MUSILM EVANGELICAL TALKING

Description
በኔ ዘመን ወንጌል እንጂ ተረት ተረት አይሰበክም
" ሰዎች ሁሉ ሊድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ ሊደርሱ በሚወድ በእግዚአብሔር በመድኃኒታችን ፊት መልካምና ደስ የሚያሰኝ ይህ ነው።" (1ጢሞ2:3-4)

መሰረታዊ ትምህርቶችንም መማር #ለሚፈልጉትም ሊንኩን ሼር በማድረግ አገልግሎቱን ይደግፉ!!!

-ለማንኛውም
👇
@YeljinetHiwet 0919935413
@Cre8ed4purpose
@Melody128
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago

2 months, 3 weeks ago

1ኛ ዮሐንስ 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁸ ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።
¹⁹ ከእኛ ዘንድ ወጡ፥ ዳሩ ግን ከእኛ ወገን አልነበሩም፤ ከእኛ ወገንስ ቢሆኑ ከእኛ ጋር ጸንተው በኖሩ ነበር፤ ነገር ግን ሁሉ ከእኛ ወገን እንዳልሆኑ ይገለጡ ዘንድ ወጡ።

4 months ago
ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ Pastor Tesfaye Gabiso …

ፓስተር ተስፋዬ ጋቢሶ Pastor Tesfaye Gabiso | ቁጥር 8 ሙሉ አልበም Volume 8 Full Album
https://youtube.com/watch?v=cUrc-ZnGRAU&si=8rj1--sLAJZDL1f1

4 months, 1 week ago

እውነት አላህ የቁርኣን ጠባቂ ነው ተብሏልን? The Islamic Dilemma

ሙስሊሞች ከሚያነሱት ሙግቶች አንዱ፣ ቀጥሎ ያለው ነው:

"መፅሐፍ ቅዱስ የተበረዘው ሰዎች ጠባቂዎቹ ስለተባሉ ሲሆን የቁርአን ጠባቂ ግን አላህ ነው ተብሏል።"

የሚጠቅሱትም ሱራ ይሄ ነው: ሱራ 15:9

إِنَّا نَحْنُ نَزَّلْنَا الذِّكْرَ وَإِنَّا لَهُ لَحَافِظُونَ

እኛ "ቁርኣንን" እኛው አወረድነው፡፡ እኛም ለእርሱ ጠባቂዎቹ ነን፡፡

ነገር ግን እዚህ ላይ "ቁራኣን" ተብሎ የተተረጎመው - "አል-ዚክራ" የሚል ቃል እንጂ ቁርአን አይደለም

ዚክር- ማለት "reminder- ማስታወሻ፣ admonition- ምክር" ማለት ነው።

ታድያ መፅሐፍ ቅዱስ ዚክር አልተባለምን? መልሱ ተብሏል ነው።

ሱራ 21:48

وَلَقَدْ آتَيْنَا مُوسَىٰ وَهَارُونَ الْفُرْقَانَ وَضِيَاءً وَذِكْرًا لِّلْمُتَّقِينَ

ለሙሳና ለሃሩንም እውነትንና ውሸትን የሚለይን ብርሃንንም ለጥንቁቆችም መገሰጫን (ወዚክራ) በእርግጥ ሰጠናቸው፡፡

ሱራ 16:43

وَمَا أَرْسَلْنَا مِن قَبْلِكَ إِلَّا رِجَالًا نُّوحِي إِلَيْهِمْ ۚ فَاسْأَلُوا أَهْلَ#الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ

ከአንተም በፊት ወደእነሱ ወሕይን (ራእይን) የምናወርድላቸውን ሰዎችን እንጂ ሌላን አልላክንም፡፡ የማታውቁም ብትኾኑ #የዕውቀትን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

በዚህ ክፍል ላይ أَهْل الذِّكْرِ (አህላል-ዚክሪ) የሚለውን- የዕውቀትን ባለቤቶች ብለው ተርጉሞውታል። ኢብኑ ከሢር ግን በተፍሲራቸው አህለል ዚክር ማለት "the people of the previous Books" " የቀድሞ መጽሓፍት ባለቤቶች" ማለት እንደሆነ አስቀምጧል ።

ስለዚህ ለሙሴ የወረደውና ከቁርኣን በፊት የወረዱት መፅሓፍት "ዚክር" ከሆኑ፣ ሙግቱ ቀጥሎ ያለው ይሆናል:

1- አላህ ዚክሩን ያወረድነው እኛው ነን፣ እኛው ጠባቂዎቹ ነን ካለ እና ተውራት ዚክር ከሆነ፣ ተውራት ተበርዟል ካልን አላህ ውሸታም መሆኑ ነው። ምክኒያቱም አልጠበቀውማ።

2- አይ፣ ተውራት አልተበረዘም ከተባለም፣ አላህ ውሸታም ይሆናል። ምክኒያቱም ፔንታቱክ የምንላቸው ወይም "ተውራት" ውስጥ እግዚአብሔር ያስተማረው የቁርአን ተቃራኒ ናቸው።

ለምሳሌ: ዘጸአት 4

23 እስራኤል የበኵር ልጄ ነው፤ ይገዛልኝ ዘንድ ልጄን ልቀቅ አልሁህ፤ አንተም ትለቅቀው ዘንድ እንቢ አልህ፤ እነሆ እኔ የበኵር ልጅህን እገድላለሁ ትለዋለህ።

እንደ ቁርአን ትምህርት ግን አላህ ባሪያ እንጂ ልጅ የለውም!

3- አይ፣ ኦሪት ከተውራት ይለያል አልተጠበቀም ወይም አሁን ላይ ተውራት ጠፍቷል ከተባለም፣ አላህ መጀመሪያ ያወረደውን ዚክር አሁንም መጠበቅ አልቻለም ማለት ነው።

Hence, Islamic Dilemma! Damned if you do, damned if you don't!😄

4 months, 2 weeks ago

**.           ይገዛ ጉልበቴ
ዘማሪት መስከረም ጌቱ|New Song

⌚️5:00 ደቂቃ | ? 4.7 MB
sʜᴀʀᴇ? sʜᴀʀᴇ ? sʜᴀʀᴇ?**

5 months, 1 week ago

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያስተማረው ትምህርት ብቻ ሳይሆን ራሱ ማንነቱ፣ ሕይወቱና አገልግሎቱ የአስተምህሮ መሠረት ናቸው። የትኛውም በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተጠቀሰ ሰው በዚህ ሁኔታ የአስተምህሮ መሠረት ተደርጎ አይቆጠርም፣ ሊሆንም አይችልም። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፍፁም እንከን የለሽ ቅዱስና ጻድቅ በመሆኑ ስብዕናው የአስተምህሮ መሠረት ነው። የፍፅምናው ምክንያት ደግሞ ፅንፈ ዓለሙን የፈጠረ መለኮት መሆኑ ነው። ሥጋን ከለበሱት መካከል "ከእናንተ ስለ ኃጢአት የሚወቅሰኝ ማን ነው?" በማለት በራስ መተማመን ሊጠይቅ የሚችለው እርሱ ብቻ ነው (ዮሐ. 8:46)። እርሱ በሥጋ የተገለጠ አምላክ ነውና። የክርስትና መሠረቱ በፍፅምናው ፍጥረት ሁሉ የመሰከረለት ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
-------
ከክርስትና በተጻራሪ እስልምና በብዙ ኃጢአቱ የሚታወቀውን ሙሐመድ የተሰኘ ግለሰብ የአስተምህሮ መሠረት አድርጓል። በሙስሊሞች ዘንድ የሙሐመድ ትምህርቱ ብቻ ሳይሆን ሁለንተናው የአስተምህሮ ምንጭና መሠረት ነው። በዚህም ምክንያት ለሙስሊሙ ዓለም ዕዳ የሆኑ እርባና በሌላቸው ትረካዎች የተሞሉ ኁልቊ መሣፍርት የሌላቸው መጻሕፍት ተጽፈዋል። የሁሉም ትኩረት ደግሞ አንዱ ግለሰብ ነው። በአንድ ወገን እርሱ የፈፀማቸውን ጆሮን ጭው የሚያደርጉ የነፍሰ ገዳይነት፣ የሴት-አውልነትና የዝርፊያ ታሪኮች እየነገሩን በሌላ ወገን ደግሞ የዚያኑ ግፈኛ ግለሰብ ቅድስና ይነግሩናል። በተግባሩ ርኩስ እንደሆነ የነገሩንን ያንኑ ሰው በቃላት ቅዱስ ያደርጉታ። የሙስሊሙ ዓለም ምንኛ የከሰረ ነው! ክርስትናና እስልምና ልዩነታቸው የብርሃንና የጨለማ፣ የሕይወትና የሞት፣ የጽድቅና የኩነኔ ያህል ነው!

11 months ago

የሱራ 9፡31 ሁለት መሠረታዊ ችግሮች“ከርሱ በቀር ሌላ አምላክ የሌለዉን አንድን አምላክ ሊገዙ እንጂ ያልታዘዙ ሲሆኑ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን የመርየምን ልጅ አልመሲሕንም ከአላህ ሌላ አማልክት አድርገው ያዙ፤ ከሚያጋሩት ሁሉ የጠራ ነው።” (ሱረቱ አል-ተውባህ 9፡31)

የመጀመርያው የዚህ ጥቅስ ችግር እስላማዊ አስተምህሮን በመጻረር ኢየሱስ አምላክ መሆኑን መናገሩ ነው፡፡ የአማርኛና ብዙ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች ከላይ በሚገኘው መንገድ “የመርየም ልጅ አልመሲሕ” የሚለውን “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን” ከሚለው ጋር በመደመር ቢተረጉሙትም የአረብኛው ጽሑፍ “አልመሲሕ” የሚለውን ከአላህ በኋላ በማምጣት “ወ” (እና) በሚል መስተጻምር ያያይዛቸዋል፡-

اتَّخَذُوا أَحْبَارَهُمْ وَرُهْبَانَهُمْ أَرْبَابًا مِنْ دُونِ اللَّهِ وَالْمَسِيحَ ابْنَ مَرْيَمَ
“አትተኸዙ አሕባረሁም ወ ሩህባነሁም አርባባን ሚን ዱኒ አላሂ ወ አል-መሲሐ ኢብነ መርየም …”

ቀጥተኛው ትርጉም “ከአላህና ከአልመሲሕ የመርየም ልጅ ሌላ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ጌቶች አድርገው ያዙ…” የሚል ነው፡፡ ለዋናው የአረብኛ ንባብ ሃቀኛ መሆን የፈለጉ አንዳንድ የእንግሊዝኛ ትርጉሞች በዚህ ጉዳይ የተፈተኑ ይመስላሉ፡፡ በዚህም ምክንያት በአረብኛው ጥቅስ ውስጥ የማይታይ የኮማ ስርዓተ ነጥብ በመጠቀም ለማስተካከል ሞክረዋል፡-

They have taken their doctors of law and their monks for lords besides Allah, AND (also) the Messiah son of Marium… (Shakir)

They take their doctors and their monks for lords rather than God, AND the Messiah the son of Mary… (Palmer)

They take their priests and their monks for [their] lords, besides God, AND Christ the son of Mary… (Sale)

ይህ የቁርአን ጥቅስ ክርስቲያኖች ከአላህ እና ከመሲሑ ውጪ ሌሎችን ማምለክ የማይገባቸው ሆነው ሳሉ ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን ያመልካሉ በማለት ወቀሳ ያቀርባል፤ ስለዚህ በጥቅሱ መሠረት ኢየሱስ አምልኮ የተገባው አምላክ ነው፡፡

ሙስሊም ሰባኪያን ይህንን እውነታ ለማስተባበል “መሲሐ” የሚለው حَ በፈትሃ ስለተጻፈ የዓረፍተ ነገሩ ባለቤት ሳይሆን ተሳቢ በመሆኑ ከሊቃውንትና መነኮሳት ጋር መቆጠር አለበት ይላሉ፡፡ ነገር ግን ይህ አጻጻፍ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች ውስጥ ያልነበረ ሲሆን ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ነው፡፡ ጥንታዊው የአረብኛ አጻጻፍ አናባቢ ነቁጦች (diacritical marks) ስላልነበረው ከጊዜ በኋላ የተጨመረ ምልክት በመጠቀም መሞገት አሳማኝ አይደለም፡፡ የቁርአን ደራሲ ይህንን ችግር ለማስወገድ ቢፈልግ ኖሮ በቀዳሚያን ማኑስክሪፕቶች መሠረት ክርስቶስ አምላክ መሆኑን በሚያረጋግጥ መንገድ ሐሳቡን ከመግለፅ ይልቅ አላህና መሲሑን ነጣጥሎ “አልመሲሕ” የሚለውን ቃል “ሊቃውንቶቻቸውንና መነኮሳታቸዉን..” ከሚለው በፊት ወይም በኋላ ማስቀመጥ ይችል ነበር፤ ነገር ግን አላደረገውም፡፡

ሁለተኛው የዚህ ጥቅስ ችግር ክርስቲያኖች የሃይማኖት አባቶቻቸውን እንደሚያመልኩ በሐሰት መክሰሱ ነው፡፡ በሙሐመድ ዘመን የነበሩ ሰዎች ይህንን ችግር በመረዳት “ክርስቲያኖች ሊቃውንትና መነኮሳትን አያመልኩም እኮ” በማለት ሙሐመድን ለማረም እንደሞከሩ እስላማዊ ምንጮች ይናገራሉ፡፡ የሙሐመድ ምላሽ የነበረው “አይሁድና ክርስቲያኖች ረበናትና መነኮሳት የተፈቀደውን ሲከለክሏቸው ወይም የተከለከለውን ሲፈቅዱላቸው ይታዘዟቸዋል፤ ይህ አምልኮ ነው” የሚል ነበር፡፡ (Tafsir Ibn Kathir (Abridged), 2000, Volume 4, pp. 409-410)

የተፈቀደውን የሚከለክልና የተከለከለውን የሚፈቅድን ሰው መታዘዝ አምልኮ ከተባለ በቁርአን መሠረት ዒሳ የተከለከለውን የመፍቀድ ሥልጣን እንዳለውና የእርሱን ትዕዛዛት መከተል አስፈላጊ መሆኑ ስለተነገረ በተዘዋዋሪ ቁርአን ኢየሱስን ማምለክ ትክክል መሆኑን ያረጋግጣል ማለት ነው!

“ከተዉራትም ከኔ በፊት ያልለዉን ያረጋገጥሁ ስሆን የዚያንም በናንተ ላይ እርም የተደረገዉን ከፊል ለናንተ #እፈቅድ_ዘንድ፥ (መጣኋችሁ) ከጌታችሁም በሆነ ታምር መጣሁዋችሁ አላህንም ፍሩ፤ #ታዘዙኝም።” (ሱረቱ አሊ-ዒምራን 3:50)

እንደ እስልምና አስተምህሮ ሁሉ ነገር የተምታታበት አስተምህሮ በምድር ላይ ይገኝ ይሆን?

11 months, 2 weeks ago

ይቀጥላል

11 months, 2 weeks ago

ሙስሊም ወገኖቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስ ያስተማረው በአረማይክ ቋንቋ ስለነበረ የአረማይክ ወንጌል አምጡ ይሉናል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ቁርአን መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ቋንቋቸው እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች አልተላኩም በማለት ስለሚናገር ነው፡- “ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።”…

11 months, 2 weeks ago

ሙስሊም ወገኖቻችን ብዙ ጊዜ ክርስቶስ ያስተማረው በአረማይክ ቋንቋ ስለነበረ የአረማይክ ወንጌል አምጡ ይሉናል፡፡ ለዚህ ምክንያታቸው ቁርአን መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ቋንቋቸው እንጂ በሌሎች ቋንቋዎች አልተላኩም በማለት ስለሚናገር ነው፡-

“ከመልክተኛ ማንኛውንም፤ ለነርሱ ያብራራላቸው ዘንድ በወገኖቹ ቋንቋ እንጂ በሌላ አልላክንም፤ አላህም የሚሻውን ያጠማል፤ የሚሻውንም ያቀናል፤ እርሱም አሸናፊው ጥበበኛው ነው።” (ሱረቱ ኢብራሂም 14፡4)

ነገር ግን ቁርአን ለዒሳ “ኢንጂል” የተባለ መጽሐፍ እንደተሰጠው ይናገራል፡-

“በፈለጎቻቸውም (በነቢያቶቹ ፈለግ) ላይ የመርየምን ልጅ ዒሳን ከተውራት በስተፊቱ ያለውን አረጋጋጭ ሲሆን፣ አስከተልን፤ ኢንጂልንም በውስጡ ቀጥታና ብርሃን ያለበት በስተፊቱ ያለችውን ተውራትንም የሚያረጋግጥ ለጥንቁቆችም መሪና ገሣጭ ሲሆን ሰጠነው።” (ሱረቱ አል-ማኢዳህ 5፡46)

“ኢንጂል” የሚለው ቃል Εὐαγγέλιον “ኤዋንጌሊዮን” ከሚለው የግሪክ ቃል የተወሰደ መሆኑን ሊቃውንት ይስማማሉ፡፡ ስለዚህ መልእክተኞች ሁሉ በገዛ ሕዝባቸው ቋንቋ ብቻ ተልከው ከነበሩ ለዒሳ ተሰጠ የተባለው መጽሐፍ ቋንቋው ግሪክኛ ሊሆን እንዴት ቻለ? የቁርአን ደራሲ መልእክተኞች በገዛ ቋንቋቸው ብቻ እንደተላኩ ተናግሮ ካበቃ በኋላ በግሪክ ቋንቋ የተጻፈ መጽሐፍ ለዒሳ እንደተሰጠው መናገሩ የአይሁድን ቋንቋ ባለማወቁ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ እንዲህ ያለ የተምታታ ጽሑፍ በዘላለማዊነት በፈጣረ ዘንድ እንደነበረ ማመን መታወር ነው!

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 months, 1 week ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 4 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month ago