AL MADAD ( المدد )

Description
Advertising
We recommend to visit

القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75

Last updated 1 year, 3 months ago

القناة الرسمية لابن بابل
الحساب الرسمي الموثق على فيسبوك: https://www.facebook.com/Ibnbabeledu?mibextid=ZbWKwL

الحساب الرسمي الموثق على يوتيوب :https://youtube.com/@iraqed4?si=dTWdGI7dno-qOtip

بوت القناة ( @MARTAZA79BOT

Last updated 3 weeks, 6 days ago

القناة الرسمية لشبكة ملازمنا كل مايحتاجه الطالب.

((ملاحظة : لايوجد لدينا اي حساب تواصل على تلكرام ولا نقوم بنشر اعلانات في القناة))

Last updated 5 days, 21 hours ago

2 Monate, 2 Wochen her

ታላቁ ሰሓብይ ጃቢር ቢን ዓብዲላህ (رضي الله عنه) ከሰይዳችንﷺ እጅ ስለፈለቀው ውሀ ሲናገሩ እንዲህ ይሉናል :

"عَطِشَ النَّاسُ يَومَ الحُدَيْبِيَةِ والنَّبيُّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ بيْنَ يَدَيْهِ رِكْوَةٌ فَتَوَضَّأَ، فَجَهِشَ النَّاسُ نَحْوَهُ، فَقالَ: ما لَكُمْ؟ قالوا: ليسَ عِنْدَنَا مَاءٌ نَتَوَضَّأُ ولَا نَشْرَبُ إلَّا ما بيْنَ يَدَيْكَ، فَوَضَعَ يَدَهُ في الرِّكْوَةِ، فَجَعَلَ المَاءُ يَثُورُ بيْنَ أصَابِعِهِ كَأَمْثَالِ العُيُونِ، فَشَرِبْنَا وتَوَضَّأْنَا. قُلتُ: كَمْ كُنْتُمْ؟ قالَ: لو كُنَّا مِئَةَ ألْفٍ لَكَفَانَا، كُنَّا خَمْسَ عَشْرَةَ مِئَةً.."

?متفق عليه

" የሑደይቢያ'ህ ቀን ሰዎች ተጠሙ ..የአላህ መልክተኛﷺ ዘንድ ደሞ በትንሽ እቃ ውሀ ነበር ዉዱ አደረጉ .. እሳቸው ጋር ውሀ ያዩ ግዜ ሰው ወደሳቸው በፍጥነት ጎረፉ...

እሳቸውም : "ምን ሆናቹ ? " ብለው ጠየቋቸው

እነሱም : " እርሶ ጋር ካለችው ውሀ በስተቀር ውዱ የምናደርግበትም ሆነ የምንጠጣው ውሀ የለንም " ብለው መለሱላቸው::

ያኔ እጃቸውን ትንሿ እቃ ላይ አደረጉት .. ውሀውም ልክ እንደ ምንጭ በጣቶቻቸው መሀከል መፍለቅለቅ ጀመረ.. ጠጣንም ውዱም አደረግን ...

" ስንት ነበራቹ ?" ተብለው ተጠየቁ

ጃቢርም (رضي الله عنه) : "መቶ ሺ ብንሆንም ኖሮ በእርግጥ ይበቃን ነበር..! አንድ ሺ አምስት መቶ ነበርን .." ብለው መለሱ ::
:-------------------------

ከውሀዎች ሁሉ በላጩ ይሀ ከተከበረው እጃቸው የፈለቀው ውሀ ነው ... የሰሓባዎቹ እድል ዐጀብኮ ነው:: እንደው ጀነትም ውስጥም ቢሆን ይሄ ውሀ ይገኛል ?!
እንደው ከተገኘ በተገኘበት ቦታ አላህ የምንጠጣ ያድርገን በሰይዳችን ﷺ መጀን ☺️?
https://t.me/mededulhabib

2 Monate, 2 Wochen her

ዛሬ ከመግሪብ ቡኃላ ተፍሲር ደርስ ይኖረናል ቢኢዝኒላህ

ቦታ : ጠሮ- ዑስማን ቢን ዐፋን መስጊድ

አህለን ወሰህለን
https://t.me/mededulhabib

2 Monate, 3 Wochen her

ከ6ኛው ወይም ከ7ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ በተለያየ ዘመንና በተለያዩ ሀገሮች በየጉራንጉሩ በሀገራችንም ጭምር መውሊድን ሲያደርጉ ሲያስደርጉ ሲያከብሩ ሲያስከብሩ የነበሩት ተራው ህብረተሰብ ሳይሆን ዑለማዎቹ ሷሊሆቹ ምርጦቹ ነበሩ:: የፊቂ የተፍሲር የሲራ የተለያዩ የዒልም ሊቆችና ኡመቱን የሚመሩ አርአያ የነበሩ የሰይዳችን ﷺ ወራሾች ነበሩ::አሁን ሀገራችን ላይ የምናየው የወጣቱ ምናንም እንቅስቃሴ በቅርብ ግዜ የመጣ መሆኑን ሁላችንም እናውቃለን::

ታድያ እነዚህ ዑለማዎች በዒልምም በተቅዋም በላጮች የነበሩ ከዒልምም ከሸሪዓም አንፃር መዝነው አይተው የፈቀዱትንና የሰሩትንም ጭምር በክህደት በጥመትና በተለያየ መጥፎ ነገር መፈረጅና የነብያችንﷺ ኡመት 700ውን የሚያክል እድሜውን በነዚህ መጥፎ ሰዎች እየተመሩ ዲኑን አበላሽተውት .. ዲኑን እያወደሙት ቆይተው ገና አሁን እነ እንትና እንትና ሳውዲ ላይ መጥተው እያስተካከሉትና እየመለሱት ነው ማለት አያሳፍርም ?!

ቆይ ቆይ ነብያችን ﷺ እልሰሩትም ! ሰሀባው አልሰሩትም ! እንትና አልሰሩትም እንትና አልሰሩትም የምትለዋ ብዥታና ጥያቄዎች ይሄ ሁሉ በኡመቱ ውስጥ የነበሩ የ700 አመት የተለያየ ሀገርና ዘመን ዑለማዎች የአራቱ መዝሀብ ሊቃውንቶች ለምን አልመጣላቸውም ? ለምን ይቺ ብዥታ ትዝ አላላቸውም ?! ወይስ ዒልማቸው ይሄን ብዥታ ከሚነዙ ሰዎች በታች ነበር ነው ?!

ሱብሓነሏህ! ሀዛ ቡህታኑን ዐዚም!!

ያለማክበር መውሊድንም ያለማውጣት መብት የተከበረ ከመሆኑ ጋር ማውገዝ ግን የወገዘና የወደቀ አስተሳስብ ባለቤትነት ምልክት ነው

#መውሊድ
#የዊላዳው_ወር
https://t.me/mededulhabib

2 Monate, 3 Wochen her
AL MADAD ( المدد )
2 Monate, 3 Wochen her
AL MADAD ( المدد )
2 Monate, 3 Wochen her
AL MADAD ( المدد )
3 Monate her

በእርግጥ መዉሊድ ሲቃረብ እንዲህ ዓይነት የነቀፌታ አጀንዳዎች ከመለመዳቸዉ የተነሳ የባዕሉ ድምቀት አካል እየመሰሉ መጥተዋል፡፡ እነርሱ ባይኖሩ ቅር የሚለን ይመስለኛል፡፡ ሁለታችንም ወገኖች በየራሳችን መንገድ መዉሊዱን እያከበርን እንደሆነም ይሰማኛል፡፡ አንደኛችን ‹‹ፈልየፍረሑ›› ባለዉ መሠረት በዱዐ፣ በዚክር፣ በሶደቃ፣በመድሕ…እና በደስታ፣ሌላኛችን ደግሞ በትችት /በሀሜት/ እና በሁካታ፡፡ ‹‹ኩሉ ሙየሰሩን ሊማ ኹሊቀ ለሁ›› ነዉና መልካም የዒባዳና የመደሰት ወይም የነቀፌታና የመብከንከን ሳምንታት፡፡

በሸይኽ ሐሰን ታጁ የተፃፈ
https://t.me/hassentaju

3 Monate her

ሰሞኑን አንዳንድ ወንድሞች በሸይኽ ሙሐመድ አወል ሐምዛ ላይ የሰነዘሩትን ሂስ በወንድሞች ጥቆማ ሰማሁት፡፡ ‹‹የምነግራችሁ ሀዲስ አይደለም፤መሻኢኾቹ እንዳሉት ነብዩ (ﷺ) እንዲህ ብለዋል…›› በማለት ሸይኹ ያስተላለፉትን መልዕክትም አደመጥኩት፡፡ የተችዎቻቸዉ የሂስ ጭብጥ፡- ‹‹ከሀዲስ መዛግብት ዉስጥ የሌለ ነገር ‹ነብዩ አሉ› ተብሎ እንዴት ይወራል? በነብያችን (ﷺ) ላይ መቅጠፍ አይሆንምን?›› የሚል ነዉ፡፡ በእርግጥ የሸይኽ ሙሐመድ አወል መረጃ ምንጭ ከርሳቸዉ ዘንድ የታመኑ መሻኢኾች ሲሆኑ የመሻኢኾቹ የመረጃ ምንጭ ደግሞ ህልም/መናም እንደሆነ ባለቤቱን ጠይቆ መረዳት በተቻለ ነበር፡፡ የተሰነዘረዉን ሂስ ስሰማ ከዚሁ ጋር የምትመሳሰል አንዲት ክስተት አስታወስኩ፡፡ ክስተቷን መዝግበዉ ያስተላለፉልን ኢማም ኢብነልቀይም አልጀዉዚ ናቸዉ፡፡ ሸኻቸዉ ኢማም ኢብን ተይሚየህ የነገሯቸዉን አንድ አጋጣሚ እንዲህ አስፍረዋል፡-

كَانَ يُشْكِلُ عَلَيَّ أَحْيَانًا حَالُ مَنْ أُصَلِّي عَلَيْهِ الْجَنَائِزَ، هَلْ هُوَ مُؤْمِنٌ أَوْ مُنَافِقٌ؟ فَرَأَيْت رَسُولَ اللَّهِ - صَلَّى اللَّهُ عَلَيْهِ وَسَلَّمَ - فِي الْمَنَامِ فَسَأَلْته عَنْ مَسَائِلَ عَدِيدَةٍ مِنْهَا هَذِهِ الْمَسْأَلَةُ، فَقَالَ: يَا أَحْمَدُ الشَّرْطَ الشَّرْطَ، أَوْ قَالَ: عَلِّقْ الدُّعَاءَ بِالشَّرْطِ،

‹‹ሶላተል ጀናዛ የምሰግድበት ሰዉ ሙዕሚን ይሁን ሙናፊቅ ለመለየት አንዳንድ ጊዜ እቸገራለሁ፡፡ የአላህን መልዕክተኛ በህልም አየሁዋቸዉና ይህንን ጨምሮ በርካታ ጥያቄዎችን አቀረብኩላቸዉ፡፡ ‹አህመድ ሆይ ዱዐህን ከቅድመ ሁኔታ ጋር አቆራኝ› አሉኝ፡፡›› (ኢዕላሙል ሙወቂዒን 3/300፣ዳሩልኩቱበል ዒልምየህ፣ቤይሩት፣1991)

የበርካታ መድሕ መድብሎች ባለቤት የሆኑት ኢማም ቡሶይሪም፡- ‹‹ ፈመብለጉል ዒልሚ አነሁ በሸሩን›› የምትለዋን ስንኝ ካዋቀሩ በኋላ ቤት ሳይደፉ እንቅልፍ አሸለቡ፡፡ ወዲያዉም አሽረፈል ኸልቅ (ﷺ) በመናማቸዉ መጡ፡፡ ቡሶይሪ ግጥሙን አነበቡላቸዉ፡፡ ነብዩም (ﷺ) ጋቢ (ቡርዳ) ሸለሟቸዉና፡- ‹‹ወአነሁ ኸይሪል ኸልቂ ኩሊሂሚ›› በማለት የጀመሩትን ስንኝ እንዲሞሉ አመላከቷቸዉ፡፡ ግጥማቸዉም ‹‹ቡርዳ›› ተብላ ተጠራች፡፡

ኢማም ፈኽሩዲነ ራዚ፣ዑትቢና ሌሎች ዑለሞችም ከነቢዩና ከሸኾቻቸዉ ጋር ተመሳሳይ ተሞክሮዎች አሏቸዉ፡፡ እነዚህ በተደጋጋሚ የታዩ ክስተቶች እና ኢማም ኢብንሐጀር ‹‹አልፈትሕ፣ 12/384-385 የሪያድ ዕትም›› ላይ የሰጡት ገለጻ፣እንዲሁም ኢብነልቀይም ‹‹አልሩሕ›› በተሰኘ ኪታባቸዉ ዉስጥ ያሰፈሯቸዉ በርካታ ዕዉነታዎች ‹‹ነብዩና ሌሎች ሙታን ከሞቱ በኋላ አይጠቅሙም›› የምትለዉን አስተሳሰብ ጥያቄ ዉስጥ ይከታሉ፡፡

ከላይ ከተጠቀሰዉ የኢብን ተይሚየህ አጋጣሚ የሚከተሉትን ሀሳቦች መምዘዝ ይቻላል፡-

  1. ኢብን ተይሚየህ ከነብያችን (ﷺ) በመናም የደረሳቸዉን መልዕክት ዕዉነት ብለዉ እንደወሰዱት፣
  2. ‹‹ነብዩ ይህን አሉኝ›› በማለት ከሐዲስ መዛግብት ዉስጥ የሌለ ነገር እንዳስተላለፉ፣
  3. በመናም ካገኙት መልዕክት ላይ አሕካም እንደገነቡ፣
  4. ይህን ያመኑበትን ዕዉነት ለተማሪዎቻቸዉና ለህዝብ እንዳወጉ፣
  5. ተማሪዎቻቸዉም ከሸኻቸዉ የሰሙትን ለትዉልድ እንዳስተላለፉ፣
  6. ተማሪዎቻቸዉ ሸኻቸዉን በነብዩ (ﷺ) ላይ ቀጠፉ ብለዉ እንዳላሟቸዉ፤

እነዚህን ነጥቦች ከሸይኽ ሙሐመድ አወል መልዕክት ጋር ስናገናኘዉ ሸኾቻቸዉ ልክ እንደ ኢብን ተይሚየህ ሁሉ ነብዩን (ﷺ) በመናም አይተዉ መልዕክት ደረሳቸዉ፡፡ በመልዕክቱ አመኑበት፡፡ ለደረሶቻቸዉም ልክ እንደ ኢብን ተይሚየህ ‹‹ነብዩ እንዲህ ነገሩን›› በማለት አስተላለፉ፡፡ ሸይኽ ሙሐመድ አወልና ሌሎች ደረሶቻቸዉም ልክ እንደ ኢብነል ቀይም የሰሙትን ሳያዛቡ ለህዝብ አስተላለፉ፡፡ ቢያንስ በዚህ አጀንዳ ሁለቱም ወገኖች ተመሳሳይ ናቸዉ፡፡ ለተመሳሳይ ድርጊቶች ደግሞ የሚሰጠዉ ‹‹ሑክም›› ተመሳሳይ ነዉ፡፡ ስለዚህ አንደኛዉ ‹‹ቀጣፊ›› ከተሰኘ ሌላኛዉም ቀጣፊ ነዉ፡፡ በዚህ ሰበብ አንዱ ከከፈረ ሌላኛዉም ካፊር ነዉ፡፡ ወንድሞቻችን ኢማም ኢብን ተይሚየህንና ተማሪያቸዉን በኩፍር ወይም በቅጥፈት የሚጠረጥሩ አይመስለኝም፡፡

እዚህች ላይ አንዲት የሸሪዐ መርህ ላስታዉስ፡፡ እንዲህ ዓይነት ጉዳዮች ሲያጋጥሙን ለትችት ከመሮጥ ይልቅ በሰከነ መንፈስ መመርመር ማጣራት እንዳለብን የእስልምና ቁርአናዊዉ የ‹‹ተበዩን›› ህግ ግዴታ ያደርግብናል፡፡ ‹‹ሑስነ ዞን›› እንድናስቀድምና ለወንድም ንግግር ወይም ድርጊት በጎ ትርጉም ለመስጠት የቻልነዉን ሁሉ እንድንተጋም ያስተምረናል፡፡ ለድርጊቱ በጎ ትርጉም ካጣን እንኳ ተገቢዉ አቋም ‹‹ተወቁፍ›› ማድረግ ነዉ፡፡ ከአንድ ሰዉ ከንፈር ወይም ጺም ላይ አስካሪ መጠጥ ተረጭቶ ብናይ ሳናጣራ በፊት ‹‹ጠጥቶ ነዉ›› ብሎ መደምደም የኢስላማዊ ስብዕና ባህሪ አይደለም፡፡ ከዚያ ይልቅ ‹‹ሰዎች ረጭተዉበት ሊሆን ይችላል›› ብሎ ማሰብ ይቀድማል፡፡ አንድ ሰዉ ‹‹አነ ረቡኩሙል አዕላ›› ሲል ብንሰማዉ ‹‹ራሱን አምላክ አድርጎ ከፈረ›› የሚል ድምዳሜ ከመስጠት ይልቅ ‹‹ከሱረቱ ናዚዐት 24ኛዉ አንቀጽ እያነበበ ነዉ›› ማለቱ ኢስላማዊ ነዉ፡፡ ‹‹ኢነ ባዕደ ዞኒ ኢስሙን›› የሚለዉ የአላህ መልዕክት በዚህ የሥነ- ምግባር ጎዳና እንድንጓዝ ያስገድደናል፡፡ ቁርአንንና ሀዲስን ወይም ሰለፎችን መከተል ለእንዲህ ዓይነት መለኮታዊ ዕሴቶች መገዛትን በዋነኛነት ያካትታል፡፡ ስብዕናን ሳይገሩ፣አንደበትን ሳይቆጣጠሩ፣ለትንሽ ሳያዝኑና ትልቅን ሳያከብሩ ላይ ላዩን ብቻ መጋለብ የ‹‹ሰለፎችን›› ‹‹ሙሪድነት›› ያሳጣል፡፡ በእርግጥ በግሌ አሻሚ መልዕክቶች በህዝባዊ መድረክ ባይነገሩ እመርጣለሁ፡፡ ‹‹ዐሊሙ ናሰ ዐላ ቀድሪ ዑቁሊሂም›› እንዲል መመሪያዉ፡፡

ሸይኸ ሙሐመድ አወል ሀምዛን በቅርበት አዉቃቸዋለሁ፡፡ ማዲሕ ብቻ ሳይሆኑ ዐሊምም ናቸዉ፡፡ የሻፊዒ መዝሀብ ፊቅህ ጥንቅቅ አድርገዉ ቀርተዋል፡፡ ነህዉና ሶርፍ የተባሉ የዒልም ቁልፎችንም በወጉ ተምረዋል፡፡ ይህም ስለሆነ በዐረብኛ መንዙማዎቻቸዉ ዉስጥ ያቀራር ግድፈት እምብዛም አይገኝም፡፡ ከዚህ ሁሉ በላይ ግን የመሻኢኾችን ‹‹ተርቢያ›› ያገኙ መሆኑ በስብዕናቸዉ ላይ ይንጸባረቃል፡፡ የጠዋትና የማታ ዚክሮችን የማይተዉ፣ የሳምንቱን አብዛኛዉን ቀናት በዱዐና በዚክር የሚያሳልፉ፣ ከሰዎች ጋር ብዙ ባለመቀላልና ከሚዲያ በመራቅ ምላስና ቀልባቸዉን የታደጉ፣ ዘወትር ጠዋት ረዥም ርቀት በእግር በመጓዝ አካላዊ ጤንነታቸዉን የሚጠብቁ፣ የቤት ዉስጥ ሥራዎችን በመሥራትና ባለቤታቸዉን በማገዝ መልካም የትዳር አጋርነታቸዉን ያስመሰከሩ፣ መኪናቸዉን በማጠብ፣አትክልቶች በማጠጣት፣ግቢያቸዉን በመጥረግ ወዘተ ነፍስያቸዉን የረገጡ ስብዕና መሆናቸዉን በጉርብትና አረጋግጫለሁ፡፡

ይልቅስ ‹‹ኢማም ኢብን ተይሚየህም ሆኑ ሌሎች ዑለሞች ህልምን በዚህ ልክ ለምን ክብደት ሰጡት? ህልም የሸሪዐ ምንጭ መሆን ይችላልን?›› የሚለዉ ጥያቄ በቅርበት ሊመረመር የሚገባዉ ነዉ፡፡ ይህ አጀንዳ ወደሰፊ የዕዉቀት ባህር የሚከተን ቢሆንም በስሱ እንዳስሰዋለን፡፡ በተጨማሪም በሸይኽ ሙሐመድ አወል ላይ የተሰነዘረችን ሌላ ሂስ እንደዚሁ በመጠኑ እናያለን፡፡

3 Monate her

ዛሬ ከመግሪብ ቡኃላ ተፍሲር ደርስ ይኖረናል ቢኢዝኒላህ

ቦታ : ጠሮ- ዑስማን ቢን ዐፋን መስጊድ

አህለን ወሰህለን
https://t.me/mededulhabib

5 Monate, 3 Wochen her

ዐፍወን ያጀማዐ ወደ ክፍለሃገር ስለወጣው ደርስ አይኖረንም

We recommend to visit

القناة الرسمية والموثقة لـ أخبار وزارة التربية العراقية.
أخبار حصرية كل مايخص وزارة التربية العراقية.
تابع جديدنا لمشاهدة احدث الاخبار.
سيتم نقل احدث الاخبار العاجلة.
رابط مشاركة القناة :
https://t.me/DX_75

Last updated 1 year, 3 months ago

القناة الرسمية لابن بابل
الحساب الرسمي الموثق على فيسبوك: https://www.facebook.com/Ibnbabeledu?mibextid=ZbWKwL

الحساب الرسمي الموثق على يوتيوب :https://youtube.com/@iraqed4?si=dTWdGI7dno-qOtip

بوت القناة ( @MARTAZA79BOT

Last updated 3 weeks, 6 days ago

القناة الرسمية لشبكة ملازمنا كل مايحتاجه الطالب.

((ملاحظة : لايوجد لدينا اي حساب تواصل على تلكرام ولا نقوم بنشر اعلانات في القناة))

Last updated 5 days, 21 hours ago