ስሜቴን በግጥም

Description
ግጥም እምቅ ነው ግጥም ስሜት ነው እኛም የያዝናቸውን የተሰሙንን ስሜቶች በግጥም እና በተለያዩ ስነ_ ፅሁፎዎች የምናጋራበት ግሩፕ
@smetoch12_be_gtm
@smetoch12_be_gtm
for any comment
@eluuu2112
@ediwub
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 months ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 months, 2 weeks ago

6 months, 3 weeks ago

እሷን ይመስለኛል
.
.
በብሩሽ ቢቀለም የሴትነት መልኩ፤
ተለክቶ ቢሰፈር የቀሚሷ ልኩ፤

እሷን ይመስለኛል.........

በጥለቷ እራፊ እንባዋን ሸፍና፤
የልቧንን እህታ በሳቋ አፍና፤

ራሷ በርትታ 'ምታበረታዋን፤
ራሷ ጀግና 'ምታጀግነዋን፤

የዘወትር አመስጋኝ ደጃፉን ናፋቂ፤
አድባር የመረቃት ጠበኛ አስታራቂ፤

ቃሏ 'ማይታበይ እዉነተኛይቱን፤
የእግዚአብሔር ወዳጅ ባለማተቢቱን።

እሷን ይመስለኛል........እ'..ሷ'..'ን

ኤደን ታደሰ
@ediwub
@topazionnn
@topazionnn

8 months ago

ድንቅ መንፈሳዊ ግጥም ❤️
በዕሌኒ እና በዔደን .....

@smetoch12
@smetoch12

8 months, 1 week ago

እንኳን መጣህልኝ...

ለምን ሄድክ አልልም፤
እንዲህ አደረገኝ ብየም አልወቅስህም፤
እንኳን መጣህልኝ፤
እንካንም አወከኝ፤
እንኳንም አቀፍከኝ፤
አንኳንም ዳበስከኝ።

በቅንጭብጭቡ ትርክት፤
በደራሲያ መፀሀፍት፤
ፍቅርን ላወቀችው ፍቅርን ላጠናችው፤

ለእደእኔ አይነቷ ሴት፤
መምጣት ሀሴት ናት።

ተለያዩ እያለ ሀገሬው ተረተ፤
ፊደል ያወኩ ባንተ፤
ፍቅርን ያየሁ ባንተ፤
ጣት አየጨበጠ ቃል ያስደረደረ፤
አድስ ማንነትን ሰብኮ የፈጠረ፤
መጥፌየን ከጥሩ ለይቶ የሳየኝ፤
የህይወቴን ቅመም ትዝታ የሰጠኝ፤
የልብህ ብራና ቢሰርዘኝ እንኳን።

የመውደድ ልኩ፤
የመኖሬ መልኩ፤
ፍቅርህ ዘላለሜ፤
መኖርህ አለሜ።

የትም ሁን ግደለም፤
ብትሄድም ብትቀርም፤
ቃሌን እኔ አላጥፍም፤
ያዳም ዘር ቢሞላም፤
እመነኝ መውደድ፤
ካንተ ሌላ አላቅፍም።

✍️ዕሌኒ

@eluuu2112
@smetoch12
@smetoch12

8 months, 1 week ago

ሞት
.
ያ....ክፉ ነጣቂ፤
ከሥጋ ለይቶ እስትንፋስ ፈልቃቂ፤

ወሳጅ መልአከ ሞት በሰዎች ጀርባ ላይ፤
ተንጠልጥሎ ሚኖር በእድሜ ገደብ ጣይ፤

ቀናትና ወራት በቀመር ሲለኩ፤
ወራትና አመታት ፈጥነዉ ሲተካኩ፤

የሰዉ ልጅ ማለፊያዉ፤
የእስትንፋሱ ማብቂያው ፤

ከአይን ጥቅሻ እጅጉን ይቀርባል፤
ከአፈር እንደመጣ ከአፈር ይከተታል።
.....................................................
በዔደን ታደሰ
@topazionnn
@smetoch12

8 months, 1 week ago

# ተወዳጇ # ገጣሚ ህሊና ከግጥሙቿ ይበልጥ የምትወደውን ግጥም እነሆ ተጋበዙልኝ ...

@smetoch12
@smetoch12

8 months, 2 weeks ago

ሌላ አመትን ጨመረልኝ ...???

እንደዘበት አድርሰኝ ከርሞ ብየ አምና፤
አልፈዋለሁ ያላልኩትን ያን ጎዳና፤
ፊቴ ቀድሞ እየመራኝ ይኸው ዛሬ አደረሰኝ፤
ምን ቃል አለኝ የድንግል ልጅ ይክበርልኝ።

ከማህፀን ከእናቴ እቅፍ፤
በእግሬም ቆሜ እመሬት ሳርፍ፤
የደገፍከኝ ስደናቀፍ፤
አባቴ ነው የእኔ እንስፍስፍ።

ከልጅነት ወጣትነት ሳፈራርቅ በየአመቱ፤
ከፅድቅ ይልቅ ስመላለስ በሀጢያቱ፤
ያልጠፋሁት ከልሎኝ ነው በምህረቱ።

የእኔ ወዳጅ፤
ውሎ አዳሬን የእኔ ፈቃጅ፤
ስለክብሩ ሳይጨነቅ ከጌትነት ዝቅ ብሎ፤
አይቻለሁ ያለስራው ሲንገላታ እኔን ብሎ።

ይኸው ዛሬም በትዕቢት ውስጥ ትቢያ ሁኘ፤
ቸር አይደለ መልካም ልደት እየተመኘ፤
ሌላ አመትን ጨመረልኝ እኔን ቃኘ።

ተመስገን።።።።???

? ? ?
? መልካም ልደት ለእኔ ?
? ? ?
03/08/2016 ዓ.ም

@eluuu2112
@smetoch12
@smetoch12

8 months, 3 weeks ago

# እንኳን አደረሳችሁ .... መጋቢት መድሀኒአለም ??? 27

@eluuu2112

@smetoch12
@smetoch12

8 months, 3 weeks ago
9 months, 1 week ago

ግራ ገባኝ እኮ

ቆይ ግን ጓድኞቸ ምን እየሆኑ ነው፤
የሚጣፍጣቸው እኔ የምበላው፤
የሚሽቀረቀሩት እኔ በምገዛው።

ይሁን እንዳሻቸው እስካለን አንድነት፤
ኩሌንም ይካሉት ሽቶየን ይቀቡት ፤
ንብረቴን ይውረሱት፤
ታዳ ጓድኝነት ምኑ ላይ ነው ብየ፤
ቃል አልተነፈስኩም ስኖር ተቻችየ።

ካማራቸው ሁሉ ውሰዱ ማለቴ፤
በሰጠሁትም ልክ መልስ አለመሻቴ፤
መጠሪያ ሲያሰጠኝ የሚባል ሞኝቴ።

እራሴን ሳፅናናው መልካምነት ለራስ ፤
ሞኝነት ምንድነው ሰጠኋቸው እንጂ ፤
እኔ ሰእነሱ አላንስ፤
እያልኩ ስደሰኩር እያልኩ ስፈላሰፍ፤
ፍቅረኛየ ብየ ያስተዋወኩትን አየሁት ካአንዷ አቅፍ።

ሌብነታቸውን አሁን ነው መለፈፍ፤
አሁን ነው መለፍለፍ፤
ንብረቴን ጨርሰው ፍቅሬን ወሰዱብኝ፤
ከጀርባየ ናቸው እባካችሁ ያዙልኝ ።

✍️ዕሌኒ

(@eluuu2112)
@smetoch12
@smetoch12

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 months ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 months, 2 weeks ago