Hana Hailu

Description
መንቃት እና ማንቃት
መብቃት እና ማብቃት
የሰው ልጅ ልክ እንደውቅያኖስ ነው ስፋቱ እንጂ ጥልቀቱ አይታይም!
በየቀኑ እማራለሁ- የተማርኩትን ላካፍላችሁ ወደድኩ!

በዚህ ቻናል የተማርኩትን የገባኝን ከሌሎች ከራሴ ለእናንተ አካፍላለሁ!
ራሴን እና ሌሎችን ለማንቃት እጠቀማለሁ


አስተያየት
@HanahailuEth

ዌብሳይቴን ይጎብኙ
Www.hanahailu.com
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

4 weeks, 1 day ago

#የእኔ_ልደት_እና_ገዢው_መንግስት
ነገሩ ፖለቲካ የሆነበትን ምክንያት ከታች አንብቡት !
(ጉዳዩ ላይ ይበልጥ ለማተኮር እና ለመረዳት እንዲጠቅማችሁ ከኢትዮጲያ መንግስት ውጪ አስቡ) አንድ ሰው የአንድ ሀገር ጠቅላይ ሚኒስቴር ከመሆኑ በፊት እያንዳንዱ የግል እና የቤተሰብ ጉዳይ ፣ ጥቃቅን እና ትልልቅ የቤት ውስጥ ሀላፊነት ያስጨንቀዋል።
ወደ መንግስት ስልጣን ከመጣ በኋላ ግን ስለሚበላው ምግብ ፣ ስለመኪናው ነዳጅ፣ ስለተገዛው አስቤዛ ወይም ሌላ ጥቃቅን ወጪዎች አይመለከተውም።
መሪው ጥሩ ይሁን መጥፎ ፤ትክክል ቢሰራም ባይሰራም - የቀን እና የሌሊት ሀሳቡ መንግስት እና የመንግስት ጉዳይ ይሆናል።

ታዲያ በዚህ ጊዜ አስቀድሞ ያስጨንቀው የነበረውን የግል ጉዳዮቹን የሚያስፈጽም እና የእርሱ ጉዳይ የሚያስጨንቃቸውን ሰዎች መንግስት ይመድባል። እርሱ ትኩረቱን መንግስት ላይ ሲያደርግ መንግስት ደግሞ ትኩረቱን እርሱ ላይ ያደርጋል።
በተለየ መልኩ ለሚበላው ፣ ለሚለብሰው ፣ ለሚቀመጥበት፣ለሚጠጣው ሻይ ሳይቀር ሳይቀር ሀላፊነት በሚወስዱ ሰዎች ይከበባል ለዛም የሚሆነውን በጀት የሚመድበው መንግስት ነው!

እናንተ የእግዚአብሄር ጉዳይ ላይ ስታተኩሩ እግዚአብሄር የእናንተ ጉዳይ ላይ ያተኩራል። እናንተ የእግዚአብሄር መንግስት ዋናችሁ ሲሆን የእግዚአብሄር መንግስት የእናንተን ጉዳይ ዋናው ያደርጋል። ይበልጥ ወደ እግዚአብሄር መንግስት ስትጠጉ ይበልጥ የእግዚአብሄር መንግስት በእናንተ ጉዳይ ሀላፊነት ይወስዳል።ቤተመንግስት አካባቢ ስትጠጉ የመንግስት ያህል ትጠበቃላችሁ…አንድ ባለስልጣን ሌላ ሀገር ሲሄድ እንዴት ደንነቱ እንደሚጠበቅ ሰምቼ ነበር ጉዳዩ የግለሰብ ሳይሆን የመንግስታት ጉዳይ ይሆናል።

በቃ ይሄው ነው
ገዢው እና ትልቁ መንግስት የሰማዩ ነው!

ስለዚህ፣ ‘ምን እንበላለን? ምን እንጠጣለን? ምንስ እንለብሳለን?’ ብላችሁ አትጨነቁ፤ አሕዛብ እነዚህን ነገሮች ሁሉ ለማግኘት ይጨነቃሉና፤ የሰማዩ አባታችሁም እነዚህ ሁሉ ለእናንተ እንደሚያስፈልጓችሁ ያውቃል። ከሁሉ አስቀድማችሁ ግን የእግዚአብሔርን መንግሥትና ጽድቁን እሹ፤ እነዚህ ሁሉ ይጨመሩላችኋል።
ማቴዎስ 6:31-33

ያለፈው አመቴ በብዙ መናወጥ እና በጣም ትልልቅ ድሎች ነበሩት ግን ጉዳዬ ሁሉ በቁጥጥሩ ውስጥ እንደሆነ ደጋግሜ ተረድቻለሁ። ፈተናዎቼ ቀጠዩን መጽሐፎቼን ወልደዋል ፤በመልካምም ሆነ በክፉ በህይወቴ ውስጥ የነበሩት ሰዎች ደግሞ የመጽሐፉ ገፀ ባህሪ ሆነው የራሳቸውን አሻራ አኑረዋል።

???የ28ተኛ አመት የልደት ቀኔ ላይ ሆኜ ለራሴ እንዲ እለዋለሁ አይንሽን ከራስሽ ጉዳይ ላይ አንሺ ....የእግዚአብሄር ጉዳይ ዋናሽ ይሁን!

የበለጠ ትኩረት የሚስበውን የፖለቲካ ወሬ ስለሆነ ይህንን መልዕክት እንድታነቡት እድሉን ልጠቀም ብዬ ነው ጉዳዩን መንግስታዊ ያደረኩት። ይቅርታ ??

@hanahailu

1 month ago

ዛሬ እንዲ ሆን.....

የተሰበረ የመሰላችሁ ነገር መልሶ እንደገና ይሰራላችሁ!
በሸክላ ሰሪው እጅ ተይዛችሁ ቅሩ! እንደገና ለመሰራት ከእርሱ መራቅ አይሁንባችሁ....

እጄ ላይ የነበረን ነገር ተበላሸ በቃ ብዬ በተለይ ዛሬ በጣም ከፍቶኝ ነበር!

ደሞ በሌሊት እንዲህ አለኝ መፍትሄውንም ነገረኝ

ከጭቃ ይሠራው የነበረውም ሸክላ በእጁ ላይ ተበላሸ፤ ሸክላ ሠሪውም በሚፈልገው ሌላ ቅርጽ መልሶ አበጀው።
ሸክላ ሠሪው እንደሚሠራው፣ እኔ በእናንተ ላይ መሥራት አይቻለኝምን?” ይላል እግዚአብሔር፤ “የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ጭቃው በሸክላ ሠሪው እጅ እንዳለ፣ እናንተም እንዲሁ በእጄ ውስጥ ናችሁ።
ኤርምያስ 18:4-6

የሚናገረው፣ የሚሰማው ፣ የሚያየው አንድ አምላክ ይቅረባችሁ!

1 month ago
እኔም [#ባለጊዜ](?q=%23%E1%89%A3%E1%88%88%E1%8C%8A%E1%8B%9C) ነኝ!

እኔም #ባለጊዜ ነኝ!

በከባዱ የተፈተነች በከባዱ የተሸለመች
ድካሟን እየተሸፈነላት ስኬቷ ያደመቀላት
ልወድቅ ነው እያለች እጇን ይዞ ያሻገራት
ውለታዋን ያልከፈለች የምንጊዜም ባለዕዳ ፣በምህረት ኑሪ የተባለች ፣ እስትንፋስ የተቀጠለላት ፣ ሳይገባት በአምላኳ የተወደደች እሷ ባለጊዜ ሴት እኔ ነኝ!

በህይወት እስካለን፣እግዚአብሄር እድሜ እስከጨመረልን ድረስ እስትንፋሳችን ካልቆመ እኛም ባለጊዜ ነን!

3 months, 2 weeks ago
Hana Hailu
3 months, 2 weeks ago
Hana Hailu
3 months, 2 weeks ago
Hana Hailu
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago