Unlock a World of Free Content: Books, Music, Videos & More Await!

ስሜቴን በግጥም

Description
ግጥም እምቅ ነው ግጥም ስሜት ነው እኛም የያዝናቸውን የተሰሙንን ስሜቶች በግጥም እና በተለያዩ ስነ_ ፅሁፎዎች የምናጋራበት ግሩፕ
@smetoch12_be_gtm
@smetoch12_be_gtm
for any comment
@eluuu2112
@ediwub
Advertising
We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago

2 months ago

ግራ ገባኝ እኮ

ቆይ ግን ጓድኞቸ ምን እየሆኑ ነው፤
የሚጣፍጣቸው እኔ የምበላው፤
የሚሽቀረቀሩት እኔ በምገዛው።

ይሁን እንዳሻቸው እስካለን አንድነት፤
ኩሌንም ይካሉት ሽቶየን ይቀቡት ፤
ንብረቴን ይውረሱት፤
ታዳ ጓድኝነት ምኑ ላይ ነው ብየ፤
ቃል አልተነፈስኩም ስኖር ተቻችየ።

ካማራቸው ሁሉ ውሰዱ ማለቴ፤
በሰጠሁትም ልክ መልስ አለመሻቴ፤
መጠሪያ ሲያሰጠኝ የሚባል ሞኝቴ።

እራሴን ሳፅናናው መልካምነት ለራስ ፤
ሞኝነት ምንድነው ሰጠኋቸው እንጂ ፤
እኔ ሰእነሱ አላንስ፤
እያልኩ ስደሰኩር እያልኩ ስፈላሰፍ፤
ፍቅረኛየ ብየ ያስተዋወኩትን አየሁት ካአንዷ አቅፍ።

ሌብነታቸውን አሁን ነው መለፈፍ፤
አሁን ነው መለፍለፍ፤
ንብረቴን ጨርሰው ፍቅሬን ወሰዱብኝ፤
ከጀርባየ ናቸው እባካችሁ ያዙልኝ ።

✍️ዕሌኒ

(@eluuu2112)
@smetoch12
@smetoch12

2 months, 1 week ago

ፅጌዋ ወፊቱ
🐧🥀🐧 🌹 🐧

🌹🐧🥀🐧🌹🐧

አብስትራክት ብሎ ስዕሉን የቀመረ፤
አንድ ሳሊ አለ ስዕሉን ያፈቀረ፤
ከሰው መነጋገር የጠላ ሚመስል፤
እጠባብ ክፍሉ ውስጥ ዘግቶ እሚብሰለሰል ።

ከሰወች ምስዕ ላይ ቀለምን የሚረጭ፤
ከሸራው እራቅ ሲል ከራሱ የሚጋጭ፤
ስም የተወጣለት ሱሰኛ ተብሎ፤
ግን ደግሞ ።።።።
የሚኖር ታሪኩን በሙሉ በስዕሎቹ አዝሎ፤
ይህን ሰው ላጤ ነው፤
ዝምታው ሀያል ነው።

ታዳ የዚህ ሰው ስዕል፤
ተርጓሚ ያሻዋል።

ጭር ካለ በረሀ ቀይ ፅጌ ሬዳ፤
በቃጠሎ ብዛት ካቋማ ተንጋዳ፤
ውሀ እንዳታገኝ በጎራ ተጋርዳ።

አንዲት ቆንጀየ ወፍ፤
ብዙ ዛፍ እያለ፤
ማረፊ ጠፍቶባት የምትርገገፍ፤
መወሰን አቅቷት የምትንከረፈፍ።

ለስዕሎች ትንትን ትርጓሜ ሲገባ፤
አንዲት ሚስኪን አለች ከሳዕሊዎች ጀርባ።

እንዳት ሄድ ወስና ፍቅር አስሮ ይዟት፤
ከጎኑ መኖሯን ባሏ የዘነጋት፤
ፍካቷ ሳይቀንስ የሚጠማት ፍቅር፤
እድሜዋ መሄዱ እምያስነባት ዘወትር ።

እሚረዳት ማጣት ፍቅር ሰቶ ማጣት፤
ካቋሟ አንጋዶ አንገቷን ያስደፋት፤
መሄጃ ማረፊያው ሁሉም የጠፋባት፤
ፅጌዋ ወፊቱ አለች አንድት እንስት።

አለች አንዲት ሚስኪን ፤
በግልፅ የነቀሰች በፊቷ ላይ ፍቅሯን።

✍️ በዕሌኒ
(@eluuu2112)

@smetoch12
@smetoch12

2 months, 2 weeks ago

አድዋ
.
አንድ ተአምር አለ ከሶሎዳ ሰማይ ከተራሮቹ ስር፤
በሰዉኛ ልማድ በልሒቃን ምጥቀት የማይመረመር፤

የማንነት ስፍር ወሰን የተቸሩት፤
በአጥንትና በደም ከፍለው ያሰመሩት፤
አድዋ ድንበር ነው ደፍረው የማይረግጡት።

ከወይን ይልቅ ጣፍጦ የሚደጋግሙት፤
በግጥም አዋዝተው የሚያቀነቅኑት፤
አድዋ ዜማ ነው ሁሌ እየታደሰ የሚያንጎራጉት።

የህብረቃል ድምር ሰሙን የታጠቀ፤
በኩታ አከናንቦ ዕዉቀትን ያጨቀ፤
አድዋ ቅኔ ነው ወርቁን የደበቀ።

በባህረ ሀሳብ ያልተገኘ ስሌት፤
የአለት ምሰሶ የጊዜ ድንቅነት፤
አድዋ ዘመን ነው የትናንት ዛሬነት።

ባንዲራዋን አዝሎ ጦርሜዳ የወጣዉ፤
ቅንጣትም ሳይሰስት ራሱን የሰጠዉ፤
አድዋ ሰው ክቡር የሰው ልጅ ነው።
.............................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@smetoch12

4 months ago

@smetoch12
@smetoch12

ሂድ..... 🚶‍♂️🚶‍♂️🚶‍♂️

✍️ በዕሌኒ

07/5/2016 ዓ.ም

4 months, 1 week ago

ይህ ቴሌቪዥኔ
የተዋበ ጥበብ _ ያማረ ነጠላ
ሙክት.ሰንጋ በሬ _ ቆሎ.ድፎ.ጠላ
ምናለበት አሁን ባያስመለክተኝ
"ተመስገን" ማለት ነው ዘወትር የታከተኝ።

.........

ጉልቻሽ ከቦታው አልተወዛወዘም?
ድስትሽ ቂጡ አልያዘም?
እና ጥንስስ ጠላሽ ተካዡን አሞቀው? ፈዛዡን አነቃው?
(እንጨፍራ በቃ ... ይከፈት ሙዚቃው!)

አንገት ወዝወዝ ወዝወዝ .. ጀርባ ደፋ ቀና
ደረት እስክስ እስክስ .. እግር አንከል አንከል
እንዴት ይጨፈራል በሬሳ መካከል!?

......

ዓመት ባል ቢመጣ
ዳግም ተሽከርክሮ ዓመት ባል ይመጣል፤
የትላንት ውጥኔ
ከመቋጫው ሳይደርስ ዳግም ይለወጣል፤

ዳቦ ብርቅ አይደለም
ውስኪ.ብርቅ አይደለም ሞልቷል በየስፍራው
"ደህና ነኝ" ማለት ነው ልቤን የሚያስፈራው

ቦንብ ዳር አበባ ፈንጂ መሐል እሸት
"እንኳን አደረሰህ" መባባሉ ውሸት

ዘመን ደም ገባሪ ቢላ መቁረጫውን
በሳት እያጋጨ እንዳዲስ ሞረደው፤
የዛሬን አለፍኩት ...
የነገው ተስፋዬን ማን ይሆን የሚያርደው!?

.......

"ካገሩ የወጣ ሃገሩ እስኪመለስ
ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ"

ምናምን ምናምን እያልኩ አልሞግትም
ኸረ ፈጣሪዬ ከዚች ሃገር ነቅለህ ወዲያ ጣለኝ የትም!

ጦርነት....ሞት...እንባ ......ጣር .ስቃይ.በሽታ
በሞላበት ቀዬ... (እንዴት ይናፍቃል የኩበቱ ሽታ!?)

(የሰው ሃገር ልሁን)
ናፍቆት ደጄ ይቁም በተርታ በመደድ
ብቻ አንዴ ልሰደድ

ያገሬ አፈር ይብላኝ
ባይፈልግ አይብላኝ

ለበድኔ አያልቅሱ አይኳሉት አይሳሙት
ብቻ ሰላም ሁኜ ሰላም ኑሬ ልሙት።

Astu

4 months, 1 week ago

በዕሊኒ በልደትህ

🙏
🙏

🙏

በዚች ብርክት ቀን በተወለድክባት፤
ንጉሡ ዝቅ ብለህ ሎሌ በሆንክባት፤
የአባቶች ትዕንቢት እውን ተፈፀመ፤
የሂዋን መርገሟም በድንግል ታረመ።

የአዳም መስዋዕቱ ጩኸቱ ተሰምቶ፤
ፍቅር አወረደህ ካአባትህ ለይቶ፤
በረት ተወለድክ ጌታ ቦታ ጠፍቶ።

የሁሉ ፈጣሪ እንደት ብትወደኝ ነው?
በጠባብ ማህፀን ፀንተህ የከተምከው፤
እኔ ምግባረ ቢስ አንተ ቅዱስ አምላክ፤
ምን አገኝ ብለህ ነው ስጋየን የለበስክ?

ለሀጣኗ ነፍሴ ባለጌ ወንበር ላይ፤
አካሏን ቁጭ አርጋ ጭፈራ እያስነካይ፤
ጭሳ ለመነነይ፤
የአለምን ካባ በአካሏ ለደፋይ።

አንዱን ተመልክታ ዛላውን አድንቃ፤
ለሌላኛው ደግሞ በቀልዶቹ ስቃ፤
ተጣብሳ ተጣቅሳ .....
እንድሁ ለቀረች ካንተ ተነጥላ፤
በልደትህ ዕለት ምን አሰብክ መላ?

የድሮ ዘማሪ የመርከስ ምሳሌ፤
መጠጥ ያበከታት ያሁኗ አካሌ፤
ማለዳ ተነስታ ደጅህን ስማለች፤
ከስዕት በኋላ ማህተቧን ፈታለች፤
እውን በፍርድህ ቀን እንደት ትዳኛለች?

ልደት ስትጠራት ነጠላየ አድፎ፤
የሰውነት ግብሬ በስጋ ጎደፎ፤
እንደ ሰባ ሰገል እጣን ወርቅ ከርቤ፤
ምን እሰጠው አለሁ በፊቱስ ቀርቤ።

እያለች ለቀረች በፍቅር እጦት አራ፤
አርቲ ቡርቲ ምክኒያት በሀሳቧ ስላ፤
አመት ላስቆጠረች አንተን ሳታወራ ፤
ለናፋቂህ ነፍሴ ይኖርሀል መላ።

በልጅነት ልቧ ወንጌል ለከተመ፤
ልምሽምሽ አካሏ በቤትህ ለቆመ፤
ወፊ ቆመች ተብሎ ገና ሳይጨረስ፤
ዛፍ አገኘሁ ብላ ጥላህ ላለች እብስ፤
ዛሬ በልደትህ ቢቀርብባትስ ክስ፤
ከናፍቆት ያለፈ እውን የላትም መልስ፤
ከሀጢአት የተረፈ አዎ የላትም ነፍስ።

እናም ትልሀለች ፤
የነፍሴ ባለቤት ፤
አሁን በዚች ዕለት ፤
በተወለድክባት፤
የመጀመርያዋን ልጅነት አስበህ
በምህረት አይኖቹ ከደዌየ አንፅተህ፤
ወዳንተ ውሰደኝ ከአለም ነጥለህ።

✍️ዕሌኒ

(@eluuu2112)
@smetoch12
@smetoch12

6 months, 1 week ago

እኔ ደዊይ
🙏

🙏

🙏

አምላኬ ሆይ ከጥፋቱ ስታገኘኝ ፤
ወደት አሰብክ ልትልከኝ ?

አንዱን ሰቀምስ አንዱን ሳጥም፤
ሳሰናዳ ስጨማምር የበደል ክምር፤
ወደት ሆነ የነፍሴ ቅኝት የነፍሴ ድርድር።

የቱ ላይ ነው የሌለሁት ከዝሙቱ፤
ከሱሱ አለም ከስካሩ ከስርቆቱ፤
ከየት ጎደልኩ ከምሽቱ ከንጋቱ፤
ታውቀኝ የለ እንደማልጠቅም፤
እደማልሰለች እንደ ማላቆም ፤
አንተን መበደል።

ታውቀኝ የለ እንደሆንኩኝ ከንቱ ስጋ፤
ባንተ ስታይ ምን ብታገኝ የነፍስ ዋጋ፤
አከበርከኝ ባንተ ፀጋ።

ይገርመኛል .......

ሀጢያተኛን መማር ስራህ፤
ጥላትህን ትወዳለህ፤
እየሞትክም ህይወትህን ትሰጣለህ።

ምሀሪ አምላክ ተመስገን እልኝ፤
እኔ ደዊይ ቃልም የለኝ ።

✍️✍️✍️ዕሌኒ

(@eluuu2112) 01/03/2016 ዓ.ም
@smetoch12
@smetoch12

6 months, 2 weeks ago

በዕሌኒ እና ዔደን ተፅፌ እንደቀረበ

@smetoch12
@smetoch12

6 months, 2 weeks ago

ፍቅር አይወራም


አትደርድርልኝ እልፍ የቃል መንጋ፤
ፍቅር ቃል አይደለም ተው ብዙ አታውጋ፤
እውነት የሚጠይቅ፤
በዕምነት የሚጠብቅ፤
ፍቅር ክብር አለው ሰማይ የሚዘልቅ።

ተው አትቀልድብኝ ......
ፍቅር ቀልድ አያውቅም፤
ቦታውን ካገኘ ባሉቧልታ አይፈርስም።

ፍቅር እኮ ማለት........
በተግባር የሚኖር ለገባው ህይወት ነው፤
ካምላክ የሚታደል የደስታ መባ ነው።

እናም አታውራልኝ ብዙ ሰምቻለሁ፤
መኖር ሲያቅታቸው አሰናብቻለሁ፤
ቃልህን ኑርልኝ ያኔ አምንሀለሁ፤
አንተ ሳትጠይቀኝ ልቤ አስገባሀለሁ።

✍️✍️✍️ ዕሌኒ
(@eluuu2112)
@smetoch12 23/02/2016 ዓ .ም
@smetoch12

7 months, 2 weeks ago
"ማር" በምድርም "ያም" በሰማይ

"ማር" በምድርም "ያም" በሰማይ
.
.
.
ሀዘኔ በርትቶ፣
ስትጨነቅ ነፍሴ፣
ፈገግታዬ ጠፍቶ፣
ሲታወክ መንፈሴ፣
ወድቄ ከፊትሽ፣
አድኚኝ እላለሁ፣
አልቅሼ ከደጅሽ፣
ከሀዘኔ እወጣለሁ፣
ማንስ ብዬ ልጥራዉ?
እናቴ ስምሽን፣
በምንስ ልግለፀዉ?
ጥዑም መዓዛሽን፣
ማር በምድር፣
ያም በሰማይ፣
የሥላሴን ክብር፣
አጉልታ ምታሳይ፣
እሙ ለፀሐይ ጽድቅ፣
የእግዚአብሔር ከተማ፣
ጥምን የምታርቅ፣
ፍቅር ለተጠማ።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በኤደን ታደሰ እንደተፃፈ
@smetoch12

We recommend to visit

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 1 month ago

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 1 week ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 4 months, 4 weeks ago