ማራኪ

Description
please dont touch the leave button?

ሀሳብ እና.....@Nanilat
Advertising
Tags
We recommend to visit

The largest AI art gallery on Telegram!

Ads: https://telega.io/c/images_pictures
Admin: @CaptainJamesCook

Last updated 2 months, 2 weeks ago

素材 三方

Last updated 1 year, 1 month ago

غرگان بذنوبي وثوب الفرح مو ثوبي .
@thing100bot

Last updated 3 weeks, 3 days ago

7 months, 1 week ago

ሸክላ ሰሪ ሸክላን  እደሚሰራዉ  በእጆችህ ያበጃጀኸኝና የፈጠርከኝ አምላኬ ሆይ በእያዳዱ መዉጣትና መዉረድ፣  መነሳት መዉደቅ፣ማግኘትና ማጣት፣ጤና እና ህመም ዉስጥ ስላልተለየኸኝ አመሰግንሀለሁ።ከደረሰብኝ የደረስክልኝ፣ከታየብኝ ያየህልኝ፣ከሆነብኝ የሆክልኝ ይበልጣልና ምስጋናዬ ይድረስህ።ትላት ድልድይ ሆነህ አሳልፈህ፣ዛሬን መሰረት ሁነህ አኑረህ ለነገ ተስፋ  ሆነኸኛአልና ተመስገ።ሁሉም ለበጎ የምታደርግ በአላማ የምትሰራ ነህና በመዳፍህ ያለዉን እኔነቴን አጥብቀህ ትይዘዉ ዘንድ አደራ ሰጠዉህ። አሜን  

@kezimkesam
@kezimkesam

7 months, 1 week ago
7 months, 1 week ago
7 months, 2 weeks ago

ያሰደመማት..ምናልባት ለአሁን ጊዜ ዬኒቨረስቲ ተማሪ ሻራተን እና ኮንትኔታል መጋበዝም ቢሆን ብርቅ ላይሆን ይችላል…አለፍም ካላም ባህር ተሸግሮ ድንበር አቋርጦ አየር ሰንጥቆ ዱባይና ኢስታንቡል ቅዳሜና እሁድን ማሳለፍ እንደው ትንሽ ጉራ ለመንዛት ይጠቅም ይሆን እንጂ ያን ያህል አፍ የሚያስከፍት አይደለም..የዛን ጊዜ ግን ለአንድ ሴት ሻይ ቤት ወንበር ላይ ለዛውም ከጎረምሳ ጋር ቁጭ ብሎ ቀይ ሻይ መጠጣት በአሁን ጊዜ በአደባባይ ሀሽሽ እንደማጬስ ያህል ነውር ነበር…ለሁለቱም እንደዛ አይነት ቦታ ሲገቡ የመጀመሪያ ቀናቸው ነበር…በዛፎች በተከበበውና አረንጎዴ በለበሰው ግቢ ውስጥ አንድ ነጠል ያለ ቦታ ፊት ለፊት ቁጭ ብለው ሚርንዳቸውን እየጠጡ ማውራት ቀጠሉ
‹‹እንዴት ይሄን ቦታ አወቅከው.?››
‹‹ሰው አሳይቶኝ››
‹‹ከዚህ በፊት መጥተህ ነበር››
‹‹አልገባውም…ከውጭ ነው ያየውት››
‹‹እንዴት እዚህ ደርሰህ ሳትገባ ተመለስክ ››
‹‹ካንቺ ጋር ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት ስለፈለግኩ..ቀድሞ መግባት አላሻኝም፡፡››
‹‹አመሰግናለው…አንተእኮ ምርጥ ጓደኛዬ ነህ››
‹‹ጓደኛዬ ስትይ?››
‹‹ጓደኛዬ ነዋ…ጓደኛ አታውቅም››
‹‹እናም ጓደኛሽ ብቻ ነኝ…››
‹‹አይ አባቴም ነህ››ሀሳቡን ብትጠረጥርም ያልገባት መስላ ቀለደችበት
‹‹እኔ ቀልድም አይደልም ማወራው..ስላንቺ ሳስብ ልቤ ፍርፍር ነው ምትልነብኝ፤ውስጤ እርብሽብሽ ይላል፤እኔ ወዳጄ እንድትሆኚ ነው የምፈልገው››
‹‹ወዳጂ..ምን ማለት ነው?››
‹‹የወደፊት ሙሽራዬ እንድትሆጎኚ እፈልጋለው…እኔ ካንቺ ተለይቼ መኖር አይሆንልኝም…እምቢ ብትይኝ እንኳን ሞጭልፌም ቢሆን የራሴ አደርግሻለው››
እናቴ በገረሜታ‹‹ሞጭልፌ ስትል?››
‹‹ምኖ ነሽ ባክሽ ..አይገባሽም፡፡እጠልፍሻለው እያልኩሽ ነው….››
ከብዙ ማብራሪያና ልመና ቡኃላ ‹‹ላስብበት›› አለችው ፡፡በዛን ጊዜ ላስብበት ማለት ያው ግማሽ እሺታን ይወክል ነበር..አባቴ ፈነጠዘ…ለሚቀርቡት ሁሉ አዋጅ አስነገረ…የመጨራሻው መልስም እንደገመተው እሺ ሆነ …መቼስ በሴት ፍቅር የተማረከ የወንድ ልብ ነፍሱንም ጭምር አሳልፎ ቢሰጥ የሚገርም አይሆንም እና ሁለቱም እንደተመረቁ አዲስ አባባ ነበር ስራ መፈለግ የጀመሩት ያው የትምህርት ውጤታቸው ሁለቱም አሪፍ የሚባል ስለነበረ ወዲያው ነበር በአስተማሪነት አንድ ትምህር ቤት የተቀጠሩት….
ከሁለት ወር ቡኃላ ነበር የተጋቡት….ይሄ አሁን ያለንበትን ቤት አያቴ ነው ማለቴ የእናቴ አባት የሰርግ ስጦታ ገዝቶ ያበረከተላቸው…ይሄ ሲሆን ደግሞ ከዛ እናቴ እንደነገረችኝ ሁሉ ነገር ፍጽማዊ ይመስል ነበር፡፡..ሲጋቡ፤ ሲዋሀዱ፤አንድ መሶብ ቆርሰው አንድ አልጋ ላይ ለሊቱን ሲያሳልፉ በአለም ላይ ያለው ደስታ ሁሉ ተጠራርጎ እቤታቸው ገብቶ ነበር፡፡..እናቴ በስድስት ወሯ አረገዘች፡፡ይሄ ደግሞ ሌላ ደስታ፤ሌላ ፈንጠዝያ በቤታቸው እንዲዘንብ ተጨማሪ ምክንያት ሆነ..፡፡ቀኑ ደርሶ እናቴ ስትወልድ ሁለት መላአክ የመሰሉ መንትያ ሴቶች፡፡…እናቴ አንዷን ፌናን ብላ ስታወጣላት ሌላኛዋን ደግሞ አባቴ ሮዛ ብሎ ሰየማት፡፡መነጋገሪያና ደስታኛ ቤተሰብ ሆነ፡፡እህቶቼ ሁለት አመት ሞልቶቸው ድክ ድክ ማለት ሲጀምሩ እኔ ተረገዝኩ፡፡ አሁንም ሌላ ደስታ ፡፡ሁሌ ሳቅ የሞላበት ቤት፤ሁሌ ጫወታ የደራበት ቤት፤ሁሌ ፈገግታ ማይነጥፍበት ቤት…፡፡ከዛ በሶስተኛ አመት የጋብቻ በአላቸው አካባቢ እኔ ተወለድኩ..ወንድ ልጄ ከነቃጭሉ …፡፡አቤት እግዜር ሲመርቅ ተባለ፡፡ተደገሰ፤ተጨፈረ፡፡…ግን ቀናቶች እየገፉ ሲመጡ ሁኔታዬ ግራ እያጋባ መጣ፡፡እንደ መወራጨት እና መነጫነጭ የመሳሰሉት የልጅ ባህሪዎች ከእኔ ዘንድ ሊታዬ አልቻሉም፡፡ሀኪም ቤት ወሰዱኝ፡፡….አስመረመሩኝ
፤ለውጥ የለም፡፡..ለውጥ ብቻ ሳይሆን ይሄ ነው በሽታው የሚል በእርግጠኝነት የሚናገር ሀኪም ጠፋ፡፡አንድ የነርብ ችግር ነው ይላል፤ሌላው አዕምሮው መልዕክት ሰለማይቀበል ነው ይላል፤ቀስ በቀስ ደስታ ያረበበበት የነበረው ቤተሰብ ሀዘን ይጎበኘው ሲጀምር በፈገግታ ብቻ ተውጦ የኖረው ቤተሰብ የተጨማደደ ፊት ማሳየት ጀመረ፡፡
….ቢሆንም ከአመት ከስምንት ወር ቡኃላ ሌላ ልጅ ተወለደ.. ማሀሪ ፡፡ይሄ በመጠኑ መደበታቸውን ጋብ ቢያደርገውም ብዙም አልዘለቀ…በእኔ ላይ ምንም ለውጥ ባለመታየቱ ጭቅጭቁ እንደአዲስ ተጀመረ፡፡መላ አካሌ በድን ነበር..ብቸኛ መንቀሳቀስ ሚችሉት አይኖቼን ብቻ ነበሩ፡፡ከዛ ወዳጅ ዘመድ ነን ባይ ጭራሽ ለወላጆቼ እዚህ ውሰዱት እዚህ ወሰዱት እያለ ድንግርግራቸውን ያወጧቸው ጀመር፡፡…ጠበል ውሰዱት፣አዋቂ ቤት ውስዱት፤እከሌ ሚባል ሀኪም ቤት ውሰዱት….በመጠየቅ ሰበብ እቤታችን ጓራ ያለውን አስተያየት ይሰጥ ነበር፡፡ ወላጆቼም ከእምነታቸውም እየተጋጪ የእኔን መዳን ብቻ ተስፋ በማድረግ ብዙ ነገር ሞከሩ፡፡…ጉልበታቸውን፤ ጊዜያቸውንም፤ ገንዘባቸውንም በተኑ ፡፡ እኔ እንደሆነ ቅንጣት የተባለች ለውጥ እንኳን ማምጣት አልቻልኩም..እኔን ለማስታመም እና ለመንከባከብ ስትል እናቴ ስራዋን ለቀቀችና በአባቴ ገቢ ብቻ መተዳደር ጀመርን፡፡..ሰውነቴ በድን በሆንኩበት እያደገ እና እየተመዘዘ መጣ፡፡ከእኔ ኃላ የተወለደው ወንድሜ መሀሪ ቀድሞኝ መራመድና መናገር ጀመረ፡፡ አራት አመት ሞላኝ፡፡ምንም ለውጥ የለም..የምፈልገውን መጠየቅ አልችል፤ምጸዳዳው በራሴ ላይ፤ምግብ የምበላው በእናቴ እጅ፤ለዛውም በጣም የራሰ እና ለፈሳሽነት የቀረበ ምግብ ሆኖ በግድ በአንድ እጆ አፌን እየፈለቀቀች በእንድ እጇ ምግቡን ወደአፌ በመሰግሰግ፡፡
…ውሀም ሆነ ወተት..ቀና አድርጋ አንገቴን ደረቷ ላይ አስደግፋ አንድ እጇን እንደኩሬ አጎድጉዳ ከታችኛው ከንፈሬ ላይ በመደቀን ወተቱን ወይም ውሀውን እዛ መዳፌ ላይ በማንጮረር በመጋት ነበር ምትመግበኝ…፡፡
አምስተኛ አመት ላይ ስደርስ ግን አባቴ ተስፋ ቆረጠብኝ፤መነጫነጩ ጫፍ ደረሰ፡፡…ከእናቴ ጋር ንትርክ፤ጠጥቶ መግባት፤በአሽሙር መሳደብ ጀመረ…፡፡እናቴም ሰምቶ እንዳልሰማ ማሰለፍ፤ ሲብስባት ማልቀስ የእየእለት ድርጊቷ ነበር ፡፡ቡኃላ ግን ነገሮች በመሻሻል ፋንታ እየባሱ መጡ…የአባቴ ፀባይ እየከፋበት ሄደ፤ውጭ ማድርና ለእናቴ የሚሰጣት የወር ወጪም እየቀነሰ መጣ..በስተመጨረሻ ለእናቴ አስደንጋጭ ምርጫ አቀረበላት‹‹…ከእኔ ወይ ከልጅሽ አንዳችንን ምረጪ››.......

?ይቀጥላል
share???
@kezimkesam
@kezimkesam
@kezimkesam
​​​​​​​​​​​​​​​
​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽‌»‌? ሀርሜኮ ??‌✽‌┄┄
​​​​​​​​​​​​​​​​​┄┄✽‌»‌? ሀርሜኮ ??‌✽‌┄┄

7 months, 2 weeks ago

#ሀርሜ_ኮ :#ክፍል**-2

...ይሄ ታሪክ እናቴ እና አባቴ እንዴት እንደተዋወቁ የሚያትት ነው፡፡ታሪኩን የነገረችኝ እናቴ ነች፡፡እርግጥ ታሪኩን አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በስድስት ወር እና በዓመት ልዩነት አቀራረብን ለወጥ እያደረገች የተወሰነውን እየቀነሰች እና በፊት ነግራኝ ከነበረው ውስጥ ያልተካተተ አዲስ ታሪክ እየጨመረችበት ነግራኛለች፡፡እናቴ ስለአባቴ የምታወራኝ ብሶት ሲሰማት ነው..ውስጧን ሀዘን ሲቦረቡረው ነው…ልቧ ውስጥ ያለ ጥልቅ ባዶ ሽንቁር ሲረብሻት ነው፡፡የዛን ጊዜ ትናንቷን ታስታውሳለች፤የድሮ ፍቅሯ ትዝ ይላታል፡፡የዛን ጊዜ አባቴን ታስታውሳለች፤የዛን ጊዜ የሚያዳምጣትን ሰው ትፈልጋለች፤ለማዳመጥ ደግሞ በዚህ አለም ላይ ከእኔ ከልጇ በላይ ችሎታ ያለው ሰው የለም..ድንቅ የተባልኩ አድማጭ ነኝ የማንንም ንግግር አላቋርጥም ደግሞም ሚስጥር ጠባቂ ነኝ ..ማንም የፈለገውን ነገር ለእኔ ቢነግረኝ በቃ ለአምላኩ በሽኩሽኩታ እንደነገረው መቁጠር አለበት.ስለዚህ የቤታችን አባል መተንፈስ እና እፎይ ማለት ሲያስፈልጋቸው ወደ እኔ ነው የሚሮጡት..ይህ እናቴንም ያጠቃልላል፡፡
እና ይሄንን ከአባቴ ጋር የነበራትን የፍቅር ታሪክ ደጋግማ ስለነገረችኝ ልክ በእያንዳንዷ ግንኙነታቸው ወቅት አብሬያቸው የነበርኩ መስሎ ነው ሚሰማኝ …ሁሉ ነገር ልክ አሪፍ ደራሲ እንደደረሰው መሳጭ የፍቅር ድርሰት ፍንትው ብሎ ይታወሰኛል፡፡
የተገናኙት ሁለቱም የአዲስ አበባ የአንደኛ አመት ተማሪ እያሉ ነው፡፡እሱ የኬሚስትሪ እሷ የባይሎጂ ዲፓርትመንት ተማሪ ነበሩ …ያው ፍረሽ ማን ላይ ሁለቱም የሚወስዱት ተመሳሳይ አይነት ኮርስ ነበረ እና የገና ማዕበል ለማምለጥ ሁሉም ተማሪ በፍራቻ ተውጦ፤በስጋት እየተናጠ አንገቱን አቀርቅሮ በየዩኒቨርሲቲው ጥጋ ጥግ እና በላይብረሪው ከወረቀት ጋር እራሱን አጣብቆ ፍዳውን በሚያበት ወቅት ነበር..በተለይ መምህሩ አንብቡ ብሎ የጠቆማቸውን መጽሀፍና፤ሲኒየር ሚባሉት ተማሪዎች ለፈተና ያንን መጽሀፍ አንብቡት ብለው የጠቆሙትን መጽሀፍ ለማግኘት ላይብረሪ ውስጥ ያለው መራኮት እና መሻማት ያስቃልም .ያስተዛዝባልም፡፡ በተለይ የፈተናው ወቅት እየተቃረበ በመጣ ቁጥር ውጥረቶቹ በዛው ልክ እየከረሩ ይሄድ ነበር፡፡
በዚህ ወቅት ነው እንግዲህ ሞጋስ ባሴ የተባለው ከጎንደር አርማጭኦ አካባቢ ብዙ ኪሎ ሜትሮችን አቋርጦ የመጣው ወጣት በዚህ መራኮት ውስጥ በመደነጋገርም ቢሆን መፋለም ጀምሮ የነበረው..ግን ሁሌ ተሸናፊ ነበር…፡፡ካደገበት ማህበረሰብ የወረሰው ይሉኝታ ለተሸናፊ እንዲዳረግ አመቻችቶታል፤ከመናጠቅ ይልቅ መካፈልን ነበር የሚያውቀው ጓደኛን ወደ ኃላ ስቦ በማስቀረት ወደ ፊት ከመሸምጠጥ ይልቅ አንተ ቅደም ወንድሜ ብሎ ከመንገድ ገለል ብሎ ሌላውን የማሰቀደም ስነ ልቦና ነበር የነበረው፡፡ንጽህ የዋህነት፤የጠራ ሰባዊነት የግል ንብረቶቹ ነበሩ…፡፡ግን አዲስ አበባ ሌላ ነው፡፡እርግጥ ከእሱ ጋር ተመሳሳይ የሆኑ ብዙ የክፍለሀገር ልጆች ነበሩ..ግን በተለይ በመጀመሪያው አመት የሚደምቁትና ፈካ ብለው የሚታዩት የትላልቅ ከተማ ውልዶቹ ናቸው፡፡አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ..በምዕራባዊውና በምሰራቃዊው ፍልስፍና መካከል የሚዋልል ከተሜን በውስጧ የያዘች መንጠቅ እንደብልጠት፣መቅደም እንደአራዳነት የሚታይባት የተለየች ቦታ ..እና አንድ መጽሀፍ ለማግኘት ለ5 ቀን የላይብረሪውን ደጅ ፀንቶ ነበር..አልቀናውም እንጂ..፡፡
‹‹አረ ወዲያ….›› እያለ ላይብረሪውን ለቆ በቅሬታ ሲወጣ ..ያንን የሰሙ ሌሎች እኩዬቹ ሲገለፍጡበት ለሶስት ቀን የታዘበችው እናቴ ታዝባ ቅር ብሎት ነበር…በአራተኛው ቀን ግን ከተቀመጠችበት ወንበር ላይ ሳትንቀሳቀስ በምልክት ጠራችው..እሷ ወደ ተቀመጠችበት መቀመጫ ግራ በተጋባ እይታ ተገትሮ ሲያማትር መልሳ በእጇ ምልክት ጠራችው…፡፡በንዴቱ ውስጥ ቢሆንም…ወደ እሷ ተጠጋ..ስሯ ደረሰ….
‹‹ተቀመጥ አለችው…››በሹክሹክታ
‹‹ምን ይሁነኝ ብዬ….?.››መለሰላት ከእሷ ትንሽ ከፍ ባለ ድምጽ ሌሎችን የላይብረሪ ተጠቃሚዎችን እንዳይረብሹ በመስጋት ግራና ቀኝ በመሳቀቅ ተመለከተችና‹‹ ቁጭ በል›› ብላ ልክ ከዚህ በፊት በደንብ እንደምታውቀው የቅርብ ጓደኛዋ እጁን በመያዝ ስባ አስቀመጠችውና‹‹ይሄን አይደል የፈለከው …እንካ አንብብ››ብላ ስታነበው የነበረውን መጻሀፍ ወደ እሱ ፊት አስጠጋችለት ….ማመን አልቻለም..አንዴ መፅሀፉን ..አንዴ ልጅቷን እያፈራረቀ ማየት ጀመረ
‹‹አጥና እንጂ… ለዚህ መጽሀፍ አይደል ሳምንቱን ሙሉ ስትበሰጭ የሰነበትከው…..?እኔ በቂ ቀን አግኝቼ ማየት ያለብኝን ያህል አይቼዋለው ዛሬ ደብተሬን ነው የማነበው…››
‹‹ታዲያ እማታነቢው ከሆነ ለምን ታቀፍሺው.? ››በብስጭት
‹‹ለአንተ ብዬ.››
‹‹አረገኝ…..?.›.›
‹‹ባክህ ታጠና እንደሆነ አጥና …ካልፈለግክ መጽሀፍን አምጣው..››ለራሷም ባልታወቃት ስሜትም በቁጣ መለሰችለት፡፡…. እንግዲህ የመጀመሪያ ትውውቃቸው እንዲህ ነበር የጀመረው፡፡
እርግጥ ሁለቱም ኢትዬጵያዊ ይሁኑ እንጂ በተለያየ አካባቢ እና ባህል ውስጥ ነው ያደጉት ፡፡ ቢሆንም ይሄ ልዩነታቸው ለግንኙነታቸው እንቅፋት አልሆነባቸውም..እናቴ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት በምትገኘው አዲስ አለም ከተማ ተወልዳ ያደገችና ሀይስኩል ስትደርስ ወደአዲስ አበባ ሙሉ በሙሉ ገብታ ተምህርቷን የጨረሰች በመሆኗ ከተሜነት ሲያጠቃት አባቴ ግን ከአነስተኛ የገጠር ከተማ በመውጣቱ በተቃራኒ ስሜት ውስጥ ያለ ነበር..
ከዛን ቀን ወዲህ ለሁለተኛ ጌዜ የተገናኙት አንደኛ ሴሚስተር ፈተና ተጠናቆ የፈተና ውጤቱ ታውቆ ውጤቱም ቦርድ ላይ ተለጥፎ ተማሪ እየተተረማመሰ በሚያበት ጊዜ ሁለቱም ከትርምሱ ውስጥ የየራሳቸውን አይተው ሲወጡ እርስ በርስ በመላተማቸው ነበር…ዞር ብላ ስታየው ማንነቱ ትዝ ስላላት ‹‹…አንተ››አለቸ
‹‹አንቺው…አለሽ ኖሮል.? ››
‹‹ምነው ፈልገሀኝ ነበር እንዴ.?››ይሄንን የሚያወሩት ከተማሪዎቹ አጀቡ ተገንጥለው በመውጣት ብቻቸውን ጎን ለጎን እየተራመዱ ነበር
‹‹እሱማ አልፈለግኩሽም…በሀሳቤ ተሰንቅረሺብኝ እንጂ››
‹‹ምን ተሰንቅረሽብኝ..ማ.. እኔ .?››እናቴ በመገረም
‹‹እንደእሱም ማለቴ እማየደል.?››
‹‹እና እንዴት ማለት ነው.?››
‹‹በቃ ተይው…ለመሆኑ ፈተናይቱን እንዴት ሆንሽ…..?››
‹‹አሪፍ ነው...አንተስ….?››
‹‹እኔማ ጥሩ ነው.. እንዲሁ ባልፈራ ኖሮ የተሸለ አመጣ ነበር…ወይኔ ወንድ በሀገሬ መውዜር እና ምንሽር ቢደቀንብኝ ማልበረግግ ዠግና እዚ በወረቀት ተለቅልቆ ለሚመለስ የፈረንጄ ወሬ ልንቦቅቦቅ…...?››
ከዚህ ቡኃላ ግንኙነታቸው በጓደኝነት ይቀጥላል …ሁለተኛ አመት ግምሽ ድረስ ተመሳሳይ ይሆናል…አብረው ያጠናሉ…አብረው ከተማውን ይዞራሉ…ሚስጥር ይጋራሉ፡፡
ነገሮች የተቀየሩበት ቅጽበት አባቴ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ሁለት አመት ሲማር ከዕውቀቱ ይልቅ አራዳነቱ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አሳይቷ ነበር .ከንግግሩ ቀልጠፍ፤ከአለባበሱ ዘነጥ፤ካረማመዱ ጀነን ማለቱ ለሌላ ሰው አይደለም ለሱ ለራሱ ይታወቀው ነበር…አሁን ከየዋህነት ይልቅ ብልጠትን፤ከመበለጥ ይልቅ መሸወድን፤ከመግደርደር ይልቅ አይን አውጣነትን፤ተጎትቶ ከመቅረት ይልቅ ጎትቶ ማለፍን እለት ከእለት ከመደበኛ ትምህር እኩል እንደውም ከእዛም በላይ እየተለማመዳቸው የህይወቱ አንድ ክፍል አድርጎቸው አድርጓቸው ነበር የእኛ ስልጣኔ እንዲህ አይደል?እና እናቴንም በተመለከተ ሳይቀደም ሊቀድም ወሰነ በአንድ እለተ እሁድ የረፍት ቀን በወቅቱ ዝነኛ ወደ ነበረው እና ዘፋኞች ሁሉ የቪዲዬ ክሊፓቸወንን ወደሚያስቀሩጽበት ብሄረ-ጽጌ መናፈሻ ሳታስብ ወሰዳት** ​​​በጣም ነበር

7 months, 3 weeks ago
  • ?እኔኮ ስወድሽ❤️ *


እኔኮ ስወድሽ ቃላት ይደክማሉ፣
ፊደላት ሰልለው ድጋፍን ይሻሉ፣

ምን ቃል አለኝና ፍቅሬን ነግርሻለሁ፣
በልቤ ወድጄሽ ለፍቅርሽ ሞቻለሁ፣?

አንቺን መተው ለኔ ይገርምሻል ውዴ፣
ከሞት ከቶ አያንስም እወቂው እንግዴ፣?

አረ እንደውም መሞት ሳይሻል አይቀርም፣
የማፍቀር ሰቀቀን ጠባሳው አይሽርም፣
የናፍቆትን እከክ ጥፍር አያከውም፣
የመውደድን መሞት አይኖች አያዩትም፣

እናምልሽ ውዴ እራቀኝ ስትዪኝ፣
በቁም ሳለሁ በድን እንደሆንኩ እወቂኝ፣?

በፍቅርሽ ሰንሰለት እግረ ሙቅ ታስሬ፣
አቅም የተቀማሁ የማልቆም ዳክሬ፣
የመከነ ልፋት ሰርክ ምድርን ዞሬ፣
የድጋይ ላይ ተክል የማይበዛ ዘሬ፣
እንዲ ነኝ አለሜ ካጣሁሽ አፍቅሬ፣

ዓሳ ከውሃ ወጥቶ ይኖር ዘንድ እንዳይችል፣
ንስር ምድር ወርዶ እንደማይሄድ ቁልቁል፣
እየተገረፈ እንደማይድን ቁስል፣
ለመርዶ ነጋሪ እንዳይባል እልል፣
እኔም አንቺን ካጣሁ ፍቅሬ ይከብደኛል፣

እኔኮ ስወድሽ ከገደቡ አልፌ፣
ጧት ማታ ሳልምሽ መውደድሽን ታቅፌ፣
ሌላ ምንስ አለኝ ፍቅርሽ ነዋ ትርፌ፣?‍♂
ልተውሽ አልችልም ልቤ ላይ ሸክፌ፣?

ውሰጂው ያለኝን ልሁን ነጭ ደሃ፣
ወይኑንም ተጎንጪ ለኔ ደሞ ውሃ፣☺️

ከጮማው ቁረጪ አማርጪ ያሻሽን፣
እኔ ውዬ ልደር እየራበኝ ጦሜን፣?

@kezimkesam
@kezimkesam
@kezimkesam

7 months, 3 weeks ago
7 months, 3 weeks ago

​​‍ ​​​​.            ​----------------------      
??ባለታክሲዉ??  ክፍል 3

  እውነተኛ ልብ አንጠልጣይ የፍቅር
            ------------------------

በምን ቅፅበት ከቤት ውስጥ ተወርውሬ እንደወጣሁ አላውቅም
ብቻ ወንድሜን ፍለጋ ወደቤት ገሰገስኩ...... ጊቢውን ማንኳኳት አይበለው እየደበደብኩ እስኪከፍቱልኝ
ተጣደፍኩ እናቴ ነበረች የከፈተችው አልፌያት ወደውስጥ በሩጫ ገባሁ ምን ሆነሻል ልጄ እናቴ እየተጣራች
ተከተለችኝ ቀጥታ ወንድሜ ወደተኛበት ክፍል አመራው በሩን በርግጄ ገብቼ በተኛበት እላዩ ተከመርኩ ያለየሌለ
ሀይሌን ተጠቅሜ አነቅኩት እናቴ ኡኡታዋን አቀለጠችው ወንድሜ እጄን ካንገቱ ለማስለቀቅ ይታገላል እኔ።
ግሩሜን አንተ ነህ የደበደብከው አንተ ነህ ልትገለው የነበረው እያልኩ ይባስ እጄን እያጠበኩ ታገልኩት እንደምንም መንጭቆ አስለቀቀኝና ከላዩ ላይ ሲወረውረኝ ከግርግዳ ተጋጭቼ ወደኩ ግን ምንም አልመሰለኝም ድጋሜ ተነሳሁና ወደሱ ተንደረደርኩ የእናቴን ጩኸት የሰሙ ጎረቤቶች ቤቱን አጥለቀለቁት እኔንም ወንድሜንም
ያዙን እኔ እጮሀለሁ እሳደባለሁ ወንድሜ ትናንት ላወቅሽው ጎረምሳ እኔን ብቸኛውን ወንድምሽን ልትገይኝ
ልትገይኝ ይላል እናቴ ጥግ ላይ ሆና ታለቅሳለች ጎረቤት ይንጫጫል በቃ
ቤቱ በአንድ እግሩ ቆመ እኔን
ክፍሌ አስገብተው በር ዘጉብኝ ከዛ ቀጥታ ልብሴን በትምህርት ቤት ቦርሳዬ ውስጥ መሰብሰብ ጀመርኩ የቀረውን በፌስታል አድርጌ በመስኮት ዘልዬ ወጣሁ እናቴ አንዷ ጎረቤት አይታ ያዘችኝ ልቁቀኝ እዚ ቤት አልቀመጥም
አልኩኝ ብለመን ብሰራ ማንም አልሰማም አልኩ ወደቤት
ከመለሳችሁኝ እራሴን አጠለፋሁ ያለዛ ልሂድበት ልቁቀኝ ብዬ እሪ አልኩኝ ወንድሜ ከውስጥ ወጣና  ተዋት ትሂድ
ጎረምሳ ከበለጠባት ትሂድ ግን እወቂ እሬሳውን ባላሳቅፍሽ እኔ እዮብ አይደለሁም  አለኝ  እሬሳውን አታሳቅፈኝም ከገደልከውም አብረህ ነው
የምትገለን ከዚህ በኃላ እንኳን ቀን ለሊት እራሱ ከግሩም አጠገብ አታጣኝም  ብዬው እናቴ ደንግጣ ቁጭ ባለችበት በረንዳ ላይ። ሄጄ  እማ አንቺ ግን ይቅር
በይኝ አልኳትና ጉንጯን ስሜያት ወጣሁ ወደ ግሩም ሄድኩኝ የሆነውን ሁሉ አጫወትኩት በጣም አዘነ እንዲ
ማድረግ እንደሌለብኝ ነገረኝ ሆኖም አብሬው ልኖር በመምጣቴ ደስ አለው አባቴ ማታ ከስራ ሲገባ የሆነውን
ሰምቶ ደወለና ልጄ አንገቴን አስደፋሽኝ በተከበርኩበት ሰፈር
አዋረድሽኝ ካሁን በኃላ አባት አለኝ ቤተሰብ አለኝ ብለሽ እንዳታስቢ  ብሎ ስልኩን ዘጋብኝ ለጊዜው አባባሉ
ቢያስጨንቀኝም ትክክለኛ ውሳኔ እንደወሰንኩ ስለተሰማኝ ተውኩት ኑሮዬም ከግሩሜጋር ሆነ እሱም ድኖ ተነሳ ላዳው ታክሲውን ሽጧት አብነት አከባቢ ሰፋ ያለ ቤት ተከራይተን የቤት እቃ አሟልተን እሱም በሚኒባስ ታክሲ
ላይ በሹፍርና ተቀጥሮ እየሰራ እኔም ማትሪክ ውጤቴን እየጠበኩ ሽማግሌ ሰርገኛ አጃቢ በሌለበት ፍቅር ደግሶ
ፍቅር ሞሽሮ ፍቅር አፈራርሞ ዳረንና የአብሮነትን ህይወት ተካፍለን መኖር ጀመርን።
አቤት እንዴት ደስ ይል ነበር.... ያየን ሁሉ ካይን ያውጣችሁ እስከሚለን ድረስ በፍቅር ከነፍን እኔም ማትሪክ ውጤት አልመጣልኝም ነበር ከምቀመጥ የፀጉር
ሞያ ተምሬ ኑሮዋችንን ለማገዝ ተነጋግረን መማር ጀመርኩ እናቴን ወንድሜና አባቴ ሳይኖሩ በድብቅ እየሄድኩ አያታለሁ እሷም በድብቅ ቤቴ ትመጣለች እኔና ግሩሜን
አይታን ትሄዳለች።
በዚህ መልኩ ህይወት ቀጠለ ከ6 ወር በኃላ በፀጉር ሞያ ተመረቅኩኝ ከምርቃቴ ጋር ሌላ የምስራች ተፈጠረ
አረገዝኩ በወቅቱ የነበረን ደስታ እንዲ ተፅፎ የሚያልቅ አልነበረም። ግሩሜ ከቤተሰብ ጋር እርቅ እንዲወርድ
አግባባኝ አባቴ ተለምኖ እርጉዝ መሆኔ ተነግሮት ይቅር አለኝ ከወንድሜም ታረቅን በቃ ይባስ ቤታችን በደስታ
ተጥለቀለቀ የማናውቀውን ልጃችንን መናፈቅ ጀመርን እንዳይደርስ የለ መውለጃዬም ደርሶ ሴት ልጃችን ይህቺን
አለም ተቀላቀለች። ስሟን  ሀሴድ አልናት። ሀሴድ የመፀሀፍቅዱስ ቃል ሲሆን ትርጉሙም ተዝቆ የማያልቅ ፍቅር ማለት ነው። አቤት የነበረን ደስታ............ ታድያ ይህን ደስታ ያጠቆረ አንድ መፍፎ ቀን ተፈጠረ.........
ገና ወልጄ ከተኛሁ 2 ወሬ ነበር ያን ቀን ግሩሜ ከምሽቱ 2 ሰዓት አከባቢ ደወለልኝና ማማዬ የሆኑ የደብረዘይት
ሰዎች መኪና አጥተው ደብረዘይት ካደረስከን አንድ ሺህ ብር እንከፍልሃለን አሉኝ ደግሞ 6 ናቸው እና ገንዘቡ
ከመጣ ይጠቅመናል ይሄን እድል ማሳለፍ የለብምኝ አድርሻቸው እልለልለሁ ላሳውቅሽ ብዬ ነው አለኝ
ውስንጤ ደስ ባይለውም እሺ አልኩት ከዛም ግን 5 ሰዐት አለፈ አልመጣም ስልኩ ላይ ደወልኩ ይጠራል አይነሳም....... ደግሜ ሞከርኩ........
ይቀጥላል .....
share???አያረጋቹ
@kezimkesam
@kezimkesam
@kezimkesam

[​​](https://telegra.ph/file/8118edd17d1a03439769f.jpg)‍ ​​​​[. ​----------------------
7 months, 4 weeks ago

​​‍ ​​​​​[-----------------------------------------
???ባለታክሲው? ክፍል 2

እውነተኛ የፍቅር ታሪክ
------------------------------------------](https://t.me/joinchat/u5HgQ6PzqdhhY2Rk)

እኔ በህይወቴ ለመጀመርያ ጊዜ ትናንትና ነው ያየሁት እሱ እንዴት ስለኔ ይሄን ያህል ሊያውቅ ቻለ? ይሄን እያሰብኩኝ ተከፍቶ ወደሚጠብቀኝ በር ገባሁ። መንገድ ጀመርን ስለራሱ እንዲነግረኝ ጠየኩት ተወልዶ ያደገው ጨርቆስ አከባቢ እንደሆነና የወንድ አያቱ እጅግ ይወዱት ስለነበረ ሲሞቱ መሬት አውርሰውት ሞቱ መሬቱ ተሽጦ እቺን ላዳ ታክሲ ገዝቶ ስራ መጀመሩን አጫወተኝ ግሩም ደስ የሚል ልጅ ነው ከውበቱም በላይ በዚች 2 ቀን ውስጥ ያሳየኝ መልካምነትና ስነምግባር በጣም የሚገርም ነበር እኔን የት እንደሚያውቀኝ ጠየኩት ሁሌ ታክሲ ስጠብቂ አይሻለሁ ደግሞ ሁሌ ብቻሽን ስለማይሽ ይገርመኝ ነበር ከዛ አንድ ቀን የተሳፈርሽበትን ታክሲ ተከተልኩት አለምባንክ ስትወርጂ አየሁሽና መኪናዬን
ጥግ ላይ አቁሜ በእግሬ ተከተልኩሽ ከዛ ቤታቹ ስትገቢ አየሁሽ በራቹጋ የሆነ ጩጬ ሰላም ስትይ ስላየሁሽ
ጠራሁትና ያሁኗ ልጅ ስሟ ማነው ስለው ሊዲያ አለኝ ከዛ በቃ ሁሌ አንቺን መከታተል ስራዬ ሆነ አለኝ አሁን የቅድሙ ጭንቀቴ ለቀቀኝና ዘና ብዬ ማውራት ጀመርኩ እየተጨዋወትን ትምርት ቤት ስለደረስኩ አውርዶኝ ከትምህርት መልስ እንደሚጠብቀኝ ነግሮኝ ሄደ እሱን እያሰብኩ አይደርስ የለ ትምርት አልቆ ስወጣ አገኘሁት ደስ አለኝ ደስታዬ ዉደር አልነበረውም።
በዚህ መልኩ ጠዋት ጊቢያችን በር ላይ ከሰዓት ትምህርትቤት በር ላይ መገናኘት ስራችን ሆነ የፍቅር ጥያቄ ከማናችንም አፍ ሳይወጣ በፍቅር ከነፍን እኔማ
ትምህርቴ ግሩም ስራዬ ግሩም ውሎዬ ግሩም ህልሜ ግሩም በቃ እስትንፋሴ ይመስል የሱን ስም ሳልጠራ
የማወራው ወሬ ጠፋ እሱን ሳላስብ የምታልፍ ደቂቃ ጠፋች እራሴን እስክረሳ ድረስ ወደድኩት።
በዚ መሀል ታላቅ ወንድሜ ሰማ እንዴት ምን ሲደረግ እንኳን አንቺ አንድ ፍሬዋ ልጅ እኔ ታላቅሽም ፍቅር
አልጀመርኩም አሁኑኑ ይሄን ነገር አቁመሽ ትምህርትሽ ላይ ብቻ አተኩሪ ድጋሜ ከዛ ልጅጋር እንዳላይሽ አለኝ
እኔ ግን ማንንም የምሰማበት ሰዓት አልነበረም ከግሩሜጋር እንዳላይሽ ከምትለኝ በህይወት እንዳላይሽ
ብትለኝ ይሻለኛል  አልኩት በቃ ሁሌ ቤቱ ውስጥ ጭቅጭቅ ሆነ ሁኔታችን ግራ ያጋባት እናቴ ምንድነው ብላ
ስትጠይቅ ወንድሜ ሁሉንም ነገር ነገራት እናቴ በተራዋ እሪ አለች እኔ ግን ህይወቴ ታልፋታለች አላቆምም አልኩኝ
እንዲ እንዲ እያለ ጊዜውም ሄዶ ማትሪክ ተፈትኜ ት/ት ተዘጋ የትምህርት መዘጋት ለኔና ለግሩሜ ይባስ ምቹ ሆነልን ጠዋት ከሰፈር ይወስደኛል አዲስ አበባን ከሲኒማ ቤት እስከ ሆቴል ስናስሳት እንውልና ማታ ወደ ቤት ይመልሰኛል። የወንድሜና የእናቴ ጭቅጭቅ ከቀን ወደ
ቀን እየባሰ መጣ እኔ ግን ጆሮ አልነበረኝም ግሩሜ እስከዛሬ እንዴት ያለሱ ኖርኩኝ ብዬ እስከማስብ ድረስ
ህይወቴን በደስታ ባህር አጥለቀለቃት።
ታድያ አንድ ቀን እንደተለመደው አብረን ውለን ደስ የሚል ቀን አሳልፈን እቤት በር ላይ አውርዶኝ ተለያየን ሁሌም
ማታ ማታ ከተለያየን በኃላ እቤት ሲደርስ በሰላም መግባቱን ደውሎ ይነግረኛል ያን ቀን ግን ብጠብቀው ብጠብቀው አልደወለም እኔ ስደውል ስልኩ ዝግ ነው
ትንሽ ብጨነቅም ምናልባት ባትሪ ዘግቶበት ይሆናል ብዬ ተኛው ጠዋት ስነሳም አልደወለም ስሞክርም ዝግ ነው
አሁን በጣም አሳሰበኝና አንድ ብሩክ የሚባል ጓደኛውጋ ደወልኩ ከብዙ ጥሪ በኃላ አነሳው ሰላምታ እንኳን
ሳልጠይቀው ቀጥታ ወደጉዳዬ ነው የገባሁት ብሩክ ግሩሜ ምን ሆኖ ነው ስልኩ ማይሰራው?
አልኩት ብሩክ እየፈራ
ሊዱ ግሩሜ ማታ አንቺን ሸኝቶ መኪናውን ማደሪያ ቦታ
አቁሞ ሲመለስ ሌቦች ገንዘብ የያዘ መስሏቸው ደበደቡት አሁን እዚ አለርት ሆስፒታል ድንገተኛ ክፍል ተኝቷል እኔም
አጠገቡ ነኝ ከዚህ በኃላ የተናገረውን አልሰማሁትም ከአልጋዬ ተወርውሬ ተነስቼ ጠረቤዛ ላይ ያገኘሁትን ብር
አንስቼ እሮጥኩኝ በምን ፍጥነት ከሆስፒታሉ እንደደረስኩ አላውቀውም ከብዙ ፍለጋ በኃላ ግሩሜ የተኛበትን ክፍል አገኘሁት እላዩ ላይ ተጠምጥሜ አለቀስኩ አበድኩ እንደምንም ብሎ
አይዞዞሽ ማሬ ደና ነኝ እኮ አለኝ በቃ ውሎዬ እዛ ሆስፒታል ሆነ እቤት የምገባው ለማደር ብቻ ነው እሱንም
አባቴን ፈርቼ እንጂ ከግሩሜ ባልለይ ደስታዬ ነበር።
ከሳምንት በኃላ እቤት ሆኖ ህክምናውን መከታተል እንደሚችል ተነግሮት ከሆስፒታል ወጣ እኔም እቤቱ
እየዋልኩ ማስታመም ጀመርኩ
ታድያ አንድ ቀን ጠዋት እቤት አድሬ ወደሱ ቤት ስመጣ ጓደኞቹ ተሰብስበው እያወሩ ደረስኩ በሩ ክፍት ስለነበረ
መግባቴን ማንም አላየም አንደኛው ጓደኛው ቆይ ለምን እንሷን መደበቅ አስፈለገ ገሎህስ ቢሆን
ኖሮ? ፈጣሪ ነው ያተረፈህ እንጂ እሱማ የሞትክ መስሎት ነው ጥሎህ የሄደው ነገስ ቢጨርስህ ምን ይታወቃል?
ብሩክ ከሱ ተከትሎ እኮ እኔም ያንን ቀን ይነርራት ስል አይ ተው ብለህ አስዋሸኸኝ ቆይ እሱ ወንድሟስ ቢሆን
እንናተ ከተዋደዳቹ ምን አግብቶት ነው የሚያለያያቹ? የሰማሁትን ማመን አልልቻኩም በቆምኩበት መንቀጥቀጥ
ጀመርኩ ብሩክ ምንድነው የምታወሩት ግሩሜን ማን ነው የደበደበው? አልኩኝ ሁሉም ደንግጠው ወደኔ ዞሩ
መልስልኝ ብሩክ ማነው የደበደበው? ብሩክ ፀጉሩን እያሻሸ.....
ሊዱ ያኔ እኔ እውነቱን ልነግርሽ ስልእሱ ነው ተው ከወንድሟ ትጣላለች ብሎ ያስዋሸኝ እንጅ ግሩሜን
ወንድምሽ ነው ልጆች ቀጥሮ ያስደበደበው አለኝ በምን
ቅፅበት ከቤቱ ውስጥ ተወርውሬ እንደወጣሁ አላውቀም ብቻ ወንድሜን ፍለጋ ወደቤት ገሰገስኩ
ይቀጥላል .....
share???አያረጋቹ
@kezimkesam
@kezimkesam
@kezimkesam

[​​](https://telegra.ph/file/6de0803f5be5bea6370a9.jpg)‍ ​​​​​[-----------------------------------------
8 months ago
ማራኪ
We recommend to visit

The largest AI art gallery on Telegram!

Ads: https://telega.io/c/images_pictures
Admin: @CaptainJamesCook

Last updated 2 months, 2 weeks ago

素材 三方

Last updated 1 year, 1 month ago

غرگان بذنوبي وثوب الفرح مو ثوبي .
@thing100bot

Last updated 3 weeks, 3 days ago