ሀ ረ ጋ ት🎋

Description
መሙላትን የሚያስንቁ ጎደሎ ሀረጎች
likely ur Thoughts are hear🍃

TICKTOK :@Samiya.311

Facebook :samiya Tuha

ለ ሀሳብ አስተያየት tg@samiya311
Advertising
We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 6 days, 8 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago

1 month, 4 weeks ago

ሀድራዉን ቢተዉት
ሊቃዉን ቢተዉት ይመስላል የጠፋ
እስቲገኝ ድረስ ወንድም እና ስርፋ💜

1 month, 4 weeks ago

በወራቱ በዘመኑ ያብባል ምናምኑ
ኧረ በዘመኔ አላብብም እኔ 💔

1 month, 4 weeks ago

የአምናን ሰዉ ሰደብኹት አፌ ልጓም የለዉ
የዘንድሮዉ መጣ እግር እጅ የሌለዉ

መንዙማ💜

4 months, 3 weeks ago

ግቢ እያለሁ አስታውሳለሁ እጄ ላይ የማደርጋት አረንጏዴ ቢጫ ቀይ ጨሌ ነበረችኝ፣ I used to love her and wear her all the time. የሆነ patriotism ኖሮብኝ አላደግኩም፣ ቤተሰቦቼም ወለዬ እኔም የአዲስ አበባ ልጅ ነኝና የሚያንዘረዝር ስሜት ለተለየ ዘር የለንም፣ ሀገራችን በጥቅሉ ከመውደድ ያለፈ። ግቢ የገባሁ ግዜ ግን አላውቅም አንድ የሙጥኝ የምይዘው ነገር ፈልጌ ነበር መሰለኝ ኢትዮጲያዊነትን blindly አመናፍሰው ነበር።

past forward four years back, ሀገሬን ከከተማ ወጣ እያልኩ ዱር ገደሏን፣ ጋራ ሸንተረሯን፣ መንገዶቿን፣ ትናንሽ የገጠር ከተሞቿን እና መልክምድሯን ማየት ጀመርኩ። ወደድኳት። ስለመውደዴም ሳወራ ብዙዎች ስለ ውጪ ሀገራት ውበት እያነሱ በንፅፅር ያሳንሷት ነበር። አይጠፋኝም ልትበለጥ እንደምትችል፣ የማወቅ ጉጉቱም ስልክም እንዳላት አንድ ወጣት ኔዘርላንድስን ሰርች አድርጌ ማየቱ አልቀረብኝም። ግን እወዳታለሁ ስል እያነፃፀርኩ አልነበረም። የራሴው ስለሆነች የማውቃት እናቴ ስለነበረች እና ተፈጥሮ በምንም አይነት መልኩ ስለማይጠላ ነበር። ልክ መቆረጥ እንዳለበት ስድስተኛ ጣት ተፈጥሮ ሆኖ መቀየር መስተካከል ያለበት ህፀፆች ቢሞሏትም
“ቢጎል እንጀራ ከሞሰቡ ላይ እናት በሌላ ይቀየራል ወይ?” ነውና ከነ ነበር የወደድኳት።

Past forward today.
የትምህርት ሲስተሙ ፌል ሲያደርገን ፣ ሙዚቃውም ፊልሙም የስራ እድሉም ዘር ሲገባበት፣ ማወቅ ኢሉሚናቲ ሲባል፣ ቴሌቪዥን የፆታ ጥቃት ፣ ቲክቶክ ዘረኝነት ሲኖርበት፣ ፀብ መጠላላት እና ክፋት ሲበረታ፣ የብሄር ፀብ በወጣት ሲብስ፣ እንዲህ ሁኑ ብለው ባሳደጉን አፍረው እንዳትሆኑ ባሉን አይነት ሲኮሩ፣ የማይታይ ህልም አንግበን ደክሞን ስንዝል፣ ጩኸታችን ብርቅ ሳይሆን ከብዙሀኑ አንዱ እንደሆነ ሲነገረን፣ ታመን አሳማሚውም አብሮን ስለታመመ ስላልተሰማን፣ በጦርነት፣ በኑሮ ውድነት፣ በጥቃት፣ ጦዘን አልወደቅንም ለማለት ለመበርታት ዘንጠን ተሰቃየን።

ሀገር እኮ ሰው ነው፣ ሀገሬ ከስምንተኛ የወደቁ ያለፈላቸው ቲክቶከሮች የሚሰሙበት ነው፣ ሀገሬ 12ኛ ልትፈተን ሄዳ የምትበላውን ተዘርፋ በርሀብ እና ህመም ሳትፈተን የመጣችውን እህቴን ያስለቀሰ ሲስተም ነው፣ “ሀገሬ ኧረ አርፈሽ ቁጭ በይ የምን መብት ነው?” የሚሉት ድምፆች ናቸው፣ ሀገሬ “እሷ ሁሉንም ነገር ከሴትነት ጋ ታያይዘዋለች” ያለው ፖድካስተር ነው። ሀገሬ “ድሮም ወሎን የነካ መጨረሻው እያምርም” ብሎ አንድ ግለሰብን የሚወቅጥ ህዝብ ነው። ሀገሬ ሽንኩርት 90 ብር ነው። ሀገሬ ከወገኑጋ የማይቆም አጋጣሚ ተጠቃሚ ነጋዴ ነው። ሀገሬ አድራጊው እያለ በሞካሪው የሚኮራ መንጋ ነው። ሀገሬ ለሚችለው እድልን የሚነሳው ነው። ሀገሬ ህፃን ደፋሪን እሹሩሩ የሚለው ክልል ነው፣ ሀገሬ ቂጥ እንጂ ታለንት የማያዩ እውራን ያሉበት ነው፣ ሀገሬ ተሳዳቢን ያነገሰ ነው። ሀገሬ በወንድነቱ ብቻ የበላዬ ሊሆን የሚፈልገው በችሎታ የምበልጠው አለቃዬ ነው። ሀገሬ ስቃይ ነው። ሀገሬ ፍትህ ቅንጦት ፣መቻል ሀጢያት፣ መናገር ሞት የሆነበት ነዉ።

ፈልጌ ነበር የቴዲን ኢትዮጲያን ሙዚቃ ስሰማ የሚተናነቀኝን የማንነት እምባ ዘፈኑ ሲያልቅ እንዳይተን። ወኔው አብሮኝ እንዲቆይ ፍቅሩ ኑሮዬ እንዲሆን። ፈልጌ ነበር የምቾት፣ የመረጋጋት፣ የመዝናት፣ የመከበር የመጠበቅ ስሜት፣ ፈልጌ ነበር “ሀገሬ ላይ እኮ ነኝ “ ብሎ የመኩራት ስሜት፣ የቤትነት ስሜት፣ ፈልጌ ነበር ሀገሬን መውደድ።

ለsafety የሰው ሀገር መመኘቴ ሴንስ እንዳይሰጥ ተመኝቼ ነበር፣ ለመታየት የሰው ቋንቋ ባልመርጥ ምኞቴ ነበር፣ ነብይነቴ በሀገሬ እንዲሆን ፈልጌ ነበር።

ግን ማነው የሚያየኝ? የሚሰማኝ? ከሰው የሚቆጥረኝ? የማያስፈራራኝ? የማይዝትብኝ? የሚያከብረኝ? ቦታ፣ እድል የሚሰጠኝ?

ኢትዮጲያ ነች? ሀገሬ ነች? አንተ ነህ? አንቺ ነሽ? እናንተ ናችሁ?

በሀገሬ እንደመጤ ኖርኩ፣ ተርቤ ዝም አልኩ፣ ሲስተም ናቀኝ፣ ህልሜን በላኝ፣ ሲስተም ደፈረኝ፣ ገለባውን አስክኖ ፍሬ ፍሬው ለቅሞ ጣለን።

ልወድሽ ሞክሬ ነበር፣ ኢትዮጲያ።

4 months, 3 weeks ago

"We tend to love poems for what they are ,and what they present to us "

4 months, 3 weeks ago

እኔን የት አገኛታለሁ ብል ደሞ ምን አልባት እዚ የሚል inner voice ሰማሁ

4 months, 3 weeks ago

እንደምን አላችሁ ሸግዬ ሰወች?

4 months, 3 weeks ago

ስለጠፋሁ ይቅርታ የኔ ሰዎች?

7 months, 3 weeks ago

ብዙ መጣን እና በየመንገዱ አንድ አንድ ማንነቴን እያንጠባጠብኩ አልፌ እዚ ላይ አሁን ያለሁበት ስደርስ እርቃኔን እንደመቆም ያለ ባዶነት ከቦኛል ። የሆነ ምሽት ላይ እጅህን ይዤ እየሄድኩ እስኪ ላፍቅር ስል ትዝ ይለኛል ። እዛ መሀል ልቤ ዉስጥ መኖሪያዉን እያደላደለ የነበረ ፍቅር ነበር ። እስኪ ላፍቅር አልኩ ፣ እስኪ ልጎዳ ፣ እስኪ ፍቅር የትም ይዉሰደኝ አልኩ ።እንዳልኩት ፍቅር ወጀቡን አበረታና ይዞኝ ወደየትም ሄደ ። በየመንገዱ ያልወጋኝ የቃል እሾህ አልነበረም። እሾሁን እየነቀልኩ ተራመድኩ ግን ምን ልብ እንዳላልኩ ታዉቃለህ? እየደማሁ ነበር ። አንተ ልብህን ጠበክ እኔ ያለ ገደብ ወደድኩ ምን አልባት መዉደድ የምችለዉ እቺን ታክል ነዉ ግን ብዙ ነገር አይቸባታለሁ በዚች ሽንቁር እንኳ ። ፍቅር ባለጌ ነዉ ። የማይሆኑ ቀኖች መሀከል ዘርሮኛል ። እቀበላለሁ ሁሉም ዉድቀት የኔ አካል ነዉ ግን አለ አ በዛዉ ልክ ቆርጠዉ ባይጥሉት እንኳ ያማል ።

?????

We recommend to visit

Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10

ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno

Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...

Last updated 6 days, 8 hours ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 1 month, 3 weeks ago

🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶

✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ

📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app

YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ

📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot

Last updated 2 months ago