ለ አሻዒራና አህባሽ ጥናታዊ ምላሽ Refutation Of The Asharis & Ahbash

Description
የቻናሉ ትኩረት!

✔ የአህባሽን ግድፈቶች በመረጃ ማጋለጥ እና ጥናታዊ ምላሾችን ማሰራጨት!

✔ ተዉሒድ እና ሽርክን በማብራራት የነብያትን ተልዕኮ ማስገንዘብ

? የአህባሽ ብዥታ በዒልም ሲረታ!

قناة خاصة بنشر الردود العلمية على فرقة الأحباش الضالة باللغة الأمهرية الإثيوبية
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago

3 years, 9 months ago

አህባሾችና አላህን ከ‘ጂሀ’ እና ከ“መካን” የማጥራት እሳቤ
ክፍል 2/2

የአላህ ከፍጥረታት በላይ መሆን አላህ በተፈጥሮ በልባችን ያኖረው ግልጽ እምነት ነው። አላህ በቁርአን እንደገለፀው የአላህን ከፍጥረታት በላይ መሆን "ዑሉው" መግልጽ ብቻ ለአህሉሱና በቂ ነው።  በቁርአንም ላይ የምናገኘው አካሄድ ይኸው ነው። ‘አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጥራት’ ጥቅል በሆነ መልኩ ሲቀርብ ፤ የአላህን ባህሪያት ማጽደቅ ግን በዝርዝር ሲቀርብ እናገኛለን። ለአብነት ያክል ተከታዩን መልእክት እናስተውል፤
لَيْسَ كَمِثْلِهِ شَيْءٌ ۖ وَهُوَ السَّمِيعُ الْبَصِيرُ} الشور : 11
‹‹የሚመስለው ምንም ነገር የለም፡፡እርሱም ሰሚው ተመልካቹ ነው» አል ሹራ 11 

ይህ አንቀፅ በየትኛውም ሁኔታ በፍጡራንና በፈጣሪ መካከል መመሳሰል እንደሌለና አላህ ሰሚና ተመልካች መሆኑን ያሳያል፡፡ መስሚያና መመልከቻ የብዙ ፍጡራን መገለጫዎች ቢሆኑም ነገር ግን የአላህ መስሚያና መመልከቻ ከፍጡራኑ ጋር አይመሳሰልም።
በመስሚያና በመመልከቻ አምሳያ እንዳሌለው ሁሉ በሌሎችም ባህሪያቱ አምሳያ የለውም፡፡  ይህ አንቀጽ ሙስሊሞች ለአላህ የማይገቡ ባህሪያትን ከመረዳት አንጻር ሊኖራቸው ለሚገባው ትክክለኛ አካሄድ በመርህ መልክ ይቀርጻል።  አንቀጹ የጉድለት ባህሪዎችን ጥቅል በሆነ መልኩ ዉድቅ ሲያደርግ ምሉዕ ባህሪዎችን ግን በዝርዝር ያጸድቃል።

አቅጣጫዎች ህዋሳዊ ማነጻጸሪያ reference point በመጠቀም ብቻ የሚታወቁ ናቸው። ማንኛውም ሰው የቂብላን አቅጣጫ ለማወቅ ጸሀይን ማነጻጸሪያ እንደሚያደርገው ማለት ነው።
ሰዎች በአዕምሮአቸው የሚቀርጿቸው ማነጻጸሪያዎች ሁሉ በፍጥረተ አለሙ የተገደቡ በመሆናቸው ስለአላህ ለመናገር እነዚህን ፍጡራዊ ማነጻጸሪያዎችን መጠቀም አይገባም!

አህሉሱና ፍልስፍዎችን በቁርአን እና በሱና ላይ አይሾሙም! አላህ ለራሱ ያጸደቃቸውን ባህሪዎች ያጸድቃሉ፤ ለአላህ ተገቢዉን ክብር ስለሚሰጡ ስለባህሪዎቹ የተነገሩ መረጃዎችን የፍጡራንን ባህሪ በሚረዱበት ሁኔታ አይረዱም። ሁልጊዜ መነሻቸው አላህን ከጉድለትና ከመመሳሰል ማጽዳት ስለሆነም እነዚህና መሰል የአስተሳሰብ ግድፈቶች አይገጥሟቸውም ።
አዎን! አላህን በጉድለትም ይሁን ከፍጡራን ጋር በመመሳሰል ከመግለፅ የፀዱ ናቸው!!

በአንፃሩ አህባሾችና አርአያዎቻቸው ጀህሚዮች፤ ሁሌም መነሻቸው ስለ አላህ የተነገሩ መረጃዎችን ልክ ፍጡራን ላይ በሚያውቋቸው ባህሪያት መልኩ መረዳት ስለሆነ አላህን ከፍጡራን መለየት ያልቻሉ "ሙመሲላህ" አመሳሳዮች እነሱው ናቸው።

የሰማያትና የምድር ፈጣሪ አምላክ ሰለሆነው አላህ ሲነገር እንዴት ፍጡራዊ የሆኑ ባህሪዎች ይታወሳሉ??

አላህ ከጥመት ይጠብቀን!

አቡጁነይድ
ዙልቂእዳ 17/1436 ዓ.ሂ

@abujunaidposts

3 years, 9 months ago

አህባሾችና አላህን ከ‘ጂሀ’ እና ከ“መካን” የማጥራት እሳቤ

ክፍል 1/2

ምስጋና ለአላህ የተገባ ነው። የአላህ ሰላምና እዝነት በመልእከተኛው ላይ የሁን። በመቀጠል፤

አላህ እንዲህ ብሏል፤
{الرَّحْمَٰنُ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَىٰ} [طه : 5]
«አል ረህማን ከዓርሽ በላይ ከፍ አለ» ጣሀ 5

ማንኛውንም ጤናማ ሙስሊም ይህንን አንቀፅ ስትሰማ፤ ‘ሰማያት አላህን ተሸክመዋል፣ ፍጥረራቱ ያካብቡታል’፣ ‘አላህ ከዓርሽ ፈላጊ ነው’ ወይም ‘አላህ በፍጥረታቱ ውስጥ ሰርጿል’ የሚሉ መጥፎ መልዕክቶችን ተረድተሀልን? ብለህ ብንጠይቀው፤

“ፈጽሞ አዕምሮዬ አላሰበዉም” እንደሚለን ግልጽ ነው። በፍልስፍና ልቡ ያልታወረ ማንኛውም ሙስሊም ይህንን እና መሰል መልእክቶችን ከጥመት በራቀ መልኩ እንደሚረዳው ይታወቃል። በርግጥም ከዚህ ግልጽ ቁርአናዊ መልእክት ጥመትን የሚረዳ ልቡ ውስጥ በሽታ ያለበት ብቻ ነው!

አህሉሱና ግን አላህ ከእርሱ ክብርና ግርማ ሞገስ ጋር በሚሄድ መልኩ ከሰማያትና ከዓርሽም በላይ መሆኑን እና ከፍጥረታቱ የተለየ “ባኢን’ መሆኑን ያምናሉ። በዚህ መልኩ ንፁህ ምልከታ ኖሮህ አላህ የተናገረውን አፅድቀህ ስትመሰክር ሰላም ነህ።

ሆኖም አህባሾችና ይህንን ጥመት ያወረሷቸው ቀደምት አንጃዎች «አላህ ከአርሽ በላይ ነው» ስትል በአላህ ክደሀል ይሉሀል። ለምን ብትላቸው ለአላህ ቦታ እና አቅጣጫን ስለሰጠህ ካፊር ይሉሀል። ስለዚህም ዘወትር "አላሁ መውጁዱን ቢላ መካን" የሚል ባዶ መፈክር ሀዲስ በማስመሰል ይደሰኩራሉ።

ለመሆኑ አህባሾች...
የዚህን አንቀፅ ቀጥተኛ መልእክት በሰው አእምሮ የማይመጣን የጉድለት ባህሪ የሚያስገነዝብ የኩፍር መልእክት አድርገው ለምን ይረዱታል?

ሰሀቦችና ታቢዒዮች ከአላህ የመጣውን መልእክት ተቀብለው ሳይፈላሰፉ እንዳፀዱቀት እነርሱም አፅድቀው በማመን ፈንታ መካን እና ጂሀ የሚል ፀጉር ስንጠቃስ ለምን አስፈለጋቸው?

መነሻዎቻቸውንና ትክክለኛውን የአህሉሱና አቋም ማወቅ ጠቃሚ ነውና ልብ ብለህ ተከታተለኝ።

በመሰረቱ "ጂሀ" (አቅጣጫ) እና "መካን" (ቦታ) የሚሉት ቃላት ሸሪዓዊ መሰረት የላቸውም። ከዚህ ርዕስ ጋር በተያያዘ በቁርዓንም ይሁን በሀዲስ አናገኛቸዉም። በተመሳሳይ መልኩ ‘ሀድ’ እና ‘ጂስም’ የመሳሰሉ "ሙጅመል" ጥቅል ቃላት ሸሪዓዊ መሰረት የላቸውም።

አህሉሱና በዚህም ይሁን በሌሎች ርዕሶች ላይ መረጃን መሰረት ያደረገ አካሄድ ስላላቸው እንዲህ አይነቶቹን ጥቅል ቃላት “አል አልፋዝ አል ሙጅመላህ” መነሻ አድርገው አይናገሩም መፈተኛም አያደርጓቸውም። ነገር ግን ከቢድዓ አራማጆች በኩል ሲመጡ ለማጽደቅም ይሁን ውድቅ ለማድረግ ሳይሽቀዳደሙ ቃሉን ባለበት በመተው የሚፈለግበት መልዕክት ምን እንደሆነ ይጠይቃሉ። ከምላሹም በመነሳትም መልዕክቱ ሀቅ ከሆነ ያጸድቁታል፤ ሀቅ ካልሆነም ውድቅ ያደርጉታል።

ለምሳሌ፤ አንድ አህባሽ «ለአላህ ጂሀ ‘አቅጣጫ’ አታድርጉለት ይህ ኩፍር ነው» ቢልህ፤ ከዚህ ርዕስ ጋር በተያያዘ ‘ጂሀ’ የሚለውን ቃል በቁርአን እና በሀዲስ እንደማታውቀው በመንገር በዚህ ቃል ምን እንደተፈለገበት ጠይቀው። ሀሳቡ አላህ ከፍጡራኑ ሁሉ በላይ መሆኑን ማስተባበል ከሆነ ከቁርአንና ከሱና እንዲሁም ከተፈጥሯዊ እምነት ጋር የሚጋጭ ተራ ወሬ ስለሆነ ሀሳቡን እንደማትቀበል ትነግረዋለህ። ነገር ግን የፍጥረተ ዓለሙ አካል የሆኑትን ስድስት አቅጣጫዎች ለአላህ መገለጫ ማድረግ የለብንም ለማለት ከሆነ ይህ የታወቀ እንደሆነ እና ይህ አይነት ትርጓሜ ያለዉን ‘ጂሀ’ ለአላህ እንደማናጸድቅ፤ ቀደወሞውንም ስለአላህ ስናወራ በዙሪያችን ያሉ አቅጣጫዎች ፍፁም እንደማይታሰቡን ታስረዳዋለህ።

{أَأَمِنتُم مَّن فِي السَّمَاء} [الملك : 16]
«ከሰማይ በላይ ያለውን ‘አላህ’ ትተማመናላችሁን?» አልሙልክ 16

ልብ በል ወንድሜ፤ ይህንን እና መሰል አንቀፆችን ሲሰሙ የቁርአንን መልእክት በቀጥታ በመጠምዘዝ ‘አላህ ከሰማይ በላይ’ መሆኑን ሲያስተባብሉ ታይና ተገርመህ ይህ ሁሉ ልፋት እና መወራጨት ምን አመጣው ብለህ ችግራቸውን ስታጠና፤ አሁንም ለአላህ ቦታ “መካን” መስጠት አይገባም የሚሉት የፍጡራን መኖሪያ የሆኑትን ሰባቱን የቅርብ ሰማያት በማሰብ እንደሆነ ትረዳለህ። እንደዚሁ ‘አላህ ከፍጡራን በላይ ነው’ ሲባሉ በዙርያቸው የሚያውቋቸውን ስድስት አቅጣጫዎች በማሰብ አላህ ከጂሀ “አቅጣጫ” የጸዳ ነዉና ከፍጡራን በላይ ነው አይባልም እንደሚሉ ትረዳለህ። የስህተታቸው ሁሉ መሰረት ይህ ነው።

☞ ጀህሚያ፣ ሙዕተዚላ እንዲሁም አሻዒራ የአላህን የበላይ መሆን የሚያስተባብሉባቸው ፍልስፍናዊ መረጃዎች ሁሉ የሚያጠነጥኑት በዚህ ብዥታ ላይ ነው። መካን(ቦታ) እና ጂሀ(አቅጣጫ) ለአላህ አይገቡም በማለት የአላህን ከፍጡራኑ የበላይ መሆን ያስተባብላሉ። እውነታው ግን፤ እነሱ ለዚህ ስለ አላህ ባህሪያት ለማወቅ መነሻ ያደረጉት ከፍጥረተዓለሙ ጋር የተያያዙትን «ዉጁዲይ» ቦታ እና አቅጣጫን ነው። ስለ አላህ የሚነገሩ እውነታዎችን ሁሉ ፍጡራን ላይ በሚያያቸው ግንዛቤዎች ከሚተረጉም እውር አስተሳሰብ መጠንቀቅ ያስፈልጋል።

☞ አህሉሱና አላህ ከፍጡራን ሁሉ በላይ መሆኑን ያምናሉ፤ ‘ከሰማይ በላይ ነው’ ወይም ‘ከዓርሽ በላይ ነው’ የሚለዉን ሁሉ አላህ በነገራቸው መሰረት ሳይጨምሩና ሳይቀንሱ ይቀበሉታል። ስላልተነገራቸው የባህሪ ምንነት ‘ከይፊያ’ ግን ምንም አይናገሩም። አህሉሱና ከአላህ ባህሪያት ጋር በተያዘ ፍጡራዊ የሆኑትን ጂሀ እና መካን ለአላህ አያጸድቁም። ቁርአናዊውን የ‘ዑሉው’ አስተምህሮ ተቀብለው ሲያፀድቁም፤ ሙዓጢላዎች እንደሚያስቡት...

✘ አላህ አንደኛ ሁለተኛ ተብሎ በሚቆጠረው የመላዕክት መኖሪያ ሰማይ ላይ ይኖራል እያሉ አይደለም። መላዕክትም በሰማይ ሰዎች በመሬት በሚኖሩበት መልኩ አላህም በሰማይ ይኖራል የሚል እምነት ያለው ሰው በእርግጥም በአላህ ክዷል።
✘ እንደዚሁ ሰማይ አላህን ይሸከመዋል ወይም ያካብበዋል ከሚልም አስተሳሰብ የጸዱ ናቸው። ይህ የአላህን ከፍጥረታቱ ጋር መቀላቀልን “ሁሉል” የሚያምኑ የቢድዓ አራማጆች እምነት ነው።

✘ አላህ በፍጥረተዓለሙ ዉስጥ በሚገኙት ስድስት አቅጣጫዎች ይገለጻል፤ ፍጥረተአለሙም ያካብበዋል ማለትን ፈፅሞ አያመላክትም። ይህንን ያለ ሰውም በአላህ ላይ ውሸትን ተናግሯል፣ መንገድንም ስቷል። አህሉሱና ይህ ሁሉ ጥመት ስለመሆኑ አይወዛገቡም።

ይቀጥላል...

@abujunaidposts

3 years, 9 months ago
***?*** *አህባሾች ቢያስተውሉ*..*!*

? አህባሾች ቢያስተውሉ..!

ታላቁ የሀዲስ ዘጋቢ ቲርሚዚይ በሀዲስ ጥንቅራቸው ኪታቡዘካት ሀዲስ ቁ .662
ስለ አላህ ሲፋት አህሉሱና እና ጃህሚያዎች ያላቸውን አቋም በግልፅ አስፍረዋል!

ፍልስፍና ሳይሆን ሸሪአዊ መረጃዎችን መከተል መታደል ነው። አላህ ማስተዋልን ይለግሳችሁ!!

@emnetihintebiq

4 years ago

የሀሰን ታጁ መውሊድ መፅሀፍ ሲፈተሽ

? አቡጁነይድ ሳላህ አሕመድ
⌚️ የ 10 ደቂቃ መልዕክት

? Share Link
https://t.me/abujunaidposts/117

----------------
?የአቡጁነይድ መልዕክቶች
@abujunaidposts

4 years, 2 months ago

▪️#አሏህ_ከዐርሽ_በላይ_ነው

?ኡስታዝ አሕመድ አደም አሏህ ከዐርሽ በላይ በመሆኑ ዙሪያ በተለያዩ ጊዜያት ፈትዋ ተጠይቆ በዛዱልመዓድ ፈትዋ ፕሮግራም በኩል የመለሳቸውን መልሶች በድምፅ እና በፅሑፍ የያዘ የሊንኮች ስብስብ.

?1.ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.14 የ1ኛው ጥያቄ ምላሽ

➠ጥያቄው ፦
አሏህ - ሱብሓነሁ ወተዓላ- የት ቦታ እንዳለ ማወቅ እንችላለን ወይ? ቅዱስ ቁርአንይ ሱረቱ ጧሃ ሳነብ ስልጣኑ በዐርሽ ላይ ተደላደለ የሚል ነው። አንዳንድ ኡስታዞችን ስጠይቅ አሏህ በሁሉም ቦታ ነው እንጂ እዚህ ቦታ ነው ብለን ቦታውን መለየት አንችልም አሉኝ። ትክክለኛው የቱ ነው? በጣም ግራ ስለተጋባሁኝ ነው ፤ ብታብራሩልኝ?
°
➠መልስ ፡
በቴሌግራም ፦ https://t.me/ibnyahya7/173
በፅሑፍ ፦ https://t.me/ibnyahya7/179
°
?2.ከዛዱልመዓድ ፈታዋ ቁ.55 የ3ኛው ጥያቄ ምላሽ

➠ጥያቄ ፦ ኢስቲዋእ ማለት ምን ማለት ነው? ብታብራሩልኝ? ግሩፕ ላይ ሲከራከሩበት ግራ ገብቶኝ ነው።
°
➠መልስ ፡
በቴሌግራም ፦ https://t.me/ibnyahya7/5062
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/-NmHUfT2rI0
በፅሑፍ ፦ https://t.me/ibnyahya7/2046
°
?3.ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.74 የ1ኛው ጥያቄ ምላሽ

➠ጥያቄ ፡
1."ወሃብዮች" አላህን ዐርሽ ላይ ነው ካሉ በኋላ ወደቅርቢቱ ሰማይ ይወርዳል ይላሉ ፤ እርስ በእርሱ ይጋጫል እያሉ አሕባሾች ይከራከራሉ ፤ ቢያብራሩልን?
°
➠መልስ ፡
በቴሌግራም ፦ https://t.me/ibnyahya7/3040
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/TW-YORZwckk
በፅሑፍ ፦ https://t.me/ibnyahya7/3042
°
?4.ከዛዱል መዓድ ፈታዋ ቁ.103 ላይ የ1ኛው ጥያቄ መልስ

➠ጥያቄ ፡
1.የቁርኣን ተፍሲር በአማርኛ የተተረጎመውን ስናነብ አሏህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለውን ሲፈስሩ አሏህ በዐርሹ ላይ ስልጣኑ ተደላደለ ብሎ ተፈስሯል። ይህ እንዴት ይታያል? ያብራሩልኝ?
°
➠መልስ ፡
በቴሌግራም ፦ https://t.me/ibnyahya7/5570
በዩቲዩብ ፦ https://youtu.be/_Nwh6LNfZP0
በፌስቡክ ቪዲዮ ፦ bit.ly/2EsjtI3
በፅሑፍ ፦ https://t.me/ibnyahya777/407

✍️ ጥንቅር ፡ አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
?ሶፈር 6/1442ሂ. # መስከረም 13/2013 # Sep. 23/2020

?ጆይን ያድርጉ፦ https://telegram.me/ibnyahya777
ላይክ ያድርጉ፦ https://m.facebook.com/ibnyahya777

Telegram

🇮ዲን መመካከር ነው-الدين النصيحة🇮

4 years, 5 months ago

? ግርዶሽ እና ሸሪዓዊ ህግጋቱ

? የፀሐይ እና የጨረቃ ግርዶሽን አስመልክቶ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ የሚሰጥበት ልዩ የፈታዋ ፕሮግራም

? በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ
እና
? በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

? ነገ ሰኔ 13/2012

⌚️ ቀን 8:00 ጀምሮ

? በድጋሚ ምሽት ከ3:00 ጀምሮ

? በነሲሓ ቲቪ ይጠብቁን

4 years, 5 months ago

ለአንድ ወር የሚቆይ ልዩ የሸሪዓ ኮርስ በነሲሓ ቲቪ ከዛሬ ሰኔ 9/2012 ከ10: 00 ጀምሮ

? ነሲሓ ቁርኣን ቤት ?

?ቃዒደቱ ኑራኒያህ

? በኡስታዝ ሑሴን ሙንደታ

? የቁርኣን ሀልቃ

? በኡስታዝ ሚፍታህ ኑሪ

? የነብያት ውርስ ?

? ኪታቡ ተውሒድ

? በሸይኽ ኻሊድ ዐብዱለጢፍ

? ኪታቡ ሰላት

? በሸይኽ ኸሊል ሐሚድ ኸሊል

? መንዙመቱል ፊቅህያ

? በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

? ነሲሓ መሰረታዊ ?

? የዓቂዳ ትምህርት

? በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

? ቀዋዒዱል አርበዓ

? በኡስታዝ ሱልጣን ኸድር

? አዱሩሱል ሙሒማህ

? በዶ/ር ዐብዱ ኸይሬ

? ነሲሓ ለእህቶች ?

? የተፈጥሮ ደም እና ሸሪዓዊ ህግጋቶቹ

? በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

? የጋብቻ እና ፍቺ ህግጋት

? በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

4 years, 7 months ago
***?*** የአህባሽ ብዥታ በዕውቀት ሲረታ!

? የአህባሽ ብዥታ በዕውቀት ሲረታ!

?ሸይኽ ኢልያስ አህመድ

አሁኑኑ ሊንኩን በመከተል ያድምጡት
https://t.me/ustazilyas/400

? የ2003 ልዩ የ10 ደቂቃ መልዕክት፦ በነብያት ጥሪ ውስጥ ጉልህ መልዕክት ስለሆነው የኢስላም መገለጫ "ተውሒድ" በሚነዙት የጃሒሊያ ብዥታ ሊፈታተኑህ አይገባም!!

4 years, 9 months ago

? ልዩ ፕሮግራም በነሲሓ ቲቪ

? በሞጣ የወደሙትን መስጂዶች እና የወንድሞችን ንብረት መልሶ ለማቋቋም የተዘጋጀ ልዩ ፕሮግራም ከዛሬ ምሽት 2:30 ጀምሮ እስከ ነገ ምሽት 12:00 ድረስ በነሲሓ ቲቪ

? በተጨማሪም በነገው እለት ልዩ የጁምዓ ኹጥባ

? መርካቶ በሚገኘው ባዩሽ መስጂድ

? በሸይኽ ኢልያስ አሕመድ

? ቢላል (ኮካ) መስጂድ

?በኡስታዝ ሙሐመድ ሐሰን ማሜ

๏| ነሲሓ ቲቪ |๏

√ ኢስላማዊ ዕውቀት ለሁሉም
……
ቴሌግራም t.me/nesihatv
ፌስቡክ fb.com/tvnesiha

እንዲሁም በዌብሳይታችን
www.nesiha.tv
ይጎብኙን

Telegram

NESIHA TV | ነሲሓ ቲቪ

የነሲሓ ቲቪ ኦፊሺያል ቻነል Http://www.nesiha.tv ነሲሃ፣ ነሲሀ፣ nasiha ቲቪ

***?*** ልዩ ፕሮግራም በነሲሓ ቲቪ
4 years, 10 months ago

? جديد

نبذة من مُخالَفات (الأَحباش) العَقدِيَّة أو ما يعرف بـ جمعية المشاريع الخيرية الإسلامية

https://salafcenter.org/4470

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 month, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 3 months, 2 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 day, 11 hours ago