Ibn Yahya Ahmed

Description
የተለያዩ ዲናዊ ፅሑፎችን ብቻ የማስተላልፍበት ቻናሌ ነው።
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

1 day, 19 hours ago

▪️የ2ለ3 ፣ የ3ለ4

🔻ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " የሁለት ሰው ምግብ ለሶስት ሰው ይበቃል ፤ የሶስት ሰው ምግብ ለአራት ሰው ይበቃል። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777

5 days, 19 hours ago

▪️በደል እና ስስትን ተጠንቀቁ!

🔻ከጃቢር - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " በደልን ተጠንቀቁ ምክንያቱም በደል የቂያማ ቀን ብዙ ጨለማዎች ነውና። ስስትንም ተጠንቀቁ ምክንያቱም #ስስት ከእናንተ በፊት የነበሩ ህዝቦችን ያጠፋው እሱ ነው ፤ ደሞቻቸውን እንዲያፈሱ እና ክልክል የሆኑ ነገሮችን የተፈቀዱ እንዲያደርጉ አነሳሳቸው። ". (ሙስሊም ፥ 2578 ላይ ዘግቦታል).

@ibnyahya777

6 days, 19 hours ago

▪️ትከሻዋ ሲቀር

?ከዓኢሻህ - ረዲየሏሁ ዐንሃ - ተይዞ እንደተወራው እነሱ ፍየል አረዱና (ሰደቃ አደረጉ) እና ነብዩ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - " ከሷ ምኗ ቀረ?" አሉ ፤ (ዓኢሻም) "ትከሻዋ እንጂ ሌላ የቀረ ነገር የለም" አለች ፤ እሳቸውም " ከትከሻዋ ውጭ ሁሉም ቀርቷል " አሏት. (ቲርሚዚይ ፥ 2470 ላይ ዘግበውታል). ቲርሚዚይ ሐዲሱን ሲያብራሩ ነብያችን ከፍየሏ ትከሻዋ ሲቀር ሁሉንም ሰደቃ አወጡ እና ትከሻዋ ሲቀር ሌላው ሰደቃ የወጣው የፍየሏ ክፍል አኺራችን ላይ ቀርቶልናል አሉ።

@ibnyahya777

1 week ago

▪️ገንዘብን አይቀንስም

?ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዐለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ሰደቃ ከገንዘብ ምንም አትቀንስም ፤ አሏህ አንድን ባርያ ይቅርታ በማድረጉ ልቅናን እንጂ አይጨምርለትም ፤ አንድ ሰው ለአሏህ ብሎ አይተናነንስም ከፍ ያደረገው ቢሆን እንጂ። ". (ሙስሊም ፥ 2588).

@ibnyahya777

1 week, 1 day ago

▪️ስጥ

?ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " አሏሁ - ተዓላ - ይህን አለ ፥ የአደም ልጅ ሆይ! ስጥ ይሰጥሃል። "|| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

1 week, 1 day ago

▪️ሁለት መላኢካዎች

?ከአቢሁራይራህ - ረዲየሏሁዓንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ባርያዎች በውስጡ የሚያነጉበት አንድም ቀን የለም ሁለት መላኢካዎች የሚወርዱ ቢሆኑ እንጅ ፤ አንድኛው እንዲህ ይላል ፡ አሏህ ሆይ! የሚሰጥን ሰው ምትክን ስጠው ፤ ሌላኛው ደግሞ እንዲህ ይላል ፡ ለሚይዝ ሰው ጥፋትን ስጠው። " (ሙተፈቁን ዐለይህ).

@ibnyahya777

1 week, 1 day ago

▪️የቴምር ቁራጭ

?ከዐዲይ ቢን ሓቲም - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " እሳትን በቴምር ግማሽ ቢሆን እንኳ ተጠንቀቁ! ". (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

1 week, 1 day ago

▪️ያንተ ገንዘብ

?ከዐብደሏህ ቢን መስዑድ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው እንዲህ አለ ፡ የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ " ከእናንተ ውስጥ የወራሾቹ ገንዘብ ከራሱ ገንዘብ ይልቅ ተወዳጅ የሆነ ማነው? ". የአሏህ መልእክተኛ ሆይ! ገንዘቡ ተወዳጅ የሆነ እንጂ ከኛ ውስጥ ማንም የለም አልናቸው። እሳቸውም እንዲህ አሉ ፦ " የሱ ገንዘብ ማለት (ሰደቃ ሰጥቶ) ያስቀደመው ነው ፤ የወራሾቹ ገንዘብ ደግሞ ያቆየው(የተውከው) ነው። ". (ቡኻሪ ፥ 6442 ላይ ዘግቦታል)

@ibnyahya777

1 week, 6 days ago

ትክክለኛ ሚስኪን ማለት

?ከአቢሁረይራህ - ረዲየሏሁዐንሁ - ተይዞ እንደተወራው የአሏህ መልእክተኛ - ሰለሏሁዓለይሂ ወሰለም - እንዲህ አሉ ፦ |" በሰዎች ዘንድ እየዞረ አንድ ወይም ሁለት ጉርሻ የሚመልሰው ሰው እንዲሁም አንድ ወይም ሁለት ቴምር የሚመልሰው ሰው ሚስኪን አይደለም ፤ ሚስኪን ማለት ፍላጎቱን የሚዘጋለት የሚያብቃቃውን ነገር የማያገኝ ነው ፤ ሰዎች ለሱ ሰደቃ እንዳያደርጉለት ደግሞ ስለሁኔታው አያውቁም ፤ ሰዎችን ለመለመንም አይቆምም። "| (ሙተፈቁን ዐለይህ)

@ibnyahya777

4 months, 2 weeks ago

▪️እውነት ይህ አንቀጵ መውሊድን ለማክበር ማስረጃ ይሆናልን?

{ َقُلْ بِفَضْلَِّ لله وَبِرَحْمَتِهِ فَبِذَٰلِكَ فَلْيَفْرَحُوا هُوَخَيْرٌمِّمَّا يَجْمَعُون }
[| «በአላህ ችሮታና #በእዝነቱ (ይደሰቱ)፡፡ በዚህም ምክንያት ይደሰቱ፡፡ እርሱ ከሚሰበስቡት ሀብት በላጭ ነው» በላቸው፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 58).
°
?በዚህ አንቀጽላይ እዝነቱ ማለት ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - ናቸው እና በሳቸው እንደሰታለን። ይላሉ ፡ ለዚህ የሚሰጠው መልስ በሁለት መልኩ ነው ፦
°
?1ኛ. ቁርአኑ ላይ እዝነቱ የተባለው እንደአብዛኛዎቹ የተፍሲር ሊቃዎንቶች ገለፃ ቁርአን ወይም እስልምና ነው እንጂ ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - አይደሉም። እንደምሳሌ ተፍሲር አጥ-ጦበሪ , ቁርጡቢ , በገዊ, ኢብኑ- ከሲር, ተፍሲር አስ-ሰዕዲ እና ሌሎችንም መመልከት ይችላል።
°
?ቁርአን ወይም እስልምና ተብሎ ለመተርጎሙ ደግሞ ከበፊቱ ያለውን አንቀጽ ስንመለከት የበለጠ ግልፅ ይሆንልናል። አንቀጹ እንዲህ ይላል ፦
يَا أَيُّهَا النَّاسُ قَدْجَاءَتْكُم مَّوْعِظَةٌ مِّن رَّبِّكُمْ وَشِفَاءٌلِّمَا فِي الصُّدُورِوَهُدًى وَرَحْمَةٌ }
{ َلِّلْمُؤْمِنِين
[| እናንተ ሰዎች ሆይ! ከጌታችሁ ግሳጼ በደረቶች ውስጥም ላለው (የመጠራጠር በሽታ) መድኃኒት ለምእምናንም ብርሃንና #እዝነት በእርግጥ መጣችላችሁ፡፡ |] (ዩኑስ ፥ 57). ስለዚህ አንቀጹ እያወራ ያለው ስለቁርአን ነው ማለት ነው።
°
?2ኛ.እንደእነሱ አባባል ሙሐመድ - صلى الله عليه وسلم - ናቸው ብንል ታዲያ ይሄ እንዴት ብሎ ነው በአመት አንድ ጊዜ የተወለዱበትን ቀን ጠብቃችሁ, ተሰባስባችሁ, ምግብ እያበላችሁ አክብሩት እና አሳልፉት ለማለት ማስረጃ የሚሆነው? የተወለዱበትን ቀን ብቻ ገድቦ አመት ጠብቆ መደሰት ከየት የመጣ ነው?? አንዳንዶች መውሊድን ያዘዘን አሏህ ነው ብለውም በድፍረት ሚናገሩና በአሏህ ላይ ሚቀጥፉ አሉ .. ይህ በጣም ስህተት ነውና ልንጠቀቅ ይገባናል። .

✍️አቡልዓባስ አሕመድ ኢብን ያሕያ @ Ibn yahya Ahmed
ሶፈር 29/1440ሂ. # ጥቅምት 28/2011. ላይ የተፃፈ
https://t.me/ibnyahya7

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago