★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago
?ዘፍጥረት 2፥15-18?
------------------------------
15.“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ወስዶ ያበጃትም ይጠብቃትም ዘንድ በዔድን ገነት አኖረው።”
#ያበጃት_ይጠብቃትም_ዘንድ ፦ ስለዚህ ክፍለ ምንባብ ሰቨርያን እንዲህ ይላል «ይሰራና ይጠብቃትም ዘንድ የሚለው ሌባ ሳይኖር አላፊ መንገደኛም ሳይኖር ወይም ሆን ብሎ ክፉ የሚያደርግ ሰውም ሳይኖር ከማን ነው የሚጠብቃት? ከራሱ ነው የሚጠብቃት።ትእዛዙን ካልተላለፈ ገነትን አያጣትም፥ትእዛዙን መጠበቅ ለሰውልጅ ስራ ነው በዚህ ስራም ራሱን ይጠብቃል የተሰጠችውን ገነትንም ይጠብቃል»
ሰውን በመልኩ እንደ ምሳሌው ከፈጠረው በኋላ በኤደን ወደ አዘጋጀለት ልዩ የአትክልት ስፍራ አስገባው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
16.“እግዚአብሔር አምላክም ሰውን እንዲህ ብሎ አዘዘው፦ ከገነት ዛፍ ሁሉ ትበላለህ፤
17.ነገር ግን መልካምንና ክፉን ከሚያስታውቀው ዛፍ አትብላ፤ ከእርሱ በበላህ ቀን ሞትን ትሞታለህና።”
የታዛዥነቱ መለኪያ ቀዳሚው ትእዛዝ ይህ ነው ዛፉ መርዛማ ሆኖ ወይም የሆነ ልዩ የዕውቀት ሃይል ኖሮት ሳይሆን ቁጥር 9 እንደተብራራው መልካምና ክፉ የተባሉት የመኖር ሁኔታዎች የሰው ልጅ ለተሰጠው ትእዛዝ ባለው ግብረ መልስ የሚወሰን ነው።ምክንያቱም መልካም ብቻ ነው የሚያውቀው ዛፏን አትንካት ተብሏል ካልነካትም በዚህ መልካምነት ብቻ ይኖራል፥ትእዛዙን ከተላለፈና ዛፏን ቢበላ ግን ክፉን ያውቃል ማለትም በሞት(ከእግዚአብሔር መለየት፥የስጋና የነፍስ መለያየት) መቀጣት መጎስቆልን ያውቃል።ክፉና መልካም የሚያስታውቅ መባሉ ስለዚህ ነው።
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
18.“እግዚአብሔር አምላክም አለ፦ ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት።”
#የሚመቸውን_ረዳት ፦ ረዳት ባርያ ወይም ተገዢ ሳይሆን በባህርይ በሙላት እርሱን የምታክል ሆና ለዓይኑ ደስ የምታሰኝ ከእርሱ ጋር በደስታ የምትነጋገር በሁሉም ከእርሱ ጋር የምትስማማ ለሁኔታውና ለፍላጎቱ በሙሉ መልስ የምትሰጥ...
#እንፍጠርለት ፦ በምዕራፍ 1፥26 እንዳለው ትንታኔ በተመሳሳይ እዚህ ምንባብም እንጠቀመዋለን። እግዚአብሔር ሌሎች ፍጡራንን እያማከረ ሳይሆን፥ የመፍጠር ውሳኔ ምክረ-ሐሳብ ከራሱ ጋር ብቻ እንጂ ሌሎችን አላማከረምና በራሱ ከራሱጋር ማሰቡንና መወሰኑን የሚያሳይ ነው፥ ልክ እኛ እስኪ ዛሬ ይሄን ላድርግ ይሄን ልስራ ብለን በህሊናችን ከራሳችን ጋር እንደምንመክረው ነው።
?ኦሪት ዘፍጥረት 2፥11-15?
_____
#ማስታወሻ ፦ የተለያዩ ትናንሽ ምንጮች በተለያየና ዝቅተኛ ወደሆነ ቦታ በመፍሰስ እየተቀላቀሉ #መጋቢ_ወንዝን ይፈጥራሉ፤እነዚህ የተፈጠሩት መጋቢ ወንዞችም እየተቀላቀሉ አንድ ትልቅ ወንዝ ይፈጥራሉ።ትላልቅ የተባሉት ወንዞችም ወደሌላ ቦታ እንደፈሰሱ ከነርሱ ለሚበልጥ ወንዝ መጋቢ ሊሆኑ ይችላሉ።ይህ በዘመናችን ያለ የወንዝ አፈጣጠር ሂደት ነው። የመጀመርያው ግን የተለየ ነበረ ከኤደን የሚፈልቀው ትልቁ ወንዝ ወደ አትክልቱ ስፍራ(ገነት) ገብቶ እንዳጠጣ ሌላ አራት ወንዞችን ፈጥሮ ይወጣል።እዚህጋ መጋቢው ትልቁ ወንዝ ነው።
????????
11.“የአንደኛው ወንዝ ስም ፊሶን ነው እርሱም ወርቅ የሚገኝበትን የኤውላጥ ምድርን ይከብባል የዚያም ምድር ወርቅ ጥሩ ነው፤”
#ኤውላጥ(ሐዊላ) ፦ በኩሽ ልጅ (ዘፍ10፥7) የተሰየመ በሲና አከባቢ ያለ አገር(ዓረቢያ) ነው።ከገነት የወጣው የወንዙ አንደኛው ክፍል(ፊሶን) በዚህ አካባቢ ይፈስ የነበረ።
------------------------------------
13.“የሁለተኛውም ወንዝ ስም ግዮን ነው፤ እርሱም የኢትዮጵያን ምድር ሁሉ ይከብባል።”
#ኢትዮጵያ ፦ ይህ በዕብራይስጡ የኩሽ ምድር ብሎ ነቢዩ ሙሴ የፃፈውን ”ኢትዮጵያ” ተብሎ በግሪክኛ ሰባ ሊቃናት(septuagint) የተተረጎመ ነው።ፀሓፊው (ነቢይ ሙሴ) ቦታውን በቀጥታ ሲገልጥ፥የሰባ ሊቃናት ትርጉም ግን የፊትን ቀለም ስለሚገልፅ አሻሚ እሳቤ እንዲፈጠር አድርጓል።ምክንያቱም በግሪክኛ «ኢትዮጵያ» #ጥቁር ማለት ስለሆነ። ብዙ ሊቃውንት ደግሞ ወንዙ ከቪክቶሪያ ሃይቅ የሚነሳውና ዓባይን ጨምሮ ብዙ የብዙ ሃገራት ወንዞች እየመገቡት ወደ ግብፅ የሚፈሰው «የናይል-ወንዝ» ነው ብለው ተርጉመውታል።ነገር ግን ናይል ከጥፋት ውሃ በኋላ ባለው የመልክአ ምድር አቀማመጥ የተፈጠረ ወንዝ ስለሆነ ትርጓሜው አያስኬድም አመጣጡ ከኤደን እንደመሆኑ።ዞሮ ዞሮ ግዮን ወደ የአሁኑ አፍሪካ ይፈስ የነበረ ወንዝ ነው።
--------------------------
14.“የሦስተኛውም ወንዝ ስም ጤግሮስ ነው እርሱም በአሦር ምሥራቅ የሚሄድ ነው።”
#አሦር ፦ በሴም ልጅ ዘፍ10፥11 የተሰየመና ነነዌ መናገሻውን ያደረገ የአሁኖቹ ኢራቅ፣ቱርክ፣ኢራን ወዘተ የሚያጠቃልል ግዛት ነው።ጤግሮስ(tigris,hiddekel) በዚህ ግዛት በስተምስራቅ የሚፈስ ወንዝ ነው።
---------------------------
15.አራተኛውም ወንዝ ኤፍራጥስ ነው።”
ኤፍራጥስ ከአሶር በስተምዕራብ የሚፈስ ወንዝ ነው።እግዚአብሔር ለአብርሃም የሚሰጠው ርስት ድንበሩ እስከዚህ ወንዝ እንደሆነ ተጠቅሷል።??
“በዚያ ቀን እግዚአብሔር ለአብራም እንዲህ ብሎ ቃል ኪዳን አደረገ፦ ከግብፅ ወንዝ ጀምሮ እስከ ትልቁ ወንዝ እስከ #ኤፍራጥስ_ወንዝ ድረስ ይህችን ምድር ለዘርህ ሰጥቼአለሁ፤”— ዘፍጥረት 15፥18
#ትንሣኤ_ዘጉባኤ
⚠️የክርስቶስ መምጣት ቀርቧልና አለም ትገለበጣለች “ከበረሃ የመጣን ባሕታውያን ነን” የሚሉ ብዛታቸው... እውነተኛው በመፃሕፍት ያለው ሳይሆን ተለምዷዊው የሙታን ትንሣኤ ትምህርት “ #ሁሉም ሰው ሞቶ ይነሳል” የሚል ትምህርት በር ከፍቶላቸዋል።ስለዚህ ሲያስተምሩ “አለም ግልብጥብጥ ትልና ሁሉም ሰው ይሞታል ከዛ ክርስቶስ ይመጣል፡ክርስቶስ እንዲመጣ በአለም ያለው ሁሉም ሰው መሞት ግድ ነው ሞት መቅመስ አለበት!!” ይላሉ።
መድረክ ያገኘ እንደራሱ እሳቤ ብዙ ያልተፃፈ መናገር ልማድ ቢሆንም ቤተ ክርስቲያን ግን እንዲህ አላስተማረችም!!ታድያ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት ምን ይላል የሚለውን ስናይ:-
⚠️በርግጥ ጌታችን ኢየሱስ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ድርቅ፣ወረርሺኝና ጦርነት ለመምጣቱ #ምልክት እንደሆኑ ተናግሯል። በነዚህም ክስተቶች ሰው እንደሚሞትም የታወቀ ነው ነገር ግን ሁሉም ሰው ሞቶ ያልቃል አላለም።ይልቁን ክርስቶስ መጥቷል በዚህ አለ ቢሏችሁ እንዳታምኑ የመብረቅ ብልጭታ ለሁሉም እንደሚታይ እኔም ለሁሉ በግልጥ እየታየሁ በብዙ ክብር በደመና ነው የምመጣው ነበር ያለው። (ማቴ 24፥24-31)
ስለዚህ ጌታችን ክርስቶስ ዳግመኛ እኪመጣ ድረስ የሰው ልጅ እየተባዛና እየሞተ ኑሮው ይቀጥላል። ሲመጣም ሞት ያቆማል የሞቱም ሰዎች ይነሳሉ በሕይወት የነበሩትም የማይሞቱ በአንድነትም ዘለአለማውያን ወደመሆን ይለወጣሉ።ቅዱስ ጳውሎስም ይህንን የጌታችን ኢየሱስ መምጣትና የሙታን ትንሣኤ በሁለት መልእክታት አጠር አድርጎ በደምብ ገልፆታል።
?1ኛ ቆሮንቶስ 15
⁵¹-⁵² እነሆ፥ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ፤ ሁላችን #አናንቀላፋም ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋልና ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው #ይነሣሉ እኛም #እንለወጣለን ።
⁵³ ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሊለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሊለብስ ይገባዋልና።
⁵⁴ ዳሩ ግን ይህ የሚበሰብሰው የማይበሰብሰውን ሲለብስ ይህም የሚሞተው የማይሞተውን ሲለብስ፥ በዚያን ጊዜ፦ ሞት ድል በመነሣት ተዋጠ ተብሎ የተጻፈው ቃል ይፈጸማል።
?በተጨማሪም የተሰሎንቄ መልእክቱም ይህንን ያጠናክራል
1ኛ ተሰሎንቄ 4
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።
¹⁸ ስለዚህ እርስ በርሳችሁ በዚህ ቃል ተጽናኑ።
?መደምደሚያ:- የቤተ ክርስቲያን ምሥጢረ ትንሣኤ ሙታን ትምህርት በአጭሩ ይህ ነው።ምድርና ሰማይ የሚጠፉት ከተነጠቅን በኋላ ነው።እስከዛው ፍጥረት ሁሉ እንዲህ አሁን እንዳለው ይቀጥላል።
“በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።”
?ለማስታወስ ያክል
#መልካምንና_ክፉን_የሚያስታውቀውንም_ዛፍ :- ይህ ዛፍ በውስጡ የዕውቀት ሐይል ኖሮት አይደለም።ነገር ግን ባይነካው ፍጥረታት ሁሉ መልካም እንደሆኑ የተፈጥሮን መልካምነት ብቻ ያውቃል ቢበላው ደግሞ መቀጣትን መጎስቆልን ይቀምሳል ስለዚህ ዛፉ የሚያስታውቀው ኑሮን ነው ከመታዘዝ በፊትና በኋላ ያሉ መልካምና ክፉ ኑሮዎች በዛፉ ላይ በሚፈፀሙ ድርጊቶች ይወሰናል።ለምርጫ የተዘጋጀ ዛፍ ነው።
10.“ወንዝም ገነትን ያጠጣ ዘንድ ከዔድን ይወጣ ነበር፤ ከዚያም ለአራት ክፍል ይከፈል ነበር።”
ወንዙ ከኤደን ፈልቆ ገነትን ኣጠጥቶ ሲወጣ ወደ አራት ወንዞች ይከፈላል
ልብ በል:- ወንዞቹ ለአራት ተከፍለው የሚኖራቸውን ፍሰት በመፅሓፉ የተፃፈውና ኣሁን ያለው ጂኦግራፊያዊ የግዛቶቹ ኣቀማመጥ የተለያየ ነው በምዕራፍ 1፥9 ላይ
“⁹ እግዚአብሔርም፦ ከሰማይ በታች ያለው ውኃ #በአንድ ስፍራ ይሰብሰብ፥ የብሱም ይገለጥ አለ፤ እንዲሁም ሆነ።¹⁰ እግዚአብሔርም የብሱን #ምድር ብሎ ጠራው የውኃ መከማቻውንም #ባሕር አለው፤”
ብሏል ስለዚህ የብሱ እንዳሁኑ ክፍለዓለማት ተብሎ በባሕር ያልተከፋፈለ አንድ የብስ ነበረ ባሕሩም በአንድ የተሰበሰበ ውሃ ነበር ማለት ነው።እንዲህ ከነበረ የምድሪቱ ገፅታ እንዴት ሊቀየር ቻለ ካልን በኖህ ዘመን የነበረው የጥፋት ውሃ የብሱ መጀመርያ ላይ አንድ ከነበረበት ገፅታ እየተሰነጣጠቀና እየተንሸራተተ በመሃሉም ባህር እየፈጠረ አሁን ላይ ያለውን በኣህጉር የተከፋፈለ መልክአ ምድር እንዲይዝ ኣድርጎታል።
ሁሉንም የሚያሳልፍ ቅዱስ አምላክ ክፉውን ጊዜ አሳልፎ እንኳን ድጋሚ ኣገናኘን ምስጋና ውዳሴ ለስሙ ይሁን ለሰው ልጅ በሙሉም ሰላም ይሁን???
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
? Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 weeks, 1 day ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 2 months, 1 week ago