Sharing my thoughts, discussing my projects, and traveling the world.
Contact: @borz
Last updated 2 days, 20 hours ago
Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.
Last updated 2 months, 1 week ago
Official Graph Messenger (Telegraph) Channel
Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph
Donation:
https://graphmessenger.com/donate
Last updated 3 months, 3 weeks ago
👳♂አባቶች ይህንን ይመክሩናል
እኛ የአባቶቻችን ልጆች ነን
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን
ለኦርቶዶኮስ አማኞች ብቻ የተከፈተ ቻናል ።
✝ክርስትናችን እንዳንኖረው የሚያደርጉን ምክንያቶች በእውኑ ታውቋቸዋላችሁ⁉️
ለዚህ ችግር አባቶች ምን አሉ⁉️
የምትፈልጉትን ለማግኘት ወደ ቻናላችን ተቀላቀሉ
ይህ ምክረ አበው ነው ሁላችሁም ተቀላቀሉ ትጠቀሙበታላችሁ open የሚለውን በመንካት ይቀላቀሉን👇👇👇👇👇👇👇
⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ⬛️⬛️⬛️⬛️
⬜️◻️◽️▫️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
⬜️⬜️⬜️⬜️ⓄⓅⒺⓃ▪️◾️◼️⬛️
@abenawaver
[⛪️📚🙏
1, እመጓ
2, ዝጎራ
3, መርበብት
4, ዴርቶጋዳ
5, ዮራቶራድ
6, ዣንቶዣራ
7,መጽሐፈ ሄኖክ
8, ቤተክርስቲያንህን እወቅ እንዳትሆን መናፍቅ
9, ፍኖተ አእምሮ
9, አዳም እና ጥበቡ
10, ዝክረ መስቀል
11, ሰይፈ ሥላሴ
12, ፍትሐ ነገስት
13, መጽሐፈ መነኮሳት
14, ከአክራሪ እስልምና ወደ ክርስትና
16, ህግጋተ ወንጌል
17, ነገረ ማርያም በጥንታዊቷ ቤተከርስቲያን
18, ድርሳነ ሚካኤል ወ ገብርኤል
19, ውዳሴ ማርያም በግእዝ
20, ግድለ ተክለሃይማኖት
21, ገድለ አባ ጊዮርጊስ ዘጋሰጫ
22, የወጣቶች ህይወት
23, መጽሐፈ ገድለ ሐዋርያት
24, ኦርቶዶክስ መልስ አላት
25, የዋልድባ ገዳም ታሪክ
📚📚የቱን ኦርቶዶክሳዊ መፅሀፍ ማንበብ ይፈልጋሉ የሚፈልጉትን መፅሀፍ በመንካት ያንብቡ መልካም ንባብ📖
✝ ይቀላቀሉን ✝](https://t.me/addlist/TLRjDo_KBNFiZWU0) @abenawaver
✝ ኦርቶዶክስ ኖት ?
ለመሆኑ እስካሁን በቴሌግራም ትልቁን የኦርቶዶክስ ቻናል ተቀላቅለዋል ? ካልተቀላቀሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉ ።
➱ የብራና መፃህፍት በpdf ፣
➱ የታላላቅ መምህራን ስብከቶች በቮይስ ፣
➱ አስተማሪ ፅሁፎች ፣
➱ መንፈሳዊ ግጥምና ልቦለዶች ፣
➱ መንፈሳዊ ፊልሞች ፣
➱ ኦርቶዶክሳዊ መዝሙሮች ይቀርቡበታል።
ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል ነው። @abenawaver
⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️⚡️
በቤቲንግ ብር እየተበላችሁ የምትገኙ በሙሉ ይሄ ቻናል ለናንተ ነው ምርጥ ቲፕ የምታገኙበትን ቻናል ይዘን መጥተናል *✅ *ማየት ማመን ነው*🏆*👇****
የስልክ ቁጥሮን የመጨረሻ ቁጥር በመምረጥ እድሎን ይሞክሩ 🤩
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻
💙 የእናቴ ልጅ 🌹🔸
❤️ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️
አዘጋጅ ✍የፍቅር ክሊኒክ
#ክፍል_ 3️⃣2️⃣
የመጨረሻው ክፍል
ቀን ቀንን እየተካ በሄደ ቁጥር በወንድሜ ላይ የነበረኝ የመረረ ጥላቻ እና ቂም እየደበዘዘ ሲመጣ ይታወቀኛል ይህን ስሜት ወደድኩት ምክንያቱም እኔ ቂመኝነት በውስጤ ሰርፆ ቤቱን እንዲሰራብኝ የምፈልግ ሰው አይደለውም ። መጥፎ እና ልክ ያልሆኑ ጉዳዮች ጭንቅላቴ ውስጥ ጊዜ ወስደው በቁዩ ቁጥር እታመማለው ፡መረጋጋት አልችልም ። ያንን ስሜት ለማስታገስ ስል ነውጠኛ ነው የምሆነው ፡ከዚበፊት የእናቴን ጥላቻ እና የሰፈሬን ሰው ግልምጫ ለመወጣት ስል ንዴቴን ካገኘውት ሰው ጋር ሁሉ ነገር ፈልጌ እጣላ ነበር ። አሁን ላይ ከጉርምስናውም እየወጣው ነው እና ያ ስሜት እንዲቆጣጠረኝ አልፈልግም ። ስለዚ በወንድሜላይ ያለኝ ብስጭት እየቀነሰልኝ ሲመጣ ተጠቃሚ ነኝና ደስታ እየተሰማኝ ነው ። እሱ በሰው አገር ላይ ምን እያሳለፈ እንዳለ የምናውቀው ነገር የለም ። ሲዊዲን መድረሱን ከተቀባዮቹ ጋር ሆኖ ለእናቴ ደውሎ ከነገራት በዋላ ።ድጋሚ ደውሎም አያውቅም ። እናቴም ብትሆን ጨከን ብላበታለች ። 'ከአሁን በዋላ ቤተሰብ አለኝ ብለህ ወደእኛ እንዳታስብ 'ብላ እንደተናገረቸው አባቴ ነግሮኛል ። በእርግጥ ምንእንደሚሰማት እሷው ነው የምታውቀው ።የእናት አንጀት እንዲ በቀላሉ ይቆርጣል ማለት ዘበት ነው ። አባታችንም ቢሆን ስሙን ለማንሳት ድፍረቱ ባይኖረውም አንዳንዴ በጨዋታችን መሃል ተክዞ ተክዞ በረጅሙ ሲተነፍስ አጋጥሞኛል ።ምን አልባት ስለ አቤል እያሰበ ይሆናል ብዬ እጠረጥራለው ።
እኔ እራሱ ሳስበው ለአቤል እንዲመሆን ጥፋተኛው ማነው ? ብዬ አስባለው ። ያለ አባት አድገናል ፣እናታችን የሌለ አቅርባው አቅብጣውም ነበር ። የራሱስ አስተዋፆ ? እኔስ ብሆን ጥፋቶቹን በኔ ሲያላክክ የረዘመ ዝምታ አሳይቼስ አልነበረ ? ብቻ አንዳንዴ ሳስበው አቤል እንዲ እንዲሆን ትንሽ አስተዋፅዖ ሳይኖረን አይቀርም እላለው !!!!
🍑እሁድ ቀን ተሰብስበን እንደተለመደው እየተጨዋወትን ፡ ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገነዋል ፣ አባታችን እናቴን እየቀለደባት ያስቀናል ማማ በእናቴ ዙሪያ እየዞረች ባልገባት ነገር ትፈነድቃለች የኛ ሳቅ ሳይጋባባት አይቀርም ፣ እናቴ ስለተሳቀባት አልከፋትም በጣም ደስተኛ ትመስላለች በባሏ ጎኗ መሆን ሙሉነት ሳይሰማት አይቀርም ልዩ ሆናለች ፡ በዛላይ ትላንትና የማማን እናት በማግኘቷ እፎይታ ተሰምቷታል ፡ የአቤልን ትልቅ ስህተት እንዳረመች ሳይሰማት አይቀርም ፡ የማማን እናት ይዛት መጥታ በማንኛውም ሰአት ልጇን የማየት መብት እንዳላት ነግራ ፡ ነገር ግን እፃኗ ከኛጋር መኖር እንዳለባት አስረግጣ አስረድታታለች እሷም ብትሆን ለልጇ ያን ያክል የምትጓጓ መስላ አልታየችም ።እንዲ መሆኑን የፈለገች ነው የምትመስለው ይሄ በራሱ ለኔም እንደ ግልግል ነው ።በአራስነቷ የተረከብኳትን ስንት ነገር ያየውባትን ልጅ ልውሰድ ብትል ምን እንደሚሰማኝ አላውቅም ። ማማ ለኔ ትምህርት ቤቴ ናት በሷ የተነሳ እራሴን ገዝቻለው ስለ ዓለም ክፋት ደግነት አይቻለው ማጣት ምን ያክል እንደሚፈትን ገብቶኛል ። ብቻ ብዙ ብዙ ,,,,,
ዛሬ ላይ ግን በዛ ሂደት ውስጥ ስንት የምወዳቸውን ሰው አውቄ አለው ።ለየት ባለ መልኩ ባዩሽን የክፉ ቀኔ ። ብሌኔን ፍቅሬን የወደፊት ሚስቴ የአይኔን ማረፊያ ፡የልብ ምቴ የሕይወቴ ቅመም ማጣፈጫዬን ፡ ብሌኔ ውዴን ብሌኔ ብሌኔ ፡ስሟን እንኳ ስጠራው የሆነ መሃዛ ከአፌ ወጥቶ አብሮ ያውደኛል ብሌኔ ብሌኔ ......
እረፋዱ ላይ አንዳችን በአንዳች እየሳቅን ጨወታችን ደርቶ ፡ ሳለ የእናቴ ስልክ ጮኽች ።እናቴ እንደሌላው ጊዜ አልፈጠነችም ታነሳዋለች ብለን ስንጠብቅ ፡ወደኛ ማየት ሆነ ። ስትዘገይብኝ ስልኳን አንስቼ ቁጥሩን አየውት የውጪ ለጠ ር ነው ደንገጥ አልኩ ። እናቴ በፍርሃት ስታየኝ
"የውጪ ስልክ ነው አንሺው አልኳት "
"አንተአንሳው "አለች እንደፈራች ስለገባኝ ፡ እኔው አነሳሁት
"ሄሎ "
"ሄሎ የወይዘሮ ዘውድነሽ ስልክ አይደለም "አለኝ የሴት ድምፅ ድንጋጤዬ ጨመረ አቤል ምን ሆኖ ነው
"ነው ማን ልበል አንቺን"አልኳት
"ዲና እባላለው እእ ከሲዊዲን ነው የምደውለው "አለች
"እሺ ምምን የየተፈጠረ ችግር አለ ወንድሜ ምን ሆኖ ነው "አልኳት እየተርበተበትኩ ።እናቴ ስታቃስት ሰማው ዞሬ ሳይ ዕንባዋ ቀድሟል ።
"ኧረ ተረጋጋ እሱ ምንም አልሆነም እኔ ፍቅረኛው ነኝ ያው ብቻ ስለ እናንተ ብዙጊዜ ያወራኛል እና ዛሬ አበረታትቼው አብረን እናወራቸዋለን ብዬ ነው በስንት መከራ የደወልኩት "አለች ፈጠን ፈጠን ብላ
"ድምፁን መስማት እንችላለን "አልኳት
"አዎ እባክህ አንተ ወንድሙ ከሆንክ በጣም ተፀፅቷል እና ይቅር በለው "አለች
"ችግር የለም ይቅር ብዬዋለው አጠገብሽ ካለ ስልኩን ለሱ ስጪው እናቱን ያናግራት "አልኳት
"እሺ "ብላ ስታስተላልፍ እኔም ስልኩን ለእናቴ ሰጠዋት ።እናቴ ልትደብቀው የማትችለው የልጇ ፍቅር ገንፍሎ ወጣ ፡ በቃ ከአቤል ጋር በናፍቆት አወሩ በተደጋጋሚ ይቅር በይኝ ሲላት ይሰማል ልቡ የተሰበረ ይመስላል ፡ ከአባታችንም ጋር አወራ ፡አባታችንም አለቀሰ ፡ብዙ ነገር ተናገረው እንደዚ አይነት ክፋት ከገዛ ልጁ ስላልጠበቀ እስካሁንም ድረስ እየተሰቃየ እንደሆነ ነገረው አቤል ስቅስቅ ብሎ ሲያለቅስ ይሰማል ፡ጓደኛው ነኝ ያለችው ሴት ታባብለዋለች ፡ላውድ አድርገነው ስለሆነ የምናዳምጠው ፡አክስቴ ደግነሽም ባዩሽም ማልቀሳቸው አልቀረም ፡ አክስቴ ደግነሽ ወደኔ እያየች "ይቅር በለው ልጅነት ነው አውሬ ያደረገው "አለችኝ ሆደባሻነቷ አይሎ ፡ እኔ ውስጤ ተረጋግቷል ሞተ የምባል መስሎኝ ስለነበር ክፉ ነገር ስላልሰማው ሰላም ሰፍኖብኛል ። ዓለም እንግዴ እንደዚ ናት እንደ ዥዋዥዌ ነው ነገሯ ወደዚ ወደዚያ ፣ እንደ ፈለገች አንተ ጠንክረ ገመዷን ይዘህ እየተቆጣጠርክ ካልተጫወጥክ ፈንግላ ልትጥልህ ትችላለች ፡ እራስህን ከማንም ጋር ሳታወዳድር የማንንም ንዋይ ሳትመኝ የሕይወት መንገድህን በራስህ በንፁ ሕሊናህ ታግዘህ አስምር መስመሩ ሲበላሽ በትህግስት እያስተካከልክ ወደፊት ቀጥል ። ለሌሎች የደስታ የሰላም ምንጭ እንጂ ፣የስቃይ የመከራ ምንጭ አትሁን ፣ አንተ ደስተኛ የምትሆነው በዙሪያህ ደስተኞች ሲኖሩነው ፡ 'ብቻህን በሚያለቅሱ ሰዎች መሃል ብትስቅ እብድ ነው የምትባለው'
♥️ተ♥️ፈ♥️ፀ♥️መ
ታሪኩን እንደወደዳችሁት እና እንደ ተማራችሁበት እምነታችን ነው።
በቅርቡ አዲስ ታሪክ እንጀምራለን ሀሳብ አስተያየታችሁን እንዲሁም ማስተካከል ያለብን ነገር ካለ comment ላይ አድርሱን እናመሰግናለን። ❤️
🔺🔺🔺🔺🔺😀😀😀😀😀
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
የስልክ ቁጥሮን የመጨረሻ ቁጥር በመምረጥ እድሎን ይሞክሩ 🤩
🔻🔺🔺🔺🔺🔹🔹🔻🔻
💙 የእናቴ ልጅ 🌹🔸
❤️ ልብ አንጠልጣይ እውነተኛ ታሪክ❤️
አዘጋጅ ✍የፍቅር ክሊኒክ
#ክፍል_ 2️⃣3️⃣
ወደ ጊቢ ስገባ ሸማግሌው የሚበሉትን ጨርሰው ውሃ ሲጠጡ አገኘዋቸው። እናቴም እነደግነሽም ወደውስጥ ገብተው ነበር ፡አቤል ብቻ በረንዳው ላይ ቁጭ ብሎ ሰውዬው አንዳች ነገር ያነሱ ይመስል ይከታተላቸዋል የአቤል ሁኔታ ገረመኝ አሁን እኚ ሽማግሌ ምኔን ይነኩኛል ብሎ ነው ጠምዶ የያዛቸው ለራሳቸው የያዙትን ብርጭቆ እንኳ በቅጡ ወደአፋቸው ለማድረስ የተቸገሩ ነው የሚመስሉት ።
አቤልን ችላ ብዬ ወደ ሽማግሌው ተጠግቼ ቁጭ አልኩ ደንገጥ አሉ ምንም እንዳልተፈጠረ ሆኜ ፈገግ አልኩ እናም የሚንቀጠቀጠው እጃቸው ላይ ያለውን ብርጭቆ ተቀብዬ መሬት አስቀመጥኩት ።
"አአመሰግናለው ልልጄ "አሉኝ
"ኧረ አባት አይጨነቁ "አልኳቸው በተቀደደ ቲሸርታቸው ውስጥ የሚታሁኝ አጥንቶቻቸው የተሸበሸበው ቆዳቸው ብዙ ስቃዮችን እንዳሳለፉ ይናገራሉ
"እሺ ልጄ አሁን በልቼ ጨርሻለው ልሂድ መሰለኝ "አሉ
"አይ ቆይ ቆይ ትንሽ ከኔ ጋር ይጫወታሉ "አልኳቸው
"አይ ልጄ ስለምን ልንጫወት ነው"አሉ ፈራ ተባ ብለው
"እዚ በተደጋጋሚ ይመጣሉ እንዴ ሁሉም ሰው ያውቆሆታል ከኔ በቀር"አልኳቸው
"እእ አዎ አልፎ አልፎ ርሃብ ሲጠናብኝ እዚ እመጣለው እናትህ ደግ ሴት ናት "አሉ አዘን ብለው
"አዎ እናቴ ደግ ናት "አልኳቸው እንዳቀረቀሩ ዝም አሉ
"ስሞት ማነው "አልኳቸው
"አበራ አበራ አይሉ እባላለው "አሉ
"ደስ የሚል ስም ነው አበራ አይሉ ደስ ይላል"አልኳቸው ።ዝም አሉ በጣም የጨነቃቸው ይመስላሉ የበታችነት ስሜት ሳይሰማቸው አይቀርም
"አባት በማንኛውም ሰአት ወደዚ ቤት መምጣት ይችላሉ ምንም ነገር እንዳያሳስቦት ፡ ከፈለጉ ደሞ እርሶ እሺ ይበሉኝ እንጂ እዚ እኛጋር አትክልተኛ ሆነው እንዲሰሩ እናቴን ላሳምንሎት እችላለው "አልኳቸው ።ይሄን ስላቸው አሻግረው ወደ አቤል አየት አደረጉ
"ምነው አልፈለጉም "አልኳቸው
"አይ ይቅርብኝ ያለውበትን ሁኔታ ለምጄዋለው አታስብ "አሉ
"በቃ አሳቦትን ከቀየሩ በማንኛውም ጊዜ ይጠይቁኝ "አልኳቸው ።እሺ በሚል እራሳቸውን ነቀነቁልኝ ለምን እንደው አብሬ አቸው መቆየት ፈልጌ ነበር እሳቸው ግን ተጣደፉ ።ይሁን ብዬ አሰናበትኳቸውና ወደ ትልቁ ቤት ሄድኩ አቤል ሽማግሌው እንደወጡ ካረጋገጠ በዋላ ወደውስጥ ገብቷል ስገባ ቁርሰሸ ቀርቦ ቡናው ተጥዶ ሞቅ ሞቅ ብሏል ። ይሄ የቤተሰብ ስብስብ ይመቸኛል ደስስስ የሚል ስሜት ይሰጠኛልም።
🎈ሕይወት እኔንና ቤተሰቤን በፍቅር ይዛን ወደፊት መጓዛን ቀጥላለች ።እናቴ ደግነሽ ባዩሽ ማማ አቤልን ጨምሮ ሁላችንም ሰላማዊ በሆነው ትልቁ ቤታችን በደስታ እያሳለፍን ቀናቶች ተቆጠሩ ። የኔ የደስታ ምንጭም ጨምሯል በብሌን ግልፅና ያልተገደበ የፍቅር አዙሪት ምክንያት። የብሌንን ፍቅር ብፈራውም እስካሁን የፈራውት አልደረሰም። ያልተለመደው ግልፅነቷ የኔንም ድብቅነት ገላልፆ ፊለፊት አውጥቶ ከማሳየት በስተቀር አልተጎዳውም ። እንደዛተችው ጥላኛለች እቅፏ ውስጥ ፡ ለመጀመሪያ ጊዜ የሴትልጅ ገላ እንዳውቅ ስሜቱንም እንዳጣጥም አድርጋኛለች ፡ በፍቅር ጠብ አድርጋኛለች ። እናም በዚ ደስተኛ ነኝ ዙሪያዬን የሚያስብልኝ ሰው ነው የከበበኝ ማለት እችላለው ፡ አቤልም ደና የሆነ ይመስላል እናቴም አቤልን ወደ ውጭ ለመላክ ያሰበችው አሳብ ሊሳካላት ተቃርቧል ፡ መጀመሪያላይ እሱም አቅማምቶ የነበረ ቢሆንም አሁን ላይ ግን ፍቃደኛ ሆኗል በተለይ የሚሄድበት ሀገር ሲዊዲን ነው ሲባል እዛ ያስቀመጠው ነገር ያለ ይመስል ደስ ብሎታል ፡ እኔ ግን በአቤል መሄድ እርግጠኛ መሆን ከብዶኛል ፡የሚሄድም ከሆነ ደርሶ የሚመለስ ነው የሚመስለኝ አቤል እኮ ነው። ተቀብሎ መኖር የለመደ እጁ ለስራ ይሰለጥናል ማለት ከበደኝ ።
እናቴ ደሞ የመጀመሪያ ስራዋ አቤልን ከእኛ ማራቅ የሆነ ይመስል በገንዘብም ላይታች በማለትም እየበረታች ነው ። እሷ አሁንም ድረስ አቤል ላይ ያላትን አቋም አልቀየረችም እሱን ማመን ከብዷታል ከእኛጋር በቆየ ቁጥር አንዳች ዱብዳ እንደሚያወርድ ነው የምታስበው እኛ ሽማግሌ እንኳ ሲመጡ ሁሌም አቤል እንደተቆጣ ነው እሷ ደሞ ስለ አቤል ሆና ይቅርታ እንደጠየቀች ነው ። ይሄ በራሱ እንኳ እንድትፈራው አድርጓታል ፡ሁሌም እኔን ወንድምህ ነው ውደደው ነገርግን እየተጠነቀከው ትለኛለች ።
🎈ከቀናቶች በዋላ የአቤል የውጪ ፕሮሰስ ጉዳይ ተሳካና የሚሄድበት ቀን ተቆረጠ እናቴ ትልቅ እፎይታ ሆነላት የሚያስፈልጉትን ነገር ሁሉ አዘጋጀች ባዩሽና አክስቴ ደግነሽም ዳቦ ቆሎ በርበሬ ሲያዘጋጁ ከረሙ ።ብሌን እራሱ አልቀረችም ስለ እኔ ብላ ስዊዲን አገር ከሚኖሩ ጓደኞቿ ጋር ተደዋውላ ነገሮችን በማመቻቸት የበኩሏን ስትወጣ። እኔ ግን በጣም ቅር ብሎኛል አቤል ምን ሊሆን ነው እዛ ሄዶ ስራ ሰርቶ አያውቅ በሰው አገር ሲቸገር ሲያዝን እየታየኝ ጨነቀኝ ።
🎈የማይቀር ነገር ሆነ እና ይኽው ልንሸኘው ተዘጋጀን እንደነገ ሊሄድ ማታ ላይ ተሰባስበን የመጨረሻ ምሽት እያሳለፍን ነው ሁላችንም ዘና ልናረገው ሞከርን እሱ ግን ምንም አይነት የስሜት ለውጥ ሳያሳይ ቆይቶ ነበር ወደ ምሽት አራት ሰአት አካባቢ ግን የስሜት ለውጥ ይታይበት ጀመር ምን አልባት ሰአቱ ሲደርስ ተረብሾ ይሆናል ብዬ ነበር ፡ እናቴ በትኩረት ትከታተለዋለች ፡ አቤል መቁነጥነጥ ጀመረ ፡አሁንም አሁንም ወደውጪ እየወጣ ይመለሳል ፡ በመጨረሻ ስልክ ተደውሎለት ወጣ ፡ደግነሽ ተከተለው ብላኝ ነበር ልከተለው ስንቀሳቀስ እናቴ ተመለስ አለችኝ እሱም ሰው አግኝቼ እመለሳለው አታስቡ ብሎን ፈጠን አለ እርስ በእርስ ተያየን ። እናቴ በቤት ውስጥ ወዲ ወዲያ እያለች ታስባለች እኔም እስኪመጣ ተጨነኩ ፡ ለምን ድነው ተጣድፎ የወጣው የሁላችንም አሳብ እሱው ጋር ሆነ,,,,,,,
ይቀጥላል.....
ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
👇👇👇👇👇👇👇👇
ልጅ ነው ሲያየኝ እጁን ወደ ቆመ መኪና አመላክቶኝ እሮጠ የብሌን መኪና ከቤታችን ፊት ለፊት ቆሟል ጥድፍ ጥድፍ እያልኩ ተጠጋዋት የመኪናዋን በር ከፍታ አስገባችኝ ስገባ ያየሚያስደነግጠኝ ፊቷ ቀረበኝ
"አንተ የመጨረሻ የምታናድድ ልጅ "አለችኝ
"ምን አደረኩ "አልኳት
"ለምንድነው ስልክ የምትዘጋው በጣም ነው የተበሳጨውብህ ግን ሳይህ እረሳውልህ "ብላ ጉንጬን ሳመችኝ ኡፍፍፍፍ እሳቷን ለቃ ምንም እንዳልተፈጠረ ነው የምትሆነው
"ቻርጅ ጨርሶ ይሆናል "አልኳትና ጉንጬን ዳበስኩ
"እና ቻርጅ ማድረግ ነው እኔ መጥቼ ላርግልህ እንዴ"
"አይ እኔ አደርገዋለው"
"አድርገዋ ታዲያ"ብላ ተጠጋችኝ
"ተይ በቃ አታስጨንቂኝ እንዴ ማታ ኳስእያየው ስለነበር እረስቼው ነው ያደርኩት"አልኳት እኔን ማሳፈር ደስ ይላታል ፡
"ኪኪኪኪ ደስስስ ይለኛል አንተን ማስጨነቅ ፡አሁንማ ይሄንን ሁኔታህን ለምጄው ነው መሰል ከጠዋት እስከማታ ነው የማስብህ "
"ስራ የለሽም ማለት ነው"
"ስራዬ አንተ ሆነሃል ከልቤ ነው እየወደድኩህ ነው መሰል"
"አሂሂሂ ያዋከቡት ነገር ሆኖ በጊዜ እንዳታባርሪኝ "
"እንዳትባረር ከፈለክ ፀባይ ይኑርክ ፡አሁን ለምን ቁርስ አብረን አንበላም "
"አይ ቤት እየጠበቁኝ ነው በዛላይ ሻወር አልወሰድኩም በዋላ እንገናኝ "አልኳት
ዝምብላ አየችኝ አስተያየቷ አንዳች ነገር የፈለገሰው ይመስላል ስሜት አለው
"ምነው "አልኳት
"ይሄን ሰውነት ያለ ጨርቅ ሳልኩት እናም በቃ......."ብላ ዝም አለች
"አንቺ ልጅ ግን እኔ ማለት ያለብኝን ሁሉ አንቺ ካልሺው እኔ ምን ልል ነው ግልፅነትሽ በዛብኝ"አልኳት እያፈርኩ
"አንተ ማለት አይጠበቅብህም በታማኝነት ድርጊቱላይ ተሳተፍ ፡ አሁን አንድ ቦታ ብንሄድ በጣም ነበር ደስስስ የሚለኝ ግን ያው በቃ እንዳልክ በዋላ ላግኝህ ስልክህን እንዳትዘጋው ደሞ"አለችኝ
"እሺ አደራ ግን ይሄ የምታሯሩጭኝን ነገር በልኩ አድርጊው "አልኳት ፈገግ እያልኩ
"እጠነቀቃለው "ብላ ጠጋ አለችኝ እናም ሳላስበው ከንፈሬን ምጥጥጥ አድርጋ ሳመችኝ ፡ሰማይ ምድሩ ሲዞር ይሰማኛል ፀሐይ ሙቀቷን እንዳለ ከላይ የለቀቀችብኝ መሰለኝ ኧረ ደግነሽም እልልልልልልልልልልል ያለች መሰለኝ ,,,,
ይቀጥላል.....
🔻ቶሎ እንዲቀጥል አንብበው ሲጨርሱ Like👍💝 ሼር ማድረግ አይርሱ።
ይ 🀄️ላ🀄️ሉን! 😀
@marakye22 @marakye22
አንዳንድ ሰዎች ይጠቀሙብሀል
አንዳንድ ሰዎች ይፈትኑሀል
አንዳንድ ሰዎች ጥለውህ ይሄዳሉ
አንዳንድ ሰዎች ይወዱሀል
ሁሉም ግን አስተምረውሀል !
@marakye22
Sharing my thoughts, discussing my projects, and traveling the world.
Contact: @borz
Last updated 2 days, 20 hours ago
Telegram stands for freedom and privacy and has many easy to use features.
Last updated 2 months, 1 week ago
Official Graph Messenger (Telegraph) Channel
Download from Google Play Store:
https://play.google.com/store/apps/details?id=ir.ilmili.telegraph
Donation:
https://graphmessenger.com/donate
Last updated 3 months, 3 weeks ago