Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 1 day, 23 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago
አጅሬን አሞራ እና አዲሾን በሚባሉ ቦታዎች ላይ ጠላት ጥቃት ለማድረስ ቢሞክርም ሊሳካለት እንዳልቻለ የአማራ ፋኖ በጎንደር የአያሌዉ ብሩ ክፍለ ጦር አስታወቀ።ሞርጠጅ እና ዳባት መስመር በመግባት አካባቢዉን ከባድ መሳሪያ ተጠቅሞ ለመቆጣጠር ቢሞክርም የጠላትን ሴራ ጠንቅቆ የሚያዉቀዉ ፋኖ በመመከት እና በተቃራኒዉ እርምጃ በመዉሰድ ላይ እንደሚገኝ የአያሌዉ ብሩ ክፍለ ጦር ቃል አቀባይ ጌታቸዉ ጌጡ ከኤቢሲ ቲቪ ጋር በነበረው ቆይታ አስታወቀ!!!ሙሉውን ከ ABC TV ዩቱብ ቻናል ታገኙታላችሁ 👇👇👇 https://youtu.be/7pfAdnnjD-o
ሰበር ዜና!
ዙ23 ተቃጥሏል፤ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ተሸኝተዋል፤ ከ250 በላይ የአገዛዙ ሠራዊት እስከወዲያኛው ተሸኝተዋል።
ዛሬ ታህሳስ 01/2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10:00 ሰዓት ጀምሮ የአብይ አሕመድ ወራሪ ሠራዊት ከሰሞኑ ከጎንደር አዘዞ ወታደራዊ ካምፕ 5 ክ/ጦር ኃይል ወደ ሻሁራ ከተማ አስገብቶ ከነበረው ኃይል 2ቱን ክ/ጦር ወደ ቋራ ደለጎ በሻሁራው መስመር ለማስገባት አስቦ እንቅስቃሴ አድርገ። የዚህን ጨፍጫፊ ሠራዊት እንቅስቃሴ በትኩረት ሲከታተሉት የሰነበቱት የአርበኛ ሳሙኤል ባለእድሉ አድዋ ክ/ጦር እንዲሁም የአርበኛ ግዛቸው አሌው ቴዎድሮስ ክ/ጦር በጋራ ተቀናጅተው በወጉ አቀዱ፤ ስልት ነደፉ፤ መውጫ መግቢያውን አነበቡ፤ ወታደራዊ ገዥ ቦታዎችን ለይተው ወደ ሥራ ገቡ።
በዚሁ መሠረት ዛሬ ታሕሳስ 01/2017 ዓ.ም ከሌሊቱ 10:00 ላይ የአብይ አሕመድ ሙትቻ ወራሪ ሠራዊት ጓዙን ጠቅልሎ በበርካታ ኦራሎች ተጭኖ፣ ለቁጥር የሚያዳግት ጦር ደግሞ በእግር በወኩ መስመር ጉዞ ወደ ቋራ ጀመረ።
ጥቂት እንዲጓዝ ጀግኖቹ ፈቀዱለትና በቀጥታ ሻሁራን ጥቂት እንደለቀቃት የአድዋ ክ/ጦር፦ ንጋት ጮራ ብርጌድ 3ኛ ሻለቂ ውርጅብኝ መቋቋም ተስኖት ያለ የሌለ አቅሙን አሟጦ ተጠቀመ፤ ዳሩ ግን አልተሳካም፤ እየበረረ ይገባል አይወጣም፤ ረመጦቹ ለብልበው አቃጥለውና ውጠው ያስቀሩታል። ሕዝብን የሚጨፈጭፍበት ዙ23 ዛሬ ላይ ምኞት ብቻ ሆኖ ቀረ፤ በነበልባሎች ጽኑ ክንድ ነደደ፤ ሁለት ኦራል፣ 1 አስር ጎማ የጭነት መኪና፣ 2 ፓትሮል ሙሉ በሙሉ በክንደ ነበልባሎቹ ጋዩ፤ 3 የሻለቃ መሪዎችን ጨምሮ 1 ትልቅ ወታደራዊ መኮንን ተመታ፤ ለሕክምና ሳይደርሱ ወዲያው አሸለቡ፤ ከባ/ዳር አየር ማረፊያ 3 ዙር ኤሊኮፍተር ተመላልሳ ሙትና ቁስለኞችን አጋዘች።
ከሻሁራ ቋራ የተዘረጋው መንገድ የደመ ጠጭው አብይ አሕመድ ሠራዊት ደም እንደጎርፍ ፈሰሰበት፤ የአስከሬን ክምር ሞልቶትም ይገኛል። ትግላችንን አንድ ሆነን፣ ተቀናጅተን፣ አቅደን በድል የመቋጨት የጀግንነት ግብራችን በእውነተኛ አርበኞች ክንድ ወደፊት አድርጎ ኦፕሬሽኑን በድል ቋጭቷል።
አሸባሪው ወራሪ ሠራዊት በክንደ ነበልባሎቹ ምት ክፉኛ ተበሳጭቶ በርካታ የአርሶ አደሩን አቃጥሎ ቋራ የመግባት እቅዱ ከስሞ እያላዘነ ተመልሶ ሻሁራ ገብቷል።
ሰበር ዜና!
በጎንደር ቀጠና ያሉ የሁለቱ ዕዞች ክፍለጦሮችና የክፍለጦር ዋና አዛዦች በተፈጠረው አንድነት ደስተኞች መሆናቸውን ገለጹ!
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ጎንደሬ በጋሻው ክፍለጦር፣ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር፣ ዞብል ጃኖ ክፍለጦር፣ ታድሎና ጓድኞቹ ክፍለጦር፣ ጎቤ ክፍለጦር፣ መብረቅ ክፍለጦር፣ ራስ አምባራስ ክፍለጦር፣ ድብ ጠለምት ክፍለጦር፣ ካራማራ ክፍለጦር፣ ጭና ክፍለጦር በአንዱነቱ የሚዲያ መግለጫ ላይ የተገኙ ሲሆን የክፍለጦሮች ዋና አዛዦችና የክፍለጦሮቹ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ ድምፅ የጎንደር አንድነት በመበረሰሩ ለትግላችን ትልቅ ምዕራፍ ከፋች መሆኑን ከሚዲያዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ ገልጸዋል።
በአማራ ፋኖ በጎንደር በኩል የአማራ ፋኖ በጎንደር ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል ጨምሮ የክፍለጦር አመራሮች የተገኙ ሲሆን የጉና ክፍለጦር፣ የአድዋ ክፍለጦር፣ የዞዝ አምባ ክፍለጦር፣ የተከዜ ክፍለጦር፣ ቴዎድሮስ ክፍለጦር፣ ልዑል ዓለማየሁ ክፍለጦር፣ አያሌው ብሩ ክፍለጦር፣ አጣናው ዋሴ ክፍለጦር፣ ሜጀር ጀነራል ውባንተ አባተ ተወርዋሪ ክፍለጦር፣ ራስ ደጀን ክፍለጦር ዋና አዛዦችና የክፍለጦሩ ከፍተኛ አመራሮች በጋራ የተገኙ ሲሆን እነዚህም በተፈጠረው አንድነት እጅግ ደስተኛ መሆናቸውን ጠቅሰው በቀጣይም በሌሎች ቀጠና ያሉ አደረጃጀቶች ወደ አንድ እንዲመጡ ጠይቀዋል።
የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ ዮሐንስ ንጉሡ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ም/ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ አርበኛ ሳሙኤል ባለድል፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር የሚዲያና ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ አርበኛ አሸናፊ ወንዶሰንና የሁለቱም ዕዞች ክፍለጦር አመራሮች የጎንደር ዕዝ የበላይ ጠባቂ አርበኞችን፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴንና አርበኛ ባዬ ቀናውን በጋራ ወደ አንድነት ስለመጡልን ከልብ እናመሰግናለን ሲሉ ገልጸዋል።
በተጨማሪም የጎንደር ፋኖ አንድነትን ተከትሎ በጎንደር ፋኖዎች አንድነት ደስ ያላላቸው አካላት የሁለት ግለሰቦች ስምምነት ነው እየተባለ እየተነዛ ያለው ወሬ መሠረተ ቢስ ነው፣ የዲያስፖራው ማህበረሰባችንም እነዚህን አካላት እንዲያስቆምልንና እንዲያወግዝልን ሲሉ ጠይቀዋል።
በመጨረሻም በዛሬው ዕለት ያልተገኙ የክፍለጦር አመራሮች አንደኛ አገዛዙ በቀጠናው የኔትወርክ ማጥፋት በማድረጉና ሌሎች ክፍለጦሮች ደግሞ ውጊያ መሆናቸውን ገልጸው፤ በቀጣይነት ደግሞ የሌሎች ክፍለጦሮችን አጋርነታቸውን ይገልጻሉ ሲሉ ገልጸዋል።
ሰበር ዜና
እስክንድር ነጋ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ አመራር እቀይራለሁ በሚል ስብሰባ ተቀምጧል።
የሕዝባዊ ድርጅት የሚባለው ስብስብ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ አመራር ለውጥ አድርጌያለሁ ለማለት እየመከረ ነው።
በዚህም ደረጀ በላይ የአማራ ፋኖ በጎንደር ዕዝ ሰብሳቢ አድርገናል ለማለት በእስክንድር ነጋ ሰብሳቢነት እየመከሩ ይገኛሉ።
በዚህ ስዓት ስብሰባ ላይ የሚገኘው የእስክንድር ነጋ ሕዝባዊ ድርጅት የጎንደር ፋኖ አንድነት መታወጅ ከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ከቶታል።
በመሆኑም ከአማራ ፋኖ በጎንደር ክፍለጦሮችን ለማስኮብለልና በደረጀ በላይ የሚመራ ነው የሚል መግለጫ ለማውጣት እየተዘጋጀ ይገኛል።
በውይይቱ ላይ በውብአንተ አባተ ከተመሠረተው የአማራ ፋኖ በጎንደር ወጥተው ሁለተኛ የአማራ ፋኖ በጎንደር የመሠረቱት እነ ጌታ አስራደና እያሱ ከእስክንድር ጋር እየመከሩ ነው።
በትናንትናው እለት ከኤቢሲ ጋር ቆይታ የነበራቸው የጎንደር አርበኞች የጎንደርን አንድ አደረጃጀት ምስረታ የሚቃወም ማንኛውም አካሔድ ተቀባይነት የማይኖረው ፀረ-አንድነት ነው በሚል ገልፀው ነበር።
ኤቢሲ ቴቪ
አማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮች ከጤና ቡድን አመራር አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል ።
ኤቢሲ ቲቪ
የአማራ ፋኖ በጎጃም አጥንት ስፔሻሊስት ሐኪሞችን፣ ጠቅላላ ሀኪም ነርሶችን፣ የድንገተኛ ቀዶ ህክምና፣ የጤና መኮንኖችን፣ ላብራቶሪ ቴክኒሽያኖችን፣ፈርማሲስቶችን፣ የአንስቴዥያ ባለሙያወችን፣ የስነ-ምግብ ባለሙያወችን እና የጤና መረጃ ባለሙያወችን ጨምሮ 66 ፕሮፋሽናል የጤና ባለሙያወች አሉ።
ሐኪሞቻችን ለሰራዊታችን ከሚሰጡት ሕክምና ጎን ለጎን ለማህበረሰባችን የጤና ምክር እና አገልግሎት ለመስጠት ከፍተኛ ርብርብ ያደርጋሉ ።
የብልጽግና ሰራዊት ያወደማቸውን የጤና ተቋማት እና የተሰባበሩ የህክምና መሳሪያዎችን በመጠገን በጦርነት መሐል ህይወትን የማዳን ታሪካዊ ተልዕኳቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።
እነዚህ ጀግኖች የመድሐኒት : የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች የህክምና ግብዓቶች ድጋፍ በእጅጉ ይሻሉ ።
የአማራ ህዝብ የህልውና ትግል ደጋፊዎች ከጀግኖች ሐኪሞቻችን ጎን ትቆሙ ዘንድ ጥሪ እናስተላልፋለን ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም
ሊናቅ የማይገባው የአገዛዙ ክፋት: "የሠላም ስምምነት" እና የአማራ የፍትሕ ጥያቄ!!!ሙሉውን ከ ABC TV ዩቱብ ቻናል ታገኙታላችሁ👇👇👇https://www.youtube.com/live/Gxwk8PEBeXE?si=bEhP72IFfHpjR_No
ሰላም የኤቢሲ ቲቪ ቤተሰብ የከፈትነውን ዩቱብ SUBSCRIBE በማድረግ የዘወትር ትብብሮን መረጃ በፍጥነት እንዲደርሷ ያሳዩን !
ገጥመናል ገጥመናል ዩቱዩብ መዝጋት የሚቆም ትግል አልተጀመረም..‼️‼️
ትግል ዘርፈ ብዙ ነው !! በተለመደው ፍጥነታችሁ SUBSCRIBE በማድረግ ሳይበር ፋኖዎች ሚሽናችሁን ተወጡ ።
👇👇👇
http://www.youtube.com/@ABCTV-v6w
Cʀᴇᴀᴛᴏʀ @Simera10
ለማንኛውም ጥያቄ እና አስተያየት @ABFenomeno
Trustworthy source of cryptocurrency news and latest information, as well as tips for crypto trading around the world...
Last updated 1 day, 23 hours ago
🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person
Last updated 1 month, 1 week ago
🔶 የቻናላችን ቤተሰብ ሲሆኑ 🔶
✏️ የHacking ስልጠናዎች
✏️ የተለያዩ Software ጥቆማዎች
✏️ አፕ ጥቆማ
📱ምርጥ አፖች ለማውረድ @Israel_app
YOUTUBE ቻናላችን SUBSCRIBE በማድረግ እንዲተባበሩን እንጠይቃለን!!👇👇
https://youtube.com/channel/UCswq6IimdcBT8oO9uRDpodQ
📲 ያላችው ጥያቄ አስተያየት ካላ @IsraelTubeBot
Last updated 1 month, 2 weeks ago