል። ቪርጎ ወላጆች ነፃነት ሚመጣው ከተስተካከለ መዋቅር እንደሆነ ያምናሉ፣ ተራማጅ፣ ቀጥተኛና ማይዋዥቅ እቅድ እንዲኖራቸው ሲፈልጉ፣ ልጆቻቸውም እሱን መስመር እንዲጓዙ ይፈልጋሉ። ሁሌም ቢሆን እቅድ አለ ውልፍት ማይል እቅድ።

»» ስሜታዊ ናቸው፣ ጥፋታቸውንም አያምኑም፣ ሁሌም ልክ ነን ብለው ነው ሚያስቡት። የልጆች ለተጨማሪ አይስክሬም፣ ኤሌክትሮኒክስና ስልኮች ጥያቄ ሁሌም እንቢታ ነው መልሳቸው። መቼ እሺ ማለት እንደለባቸውና፣ ቀለል ማለት እንደለባቸው ያውቃሉ፣ ቀልድና ቁምነገርም ሚምታታባቸው አይነት ሰዎችም አይደሉም፣ ለሁሉም ልኬትና መጠን አላቸው።

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 
? 
@zodiac_zodiac

3 years, 9 months ago

#ሊዮ_ወላጆች

»» ሊዮ ወላጆች ለልጆቻቸው ሚሰጡት ክብርና ኩራት የተማጣጠነ አይደለም፣ ሁሌም በየቀኑ እናንተን ለማስገረም አዲስ ነገር መስራት እንዳለባቹ ታስባላቹ። ሊዮ ወላጆች በአንድ ግዜ ብዙ ነገሮችን መሞከርና መስራት ሚፈልጉ ሆነው ሳለ፣ ልጆቻቸውን ለሌሎች ወላጆች በኩራትና ደማቅ አገላለፅ ሚናገሩ ሰዎች ናቸው። በልጆቻቸው ውስጥ ወኪል በመሆን መኖርን ይፈልጋሉ።

»» የልጆቻቸውን ስኬት አጥብቀው ይፈልጋሉ፣ ለሱም ትልቅ እርዳታንና እንክብካቤን በማድረግ ሲታወቁ፣ ልጆቻቸው ትላልቅ ስኬቶችን ሲያስመዘግቡ፣ ሀላፊነቱን በመውሰድ ራሳቸውን ያመሰግናሉ። ነገር ግን የልጆቻቸውን ጥረት ከግምት ውስጥ በማስገባት፣ ለነሱም ቢሆን እውቅና መስጠት አስፈላጊ ነው። ሊዮ ወላጆች ማንኛውንም የቤተሰቡ አባላት ሚኮሩበትን ስራ መስራት ይችላሉ፣ ጎበዞች ናቸው።

»» ሊዮ ወላጆች አንዴ ልጆቻቸው ይሄን ማድረግ አለባቸው ብለው ካሰቡ፣ የልጆቻቸውን ፍላጎት ከግምት ውስጥ አይከቱም፣ እነሱ ባሉት መንገድም ወጥ የሆነ መንገድ ያሳያሉ። የልጆቻቸውን ፍላጎትና ዝንባሌ ከግምት ውስጥ በማስገባት ያለ ምንም ጎንዮሽ ማየት ግዴታ መሆኑን ማዎቅ ይኖርባቸዋል። ሊዮ ወላጆች ቤት ውስጥ ጠንካራና ተናጋሪ ናቸው፣ ብዙ ነገሮችን በዝምታ አያልፉም። እርዳታም ሆነ ማግኘት ሚፈልጉትን ሲጠይቁ፣ ግዜውን ባገናዘበ መልኩ ነው፣ ይሄም ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አለው።

»» ሊዮ ወላጆች፣ ልጆቻቸው ሚያመጡት የትምህርት ውጤት ያሰጋቸዋል፣ ጥሩ ውጤት ሚያመጡ ከሆነ ማንኛውንም ሽልማት ከመሸለም ወደ ኋላ አይሉም። አንድ አንዴ ተመሳሳይ ሙድ ላይ አይሆኑም፣ ማንም ሰውም ልጆቻቸውን እንዲነካባቸው አይፈልጉም፣ ተከላካይና ተቆጪ ናቸው። ባላቸው ግዜም ከልጆቻቸው ጋ ሽርሽርና መዝናኛ ቦታ ይወስዳሉ፣ ተወዳዳሪና ትልቅ ግብ ያለው ልጅ እንዲኖራቸው ይፈልጋሉ። ስትናደዱ ግን የተሰማቹን ከመናገራቹ በፊት፣ መጀመሪያ ተረጋግታቹ፣ ቀስ ብላቹ አዏሯቸው።

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 
? 
@zodiac_zodiac

3 years, 10 months ago

#ካንሰር_ወላጆች

»» ካንሰር ወላጆች ለሰዎች ብርታትን መስጠት በአጥንታቸው ውስጥ ያለ ፀጋ ነው፣ ልጆቻቸውንም መንከባክብና መጠበቅ ተሰጧቸው ነው፣ የተካኑ ናቸው፣ ይችሉበታል። ካንሰር ወላጆች ውጪ ለብሳቹ በምትወጡት ልብስና ፋሽን ላይ ትላልቅ አስታየቶችን ሲሰጡ ይታያሉ፣ ነገር ግን ቤት ውስጥ ለመስራት በምትሞክሩት ስራዎች ከበሬታንና አድናቆትን ይሰጧቸዋል፣ እገዛም ከፈለጋቹ ያደርጉላቸዋል። የልጆቻቸው ቤተሰባዊ ፕሮግራም ላይ አለመገኘት ምንም ይቅርታ ሚያስብል አይደለም። 

»» ቤተሳበዊ ብቻ ሳይሆን ቤት ውስጥ ያሉ ተለምዷዊ ድርጊቶች ላይ ማርፈድም ሆነ መቅረት አይቻልም። ልጆቻቸው እያደጉና ወደ ጉርምስና በተጠጉ ቁጥር፣ በጉርምስና ግዜ እነሱ ያጡትን ነገር ማካከስ ይፈልጋሉ፣ ልጆቻቸው ድጋሜ እነሱ ያሳለፉትን እንዲያሳልፉ አይፈልጉም፣ ልባቸው ሲሰበርም ሆነ ሲከፉ ቀድሞ ደራሽና ጠጋኝ ካንሰር ወላጆቻቸው ናቸው፣ ስሜቱንም ይረዱታል። ሚያደርጉት እንክብካቤ ወደር ማይገኝለት ቢሆንም፣ መብዛት ግን የለበትም፣ በራሳቸው መጋፈጥና ውሳኔ መስጠት እንዲችሉ ማድረግ አስፋላጊ ነው።

»» ካንሰር ወላጆች ምንም አይነት አከባቢም ሆነ ጫዎታ ቦታ ይሂዱ፣ አብሮነታቸው እንዲጠፋ አይፈልጉም፣ ተፈጥሯዊ መረጋጋትን ይፈልጋሉ። ልጆችን መቆጣጠር የጉርምስና ግዚያቸውን እስኪያልፉ ድረስ ኖርማል ቢሆንም፣ ከዛ ባለፈ ግን ትርፉ ልጆችን ጫና ውስጥ መክተት ስለሆነ፣ ከጉርምስና ቧላ ጫናውን ላላ አድርጉት። ረጅም ግዜ አብሮ መሆንና በመቆየት ሚያምኑት ካንሰሮች፣ ለእናንተም ቢሆን ነፃ የሆነ ግዜን እንደሚያስፈልጋቹ ማሰብ ያስፈልጋለ።

»» ካንሰር ወላጆች፣ ለልጆቻቸው ሁሉንም ነገር ሳያበዙ እንዴት መስጠት እንዳለባቸው ያውቃሉ። ከካንሰር በላይ ለቤታቸውም ሆነ ለቤተሰባቸው ሚጨነቅና ቅድሚያ ሚሰጥ የለም፣ ማንኛውንም አደጋም ለማጋፈጥም ሁሌም ዝግጁ ናቸው። 

ማንኛውንም አስታየት ሆነ ጥያቄ በ @zoskales_13 ማድረስ ትችላላቹ 

ሼር፣ ጆይን እንዲሁም ጓደኞቻቹን ለመጋበዝ 

? 

@zodiac_zodiac

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago