Al Tewba -አል ተውባህ ቲዩብ

Description
وَمَنْ أَحَسَنُ قَوْلاََ مَّعَّن دَعَا الَی اللَّهِ وَعَمِل صَالحََا وَقَال اِنَّنِي مِنَ الْمُسْلِمِينِ

ወደ አላሕ ከጠራና መልካምንም ከሠራ "እኔ ከሙስሊሞች ነኝ"ካለም ሰው ይበልጥ ቃሉ ያማረ ማን ነው???

((من یرد الله به خیرا یفقهه في الدي))

For suggestion ????
@Lightofislambot
Advertising
We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 months ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 months, 2 weeks ago

6 months, 2 weeks ago

⭕️መረጋጋት የተወደሰ ተግባር ሲሆን

?መቸኮል የተወገዘ ና የተኮነነ ተግባር ነው

?يقول الله تعالى «يآئها الذين ءامنوا إن جآءكم فاسق بنبإ فتبينوا ...» الحجرات، الآية ٦

?قال المفسرون :— «التبين»
➡️አንድን ነገር እርግጥ ማለትና በሱ አለመፈጠን ማለት ነው
➡️በመጣው ዜናና በተከሰተው ክስተትማስረጃ ሊኖረን እንደሚገባ ይጠቁማል ይላሉ

?ፈትሁል ቀዲር 5/71

?قال الإمام الشوكاني رحمة الله عليه

قال الله تعالى «كلا بل تحبون العاجلة »

«كلا»
የሚለው ቃል የሚጠቁመው ችኮላን መተው እንዳለብንና መረጋጋት ላይ መፅናት እንዳለብን ይጠቁማል

?ፈትሁል ቀዲር 5/407

⬅️وروى الترميذي عن سهل بن سعد الساعدي رضي الله عنهما قال :قال رسول الله صلى الله عليه وسلم

«الأنة من الله والعجلة من الشيطان»

❝መረጋጋት ከ አላህ ነው
ችኮላ ከሸይጣን ነው❞

?و حسنه الحافظ في بلوغ المرام 1026
ورواه أبو يعلى والبيهقي عن أنس بن مالك رضي الله عنه بنحوه وحسنه جمع من أهل العلم ومنهم الشيخ الألباني في الصحيحة 1790

⬅️وروى الإمام مسلم أن رسول الله صلى الله عليه وسلم قال لأشج عبد القيس :❞إن فيك خصلتين يحبهما الله :الحلم والأنة ❝

?ነቢዩ صلى الله عليه وسلم ለአሸጅ ኢብኑ ቀይስ እንዲህ አሉት :~

«ባንተ ውስጥ ሁለት አላህ የሚወዳቸው ነገር አሉ :~
1:=አስተዋይ የሆነ አእምሮ ና
2:=መረጋጋትና መቻኮልን መተው

?قال العلمآء
«መፍጠን መቻኮል በአብዛሃኛው ግዜ የተከለከለ ነው ሰለዚህ ሙስሊም በሆነ አካል ላይ በነገራቶች ላይ አለመፍጠንና መረጋጋት ግድ ይላል»

???አደራ እናስተዉል

ለሁሉም ነገር እንረጋጋ አንቸኩል
«የተረጋጋ ቅቤ ይወጣዋል አይደል የተባለው»

➡️ስንረጋጋ በኛና በፈጣሪ መካከል ያለዉን እናስተካክላለን
➡️ስንረጋገሰ ከራሳችን ጋር እንታረቃለን
➡️ስንረጋጋ በዙሪያችን ያሉትን ሰዎች ማክበርና የነሱን ደረጃ እንረዳለን
➡️ስንረጋጋ ከሌሎች ጋር ጡሩና ያማረ ስነመግባር ስለሚኖረን ደስታ ያለዉን ህይወት እንኖራለን
.
.
.
ወዘተ

➡️በፈጠን ምክኒያት ስንቱ ካኣላህ ርቁዋል
➡️በፍጠኑ ስንቱ የሚወደዉን ተዳሩን አፍርሱዋል
➡️በፍጠኑ ስንቱ ከሚወዳቸው ጎዋደኞቹ, ቤተሰቦቹ ተራርቁዋል

https://t.me/LightofQuran2AB/2582

7 months, 2 weeks ago

14 የጁምዓ ቀን ሱናዎች

1 ገላን መታጠብ።
2. ሽቶን መቀባባት እና መዋብ።
3. ሲዋክን መጠቀም።
4. የክት ልብስ መልበስ።
5. በጊዜ መስጂድ መጓዝ።
6. በእግር እየተጓዙ ወደ መስጅድ መሄድ።
7. መስጂድ ከደረሱ በኋላ የሰዎችን ትከሻ በመረማመድ ሰዉን አለማስቸገር።
8. ኢማሙ ኹጥባ እያደረገ ቢሆንም ተህየቱ መስጂድ መስገድ።
9. ኹጥባ ወደ የሚያደርገው ኢማም መዞርና እሱን እያዩ ኹጥባ ማድመጥ።
10. ኹጥባ በሚደረግበት ሰዓት ፀጥታን መላበስ።
11. ሰደቃን ማብዛት።
12. ከሀሙስ ማታ ጀምሮ እሰከ ጁምዓ ዐስር ድረስ ሱረቱ ከሕፍ መቅራት።
13. ድዓ ተቀባይነት የሚያገኝበት ሰዓትን መጠባበቅ።
14. በነቢዩ ﷺ ላይ ሰለዋትን በብዛት ማውረድ።

-----------------------------
???
በቴሌግራም ይ?️?️ሉን!
???

https://t.me/LightofQuran2AB

7 months, 2 weeks ago

«የወራቶች ሁሉ ምርጥ ረመዳን ሲሆን የቀናቶች ሁሉ ምርጥ ደግሞ ጁምዓ ቀን ነው»።

ኢብኑል ቀይም(ረሂመሁሏህ)
ምንጭ፦?ዛዱል መዓድ (1-398)

https://t.me/LightofQuran2AB

8 months, 3 weeks ago

?ለይለተል  ቀድር

(1) إِنَّآ أَنزَلْنَٰهُ فِى لَيْلَةِ ٱلْقَدْرِ
(2) وَمَآ أَدْرَىٰكَ مَا لَيْلَةُ ٱلْقَدْرِ
(3) لَيْلَةُ ٱلْقَدْرِ خَيْرٌ مِّنْ أَلْفِ شَهْرٍ
(4) تَنَزَّلُ ٱلْمَلَٰٓئِكَةُ وَٱلرُّوحُ فِيهَا بِإِذْنِ رَبِّهِم مِّن كُلِّ أَمْرٍ
(5) سَلَٰمٌ هِىَ حَتَّىٰ مَطْلَعِ ٱلْفَجْرِ

(1) እኛ (ቁርኣኑን) በመወሰኛይቱ #ሌሊት አወረድነው፡፡
(2) መወሰኛይቱም #ሌሊተ ምን እንደ ኾነች ምን አሳወቀህ?
(3) መወሰኛይቱ #ሌሊት ከሺሕ ወር በላጭ ናት፡፡
(4) በርሷ ውስጥ መላእክትና መንፈሱ በጌታቸው ፈቃድ በነገሩ ሁሉ ይወርዳሉ፡፡
(5) እርስዋ እስከ ጎህ መውጣት ድረስ ሰላም ብቻ ናት፡፡ አልቀድር 97:1-5

አላህ(ሱወ) ‹‹መወሰኛቱ ለሊት #ከሺ ወር በላጭ ናት››  ቀድር፡3

??ይቺ #ለሊት  በአለማት ውስጥ በአመቱ ምን ምን እንደሚፈጸም ውሳኔ የሚተላመፍበት ናት.

?ቀደምት ህዝቦች ከሺ አመት በላይ እድሜ ስለነበራቸው  ይህ ህዝብ ያለችውን ትንሽ እድሜ ከነሱ ጋር ለማስተካከል የተሰጠ እድል ነው.

*?ነብዩ(ሰዐወ) እንዲህ  ያሉትም ለዚህ ነዉ ‹‹ የተባረከዉ ወር መጣላቹ … በርሱም አንዲት #ሌሊት አለች ከአንድ ሺ ወር በላይ ዋጋ ያላት፣   የዚችን #ሌሊት ትሩፋት መጎናፀፍ ያልቻለ፣ (ሌላ በጎ እድልም)  እርም   ይሆንበታል››*

?በተጨማሪ ነብዩ(ሰዐወ)  ‹‹ለሰላት ቆሞ ሀያሉዋን #ለሊት በኢባዳ በኢማን ከልብ ምንዳ አገኛለሁ ብሎ ያሳለፋት ሁሉም ያለፈ ወንጀሉ ይማሩለታል››

https://t.me/LightofQuran2AB/2564

9 months ago

**አስተውል

ረመዷን በፍጥነት መሄዱና ማለቁ ብቻ ሳይሆን በዛው ልክ አንተም በፍጥነት ወደ ቀብር እየቀረብክ መሆኑንም ጭምር አስታውስ

እያንዳንዱ ቀን ማለት እድሜህ ነው። አንድ ቀን ባለፈ ቁጥር ከድሜህ አንድ ቀን ተቀንሶ አንድ እርምጃ ወደ ሞት እየገሰገስክ መሆኑን እወቅ።**https://t.me/LightofQuran2AB/2561

9 months ago

የአደባባይ ኢፍጣር
በሸሪአ ማስረጃ እይታ።
አምና የተዘጋጀ። አሁንም በድጋሚ የተለቀቀ
https://t.me/SadatKemalAbuMeryem

https://t.me/LightofQuran2AB/2560

11 months ago

*?ካልሲ (ሁፍ) ላይ ስለ ማበስ
ምን ያህል ያውቃሉ
⁉️*

አንድ ሰው ውዱእ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ለማበስ ከፈለገ……
?ካልሲው ሲለብሰው ዉዱእ ያለው ሆኖ መልበስ አለበት።
?ካልሲው ከነጃሳ የጠራ ንፁህ መሆን አለበት።
?ካልሲው የእግሩ ለውዱእ የሚታጠበውን ቦታ መሸፈን መቻል አለበት; ቢያንስ ቁርጭምጭሚቱን የሚሸፍን መሆን አለበት።

?ካልሲው ላይ ማበስ የሚችለው ዉዱእ በሚያደርግ ጊዜ ብቻ ነው; ለጀናባ እና ለመሳሰለ ትጥበት የሚታጠብ ከሆነ ማበስ አይችልም።

?ካልሲው የተቀደደ ቢሆንም ማበስ ይችላል።
?ካልሲው ቀጭን ቢሆንም ማበስ ይችላል።

?በሚያብስ ጊዜ እጆቹ ላይ አንድ ጊዜ ውሀውን አፍስሶ ከደፋው በኋላ ጣቶቹን ይዘረጋቸውና በሁለቱ እጆቹ ሁለቱ እግሮቹ ላይ ያብሳል። በቀኝ እጁ ቀኝ እግሩ ሲያብስ; በግራ እጁ ግራ እግሩ ያብሳል።
★ሲያብስ በእጆቹ ብቻ ያብሳል እንጂ ውሃው ካልሲው ላይ አይረጭም።
★ሲያብስ የእግሩ የላይኛው ክፍል ብቻ ያብሳል እንጂ የውስጥ እግሩን አያብስም አይነካካም።

?ካልሲው የለበሰው ውዱእ ላይ ሆኖ ከነበረ ቀጣይ ውዱእ ሲያደርግ “እግሬን ማጠብ አለብኝ” ብሎ ካልሲውን ለማውለቅ መቸገር የለበትም።

?ካልሲውን ካበሰበት በኋላ ቢያወልቀው ውዱውን አይበላሽበትም አይፈርስበትም; ካልሲው ካበሰ በኋላ ቢያወልቀውም ባደረገው ውዱእ መስገድ ይችላል።

?አንዴ በለበሰው ካልሲ ማበስ የሚችለው;
★መንገደኛ ለ3 ቀናት ማበስ ይችላል።
★መንገደኛ ካልሆነ ግን ቀንና ማታ (24 ሰዓት) ነው ማበስ የሚችለው።

?የማበሻ ጊዜው የሚቆጠረው ካልሲው ከለበሰው ጊዜ ጀምሮ ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ነው።
ለምሳሌ፦
ሰኞ ቀን ዙሁር ላይ ውዱእ አድርጎ እግሩን ታጥቦ ካልሲውን ቢለብሰው። እስከ መግሪብ ድረስ ውዱእ ሳይፈታ ቆየና መግሪብ ላይ ውዱእ ተበላሽቶበት ውዱእ ሲያደርግ ካልሲው ላይ ቢያብስ; ይህ ካልሲ የማበሻ ጊዜው መቁጠር የሚጀመረው ከመግሪብ ሰዓት ጀምሮ ነው። በዚህም መሰረት ማክሰኞ ቀን ልክ የመግሪብ ወቅት ሲደርስ በዚህ ካልሲ ላይ ማበስ አይችልም ያበቃል ማለት ነው።
★ልብ ይበሉ
ይህንኑ ሰውዬ ማክሰኞ መግሪብ ከመድረሱ በፊት ውዱእ አድርጎ በካልሲው ላይ አብሶ ከሆነና ይህንን ውዱእ መግሪብም ላይ ካልተበላሸበት የካልሲው ማበሻ ጊዜ በማለቁ ብቻ ውዱኡውን አይበላሽበትም። ማበስ አይችልም እንጂ የነበረው ውዱእ እስካልፈታ ድረስ መስገድ ይችላል።
★መንገደኛ የሆነውም ሰው ምሳሌው አሁን ባየነው መልኩ ከለበሰበት ሳይሆን ማበስ ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ሶስት ቀናቶች ይቆጠሩለታል።
★★★★★★★★★★★★

?ጀሪር ቢን ዐብደላህ አልበጀሊ ባስተላለፈው;
«رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم بالَ، ثم توضأَ ومسحَ على خُفَّيْهِ»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ተፀዳድተው ውዱእ ሲያደርጉ ሁፋቸው ላይ ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።» ይላል።

?ሙጊራ ኢብኑ ሹዕባ ባስተላለፈው;
«كنت مع النبي صلى الله عليه وسلم في سفر، فأهويت لأنزِع خفيه، فقال: (دَعْهُما، فإني أدخلتهما طاهرتين»
«ከአላህ መልእክተኛﷺ ጋ በጉዞ ላይ ነበርኩኝ, ሁፋቸውን ላወልቅላቸው ዝቅ ስል "ተዋቸው ውዱእ ላይ ሆኜ ነው ያደረኳቸው" አሉኝ።» ይላል።

?ሹረይህ ቢን ሃኒ የማበሻ ጊዜው ምን ያህል እንደ ሆነ ልጠይቃት ወደ ዓኢሻ ስሄድ "ወደ ኢብን አቡ ጧሊብ ሂድና ጠይቀው, እሱ ከረሱልﷺ ጋ ጉዞ ያበዛ ነበር" አለችኝ። ሄጄ ስጠይቀው;
«جعل رسول الله صلى الله عليه وسلم ثلاثة أيام ولياليهن للمسافر، ويومًا وليلة للمقيم»
«የአላህ መልእክተኛﷺ ለመንገደኛ ሶስት ቀናቶች ከሌሊታቸው ጋ ሲያደርጉ ቋሚ ለሆነ ሰው ደግሞ ቀንና ሌሊት አደረጉለት አለኝ።» ይላል።

?ሰፍዋን ቢን ዓሳል ባስተላለፈው;
«كان رسول الله صلى الله عليه وسلم يأمُرُنا إذا كنا سَفْرًا [مسافرين] أن لا ننزِع خِفافنا ثلاثة أيام ولياليهن، إلا من جنابة، ولكن من غائط وبول ونوم»
«መንገደኛ በሆንን ጊዜ የአላህ መልእክተኛﷺ ለሶስት ቀናት ሁፋችን እንዳናወልቅ ያዙን ነበር; ጀናባ ከሆንን በስተቀር; በውሃ ሽንት፣ በሰገራ ወይም በእንቅልፍ [ውዱእ ከፈታን ግን አናወልቅም]።» ይላል።

?ዓልይ አላህ ስራውን ይውደድለት እንዲህ ይላል ነበር;
«لو كان الدين بالرأي لكان أسفل الخف أولى بالمسح من أعلاه، وقد رأيتُ رسولَ الله صلى الله عليه وسلم يمسح على ظاهر خفيه»
«ዲን በሰዎች ዕይታ (ራዕይ) ቢሆን የሁፍ የታችኛው ማበስ የላይኛው ከማበስ የበለጠ የተገባ ይሆን ነበር; በእርግጥም የአላህ መልእክተኛﷺ በላይኛው ሁፋቸው ሲያብሱ አይቻቸዋለሁ።»
★★★★★★★★★★★★

?ልብ ይበሉ‼️
?ያለንበት ወቅት በጣም ብርዳማ ከመሆኑም ጋ አብዘሃኛው ሙስሊሞች እንዴት ማበስ እንዳለባቸው ጠንቅቀው ስለ ማያውቁ ማበስ እየቻሉም ካልሲያቸውን አውልቀው እግራቸው ለማጠብ ሲደክሙ ይስተዋላሉ። በመሆኑም ይህንን አላህ ገር ያደረገው አማራጭ አውቀው እንዲጠቀሙ ሼር አድርጉላቸው።

?ረሱልﷺ እና ባልደረቦቻቸው በተደጋጋሚ የሚሰሩት ሱና ከመሆኑም ጋ አብዘሃኛው ሙስሊሞች ዘንድ ስለ ተረሳ ሁላችንም ተግባራዊ እናድርገው። ለሌሎችም እናስተላልፍላቸው።

ብዙዎች የሚዘናጉት ጉዳይ ስለሆነ ይህንን ያነበባችሁ ሁላችሁም ሼር አድርጉት ጀዛኩምሏሁ ኸይራ።**https://t.me/LightofQuran2AB
https://t.me/LightofQuran2AB/2547

11 months, 3 weeks ago

እንዲህ የምትል አንዲት ንግግር አለች … "ትናንቴን እያየህ እንዲህ ነህ አትበለኝ። በትናንቱ ሳይሆን በዛሬው መዝነኝ"

በትንሹም ቢሆም ኢስላምን የተረዳ አንድ ሙስሊም ሰው ፤ ሌላኛውን ሙስሊም ወንድሙን በፍፁም ባለፈ ነውሩ አያንቋሽሸውም። ባለፈ ሀጢያቱም እየተከታተለ አያነውረውም።

እኛ ባለንበት በዚህ ዘመናችን ላይ በአንድ የሸሪዓ አልያ የጦሪቃ ወይንም የማዕሪፋ እና ሃቂቃ ጉዳይ ላይ ከአንድ ወንድማችን ጋር ሳንስማማ ብንቀር… አላህ እንዳዘዘን ጉዳዩን ወደ አላህ እና መልእክተኛው ከመመለስ ይልቅ የምንመርጠው ፤ የወንድማችንን ነውር ተከታትለን ስሙን ማጠልሸት ነው።

ማንኛውም የተደበቀ እና የተሰተረን ነገር የተደበቀበት ምክንየት አለውና የደበቀውን ሰው ነውር አንከታተል። ድብቁን ወንድሜ ብሎ አምኖ ነግሮን ከነበርም ቅያሜ በተፈጠረ ጊዜ ለመግለጥ አንሞክር።

ስለ ሰዎች ነውር ለማወቅ መፈላፈል ፤ የበደልንና የመጥፎ ጥርጣሬን በር ይከፍታል። ይኒህ በሮች የተከፈቱ ጊዜ ደግሞ ፤ ዳግም በሮቹን መዝጋት ተራራን እንደመግፈት ያህል ከባድ ነው። ከዘጋነውም በሰውየው ሂወት ላይ የፈጠርነው ጫና እጅጉን ከባድ ነው የሚሆነው።

"ትናንት ረሱልን ሰ•ዐ•ወ ሊገል የቋመጠው ዑመር ዛሬ ክብር ተችሮት ከሳቸው አጠገብ አልተቀበረምን ? በዱንያ ሳለስ በጀነት አልተበሸረምን ?

ከሁሉም በላይ አላህ አዋቂ ነው።

https://t.me/LightofQuran2AB

https://t.me/LightofQuran2AB/2545

12 months ago

ልጅነት የራሱ የሆነ ውበት አለው። ወጣትነት የራሱ የሆነ ውበት አለው።እርጅናም የራሱ የሆነ ውበት አለው። ሞትም ራሱ ውብ ነው። ይህ ግን የሚሆነው ህይወትን አላህ ሱብሐነሁ ወታዓላ ባዘዛችሁ አኗኗር ከኖራችኋት ብቻ ነው።
አላህን ብቻ ለማስደት መኖር ብልህነት ነው
ካለበዚያ ሞት አስቀያሚ ነው።
ኪሳራ ነው ተራ ኑሮን ኑሮ ተራ ሞት ሞተ(ሞተች) ከመባል
የሒወት መስመራችንን ውብ እና የተፈጥሮ መንገድ በሆነው ዲነል ኢስላም እንምራው

https://t.me/LightofQuran2AB/2543

1 year ago

•-ከሱብሒ በኃላ እንቅልፍ -:

ኢብኑልቀይም ረሂመሁሏህ እንዲህ በማለት ይገልፀዋል

• ونـوم الصبحـة : يـمنـع الـرزق لأن ذلك وقـت تطـلب فيـه الخليقة أرزاقهـا وهـو وقت قسمة الأرزاق فنومه حرمان إلا لعارض أو ضـرورة وهـو مضـر جدًا بالـبدن

የሱብሂ እንቅልፍ ርዝቅን ይከለክላል ምክንያቱም ይህ ግዜ ፍጡሮች ርዝቃቸውን የሚፈልጉበት ሰዐት ነው ።
እሱም ሲሳይ የሚከፋፈልበት ግዜ ነው ።
ይህን ግዜ በእንቅልፍ
ማሳለፍ ለሆነ ገጠመኝ ወይም ለችግር ካልሆነ ርዝቅን ማጣት ነው በሰውነትም ላይ የሚያደርሰው ጉዳት በጅጉ የከፋ ነው ።

?| زاد المعاد في هدي خير العباد (٢٢٢/٤).

https://t.me/LightofQuran2AB

We recommend to visit

የስራ ማስታወቂያ ከጋዜጣ ፣ ከቲቪና ራዲዮ ፣ ከማስታወቂያ ቦርድ ፣ ከድህረ-ገፅና ከማህበራዊ ሚዲያና ከመሳሰሉት ቦታዎች በአንድ ቦታ ተሰብስበው ያግኙ::

#Group t.me//Ethio_Jobs2000




#የመዝናኛ ቻናል https://t.me/+UPjrnHF6QzI0ZmQ0

https://t.me/+h0l2XzeI8RQyODlk

For promotion 📩 @Share_Home

Last updated 2 months ago

ከቅዳሜ በስተቀር በየዕለቱ፣ ከሰኞ እስከ ዓርብ ረፋድ ከ3:30 እስከ 5:00፣ እሁድ ከጠዋቱ 2:00 እስከ 4:00 በብስራት ኤፍ ኤም 101.1

Last updated 5 months, 3 weeks ago

Certified Professional Life Coaches
የቻናላችንን አነቃቂ ቪዲዮ መመልከት ለምትፈልጉ
https://www.youtube.com/@inspireethiopiamedia 👈 ይሄንን ሊንክ ይጫኑ

Last updated 7 months, 2 weeks ago