● Welcome to Ethio music Channel
➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !
Last updated 4 Monate, 4 Wochen her
🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹
For promotion and Advertisements
👉 @Mussegirma
#ካሮት_ሙዚክ✋
ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo
በመኖር አጸድ ውስጥ
(በእውቀቱ ስዩም)
ጊዜ ከሰው መሀል- መርጦ ሲያቀማጥል
ማጣት አለ ደሞ፥
የወለዱትን ልጅ፥ ጉድፍ ላይ የሚያስጥል
በተፈሰከ ቀን፥ ጾምን የሚያስቀጥል::
እድልና ትግል በሚጫወቱበት
በደልዳላው ስፍራ
አለቃና ጭፍራ-
-ቃል ሲለዋወጡ፥ ውልና መሀላ
“አብረን እናድጋለን” ቢባል ለይስሙላ
ወንዙን ሳያጎድል ፥ሐይቁ መች ሊሞላ፤
ጸሐይ ብትወጣ
ፍጥረት በጠቅላላው ጸጋዋን ቢቀበል
የደመናም ጠበል፥
ለሁሉ ቢደርስም
አንደኛው አያድግም፥ አንዱን ሳያከስም::
ሰዎች እንዴት ናችሁ
ይሄን Group ግቡና እዩት እስኪ ስለዚህ Application ካልሰማችሁ ብዙ ቪዲዮዎች ሰርቻለሁ Check አድርጉት እንደዚህ አይነት ስራ መስራት የምትፈልጉ ብር ታገኙበታላችሁ
እኔ እየሰራሁበት ነው
👇መግቢያ link👇
@popolivestream
@popolivestream
@popolivestream
@popolivestream
ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ!
ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ!
(አሌክስ አብርሃም)
ፍቅር ብቻውን መልስ የሚሆንበት ጊዜ ላይ አይደለንም።
በማንም ላይ መፍረድ ከባድ ነው። ሲቸገሩ መርዳት አለመቻል ከሚፈጥረው ህመም
ለመራቅ ከምንወዳቸው ወዳጆቻችን እንርቃለን። ዓይናቸው ውስጥ ያለውን ስቃይ ላለማየት ዓይናችንን እንሰብራለን።የአቅማችንን መደገፍ እንኳን ከአቅም በላይ ሆኗል። የተወለድንበት እና ያደግንበት ስር የሰደደ አብሮነት፣ መረዳዳት አሁን እግር ከወርች ካሰረን ኑሮ ጋር አብሮ አልሄድ ብሎ አስጨንቆናል።
ረስተነው ወደወዳጆቻችን መንገድ ከጀመርን ፣ልንደውል ስልክ ካነሳን በኋላ ባዶ አይናቸው እጃችሁ ከምን ቢለንስ ብለን ተመልሰናል። ከመሄዳችን በላይ ምን ይዛችሁ መጣችሁ የሚለን አንደበታቸው ሳይሆን ኑሯቸው ሁኗል። የተጨነቀ መንፈስ፣ የተጨነቀ አየር። የማንንም እርዳታ የማይፈልጉ መንፈሰ ፅኑ ወዳጆቻችን ነገሮች ከአቅም በላይ ሆነውባቸው በዓይናቸው ባዶ ኪሳችንን ሲቃኙ ብናይ መርዳቱ ቢቀር አንታዘባቸውም። "እንትናም ተቸገረ?" ብለን አናሾካሹክም።
ይገባናል ሰው ወደገደል ቢወድቅ አዳነውም አላዳነውም አጠገቡ ያገኘውን ሳርም ይሁን ቅጠል በደመነፍስ ጨምድዶ እንደሚይዝ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።ልብሳችንን አንቀው የሚማፀኑን እኛም የሌሎችን ልብስ አንቀን መንጠልጠላችንን ያውቃሉ። የመያያዙ መጨረሻ፣ የገደሉ ጫፍ የት እንደሆነ ማን ያውቃል?! እጃችን እየዛለ ነው። ደመነፍስ ላይ ነን። ማንንም ለመዳን እንይዛለን በማንም እንያዛለን። ችግራችሁን እያየን ያልደረስንላችሁ ይቅርታ። ችግራችንን እያያችሁ ያልደረሳችሁልንም ይቅርታ። ሁላችንም ገደሉ ውስጥ ነን።
አሌክስ አብርሃም
የነገው_ነፋስ
(በዕውቀቱ ስዩም)
ያንን ገለባ ልብ
ከደጅ የወደቀው፣
"አድራሻህ ወዴት ነው?"
ብለህ አትጠይቀው፣
የነገው ነፋስ ነው
መንገዱን የሚያውቀው ።
ኖረሽ እይው በቃ
(በዕውቀቱ ስዩም)
ጨለማ ነህ ብለሽ እኔን ስትተቺ
ዘልለሽ አትጠግቢ ስቀሽ አትሰለቺ
ወርሃ ፅጌ ነው አመት ሙሉ ላንቺ
ደሞ በየቀኑ ፋሲካ ነው ኑሮሽ
ያለም ሰቀቀኑ ሩቅ ነው ለጆሮሽ
ለፍጥረት ሰቆቃ ለጋ ነው አእምሮሽ
ገላሽም ነው ጮርቃ
ሌላም አልልሽም ኑረሽ እይው በቃ
በየጎዳናው ላይ አደይ የሚነጥፍ
በየዛፉ ቅርፊት ስምሽን የሚጥፍ
በዝቶልሽ ፈልቶልሽ አንቺን ሚያሽሞነሙን
ቀስመሽው አታቂም የብቻነት ሸክሙን
አዎ
መፈቀር መታጀብ ከኔክታር ይጥማል
ግን ደግሞ ይገጥማል
በተወደሱበት አንደበት መነቀፍ
ውብ ገላ ጠብቆ ርጥብ ንፋስ ማቀፍ
አንዳንዴ ይገጥማል
የማይሰምር ምኞት የማያልቅ ጥበቃ
ሌላም አልልሽም ኑረሽ እይው በቃ
አንቺ ደስታ ወዳጅ!!!
በለምለም አፀድ ውስጥ ቢራቢሮ አሳዳጅ
ኑሮ ምትታይሽ እንደ ጣኦስ ቅማል
እንዳትሸወጂ
ባዝማሪዎች ዜማ በሸንጋዮች ቃላት
ህይወትም እንደጃርት የሾህ ቀሚስ አላት
ተድላም ከሀዘን ጋር ያልፋል በፈረቃ
ከሳቅ በስተጀርባ ይሰለፋል ሲቃ
ምንም አልልሽም ኖረሽ እይው በቃ
ይስጥሽ
(በዕውቀቱ ስዩም)
እቴ…
ይስጥሽ ከቁመቴ ከላዬ ቀንሶ
ያስረዝምሽ አንቺን እኔን አሳንሶ
ከሰጎን እረዝመሽ ስትቆሚ ከጎኔ
ቁመቴን መጽውቼሽ ጫጩት ላክል እኔ፤
ይስጥሽ ከጸጉሬ ከአናቴ ላይ ዘግኖ
ይገጠብ ራሴ ያንቺ ተጎንጉኖ
አወይ ጸጉሯ ብለው ኮረዶች ሲያወሩ
ድጥ ራስ ነህ ብሎ ይዝለፈኝ ሰፈሩ፤
እቴ…
ይስጥሽ ከወዜ ላይ ጨልፎ ከፊቴ
ይቅዳልሽ ከደሜ ጠልቆ ከጅማቴ
ከአይን ያውጣሽ እያለ ሲመርቅ አድናቂ
እስቲ እግዜር ይማርህ ይበለኝ ጠያቂ።
እቴ…
እጄን ብትፈልጊ
እግሬን ብትፈልጊ
አንገቴን ደረቴን
ተሰጥኦ ሀሳቤን
ያደምቀኛል ብለሽ ያሰብሺውን ሁላ
እግዜር ከኔ ወስዶ ከሰጠሽ በኋላ
ያስቀርልኝ አይኔን
አንቺን ማየት ብቻ ያኖረኛል እኔን።
➢➢ላ’ንዲት የገጠር ሴት➢➢
ስትፈጭ የኖረች ሴት፣
መጁ በመጠኗ፣ ወፍጮውም በልኳ፣
ጓያ ትፈጫለች
ጓያ ሽሮ ሲሆን ያበቃል ታሪኳ !!
አስባው አታውቅም…
ወደ ኦናው ምድር ለምን እንደመጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ከና’ቷ ሆድ ወጣች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ጡት አጎጠጎጠች፣
ከ’ለታት አንድ ቀን፣ ለባሏ ተሰጠች……
ተዚያን ቀን ጀምራ፣
ተዚያን ቀን ጀምሮ፣
ድንግል ድንጋይ ወቅራ፣
ትፈጫለች ሽሮ……
አታውቅም፣
ማን እንደሚባሉ፣ ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣
አታውቅም፣
ሹማምንት በ’ሷ ስም፣ ምን እንደሚሠሩ፣
አነሳኹት ‘ንጂ፣ እኔም ለነገሩ፣
ፖለቲካ ጥበብ ራስን ማራቀቅ፣
ምን ይጠቅማትና ጓያዋን ለማድቀቅ
ከቶ ማንም የለ, አበባ ‘ሚሰጣት፣
ከቶ ማንም የለ፣ ከተማ ‘ሚያወጣት፣
ከቶ ማንም የለ ፣ በዳንኪራ መላ፣ ወገቧን የሚያቅፋት፣
ልፋቷም፣ ዕረፍቷም፣
ወደዚህ መጅ መሳብ
ወደዚያ መጅ መግፋት……
እንደ ዓባይ ፏፏቴ፣
ሽህ ዓመት ቢንጣለል፣
ቢጎርፍም ዱቄቱ፣
እንደ ሲኦል ወለል፣ ጫፍ የለውም ቋቱ!
ከዘመናት ባንዱ
መስተዋት ፊት ቆማ፣ በተወለወለው፣
ራሷን ለማየት፣
ከጸጉራ ላይ ያለው
ዱቄት ይኹን ሽበት ሲያቅታት መለየት፣
ያኔ ይገባታል
የተሰጣት ዕጣ፣
ከማድቀቅ ቀጥሎ፣ መድቀቅ እንዲመጣ…
የመጅ አጋፋፏ - አምሳለ ሲሲፈስ፣
ከቋት ሥስት እንጅ፣ ሢሳይ አይታፈስ፣
ትቢያ ‘ሚተነብይ ዱቄት በዙሪያዋ፣
ከባርኔጣ አይሰፋም፣ የኑሮ ጣሪያዋ፣
"ስትፈጭ የኖረች ሴት"
ይህ ነው መጠሪያዋ!
➛➛ገጣሚ ፦ በእውቀቱ ስዩም
Notcoin ግቡና ዕድላቹን ሞክሩ ስል አሻፈረኝ ያላቹ ምን እንደተፈጠረ እስካሁን ሰምታችኋል መቼም ?
ይኼኛው ደግሞ Hamster Kombat ይባላል። ይሄም ከ Notcoin ጋር ተመሳሳይነት አለው በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ተቀባይነት አግኝቷል
ከናንተ የሚጠበቀው ገብቶ Tap ማድረግ እና በዋናነት ደግሞ Friend invite ማድረግ የሚሰጡ Task'ኦችን በመፈፀም የሚሰጣቹን Coin መሰብሰብ ብቻ !
ባለፈውም እንዳልኩት በመሞከር የምናጣው ነገር የለም
ማመን እና ማወቅ
(በላይ በቀለ ወያ)
.
.
ከቀጠርሽኝ ቦታ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ
ያወኩትን እውነት ...
ማመን ቢቸግረኝ ፣
"ትመጣለች " እያልኩ ፣ እጠብቅሻለሁ፡፡
"አትመጣም" እያለ...
ለሚነግረኝ ሁሉ ፣ መቅረትሽን አውቆ
"የቀረበት እንጂ ...
የመጣለትማ ፣ አያውቅም ጠብቆ"
ስል እመለሳለሁ
በቃ ትመጫለሽ ፣ ቀርተሻል አውቃለሁ!!!
ካንቺ ጋር...
ሠዓሊና ገጣሚ
ገብረክርስቶስ_ደስታ
,
ካንቺ ጋር ሁሉም ነገር ሄዷል
ሰዓቱ ተረስቷል ቀኑም ሌላ ሆኗል
ዓመተ ምህረቱ
በጋና ጸሀዩ
የኖርሽበት ቤቱ
አልጋ ጠረጴዛው ስጋጃ ወንበሩ
መስኮቱና በሩ
ስዕሉ ግርግዳው
ካንቺ ጋራ ጠፍቷል
ሁሉም ተለውጠው
ዛሬ ነገ የለም
ቅናትና ፍቅሩ ሀዘኑ ጨዋታው
ደስታና መከራው
ፈጥሯል ሌላ ቀለም
ገርጥቶ ጠውልጎ መልኩ የነበዘ
ሞቷል መታሰቢያሽ ሆኗል የፈዘዘ
ፈራርሷል የካብሽው
ትዝታው የድሮው
ቀርተሸ ተረስተሻል
ጠፍተሻል ከልቤ
ወጥተሻል ከቤቴ
ወጥተሻል ካንጀቴ
ወጥተሻል ካጥንቴ
ሄደሻል ካሳቤ፡፡
የለሽም የለሽም
ሙዚቃ ድምጽሽን
እንደ ዱሮ አልሰማም
ቅዠት ዘፈንሽ ዜማሽ እንጉርጉሮሽ
ጭጋግ ነው ውበትሽ
የጊዜው መለወጥ
ገላሽን ደብቆ ጋርዶታል መልክሽን
ጥላሽ ነው የቀረው አካልሽ ተሰርቶ
ጨብጦ ቅርጽሽን
ሳቅና ፈገግታሽ ጨዋታና ቀልድሽ
ለዛና ወሬሽ
ቅንድብሽ ሽፋልሽ
የሚያበሩ አይኖችሽ
ጣፋጩ ከንፈርሽ
ለስላሳው ምላስሽ
በረዶ ጥርሶችሽ
ተለውጠው የሉም
ካሳቤ ጨለማ ገብተው አይታዩም
ያ ውብ ቆንጆ ባትሽ
የሚዋጋው ጡትሽ
የሚቆጣው ዳሌሽ
ካንቺ ጋር ሄዷል፡፡
● Welcome to Ethio music Channel
➤ For any promotion and Advertising 📩 inbox @Markonal21 ወይም @ethiomusic21bot
.
.
● የበጎ አድራጎት ስራዎችን በነፃ ፖስት እናደርጋለን ለመልካምነት ቦታ አይመረጥም ! ያዋሩን
.
.
● የሀገር ውስጥ አዳዲስ
ሙዚቃዎች
አልበሞች በፍጥነት ያገኛሉ
.
● እንዲሁም በቀናነት JOIN & SHARE ያድርጉ !
Last updated 4 Monate, 4 Wochen her
🇪🇹 የምርጥ ሙዚቃዎች መገኛ 🇪🇹
For promotion and Advertisements
👉 @Mussegirma
#ካሮት_ሙዚክ✋
ሰለ ቻናላችን ማንኛውንም የፈለጉትን ሙዚቃ እና ያለወትን ቅሬታ
ሆነም አስተያየት በማለት
በዚህ #bot✍ ማቅረብ ትችላላችሁ፡፡
???????????
http://t.me/yekonjochumenahriabot
እናመሰግናለን?
Admin
@Aymu_xo