ኦርቶዶክሳዊ ጥቅስ መጽሔት

Description
"ልጄ ሆይ በክርስትናህ መጎልመስ ከፈለክ ከቅዱሳት መጻህፍት ጋር ራስህን አዛምድ"
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
🌷 t.me/bibleztewahido 🌷
🌷 t.me/bibleztewahido 🌷
  🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷🌷
https://t.me/+Q8cDirroZudEPWKP
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 day, 5 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 2 weeks ago

5 дней, 20 часов назад

የኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት
ወልደ እግዚአብሔር፣ ወልደ ማርያም (የእግዚአብሔር አብ ልጅ፣ የድንግል ማርያም ልጅ) ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለት ልደታት አሉት፡፡ የመጀመሪያው (ቀዳማዊ) ልደት ዘመን ከመቆጠሩ ዓለም ከመፈጠሩ በፊት እግዚአብሔር ወልድ ከእግዚአብሔር አብ ከሰው አእምሮ በላይ በሆነ ምሥጢር (አካል ዘእምአካል ባህርይ ዘእምባህርይ) የተወለደው ልደት ነው (መዝ 2፥7 መዝ 109፥3 ምሳ 8፥25)፡፡ ሁለተኛው (ደኀራዊ) ልደቱ ደግሞ  ዓለም ከተፈጠረ አዳም ከበደለ ከአምስት ሺ አምስት መቶ ዘመን በኋላ ከቅድስት ድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደው ልደት ነው (ገላ 4፥4 ኢሳ 7፥14 ኢሳ 9፥6 ዘፍ 3፥15 ፤18፥13 ፤ 12፥8 ፣ መዝ 106፥20)፡፡ ዘመን የማይቆጠረለት፣ በቅድምና ከአብ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር የነበረ፣ ዓለምንም በአምላክነቱ የፈጠረ የእግዚአብሔር ልጅ፣ አካላዊ ቃል መለኮታዊ አካሉን፣ መለኮታዊ ባሕርይውን ሳይለቅ በተለየ አካሉ ንጽሕት፣ የባሕርያችን መመኪያ ከምትሆን  ከድንግል ማርያም በሥጋ በተወለደ ጊዜ አምላካዊ አካልና ባሕርይን ከሰው አካልና ባሕርይ ጋር ያለመጠፋፋት፣ ያለመቀላቀል ተዋሐደ እንጅ አካሉም ባሕርይውም አልተለወጠም፡፡
ሊቁ አባታችን ቅዱስ ፊሊክስ የጌታችንን ቀዳማዊና ደኀራዊ ልደቱን በተናገረበት አንቀጽ “ዓለም ሳይፈጠር ከእግዚአብሔር አብ የተወለደው በኋላ ዘመን በእመቤታችን በቅድስት ድንግል ማርያም ማኅፀን ያደረ እርሱ ነው፤ እርሱ ሰውም ቢሆን አንድ አካል፣ አንድ ገፅ፣ አንድ ባሕርይ ነው” በማለት ሁለቱን ልደታት አስተምሯል፡፡ ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ፊሊክስ 38፡10 በተጨማሪም ቅዱስ ናጣሊስ “ከእግዚአብሔር አብ በተወለደው በቀዳማዊ ልደቱ የእግዚአብሔር አብ ልጅ ነው፤ ከድንግል በተወለደው በደኃራዊ ልደቱ የሰው ልጅ ሆነ፡፡ እርሱ አንዱ በመለኮት ከአብ ጋር አንድ የሚሆን የሚተካከል ፍጹም አምላክ ነው፤ እርሱ ብቻ ከድንግል በተወለደው ልደት በሥጋ ከሰው ጋር አንድ የሚሆን ፍጹም ሰው ነው፡፡” ብሏል፡፡ (ሃይማኖተ አበው ዘቅዱስ ናጣሊስ 46፡3-4)

5 дней, 20 часов назад

“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።”
— ሚክያስ 5፥2

“ሕፃን ተወልዶልናልና፥ ወንድ ልጅም ተሰጥቶናልና፤ አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል፤ ስሙም ድንቅ መካር፥ ኃያል አምላክ፥ የዘላለም አባት፥ የሰላም አለቃ ተብሎ ይጠራል።”
— ኢሳይያስ 9፥6

“ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኃኒት እርሱም ክርስቶስ ጌታ የሆነ ተወልዶላችኋልና።”
— ሉቃስ 2፥11

1 неделя, 5 дней назад

“የእግዚአብሔርን ቸርነት በሕያዋን ምድር አይ ዘንድ አምናለሁ።እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ፤ በርታ፥ ልብህም ይጽና፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ።”
— መዝሙር 27፥13-14

2 месяца, 3 недели назад

"እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም እንደ ሥራው መጠን እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ። አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።
ወደ ሕይወት ዛፍ ለመድረስ ሥልጣን እንዲኖራቸው በደጆችዋም ወደ ከተማይቱም እንዲገቡ ልብሳቸውን የሚያጥቡ ብፁዓን ናቸው።"

የዮሐንስ ራእይ 22:12-14

2 месяца, 3 недели назад

"ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ ይህም እንደ ራሱ አሳብና ጸጋ መጠን ነው እንጂ እንደ ሥራችን መጠን አይደለም፤ ይህም ጸጋ ከዘላለም ዘመናት በፊት በክርስቶስ ኢየሱስ ተሰጠን"
2ኛ ጢሞ 1÷9

2 месяца, 3 недели назад

1ኛ ነገሥት 12:6-11

⁶ ንጉሡም ሮብዓም፦ ለዚህ ሕዝብ እመልስለት ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? ብሎ አባቱ ሰሎሞን በሕይወቱ ሳለ በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ሽማግሌዎች ጋር ተማከረ።
⁷ እነርሱም፦ ለዚህ ሕዝብ አሁን ባሪያ ብትሆን ብትገዛላቸውም፥ መልሰህም በገርነት ብትናገራቸው፥ በዘመኑ ሁሉ ባሪያዎች ይሆኑልሃል ብለው ተናገሩት።
⁸ እርሱ ግን ሽማግሌዎች የመከሩትን ምክር ትቶ ከእርሱ ጋር ካደጉትና በፊቱ ይቆሙ ከነበሩት ብላቴኖች ጋር ተማከረ።
⁹ እርሱም፦ አባትህ የጫኑብንን ቀንበር አቃልልልን ለሚሉኝ ሕዝብ እመልስላቸው ዘንድ የምትመክሩኝ ምንድር ነው? አላቸው።
¹⁰ ከእርሱም ጋር ያደጉት ብላቴኖች፦ አባትህ ቀንበር አክብዶብናል፥ አንተ ግን አቃልልልን ለሚሉህ ሕዝብ፦ ታናሺቱ ጣቴ ከአባቴ ወገብ ትወፍራለች።
¹¹ አሁንም አባቴ ከባድ ቀንበር ጭኖባችኋል፥ እኔ ግን በቀንበራችሁ ላይ እጨምራለሁ፤ አባቴ በአለንጋ ገርፎአችኋል፥ እኔ ግን በጊንጥ እገርፋችኋለሁ በላቸው ብለው ተናገሩት።

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 1 day, 5 hours ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 1 month, 2 weeks ago