Brown Empire

Description
👋🏾
Advertising
We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 3 months, 1 week ago

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market

Last updated 3 months ago

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 3 days, 5 hours ago

4 months ago

Now let’s all forget everything I’ve wrote above and let’s focus on our patriotism, oh what a beautiful country?, with 80 and above ethnicity which loves supports and respect each others languages cultures and everything ? 13 months of sunshine? and a holy country ??? cause the lies matters, the lies has to go on.

?

4 months ago

Every time I close my eyes and open, I feel disappointed in this country. Two news updates, both addressing the same injustice but on very different grounds. Before I get into the two disappointing concerns, let me start with my own experience the other day. I was sick and was sent to the hospital, and I had a card number from my last visit. I enquired of the elderly lady behind the shelf, who wore a glass on her nose.Her hands shook slightly. No offense but She resembled the Slog from the cartoon movie Utopia. She crawls slowly and can hardly see.

I stood up on my patience in that waiting room for 14 solid minutes (don't come and compare your two hours of mistreatment to mine; instead, be a voice for your two hours of waste) while I was still sick, I was trying to compromising her being old and still working for her family or her own independence. But that was not my place to comprehend her; as an institute, particularly as a social service provider, it is always the people/customers who require all necessary service attention.

I know the she deserved to take her pension well back ten or fifteen years ago and she has to be home resting eating her retirement money, but sadly no. So If we start condemning her, she will blame her upcoming, background and ofc the system, which I know is definitely that let her down.

Oh, fast forward 30 minutes, I went to the toilet and there was no water in sight. In a giant ass hospital there was only gods water, the rain. ???, this is our dear reality that we deal every day every where.

1, I saw the interview that went down with the rappist Getnet Bayou's wife and Eyoha Media. It's long, contradictory, audaciously annoying and heartbreaking. But what got me the most was her saying "if my husband wanted to rape, why would he rape an eight-year-old when there is a 17-year-old girl who can be raped voluntarily" ??. She is not only a joke but also a mighty clown. And she isn't the only clown in it; there are others who buy this bullshit and can't see the flaw in that sentence. They claim it's politics, that an 8-year-old body being raped and brutally murdered is political. Heartbreaking

2, Another example is a tiktoker who flew with Ethiopia Airlines to Meqelle to celebrate Ashenda. They were in the airport starting from 6:00 o’clock day Time, local time and they stayed there with so many complications and lack of clear communication until they’re told to get off from the plane that they’ve waited until for almost nine hours ?and they were told to leave the plane at 4:pm night time,local time. funny.

But you know what's even more funny? The Tiktoker was broadcasting the live video on TikTok, and people who were watching were remarking, "Ethiopian Airlines is the most safest airlines." Is it? letting out people with children, old people, people with no additional money, sick people, and everyone from its plane and compound at night is marked safe? Is there even a law after steeping in the airport compound?cause we have ears, we can hear, we have eyes we can see. “this is not a taxi you can't say I'm not gonna dropped off, get off" and why not? Is the airport above the law when the right questions are asked? “Don't defame the airline's reputation." Which reputation? Seriously I want to know.
“He needs to be imprisoned” for what exactly? For asking his right? For being persecuted hours?
He is imprisoned later, so I’ve heard. ??

As a result, the system we choose to live under is continually forcing us to make sacrifices we do not have to. We overpay every day of our age, opportunity, time, and life itself. We are never given precedence as citizens of this country. And the people its self acting like an abused wife who won’t never leave the abusing husband. As who enjoys the beating, the disregarding emotion, the bruises and as the taking all the disrespect in the name of LOVE.

4 months ago
Brown Empire
4 months ago

ግቢ እያለሁ አስታውሳለሁ እጄ ላይ የማደርጋት አረንጏዴ ቢጫ ቀይ ጨሌ ነበረችኝ፣ I used to love her and wear her all the time. የሆነ patriotism ኖሮብኝ አላደግኩም፣ ቤተሰቦቼም ወለዬ እኔም የአዲስ አበባ ልጅ ነኝና የሚያንዘረዝር ስሜት ለተለየ ዘር የለንም፣ ሀገራችን በጥቅሉ ከመውደድ ያለፈ። ግቢ የገባሁ ግዜ ግን አላውቅም አንድ የሙጥኝ የምይዘው ነገር ፈልጌ ነበር መሰለኝ ኢትዮጲያዊነትን blindly አመናፍሰው ነበር።

past forward four years back, ሀገሬን ከከተማ ወጣ እያልኩ ዱር ገደሏን፣ ጋራ ሸንተረሯን፣ መንገዶቿን፣ ትናንሽ የገጠር ከተሞቿን እና መልክምድሯን ማየት ጀመርኩ። ወደድኳት። ስለመውደዴም ሳወራ ብዙዎች ስለ ውጪ ሀገራት ውበት እያነሱ በንፅፅር ያሳንሷት ነበር። አይጠፋኝም ልትበለጥ እንደምትችል፣ የማወቅ ጉጉቱም ስልክም እንዳላት አንድ ወጣት ኔዘርላንድስን ሰርች አድርጌ ማየቱ አልቀረብኝም። ግን እወዳታለሁ ስል እያነፃፀርኩ አልነበረም። የራሴው ስለሆነች የማውቃት እናቴ ስለነበረች እና ተፈጥሮ በምንም አይነት መልኩ ስለማይጠላ ነበር። ልክ መቆረጥ እንዳለበት ስድስተኛ ጣት ተፈጥሮ ሆኖ መቀየር መስተካከል ያለበት ህፀፆች ቢሞሏትም
“ቢጎል እንጀራ ከሞሰቡ ላይ እናት በሌላ ይቀየራል ወይ?” ነውና ከነ ነበር የወደድኳት።

Past forward today.
የትምህርት ሲስተሙ ፌል ሲያደርገን ፣ ሙዚቃውም ፊልሙም የስራ እድሉም ዘር ሲገባበት፣ ማወቅ ኢሉሚናቲ ሲባል፣ ቴሌቪዥን የፆታ ጥቃት ፣ ቲክቶክ ዘረኝነት ሲኖርበት፣ ፀብ መጠላላት እና ክፋት ሲበረታ፣ የብሄር ፀብ በወጣት ሲብስ፣ እንዲህ ሁኑ ብለው ባሳደጉን አፍረው እንዳትሆኑ ባሉን አይነት ሲኮሩ፣ የማይታይ ህልም አንግበን ደክሞን ስንዝል፣ ጩኸታችን ብርቅ ሳይሆን ከብዙሀኑ አንዱ እንደሆነ ሲነገረን፣ ታመን አሳማሚውም አብሮን ስለታመመ ስላልተሰማን፣ በጦርነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በጥቃት፣ ጦዘን አልወደቅንም ለማለት ለመበርታት ዘንጠን ተሰቃየን።

ሀገር እኮ ሰው ነው፣ ሀገሬ ከስምንተኛ የወደቁ ያለፈላቸው ቲክቶከሮች የሚሰሙበት ነው፣ ሀገሬ 12ኛ ልትፈተን ሄዳ የምትበላውን ተዘርፋ በርሀብ እና ህመም ሳትፈተን የመጣችውን እህቴን ያስለቀሰ ሲስተም ነው፣ “ሀገሬ ኧረ አርፈሽ ቁጭ በይ የምን መብት ነው?” የሚሉት ድምፆች ናቸው፣ ሀገሬ “እሷ ሁሉንም ነገር ከሴትነት ጋ ታያይዘዋለች” ያለው ፖድካስተር ነው። ሀገሬ “ድሮም ወሎን የነካ መጨረሻው እያምርም” ብሎ አንድ ግለሰብን የሚወቅጥ ህዝብ ነው። ሀገሬ ሽንኩርት 90 ብር ነው። ሀገሬ ከወገኑጋ የማይቆም አጋጣሚ ተጠቃሚ ነጋዴ ነው። ሀገሬ አድራጊው እያለ በሞካሪው የሚኮራ መንጋ ነው። ሀገሬ ለሚችለው እድልን የሚነሳው ነው። ሀገሬ ህፃን ደፋሪን እሹሩሩ የሚለው ክልል ነው፣ ሀገሬ ቂጥ እንጂ ታለንት የማያዩ እውራን ያሉበት ነው፣ ሀገሬ ተሳዳቢን ያነገሰ ነው። ሀገሬ በወንድነቱ ብቻ የበላዬ ሊሆን የሚፈልገው በችሎታ የምበልጠው አለቃዬ ነው። ሀገሬ ስቃይ ነው። ሀገሬ ፍትህ ቅንጦት ፣መቻል ሀጢያት፣ መናገር ሞት የሆነበት ነዉ።

ፈልጌ ነበር የቴዲን ኢትዮጲያን ሙዚቃ ስሰማ የሚተናነቀኝን የማንነት እምባ ዘፈኑ ሲያልቅ እንዳይተን። ወኔው አብሮኝ እንዲቆይ ፍቅሩ ኑሮዬ እንዲሆን። ፈልጌ ነበር የምቾት፣ የመረጋጋት፣ የመዝናት፣ የመከበር የመጠበቅ ስሜት፣ ፈልጌ ነበር “ሀገሬ ላይ እኮ ነኝ “ ብሎ የመኩራት ስሜት፣ የቤትነት ስሜት፣ ፈልጌ ነበር ሀገሬን መውደድ።

ለsafety የሰው ሀገር መመኘቴ ሴንስ እንዳይሰጥ ተመኝቼ ነበር፣ ለመታየት የሰው ቋንቋ ባልመርጥ ምኞቴ ነበር፣ ነብይነቴ በሀገሬ እንዲሆን ፈልጌ ነበር።

ግን ማነው የሚያየኝ? የሚሰማኝ? ከሰው የሚቆጥረኝ? የማያስፈራራኝ? የማይዝትብኝ? የሚያከብረኝ? ቦታ፣ እድል የሚሰጠኝ?

ኢትዮጲያ ነች? ሀገሬ ነች? አንተ ነህ? አንቺ ነሽ? እናንተ ናችሁ?

በሀገሬ እንደመጤ ኖርኩ፣ ተርቤ ዝም አልኩ፣ ሲስተም ናቀኝ፣ ህልሜን በላኝ፣ ሲስተም ደፈረኝ፣ ገለባውን አስክኖ ፍሬ ፍሬው ለቅሞ ጣለን።

ልወድሽ ሞክሬ ነበር፣ ኢትዮጲያ።

4 months ago
Brown Empire
4 months, 1 week ago

በጣም በቅርቡ “The dark web petter Scully story” የሚል ዶኪዩመንተሪ አይቼ የወንድ ልጅ ትልቁ መሳሪያው አብሮት የሚወለደው ብልቱ መሆኑን ተረዳሁ። ምናልባትም በተደጋጋሚ ስለሀይማኖት ጥቅም ሳስብ እውቀት እና አእምሯዊ ሞራልን ለመማር የሰው ልጅ ግዜ ስለሚወስድበት ገና ከስር መሰረቱ ጀምሮ ሀይማኖት ጠፍሮ ካላሳሰረው ተፈጥሮው የሰጠውን መሳሪያ እና ገደብ የለሽ የወሲብ ፍላጎት በመጠቀም እንስሳዊ ባህሪውን በማውጣት አረመኔ ይሆን ነበር ብዬ አሰብኩ። ሀይማኖተኛ ባልሆንም ስንቱን አደብ አስገዝቶ እንዳስቀመጠ ሳስብ ግን በሩብ እተነፍሳለሁ።

ምናልባት ሀይማኖትን የጀመረው ሰው የሰው ልጅ የገዛ ጭንቅላቱን ተጠቅሞ ቅዱስን እና አረመኔውን እስኪያውቅ ብዙዎች ይበደላሉ እና አረመኔውን እያለዘበ የሚያመጣ ከሰው አአእምሮ በላይ የማይታይ የሚፈራ ነገር አስፈላጊ ነው ብሎ አስቦ ይሆን ይሆናል። አላውቅም። ለትላቅ ሰዎችም እንደጆሮ ቆራጭ የሚስፈራሩበት ሲኦል ያስፈልጋቸዋል ብሎ?

ሆኖም ግን ልክ እና ጥፋት የሚለያዩበት መስመር እጅግ የቀጠነ በመሆኑ ዛሬም በሀይማኖት ከለላ ስር ብዙ አረመኔዎች ተከልለው መኖራቸው የማይካድ ሀቅ ነው። ለጥፋታቸው ጥቅስ እየመዘዙ፣ ለብልግናቸው መካሻ ቤተክርስቲያን እያሰሩ አሉ። ከነዛ ውስጥ ከሆኑትም ውስጥ ይህን ፅሁፍ ሲያነቡ ከአረመኔያዊ ድርጊቱ በላይ “ሀይማኖት” መነካቱ የሚያንገበግባቸው ዋናዎቹ ናቸው።

መደፈር ብቻውን በማንም ላይ በየትኛውም ፆታ ሲሆን ይቀፋል። በህፃናት ላይ ሲሆን ደግሞ ይበልጥ ያማል። ድፍረቱ ደግሞ ማሰቃየትንና ግድያን ሲጨምር የማይታሰብ ቁስል ይፈጥራል። ሰሞኑን በእዮሀ ሚዲያ ብቅ ብላ የሰባት አመት ልጇን አሰቃቂ የመደፈርና የግድያ ታሪክ ያጋራችው እናት ጥንካሬዋን ሳላደንቅ አልቀጥልም። ራሴን በሷ ቦታ አስቀምጬ ለሰአታት አሰብኩትና ልቤ ፍርስርስ ሲል አየሁት፣ ልጆቼ አንድ ነገር ቢሆኑ ነገንም ተስፋንም አይናቸውን ማየት የምፈልግ አይደለሁም። አደነቅኳት! በርግጥ መኖሯም አለ የሚባል አይደለም፣ ቅዝቃዜ አለበት። አቅፌያት ባለቀስኩ፣ ደረቴን በደቃሁ ተመኘሁ፣ ህመሟን ለመጋራት ቪዲዮውን ደጋግሜ አየሁት።

I did this when I watched “daisy’s destruction ” and “Junkos 44 days of hell” story. I torched myself for them. ባላቀልላቸውም፣ ጥቅም ባይኖረውም፣ ስቃያቸውን ባልመልሰውም፣ በቃ እንዲሁ ህይወት እንደናቀቻቸው እንዳልናቅኳቸው እንዲሰማቸው በመፈለግ አለቅስላቸዋለሁ።

በህይወት እስካለን ደስታ ማጋባት፣ መዋደድ እና በህይወታችን የሆነው ሁሉ አጣጥመን መኖር እንዳለብን ባምንም፣ ልክ እንደተመረጠ እና እግዚያቤር እንዳዳላለት ወይንም እድለኛ እንደሆነ አድርጎ የሚያወራ ሰው ከፋራ እና ከቲን ኤጀር በላይ የምጠላው ለዚህ ነው። ምክንያቱም እቺስ ህፃን ልጅ እግዜር ስለማይወዳት ይሆን? እናትስ ምን ብትበድል? ቢዚህ ሰቆቃ ውስጥ ያለፉት?

Everything is a coincidence የምለውም ለዚህ ነው። አጋጣሚ ይበድልሀል፣ አጋጣሚ አደላድሎ ያኖርሀል፣ we're just a coincidence.
I have nothing against deluu, but when someone uses their deluu to express gratitude for their superior life circumstances relative to those who are in despair, that's when I start to detest you and your deluu along the way.

እንስሳ እና ልጅ የሚማታ ሰውም የማልወደው ለዚህ ነው፣ ከተናገርክ በምትናገረው ልክ የሚመልስልህን ይሁን፣ ከመታሽ መልሳ ልትመታሽ አቅም ያላትን ይሁን። አቅመ ቢስን የሚያጠቃ ወኔ ቢስ ክፉ አረመኔ ነው። እሱ ነው ዲያብሎስ ማለት። ወንድ ሆነህ ወንድ የማትደፍረው ሀጢያት ስለሆነ ሀይማኖትህ ይዞህ አይደለም። ሰላሳ ሁለት ጥርስህን ሆድህ ስለሚከትልህ ነው። ህፃናት ወንድን የምትደፍረውም ሀጢያት ስላልሆነ አይደለም፣ አቅመቢስ ስለሆነ ስለምትችለው ነው።

ይሄም ሆኖ አካፋዉን አካፋ ብለን ስንነሳ፣ እንባችንን ተቆጣጣሪ፣ ህመማችንን መዛኝ፣ ድምፃችንን ገምጋሚ፣ ምላሳችንን ረጋጭ ብዙ ነው። ፌምኒዝም አይደለም ይላሉ ሰው መሆን በቂ ነው ለመፍትሄው ይላሉ፣ እስኪ እንስማው ከ በላይ በቀለ ወያ እና ከፊዩና ስድድብ በላይ ሲያነጋግራችሁ? በሉ እንይ እስኪ?

በኛ ቦታ መሆን ምን እንደሚመስል ማወቅ እንደሚከብዳችሁ የሚገባኝ በናንተ ቦታ መውረድ እንደሚከብደኝ ሳስብ ነው። የሚዳቆዋን ቦታ አታውቁትም ፣ ስትይዟትም ትበሏታላችሁ እንጂ ስትሮጥ ስትሸሽ እንዳልኖረች “ደከመሽ?” ብላችሁ እንኳ አትሏትም።

ከሚዳቋ እና ከአቦሸማኔ መናገር ቢችሉ ለመብቱ የሚከራከረው እንስሳ ማን ይመስላችሁዋል? አቦሸማኔው ምን ጎሎበት፣ ማን ገልማጭ ማን አሽቆጭቋጭ ኖሮበት አትሉም?

ዲክሽነሪ ላይ ሴት የሚለውን ቃል ትርጏሜ “ምግብ” ብለው እንዳይቀይሩት የትኛውን ፈጣሪ እንደፈሩ እንጃ!

በመጨረሻ ልል የምፈልገው ነገር እናንተ ሴቶች?! አንዱን ፕሬደተር አውጥተን ስናሰጣዉ ያልተነከሽው ታቅፊዋለሽ፣ የማይገባውን ሌላ እድል ትሰጪዋለሽ፣ ሁላችንም በምናውቀው ምሳሌ ልስጥ ክሪስብራውን ሪሀናን ካናጋት በሁዋላ ዛሬም ድረስ ለሱ የሚሰለፉት ሴቶች ብዙ ናቸው፣ ሻያ ላባፍን ከዛ ሁሉ ቫዮለንስ እና ክስ በሁዋላ ዴት የሚያደርጉት ሴቶች አሁንም አሉ።
ሁለት ሴት በተከታታይ ሰአት በአንድ ቀን ውስጥ ደፍሮ ለገደለ ወጣት መልከመልካም ስለሆነ ብቻ ፍርድ ቤት እየተግተለተሉ ሄደው የሚያዩት ሴቶች ብዙ ነበሩ።

ከዚሁ ከሀገራችን ኬዝ እንኳ የምንረዳው ይሄ ሰው በዚህ አሰቃቂ መንገድ ህፃኗን በማህፀኗም በፊንጢጣዋም ደፍሮ፣ በአፏ አሸዋ ከትቶ፣ አንገቷን አንቆ የአምስት ጣቱ ምልክት ሰርስሯት ገብቶ አንገቷ ላይ ተገኝቶ፣ ምላሷ ተጎልጉሎ መግባት አቅቶት ተገኝታ እንኳን ሌሎች ወንዶች እና ህግ ላይ ያሉ ወንድ አካላት፣ ከፖሊስ እስከ አቃቢ ህግ፣ ከሀኪም እስከ ጎረቤት በወንድነታቸው ብቻ እንዲህ ያለውን አረመኔነት ይሸፋፈናሉ! ምን ይሆን ከዚህ የሚገባሽ?

እኛስ? በተገኘው ሚዲያ፣ በተገኘው ዘርፍ፣ በተገኘው አጀንዳ፣ ከተራ እስከትልቁ ቁምነገር፣ ላንደጋገፍ ስንገፈታተር፣ አንዷን አቁስሎ ለመጣ ሌላችን አልጋችንን እየገለጥን፣ አራጅ እየወደድን ታራጅ እያገለልልን፣ የስቃያችን ተባባሪ እና ረዳት ተዋናይ ሆነን አለን። ልክ ክቡ እንደተበጠሰ መሀረቤን ያያችሁ እርስ በእርስ ለመያያዝ እና ለመደጋገፍ እጅ አጥሮን እንደተጠቃን አለን።

ራስሽን ጠብቂ፣ እህትሽን አዳምጪ ጆሮ ስጪ፣ ዞሮ ዞሮ እህትሽ ናት የምትደርስልሽ፣ የምትረዳሽ፣ አይዞሽ የምትልሽ። ከዚህ ኬዝ እንኳን የምንማረው አንዲት ሴት ፖሊስ ብቻ ነበረች የዚህች እናት ጉዳቷ ጉዳት መስሏት ከሙያዋ ባለፈ ሰዋዊ ርህራሄ ያሳየቻት። እህታዊ መከንከን የተከነከነችላት።

እሱማ፣ ገዳይማ፣ ደፋሪማ በማን አለብኝነት ወገን ገድሎ ወገን ሊጠብቅ እቺን ልጅ በገደለበት ሶስተኛ ቀን ነው መሳሪያ አንስቶ ፋኖን ተቀላቅሎ ሊያግዝ የወጣው! እስኪ ለዚህ ኮሜዲያን ያንን ተመላሽ 2 ሚሊየን ብር ሸልሙት!

I chose violence! Eye for an eye!

4 months, 1 week ago
Brown Empire
4 months, 2 weeks ago
Brown Empire
4 months, 2 weeks ago
Brown Empire
4 months, 2 weeks ago
Brown Empire
We recommend to visit

Community chat: https://t.me/hamster_kombat_chat_2

Twitter: x.com/hamster_kombat

YouTube: https://www.youtube.com/@HamsterKombat_Official

Bot: https://t.me/hamster_kombat_bot
Game: https://t.me/hamster_kombat_bot/

Last updated 3 months, 1 week ago

Your easy, fun crypto trading app for buying and trading any crypto on the market

Last updated 3 months ago

Turn your endless taps into a financial tool.
Join @tapswap_bot


Collaboration - @taping_Guru

Last updated 3 days, 5 hours ago