በዝሙት አንዘምን 🚫

Description
የተለያዩ ባለንበት ተጨባጭ በሆኑ ጉዳዮች ላይ እንመካከር እስካሁን በጣም ደስ የሚሉ አስተማሪ ፁሁፎችን አቅርበናል ቻናሉ ውስጥ ገብተው ሁሉንም ያምብቡ።
ከሃራም መንገድ(ፍቅር)መውጣት ለምትፈልጉ
በውስጥ መስመር እንመካከር
👉 @Jezakellah
ሙሂዲን ሰኢድ

ጆይን ግሩፕ👉 @bezemut_anzemn

كنتم خير أمة أخرجت للناس تأمرون
بالمعروف و تنهون عن المنكر
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 Monate her

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 Monate, 2 Wochen her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 Monate, 2 Wochen her

2 months ago

⚠️ እንንቃ ከዝሙት የባሰ ነው።❗️

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

እንትናን አወቃችሁት? እናቱጋ ዝሙት ሰራ!
.
.
ብላችሁ አፋችሁን ይዛችሁ ትደነግጣላችሁ አይደል።? ነገር ግን እገሌ በአላህ ላይ አሻረከ(ከፈረ ካደ)ብላችሁ ምንም አይመስለንም። ይሄ ወላሂ የሽርክን ከባድነት አለማወቃችን ነው።❗️

እናትን ከመድፈር በላይ ሽርክ ከባድ ወንጀል ነው።! እያሻረክን ከሞትን ተስፋ የለንም። ዘላለም ጀሃነም ላይ እንበሰብሳለን። አላህን በማስረጃ እንወቀው። በተለይ ከታች ያሉትን ርእሶች በደምብ ተረድተን ልናምንባቸው ልንሰራባቸው ይገባል። ካልሆነ ከከሳሪዎች ከእድለ ቢሶች እንሆናለን። ስማችን ሙስሊም ስልሆነ ብቻ ጀነት አይገባም።

የትኞቹን እና የት እናግኛቸው ካላችሁኝ ከታች ቻናሉ ላይ ሁሉንም ማግኘት ትችላላችሁ ተረግግተን ሁሉንም እናንባቸው ከቁርአንና ከትክክለኛ ሃዲሶች የተውጣጡ ናቸው።
*🌏 አጥብቀን እንያዛቸው የጀነት ዋስትናችን ናቸው። ርእሶችም፦
.
አላህ ለምን ፈጠረን?
.ኢባዳ ወይም አምልኮ ምንድን ነው?
.አላህን እንዴት ነው የምናመልከው?
.አላህን የምናመልከው በፍርሃት እና በተስፋ(በመከጀል)ላይ ሁነን ነዉን?
.በኢባደህ/አምልኮ ላይ?
.ኢህሳን(ማሳመር)ማለት ምን ማለት ነው ?
.አላህ መልዕክተኞችን(ሩሱሎችን) ለምድነው የላከው ?
.ተውሂድ አርረብ ምንድነው?”(አላህን በጌትነቱ ብቸኛ ማድረግ ማላት ምን ማለት ነው)?
.ተውሂድ አል-ኡሉህያ(በአምልኮ ብቸኛ ማድረግ) ምንድነው?
.ተውሂድ ሲፋቲ-አልላሂ ወአስማኢሂ(አላህን በስሞቹና በባህሪው ብቸኛ ማድረግ ማለት ምን ማለት ነው)?
. አላህ የት ነው ያለው ?
. አላህ ከኛ-ጋር ነውን ?
. የተውሂድ ጥቅሙ ምንድነው ?
. ስራ(ኢባዳ)ተቀባይነት እንዲኖረው የሚያስገልጉ መስፈርቶች እነማን ናቸው ?
.ትልቁ ሽርክ
?
.
የትልቁ ሽርክ አይነቶች?
.
ትልቁ ሽርክና አይነቶቹ?
.መቃረብና ሸፈዓን/ምልጃን መፈለግ?
.ጅሀድ መወዳጀትና ሁክሙ?
.በቁርኣንና በሃዲስ መስራት?
.ሱናና ቢድዓ በዲን ላይ ?
.ተቀበይነት ያለው ዱአ?
.አቂዳ(የእስልምና እምነት)

👉 ይቀጥላሉ*

🔥ተውሂድን ላላረጋገጠና ሽርክ ላይ ለተዘፈቀ ስሙ ይሄን የአላህ ዛቻ👇

إِنَّ اللَّهَ لَا يَغْفِرُ أَن يُشْرَكَ بِهِ وَيَغْفِرُ مَا دُونَ ذَٰلِكَ لِمَن يَشَاءُ ۚ وَمَن يُشْرِكْ بِاللَّهِ فَقَدِ افْتَرَىٰ إِثْمًا عَظِيمًا
አላህ በእርሱ ማጋራትን በፍጹም አይምርም፡፡ ከዚህ ሌላ ያለውንም(ኀጢአት)ለሚሻው ሰው ይምራል፡፡ በአላህም የሚያጋራ ሰው ታላቅን ኀጢአት በእርግጥ ቀጠፈ፡፡

🎁 እነዚያ ተውሂዳቸውን አረጋግጠው ከሽርክ ለጠሩትና መልካምን እየሰሩ ለፅኑ ደሞ በዚህ መልኩ አብስሯቸዋል።
وَالَّذِينَ آمَنُوا وَعَمِلُوا الصَّالِحَاتِ أُولَٰئِكَ أَصْحَابُ الْجَنَّةِ ۖ هُمْ فِيهَا خَالِدُونَ
እነዚያም ያመኑት በጎ ሥራዎችንም የሠሩት እነዚያ የጀነት ጓዶች ናቸው፡፡ እነርሱ በውስጧ ዘላለም ዘውታሪዎች ናቸው።

🔋 ከላይ የላኩላችሁን ርእሶች ከታች ባለው አዲሱ ቻናላችን ገብታችሁ ማግኘት ትችላላችሁ። ቻናሉንም ልናሳድገው ይገባል ለጓደኞቻችን ሁሉ ሼር እናድርግላቸው።
🚨🚨🚨🚨ሼር Share

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ

🎁 የቀደምቶች መንገድ👇👇👇
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah
https://t.me/ahlul_jenah
👆👆 ጆይን & ሼር 👆👆

2 months ago

⚠️ ዝሙተኛ ናት

🔥 ስሚኝ እህቴ አላህ ይዘንልሽና
ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

በትክክለኛ ሃዲስ ሽቶ ተቀብታ የምትወጣ ሴት ዝሙተኛ ናት ብለዋል ውዱ ነብይሽ(ሰለላሁ ዓለይሂ ወሰለም)ያውም ደጋግመው ነው የተናገሩት።! ግን አስተውለሻል የወንጀሉን ክብደት እህቴ።? ዛኒያ(ዝሙተኛ)ናት ነው የተባለው። ይህ በሆነበት ሁኔታ ብዙ እህቶች ይሄን ነገር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ ሲዳፈሩ እያየን ነው። ምን ነክቶሽ ነው እህቴ? ለምን ነው አመፅን የዘመናዊነት መገለጫ ያደረግሽው።?

አስተውሉ ውድ እህቶቸ ሽቶ ማለት የግድ የሚነፋው ሽቶ ብቻ አይደለም። ዶድራንተም ይሁን፣ ለፀጉርሽ የተጠቀምሽው የቅባት ወይም የመታጠቢያው ሻምፖ ሽታ ካለው ያው ነው። አዳርቀሽ ሽታውን አጥፍተሽ ልትወጪ ይገባል። እንዲሁም ሎሽንም ወይም ሽታ ያለው ግሪስሊም ይሁን ሌሎችም ሽታ ያላቸው ምንም አይንት ነገር ይሁን ሃዲሱ ውስጥ ይገባሉ። በተለይ እንደነዚህ አይነት ሰዎች የማያስታውሏቸው ሽታዎች ትራንስፖርት ወይም ታክሲ ቦታዎች ላይ ደምቀው ሲሸቱ ይስተዋላሉ። እንዲሁም ልብስሽን ምታስቀምጭበት ሳጥን ወይም ሻንጣ ሽታ አለመኖሩን አረጋግጭ። ብዙ ግዜ ልብሱ ተቀምጦ ሲቆይ ሌላ ሽታ ያመጣል በማለት ልብሱ ሚቀመጥበት ቦታ ላይ ሽቶ የሚያስቀምጡ ወይም ሻንጣውን ሽቶ የሚረጩ አሉ። ስለዚህ እህቴ ሆይ ጥንቃቄ አድርጊ እስካሁን በዚህ ስህተት ላይ ካለሽ ከባድ ወንጀል ስለሆነ ተፀፅተሽ ትክክለኛ ተውበት ልታደርጊ ይገባል። ከዚህ በኋላም ላለውም ጥንቃቄ እናድርግ። ለግዚያዊ ስሜት ብለሽ የዝሙተኞችን ወንጀል አትሸከሚ🔥

🚨🚨🚨 Share ሼር
ከወንድማችሁ (@jezakellah)

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል
  ጆይን👇👇👇& ሼር 👍
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

2 months ago

ውለታ ቢስ አቱኚ!

ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ
ውዷ እህቴ ከላይ ፀጉርሽ ላይ ጣል ያደረግሽው ልብስ ወይም ሂጃብ ሙስሊምነትሽን የሚገልፅ ታፔላ ነው። ያን ከላይ አድርገሽ ከታች ደግሞ ሱሪና የተጠባበቀ እንዲሁም አጭር ጉርድና ቀሚስ ለብሰሽ ስትታይ፣ ተቀባብተሽና ተገላልጠሽ ሲያዩሽ፣ ወይም ሆቴልና ጭፈራ ቤት ሲያዩሽ፣ ሚዲያ ላይ ወተሽ ስትጨፍሪ፣ እንዲሁም ወንድጋ ስትዞሪና ስትገባበዢ፣ ተቃቅፈሽ ሰዎች ሲያዩሽ ስላንች አስተዳድግ ሳይሆን የሚያስቡት ሙስሊም መሆንሽን ነው።! በዛም ምክንያት እስልምናሽ እንዲሰደብ ሰበብ ሆንሽ ማለት ነው። ታዲያ ይገባዋል መሰደብ ባንች ምክንያት።? በርግጥ የፈለገ ያክል ዲንሽን አጥብቀሽ ብትይዢና አለባበስ ቢስተካከልም ኢስላም ላንቺ የዋለውን ውለታ ልትከፍይው አትችይም። ነገር ግን እስልምናሽ በጥሩ እንዲነሳ ስበብ መሆን ባትችይ እንኳ እንዴት ለመሰደቡ ሰበብ ትሆኛለሽ።???
ሲሆን ዲንሽን ተምረሽ በዙርያሽን ያለውን ጨለማ(ጅህልና/ሽርክ ሃራም)ነገሮችን በማጥፋት ዲንሽን ከፍ ልታደርጊው ነው የሚገባው። ዲናችን ብዙ ጠንካራ እንስቶች ያስፍልጉታል ብዙዎች ፅናትን አተው ተንሸራተው በስሜት ታውረዋልና።
 ሲቀጥል በዚህ ሁኔታሽ ደስተኛ ካልሆንሽ ለምን መዘውተሩት መረጥሽ።? ለምን ቶሎ አልቅሰሽ መመለስን ዘነጋሽ።? ለምን ነው እንዲህ ለሰው ምትጨነቂው የሰዎች ሙገሳና አድናቆት ደስታን እንደማይሰጥሽ አይሽው አይደል።? ስለዚህ ከስካርሽ ንቂ ሰዎች ከላይ ለሚያዩት ነገር መጨነቁን ታይውና ሁሌም ልብሽን ለሚያየው ጌታሽ ተጨነቂና ራስሽን አስተካክይ ያኔ ከዚህ በፊት ልትገልጭው ማትችይውን ደስታ ታገኛለሽ። አዎ! ያኔ ሰዎች መጡም አልመጡም ሄዱም አልሄዱም እንዲሁም ዱንያዊ ብልጭልጭ ነገሮችም አያስጨንቅሽም ልብሽ በአላህ ፍቅር ቢዚ ይሆናልና። ወደ አላህ እንቃረብ፣ አላህንም ሳናውቀው እንዳንሞት፣ ትክክለኛዋንም ደስታ ሳናገኛት እንዳንሞት

Share ሼር Share

ወንድማችሁ ሙሂ @jezakellah

ይህ በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ነው ይቀላቀሉን ያተርፉበታል 👇👇👇 👍 👍
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

2 months, 1 week ago

ድብቁ ካንሰር!🔥

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላህ
ቢስሚላህ አልሃምዱሊላህ

ውድ ባተሰቦች ኢንሻ አላህ በአዲስ ወሳኝ ርእስ የምንመካከር ይሆናል እሱም ድብቅ የሆነ ካንሰር ነው በሚገባንም አንጋገር ሃሜትና ወሬ ማመላለለስ ናችው በማህበረሰባችን ላይ ተስፋፍቶ ያሉ ከባድ መዘዝ ያለው በሽታ ነው። በዚህ በሽታ ሰበብ ወንድም ከወንድሙ ጋር እህትም ክእህት ጋር ባል ከሚስቱ ጋር ቤተሰብ ከቤተሰብ ጋር ተለያይተው ይገኛሉ ከዛም አልፎ እስከ ነፍስ ማጥፋት ድረስ የደረሱ አሉ። ወንጀልነቱም እጅግ በጣም የከፋ ነው ሶላታችንን ፆማችንን ኢባዳዎቻችንን የሚያጠፋብን ይሆነ ከባድ ወንጀል ነው። በትንሹ ርእሱን ለማስተወዋውቅ ያክል ይሄን ካልኳችሁ በቂ ነው ኢንሻ አላህ አንገብጋቢም ርእስ ስልሆነ በክፍል ክፋፍየ እለቅላችኋለሁ ረዘም ያለ ክፍል ሊኖረው ይችላል። ክፍል አንድ ማታ ይለቀቃል እንደተለመደው ተረጋግተን በማንበብ ራሳችንን ፈትሽን ለማስተካከል እንሞክር እንዲሁም በቻልነው ሼር ልናደርገው ይገባል። ባረከላሁ ፊኩም

ወንድማችሁ muhiden
@jezakellah

ይህ በዝሙት አንዘምም የቴሌግራም ቻናል ነው የተለያዩ ባለንበት ተጭባጭ ይሆኑ ርእሶችን የምንመካከርበት ቻናል ነው። ተቀላቅላችሁ ሼር ማድረግ አትርሱ።
በኸይር ነገር ያመላከተ የሰሪውን ያክል አጅር ያገኛል ታዲያ አኼራዊ ንግድ ላይ የሚሳተፍ የለም?
ጆይን & ሼር
👇👇👇👇👇
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina
ቻናል 👆👆👆👆

እንዲሁም ከታች ባለው ግሩፕ በመግባት ስልክልችን ላይ ያሉትን ሰዎች በቀላሉ አድ በማድረግ ሃቅ እንዲዳረስ ሰበቡን እናድርስ
👇👇👇👇 ግሩፕ
https://t.me/bezemut_anzemn
https://t.me/bezemut_anzemn
ጆይን አድ አድ አድ 👆

2 months, 1 week ago

ወንድሜ ሆይ ብር ወንድም አይሆንም እናትም፣ አባትም፣ እህትም አይሆንም ለቤተሰቦችህና ለተቸገሩት ብር ለማውጣት አትሰስት።! ስጥ አሰጣጥህን አይቶ ይሰጥሃል። አከፋፋዩ ከላይ ነው።!
ሰርቸኮ ነው ያገኘሁት እያልክ አትኮፈስ ለማግኘትህ ሰብበ ማድረስህ ብቻ በቂ አይደለም አላህ ሲፍቅድ ነው የምታገኘው። በጅህ የያስከው ገንዘብ ፈተና መሆኑን አትርሳ። ከጌታህም እንዳያርቅህ ጥንቃቄ አድርግ። ከፈንህም ኪስ እንደሌለው አትርሳ። እንደሞትክ ሞባይልህን፣ ሃብትህን ይቀባበሉታል፣ አንተ ባካበትከው ሃብት እንኳ ለአባቴ፣ ለወንድሜ ሶደቃ የሚሆነው የውሃ ጉድጓድ ላስቆፍር ብሎ የሚያስብ አታገኝም።!

ከዱንያ ስካር ንቃ! ትሞታለህ ለማንም ዘላለም መኖርን አልተሰጠውም።!መሞቴ አይቀርም ስሞት ከኔጋር ምንድን ነው ወደቀብሬ አብሮኝ የሚሄደው እያልን ራሳችንን እንጠይቅ።

💐 ሼር & ጆይን
የሙሂ ማስታወሻዎች 👇👍
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

2 months, 1 week ago

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላህ ውድ በዝሙት አንዘምን ቤተሰቦች ወንድማችሁ ሙሂዲን ነኝ አንድ መልካም ስራ ላካፍላችሁ ያው ሚዲያ አላህ የሰጠን ትልቅ ፀጋ ነው ለመልካም ነገር ልንጠቀምበት ይገባልና ከኔጋ ያለውን ለናንተም ላካፍላችሁ ተጋግዘን የምንችለውን እናድርግ። ወደ ጉዳዩ ስገባ አንድ እህት በጣም ተቸግረው እንዳሉና እንዳስተባብርላቸው ጠይቃኝ ነበር ያው ጊዜውን እንደምታውቁት ብዙ ሰው በችግር ስም ሊያጭበረብር ይችላልና እኔም ሳላጣራ በቀጥታ ወደናንተ ማስተላለፍ አልፍለኩም ነበርና ቦታው ድረስ ለመሄድና ለማየት ሞክሪያለሁ ዛሬ ከዙሁር በፊት ወጥቸ አሁን ከመሸ ነው ወደ ሰፈር የገባሁት። ከቤተል መገናኛ ከመገናኛ ጐሮ ከጐሮ ወረ ገኑ የሚባል ሰፍር ረጅም የግር ጉዞ በጭቃ ተጉዤ ነው ቤታቸውን ያገኘሁት። ቤት ገብቸም አባትየውን አገኘሁት ደስ አላቸው። ያለውንም ሁኔታ አጫወተኝ የሱም አባት አለ ከ100 አመት በላይ ሁኖታል ትንሽ አቅሉን አመም ያደርገዋል ያስቸግራል ባጭሩ ቤተሰቦቹ ወደ7 ይሆናሉ እኔም እስከ ዘጠኝ ሰአት እነሱጋ ተጫውቸ ተመለስኩ እና ሌላው ቀርቶ የ4 ወር የቤት ኪራይ አልከፍሉም። ባጭሩ ይሄን ይመስላል ልጀቱ የፃፍችልኝንና አካውንት ቁጥራቸውን ኢንሻ አላህ ማታ እለቅላችኋለሁ።

በዚሁ አጋጣሚ በተለይ አዲስ አበባ ያላችሁ በችግር ላይ ያላችሁ ቤተሰብ ካላችሁ አናግሩኝ ቤት መጥቸ በማየት ለማስተባበር እሞክራለሁ ኢንሻ አላህ። በዱአም እናግዛቸው።

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ
@jezakellah

2 months, 2 weeks ago

ካለፉት እንማር ክፍል ስድስት(6)

አብዘሃኞችን ብትከተይ ከአላህ መንገድ ያስወጡሻል❗️

እናውቃለን ለትምህርት ብለው ደብተራቸውንና ዩንፎርማቸው ለብሰው የሃራም ጓደኛቸውጋ ዶርማቸው ድረስ የሚሄዱና እንደፍለጉ የሙሄነ እንዳሉ ነገር ግን መድረሳ ብላ ወታ ኪታቧን ይዛ አለባበሷን አስተካክላ ያልተፈቀደላት ወንድጋ ስትሄድ ማየት በጣም የሚያም ነገር ነው። እንዴት ይሄ ይሆናል!? አላህ እያየን መሆኑን እንኳ ብንዘነጋው ህሊናችን የት ሄደብን!? ለምን ነው ጊዚያዊ ደስታን የመረጥነው።!?

አንተስ በዲን ስም ቀርበህ እህቶችን ልትጫወትባቸው ስታስብ ህሊናህ የት ሂዶብህ ነው።!?

ከሚያጋጥሙኝ ከብዙ ትንሹን ላጫውታችሁ፦ በቅርቡ አንድ እህት ቴሌግራም ላይ ላግባሽ የሚለኝ ልጅ አለ አላውቀውም ያው በቴሌግራም ነው የማውቀው እኔም እውነቱን ከሆነ ብየ እያወራሁት ነው በአካል ላግኝሽና እናውራበት ብሎኝ እሽ ብየው ልንገናኝ ነው አለችኝ። አስቡት ስለ ልጁ ምንም ምታወቀው ነገር የለም ግን ላግኝሽ ስላላት ብቻ ልታገኘው ነው ያሰበችው። ብዙዎችም በዚህ መንገድ ላይ ናቸው ትንሽ ጊዜ በፁሁፍ ያወራሉ ከዛ ወድ ስልክ ይቀየራል ከዛ ቀጥታ በአካል ይቀጣጠራሉ ከዛም ቆሻሻ ከሆነው ዝሙት ላይ ይወድቃሉ። ያው የሃራም መንገድ መጨረሻው ምን ሊሆን እንደሚችልም ሁላችንም እናውቀዋለን።

ያለንምበን ጊዜ ሁላችንም እናውቀዋለን አይደለም ይማናውቀው ያወቅነው ሰው እንኳ መፀሃፍ ለመስጠት በሚል እየተገናኙ ማፍዘዣ መድሃኒት እያስነኳቸው ራሳቸውን የሚያገኙት ሆቴል ላይ ክብራቸውን አጠው ነው።

ወድ ልጅቱ ስንመለስ እኔም በዚህ መንገድ ያሉትን ወንዶች ባህሪ በደምብ ስለማውቀው እሽ ተረጋጊ ልጁን ከማግኘትሽ በፊት እኔጋ ትንሽ እንመካከርበት ትክክለኛ ትዳር ፍላጊ ከሆነ የምንለውን ያደርጋል አልኳት እሽ አለችኝ 

እኔም ለወደፊትም በደምብ ትምህርት እንዲሆናትና እንድትማርበት ነበር የፈለኩት ከዛም ልጁን አንቺ ከማግኘትሽ በፊት አንድ ወንድም አለ እኔን ከማግኘትህ በፊት እሱን በአካል አውራው በይው አልኳት። እኔ ሁለቶችንም አላውቃቸውም ግን ትዳር ፍላጊ ከሆነ ለትዳርም የሚሆናት ልጅ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው እንዳገኘው ንገሪው ያልኳት። ከዛም ልጁ በጭራሽ መጀመሪያ አንችን ሳላገኝሽ እሱን አላገኘውም እንዴት እንደዚህ ትሆኛለሽ ብዙ ነገር አውርተን ማለት ጀመረ። እኔም በድጋሚ ችግር የለውም ይሄኮ ቀላል ነገር ነው ለትዳር የምትፍልገኝ ከሆነ አግኘውና አውራው በይው አልኳት እሱ ግን በጭራሽ አልሰማም ከፍለግሽ ይቅር አለ። ከዛም እኔም ልጅቱ እንዲገባት ነበር የፍለኩት አይሽው አይደል ያለውን እውነታ ልጁ ለትዳር ሳይሆን ለስሜቱ ነው የሚፍልግሽ ትክክለኛ ትዳር ፈላጊ ቢሆን ይስማማ ነበር አልኳት። እሷም ምንም አላለችኝም በጣም አመሰግናለሁ እውነታውን በራሴ አይን እንዳየው ስላደረከኝ አለችኝ።❗️ከዛም ብሎክ አድርጋው ወጣች።

እና ውድ እህቶች በዚህ መንገድ ያለው እውነታ ይሄ ነው። ብዙዎችም በዚህ ሰበብ ነው በቀላሉ ወደዚና እየገቡ ያሉት። እህቶችም ሽማግሌ ላክ ሲሏቸው ወንዶችም እንዴት እኔና እንቺ በደምብ ሳንግባባ ወደ ቤተሰብ ይሄዳል ብለው ምክንያት ይደረድራሉ። ይሄ ይውሸት ማታለያ ቃል ነው። ሲጀመር ሽማግሌም ስለላከ ታገቢዋለሽ ማለት አይደለም ነገር ግን የመጀመሪያውን ፍተና ስላለፈ ከዛ በኋላ ደግሞ ቤተሰብ አውቆት ሸሪአ ባስቀመጠው ገደብ አውርታችሁ የማይሆንም ከሆነ ይቀራል። ስለ ልጁ ተጣርቶ የሚሆንም ከሆነ ኒካሁ ይታሰራል ማለት ነው።

ውድ እህቶች ንቁ ካለፉት እንማር አብዘሃኞቹ ከአላህ መንገድ ሊያስወጧችሁ ነው የሚፈልጉት። ካልነቃሽና ዲንሽን ባግባቡ ካላወቅሽ ልክ እንደብዙዎቹ አንቺም የማንም መዝናኛና መጫወቻ ነው ምትሆኝው። ወላሁ አዕለም።

🚨ሁላችንም ለጓደኞቻችን ሼር Share እናድርገው!

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ @jezakellah

በዝሙት አንዘምን የቴሌግራም ቻናል ይቀላቀሉን ያተርፉበታል
👇👇 👇👇👇 👍
https://t.me/latekrebu_zina
https://t.me/latekrebu_zina

2 months, 2 weeks ago

አላህ ሆይ ልቤ ውስጥ ለአማኞች ጥላቻ እንዲኖር አታድርግብኝ! ሁሉንም አማኞች እንድወድ እንዳከብር እንዳዝንላቸው አድርገኝ፣ ያጠፋም አማኝ ካለ እንድመክር ወፍቀኝ!!

የሙሂ ማስታወሻዎች 👇
https://t.me/sun_flowere
https://t.me/sun_flowere

2 months, 2 weeks ago

በዝሙት አንዘምን ቻሌንጅ❗️

ከዚህ በፊት ያልተሳተፍን እንቀላቀል እናተርፍበታለን!

አሰላሙአለይኩም ወረህመቱላህ
ቢስሙላህ አልሃምዱሊላህ

ውድ በዝሙት አንዘምን ባተሰቦች ከዚህ በፊት አላማዎቻችንን በትንሹም ቢሆን ለማሳካት በሚል ሁሉም እንደየ ሃቅሙ እንዲሳተፍ ከሃምሳ ብር ጀምሮ በየ ወሩ መዋጮ ጀምረን ነበር። አልሃምዱሊላህ እንደታሰበው ባይሆንም በትንሹ መንቀሳቀስ ችሏል። የተጠበቀው በብዙ ሺዎች ይመዘገባሉ ተብሎ ነበር ነገር ግን ከ60 በላይ ሰው አልተመዘገበም። አንዳንድ ስለዚህ ቻናል ስራዎች የሚያውቁ ከላይ ደረሰኙጋ እንዳያችሁት በወር እስከ 500 ብር ለማስገባት የነየቱ አሉ ትንሽ ቢሆኑም። እንዲሁም የአመቱንና የስድስት ወሩን ባንድ ያስገቡ እህት ወንድሞች አሉ የነሱም ተጠራቅሞ እስካሁን 7ሺ ብር በጋራ በተከፈተው አካውንት ገቢ ሁኗል። ነገር ግን ይሄ በየ ወሩ የሚገባ ብር አይደለም። አብዘሃኛው በወር 50እና መቶ ብር ነው የተመዘገበው። ያው ሁላችንም እንደምናውቀው ለኸይር ነገር ሲሆን ሸይጧን እንዳንሳተፍ ስለሚያደርገን እንጂ አንድ ሰው አይደለም በወር መቶ በር ከዛም በላይ ዲኑን ለማስፋፍት ይከብደዋል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። እኔም አንዴ ከተናገርኩ በኋላ ዝም ያልኩት እንዳላሰለቻችሁ ብየ በመፍራት ነው። ነገር ግን ከቀን ወደቀን ፍተናዎች እየጨመሩ ስለሆነ ዝምታው መፍትሄ ሁኖ አልታየኝም እና በድጋሚ ለዚህ ትልቅ ኸይር ስራ እንሳተፍ ስል ጥሪውን አቀርብላችኋለሁ።

ለጊዜው የታሰበው አላማ ተለቅ ያለ ኮፒ ማሽን ተገዝቶ በወጣቱ ጉዳይ በወረቀት እንዲበተኑ ያዘጋጀኋቸውን አንገብጋቢ ትምህርቶች በየ ትምህርት ቤቱ ተደራሽ ማድረግ ነው። በየ ትምህርት ቤቱ ያለውን ፈተና ሁላችንም እናውቀዋለን። አልሃምዱሊላህ እነዚህ ወረቀቶች ደግሞ ከዚህ በፊትም በትንሹ መበትን እንደቻሉት ብዙ እህት ወንድሞች ተጠቅመውባቸዋል። ወደቻናሉን ተቀላቅለው ሌሎችንም ትምህርቶች እንዲያገኙና ህይወታቸው እንዱያስተካሉ ሰበብ ሁነዋል። ነገር ግን ሌሎችም አንገብጋቢ ይሆኑ ብዙ ትምህርቶችን በማያሰልች መልኩ በማዘጋጀት በየ ሃገሩ ላሉት ለሀይስኩል ተማሪዎችና የዩንቨርስቲ ተማሪዎች ልናዳርስ ይገባል። የታሰበውም አላማ ይሄ ነው። ለዚህ ደግሞ ፍላጐቱ ካለን እኛ እንበቃለን ብየ አስባለሁ ስለዚህ በወር ከመቶ ብር ጀምረን በየ ወሩ በማዋጣት ማጠራቀም ብንችል ባጭር ጊዜ ውስጥ ይሄንን ስራ በመስራት ትልቅ ተፅእኖ መፍጠር እንችላለን። ስለዚህ ሁላችንም ንያችንን በማስተካከል እንሳተፍ ነገ አላህ ዘንድ እጥፍ ድርብ ሁኖ እናገኘዋለን፣ እንዲሁም ዱንያ ላይ ገንዘባችንም በረካ እንዲኖረው ሰበብ ያደርግልናል።

ለጊዜው የ500 ሰው የምዘገባ ቻሌንጅ ነው ያለን። ወላሂ ይሄ ትልቅ የሆነ አኼራዊ ትርፍ ነው እንደ ቀልድ አንለፈው እኛ የምናዋጣው ብር ትንሽ ነው። ነገር ግን ወረቀቶቹ ተበትነው የብዙ ሰው የመመለስ ሰብብ ሊሆኑ ይችላል እኛ ሰበብ ማድረስ ነውና የምንችለው።

የመመዝገቢያ አዲስ አካውት ስለከፍትኩ ከታች ባለው ሊንክ ገብታችሁ ተመዝገቡ
👉 @abalochachin
👉 @abalochachin
👆መመዝገቢያ👆

ወንድማችሁ ሙሂዲን ሰኢድ
👉 ሼር ሼር ሼር

የምትመዘገቡና የተመዘግባችሁ
ከታች ያለውን አዲስ ቻናል ተቀላቀሉ
👇👇👇👇 👇
https://t.me/ye_abaloch_mewacho
https://t.me/ye_abaloch_mewacho

2 months, 2 weeks ago
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 Monate her

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 Monate, 2 Wochen her

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 Monate, 2 Wochen her