Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

ወኔ እና ቅኔ -(ፈይሠል አሚን)

Description
ሐበሻ ቅኔን ያለ ምክንያት አልፈጠረም፤ በወኔ የማይነገሩ ሐሳቦቹን ሊገልጽበት እንጂ!
.
ዳገት አቀበቱን በወኔው አለፈ፤
ወኔውን ሲነጥቁት ቅኔ ፈለሰፈ!😉
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago

2 weeks ago

ገድሎ መትረፍ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
በጅምላ ሲበርደን፣
ብርዱ አጋመደን. . .
እየሣቁ መኖር፣በወል አዋሃደን!
ክፉ ቀን ሲያልፍ ግን. . .
ሙቀት አካካደን!
ምቾት አሳበደን!
.
ያለፈውን ረስተን፣
ጎዳናውን ስተን፣
ያረገዝነው ቂም፣አማዘዘን ሽመል፣
ገድሎ መትረፍ ኾነ የበረሃ አመል!
የደጉ ቀን ገድል፣ተመርዞ ቀረ፣
ያሳደግነው እባብ ቆዳ እየቀየረ!
.
@huluezih
@huluezih

2 weeks, 5 days ago

ዐውቃለሁ ተጠፋፍተናል ግን. . .
.
ይኼ ቻናል ከነ ቤተሰቦቹ በእጅጉ ናፍቆኛል። ከእናንተ ጋር ቃላትን፣ሐሳቦችንና ስሜቶችን መጋራት እኔ ዘንድ እንደ ዕድል የሚቆጠር ነገር ነው። ዕድሉ ስላለ ብቻ ደግሞ ያሰብኩትን እና የጻፍኩትን ግሳንግስ ሁሉ እዚህ አላመጣም። (መጥፋቱ ከመጠንቀቅም የመነጨ ነው ለማለት ነው)
.
ላለፉት ብዙ ቀናት በጥሞና እና ከሥነ-ጽሑፍ ካልራቁ ሌሎች ሥራዎች ጋር ስታገል እንዲሁም ትንሽ እረፍት ስወስድ ቆይቻለሁ። ከአሁን በኋላ በሚከተሉት ቀናት ውስጥ አዳዲስ ነገሮች ይዤ እንደምመጣ ተስፋ አደርጋለሁ። የሚመጡት አዳዲስ ነገሮች ይሳኩ ዘንድ ደግሞ የእናንተ እገዛ እና ተሳትፎ ከምንግዜውም በላይ ያስፈልገኛል። ብዙዎቻችሁ በዚህ ቻናል ለብዙ ጊዜያት በመቆየታችሁ፣ በቅርብ የተቀላቀላችሁን ወዳጆች ደግሞ በምትሠጡት በጎ አስተያየቶች ምክንያት ከእናንተ የምፈልገውን ነገር እንደማላጣ ልቤ ያምናል። በዚህ ጉዳይ ላይ በሰፊው እመለሳለሁ።
.
ሙስሊም ወንድምና እህቶቼ እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሒጅራ የዒድ አል ፊጥር በዓል በኸይር አደረሳችሁ!
.
ሁላችሁንም እወዳችኋለሁ
.
@huluezih
@huluezih

1 month, 3 weeks ago

"አንዳንድ ስብራት"
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih

2 months, 2 weeks ago

"ተመስገን"
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih

2 months, 3 weeks ago
3 months ago

"መፍረድ እና ማርፈድ"
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih

4 months, 2 weeks ago
. . .of the day!***😎***

. . .of the day!😎

4 months, 3 weeks ago

የማለዳ ማስታወሻ #156
.
ከትናንቴ ጋር ነው ፉክክሬ. . .
ከነበርኩበት አንድ ደረጃ ከፍ ብዬ ትናንቴን ቁልቁል ማየት፣ የትናንት መንገድ ያሳደፈው ልቤን ንፁህ አድርጎ ማቆየት፣ ያለፉ ሕፀፆቼን እንደ መጽሐፍ እያነበብኩ፣ እሾሃማ ትዝታዎቼን እንደ መስታወት እየወለወልኩ የተሻለውን እኔ በኩራት መመልከት፣ ትናንት እየጎተተ ኋላ እንዳያስቀረኝ ራሴን ከጸጸት መመከት! ወደ ኋላ እንዳይራመድ እግሬ፣ከትናንት ጋር ነው ፉክክሬ!
.
ደሞ ከዛሬ ጋር ነው ትግሌ. . .
የቆጡ ክፉኛ እያጓጓኝ፣ ያለፈው ቁጭት አባብሎ እያስጠጋኝ፣ በእጄ ያለው እንዳይበተን፤ "እደርስበታለሁ!" ያልኩት በቸልታ ወበቅ እንዳይተን፣ ወደፊት መራመድ፣ ካልኾነም መንፏቀቅ ከወደቅኩም ወደ አቅጣጫዬ ዞሬ መውደቅ. . .ብቻ ዛሬን በከንቱ፣ዛሬን በዋዛ አለመልቀቅ! ሳላሳብብ በዕጣዬ፣ሳላማኸኝ በዕድሌ፣ ባለ'ኝ እና ባገኘሁት ፈቅ ለማለት ከዛሬ ጋር ነው ትግሌ!
.
ከነገ ጋር ቃልኪዳኔ. . .
ዕድሜና ጤና በአጭር ሳያስቀሩኝ፣ የሞት መላዕክት በድንገት ሳይጠሩኝ፣ ጡቤን ልደረድር፣ የሕይወቴን ቅኔ ልሰድር፣ ልደርስበት ብዙ ለከፈልኩለት ነገ ቃል ገብቻለሁ. . . ተሸርፌም፣ተሰብሬም፣ ጎድዬም ቢኾን እመጣለሁ! የወጣሁትን አቀበት ነገ ላይ ቆሜ ቁልቁል ዐያለሁ. . .እዚህ ላለመቅረት ለነገ ቃል ገብቻለሁ. . .ለዘመናት የሚነገር ተረክ ከጉዞዬ ለቅሜ በስልቻዬ ይዣለሁ! አልቀርም እመጣለሁ!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih

4 months, 4 weeks ago

ጽሑፍና እኔ ምን አኮራረፈን?
.
ጅማሮውን ከማላውቀው ጊዜ አንሥቶ መጻፍ ይደክመኝ ጀምሯል። መጻፍ የምፈልገው ሐሳብ በምናቤ እየተከሰተ፣ ቃላት ስንኝ እየኾኑ በአዕምሮዬ እየተመላለሱ፣ ትዝብት አንቀጽ ሙሉ ፊደል አምጥቶ እንድጽፍ እየጋበዘኝ በማላውቀው ዐዲስ ስሜት ምክንያት ሳልጽፍ እቀራለሁ።በጣም ብዙ ጊዜ! ከቀናት በኋላም እነዚህ ጎትጓች ሐሳቦች ተስፋ ቆርጠው ይጠፉብኛል።
.
በምዕራባውያን ሥነ-ጽሑፍ ውስጥ "Art Attack" የሚባል ጽንሰ-ሐሳብ አለ። አንድ "የጥበብ ሰው" የሚጽፈው ሐሳብ ኖሮት ነገር ግን የሚጽፍበት ጊዜ አጥቶ ሐሳቡ አየር ላይ ሲቀርና ሲረሳ ለሚከሰት "ጥበብ-ነክ በሽታ" የተሠጠ ሥያሜ ነው። ቃሉ "heart attack" ከሚለው ቃል ስለተፈለፈለ "Art attack" ን "የጥበብ ድካም" ብለን ልንተረጉመው እንችላለን። "Hear attack"ን "ልብ ድካም" እንደምንለው ሁሉ ማለት ነው።
.
ረዥም ጊዜያትን በሥራ፣ በኑሮ በ"ወጣ ገባ"፣ በድንገተኛ ክስተቶች ውስጤ ላይ ስባትል ይኽ "Art attack" የተባለ በሽታ ሳያገኘኝ የቀረ አይመስለኝም። ወትሮም "እስቲ ልጻፍ" ብዬ የምቀመጥ ጸሐፊ አልነበርኩም። ሌላ ጉዳይ ላይ እያለሁ ጎትቶ ብዕር የሚያስጨብጥ ሐሳብ ካልመጣ በቀር በእቅድ ለመጻፍ ብዬ አልቀመጥም። ለዚያ ነው..."ሥነ-ጽሑፍ እንድጽፈው ያዘኛል እንጂ እኔ ሥነ-ጽሑፍን ተጻፍልኝ ብዬ አላዘውም" የምለው።
.
አንድ ጸሐፊ ለመጻፍ ከሐሳብ ባሻገር ብዙ ግብዓቶች ያስፈልጉታል። በዋናነት የሚጽፍበትና የጻፈውን የሚያርምበት በቂ ጊዜ፣ እንዲሁም የአዕምሮው ሰላም ፊታውራሪ ኾነው ከፊት ይሰለፋሉ።
.
አሁን ለመጻፍ የተሻለ ሁኔታ ላይ ነኝ። አሁን ቶሎ ቶሎ ሐሳብ የምንቀያየርበት፣አብረን ሕይወትን ከተለያየ አቅጣጫ የምናይበትና የምንዝናናበት ጊዜ መጥቷል። በተጨማሪ ደሞ "ክባዳም ትረካዎች" የተሰኘውን የወግ ቡፌ ከጽሑፍ ባሻገር በቪድዮም ዩቲዩብ ላይ የምንጋራ ይኾናል። ስለ ትዕግስታችሁ ላመሠግናችሁ ነው የመጣሁት...ክበሩልኝ🙏
.
#ፈይሠል_አሚን
.
@huluezih

6 months, 1 week ago

የማለዳ ማስታወሻ #155
.
"ከከፍታው ላይ ለመዝለል ትክክለኛው ሰዓት ለመዝለል የፈራኽበት ሰዓት ነው!" የሚል ጥቅስ ወደ ራሴ እንድመለከት መስኮት ከፈተልኝ። ከተከፈተው መስኮት አጮልቄ ወደ ራሴ ተመለከትኩ። ከከፍታው ላይ ለመዝለል እጅግ የፈራሁበት ሰዓት ነው። ልብ አድርጉ! የቆምኩበት ከፍታ የእኔ ቦታ አይደለም።
.
ሕሊናዬ ይነግረኛል..."ብትዘል ትወድቃለህ፣ ትሰበራለህ!" ይለኛል። ልቤም ዝም አይልም "ብትዘል ክንፍ እንዳለህ ካመንክ ትበራለህ እንጂ አትወድቅም። ዝለል! ዝለል!" እያለ ያደፋፍረኛል። በሕሊናዬና በልቤ ተቃርኖ መሐል አሁን ከፍታው ላይ በፍርሃት ቆሜያለሁ!
.
ደፍረው የዘለሉ፣ በጥሰው የወጡ፣ ቆፍረው ያመለጡ፣ ዘልለው የተረፉ ሁሉ በአንድ ወቅት እንደኔ በፍርሃት ወደ ራሳቸው ምህዋር የሚያሸጋግራቸውን ዝላይ አልፈዋል። ከፀፀት እና ቁጭት በአንዲት ውሳኔ ሳቢያ ተርፈዋል። እነዚህ ሰዎች የኾኑትን ልኾን እኔም የእኔ ካልኾነ ከፍታ ላይ ልዘል ነው። ከተረፍኩ የራሴን ከፍታ ከጠጠር ጀምሬ ልገነባ፣ ካልተረፍኩ ከስህተቴ ልማር የፈራሁትን ላደርግ፣ ግራ የገባኝን ጨክኜ ልወስንበት. . . እዘላለሁ!!
.
(#ፈይሠል_አሚን)
.
@huluezih
@huluezih

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 5 days, 11 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month ago

ጥራት ያላቸው የቤት ዕቃዎችንና የቤት ማስዋቢያ ቁሳቁሶችን ከእኛ ይግዙ። አድራሻ፦ መገናኛ ዘፍመሽ ግራንድ ሞል 3ኛ ፎቅ ከሊፍት ሲወርዱ ወደ ቀኝ ታጥፈው ቀጥታ 376 ያገኙናል። ባሉበት ሆነው ማዘዝ ይችላሉ። 0944222324

Last updated 23 hours ago