★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 12 hours ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 1 week ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago
*🔴አዲስ የገና ዝማሬ “*በፍጽም ድንግልና” ዘማሪት ሞናሊዛ ምክሬ - “Befitsum Dingelena” by Zemarit Monaliza Mekre |በዝማሬ ዳዊት የዩቲዩብ ገጽ ያገኙታል።
ከዘመን አስቀድሞ በቅድምና የነበረ ዛሬ ሰው የሆነ አምላክ እርሱ ጌታ ዛሬ ተወለደ መለኮቱ ከትስብእቱ ፤ ትስብእቱ ከመለኮቱ ሳይለያይ ለዘለዓለም ይኖራል ፡፡
የሰማይና የምድር ጌታ ዛሬ በበረት ተኛ ፣ እሳት በጨርቅ ተጠቀለለ ፤ ወተት ጠባ ሱራፌል እሳታዊ በሆነ ክንፋቸው የሚሸከሙት ጌታ በማህፀን ተወሰነ በእሳት ሠረገላ የሚበር አምላክ ድንግል ታቀፈችው ።
እመቤቴ ሆይ መንበሩ ኪሩቤል የሆኑለት ፣ ቅዱስ ቃል በአንቺ ላይ አደረ ፤ መንበሩ ታላቅ ነው ! የሰውን ኀሊና አስቀድሞ ያውቃል ከግሩማን ይልቅ ግሩም የሆነ ወደዚህ ዓለም መጥቷልና።
ምስጋናው የማያልቅ ደም ግባቱ የሚያንፀባርቅ ፣ ሕፃናትን ውብ አድርጎ የሚሥላቸው ፣ ለመላእክት የሚነግስላቸው ንጉሥ በበረት ተኛ ሰብአ ሰገል ሰገዱለት ሰባቱ ሰማያት የማይወስኑትን ድንግል ማርያም እንደምን አድርጋ ወሰነችው ቢሉ አብ ከሰማይ ሆኖ ስለወደዳት ።
የዓለም ሁሉ ደስታ የቅዱሳን ክብር የሚሆን መድኅን ክርስቶስ በቤተልሔም ተወለደ አዲስ መርከብ የፍጡር ሁሉ ሲሳይ ማርያም ሆይ በአዲስ ድንኳን ከእርሱ ጋር ያስቀምጠን ዘንድ ከቸሩ ልጅሽ ለምኚልን ፡፡
#እንኳን_አደረሰን_አደረሳችሁ
©
#ይኽ_ትምህርት_ለሁሉም_የተዳረሰ_ይሆን_ዘንድ_ሼር_ላይክ_ኮመንት_እናድርገዉ_ቻናሉንም_ለብዙዎች_ተደራሽ_እያደረግን_የሚሰጡ_ትምህርቶችን_በማዳረስ_ሐዋርያዊ_አገልግሎት_እንስጥ!
#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
መልእክተ ቅዱስ ፓትርያርክ፤
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤
የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያት በሙሉ፤
በምሉእ ፍቅሩ ሰውን ከባርነት ወደ ነጻነት ለመመለስ በሥጋ ሰብእ የተወለደው ጌታችን ኣምላካችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ሰባት ዓመተ ምሕረት የልደት በዓል በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ፡፡
“ስብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት ወሰላም በምድር ለዘሠምሮ ለሰብእ፤ ክብር በሰማያት ለእግዚአብሔር ይሁን›› በምድርም እጅግ ለወደደው የሰው ልጅ ሰላም ይሁን” (ሉቃ ፪÷፲፬)
ይህ ቃለ ሰላም በጌታችን ዕለተ ልደት የተነገረ ነው፣ ቃሉ የተነገረው እንዲሁ እንደ ተራ ነገር ሳይሆን በቃለ መዝሙር እየተደጋገመ ነው፡፡ የተዘመረውም በምድራውያን ደራሲዎች ሳይሆን በሰማያውያን መላእክተ እግዚአብሔር ነው፣ የያዘው መልእክትም ሰማያውያንና ምድራውያንን ሁሉ ያካለለ ነው፡፡ የመልእክቱ ገዢ ሓሳብም አምላክ ከሰውነታችን ጋር ባለመለያየት፣ ባለመጠፋፋት፣ ባለመቀላቀል፣ ባለመዋዋጥ፣ ባለመለዋወጥና ያለባዕድና አንድ አካል፣ አንድ ክዋኔ፣ አንድ ጠባይ ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጾኣልና እግዚአብሔር ይክብር ይመስገን፡፡ የተዋሕዶውም ምስጢር ሰላምን ያሰፍናልና እግዚአብሔር ሰውን በእጅጉ መውደዱ ከዚህ ተዋሕዶ ዓውቀናል የሚል ነው፡፡
በእርግጥም እግዚአብሔር ሰውን ለመውደዱ ከዚህ የበለጠ ማሳያ ወይም ማስረጃ የለም፤ እንከን የለሽ ንጹህ አምላክ የእኛን ኃጢአተኛ ሰውነት አካሉ አድርጎ ተወለደ ሲባል ላስተዋለው ሰው ምንኛ ቢወደን ነው የሚለው ጥልቅ አድናቆትን ያጭራልና ነው፡፡ይህ ብቻም አይደለም በዚህ ነገረ ተዋሕዶ ምክንያት ሰውነታችን አምላክ ሆኖ በመንበረ ጸባኦት እንዲቀመጥ መብቃቱ የድኅነታችንና የክብራችን ከፍታ ምን ያህል አስተማማኝ ደረጃ ላይ እንደደረሰ መንፈሳችን በአንክሮ ይረዳዋል፡፡ድምር ውጤቱም በእግዚአብሔርና በሰው መካከል ፍጹምና አስተማማኝ ሰላም መፈጠሩን ያስረዳናል፤ ሰማያውያኑ መላእክተ እግዚአብሔር በመዝሙራቸው ያበሰሩን ይህንን የምስራች ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
እኛ ክርስቲያኖች እግዚአብሔር ፍቅር ነው፣ እግዚአብሔር በእጅጉ ይወደናል ስንል እንዲሁ ከሜዳ ተነሥተን ኣይደለም፡፡ በበደላችንና በኃጢአታችን ሳይጸየፈን ሰውነታችንን በረድኤት ወይም በኅድረት ያይደለ በኩነት ተዋሕዶ ወደ አምላክነት ደረጃ ከፍ ስላደረገው ነው እንጂ፡፡ እግዚአብሔር በዚህ ፍጹምና ምሉእ ፍቅሩ ሰውነታችንን በመበረ ጸባኦት ኣስቀምጦ መላእክት ሳይቀሩ ፍጥረታትን በሙሉ እንድንገዛ አድርጎናል፤ ምክንያቱም መላእክት በዕለተ ልደት የዘመሩለት በተዋሕዶ አምላክም ሰውም ለሆነ ለቤተ ልሔሙ ሕፃን እንጂ ለመለኮት ብቻ ኣይደለምና ነው፡፡ የዕለተ ልደት መዝሙር ዛሬም በሰማያትም ሆነ በምድር በተዋሕዶ ሰውም ኣምላክም የሆነ አንዱ ኢየሱስ ክርስቶስ ይመለክበታል፣ ይመሰገንበታል፡፡የሰማዩና የምድሩ ዕርቅ ወደ ኋላ ላይመለስ ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በዚህ ተከናውኖኣል፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ የሰውም አዋጭ ምርጫ ይህ ዕርቅ ተጠብቆ እንዲኖር ነው፣ ያለ ዕርቅ ሰላም ሕይወት የለውምና፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የእግዚአብሔር ክብርና ሰላም በእጅጉ የተሳሰሩና የተቆራኙ ናቸው፤ እኛ እግዚአብሔርን ካከበርነው፣ ካዳመጥነው፣ ከታዘዝነውና ከተከተልነው ሰላም አለ ማለት ነው፡፡ ለሱ ካልታዘዝንና እሱን ካላከበርን ግን ዘላቂ ሰላምን ማግኘት ፈጽሞ የማይታሰብ ነው፤ ምክንያቱም ሰላምን ጨምሮ መልካም ነገር ሁሉ ያለው በእግዚአብሔር እጅ ነውና፡፡ ዛሬ በሁሉም የዓለማችን ማዕዘን የሚታየው የሰላም መደፍረስ እግዚአብሔርን ካለማክበራችንና ለሱ ካለመታዘዛችን የተነሣ እንደሆነ መዘንጋት የለብንም፡፡ ዓለም ከእግዚአብሔር ቃል ርቃ ለመሄድ በእጅጉ እየኳተነች ነው፤ በዚህ እኩይ ተግባርዋ ደግሞ እግዚአብሔር ለስጋትና ለጉስቁልና አሳልፎ እየሰጣት ነው፡፡ እግዚአብሔር በምስጢረ ሥጋዌው ቢታረቃትም ዕርቁን ማክበር አቅቶአታል፤ ይህንን የእግዚአብሔር ጸጋ ቸል ብላ የምታደርገው ሩጫ የትም ሊያደርሳት እንደማይችል ብታውቅና በንስሓ ብትመለስ እግጅ ተጠቃሚ ትሆናለች፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የእግዚአብሔር ቃል “እናንተስ ከማይጠፋ ዘር ተወለዳችሁ” ብሎ ተስፋውን እንደነገረን ምድባችን ከማይጠፋ ዘር እንዲሆን ክርስቲያኖች የሆን ሁላችን በአእምሮ ጐልብተን፣ በሥነ-ምግባር ኣምረን፣ ጤናማ ሕይወትን ልንመራ ይገባናል፡፡
የአምላካችንን በዓለ ልደት ስናከብር ነገረ እግዚአብሔርን፣ ነገረ ፍቅርን፣ ነገረ ዕርቅንና ነገረ ሰላምን በማኅበረሰባችን የማሥረጽ አጀንዳ ይዘን ልናከብር ይገባል፡፡
ጠቡ ፣ ጥላቻው፣ መለያየቱ፣ መጠፋፋቱ፣ ለወንድሜ ከማለት ይልቅ ለኔ ለኔ ማለቱ ሲጎዳን እንጂ ሲጠቅመን ኣላየንም፡፡ አሁንም ወደ ልባችን እንመለስና በፍቅር፣ በዕርቅና በእኩልነት፣ በስምምነትና በወንድምነት ወደሚገኝ አንድነት እንምጣ፤ የልደቱ መዝሙር ያስተማረን ይህና ይህ ብቻ ነውና፡፡ በሌሎቹ ክፍለ ዓለማት እንደሆነው ሁሉ በሀገራችን የተከሠተው አላስፈላጊ ግጭት ብዙዎችን አሳጥቶናል፤ ብዙዎችንም ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሎ ሜዳ ላይ ፈሰው የሰቆቃ ኑሮ እንዲገፉ አድርጎብናል፡፡ የሀገር ሀብት እንዲወድም ሆኖአል፤ ልጆቻችን ምናለ ከእንግዲህ ወዲህ ቢበቃንና ምድሪቱን የሰላም አየር እንድትተነፍስ ብንፈቅድላት፤ ይህ የወቅቱ የቤተክርስቲያናችን ዋነኛ መልእክትና ጥሪ ነው፡፡
በመጨረሻም፡-
በዓለ ልደት የእግዚአብሔር በዓል ነውና፣ እግዚአብሔር በምድራችን ሰላምን ያወርድ ዘንድ ካለን ከፍለን ለተፈናቃዮች፣ ለነዳያን እና ለአካል ጉዳተኞች በመለገስ በዓሉን በመንፈሳዊ ደስታና በሰላም እንድናከብር አባታዊ መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፤
መልካም በዓለ ልደት ያድርግልን፡፡
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ሕዝቦችዋን ይባርክ
ወስብሐት ለእግዚአብሔር አሜን!
አባ ማትያስ ቀዳማዊ
ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ
ተክለሃይማኖት
ታኅሣሥ ፳፱ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
#መርቆሬዎስ_ሆይ፤ ፈጽሞ ለሚያምረው ቁመናህና ደም ግባትን ለተመላ መልክህ ሰላም እላለሁ፡፡ ሥቃዩን ሁሉ የተቀበ ልክ #ሰማዕት_ሆይ፣ ሥዕልህ ተንኮለኛ ዑልያኖስን በገደለው ጊዜ ሀገሪቱ ከሰራዊቱ ጋር በአንድነት ደነገጠች፡፡
#መርቆሬዎስ_ሆይ፤ ሥቃዩን ሁሉ ከፈጸምክ በኋላ በተሳለ ሰይፍ አንገትህ በተቆረጠ ጊዜ ለወጣው ነፍስህ ሰላም እላለሁ፡፡ #ሰማዕት_ሆይ፤ እግረ ልቦናዬ በፊትህ በቆመ ጊዜ በነጋ በነጋ ጎብኘኝ፤ ሰላምንም ስጠኝ፡፡ ደግ እናትና አባት አድርጌሀለሁና፡፡
(መልክአ መርቆሬዎስ)
#በረከቱ_ይደርብን_ጸሎቱ_ትራዳን!
ውሾች የሚመላለሱበት ምክንያት የታወቀ ነው። ልክስክስ ሥጋ ወዳለበት አዘውትረው ይገሠግሣሉ። ቀጠሮ ያላቸው ይመስል የሞተ ነገር ባለበት አካባቢ አይታጡም። ታዲያ የውሾችን ምልልስ ለመግታት ምን ማድረግ ይሻላል? ዓይንን ሳይከድኑ መጠበቅ?
እሱማ እንዴት ይሆናል ከመላእክት አንዱ መጥቶ ካልጠበቀልን።
በትር ይዞ መምታት ማስፈራራት ?
እሱም አያዋጣም በትሩን እንደምንም የማይቆጥር ጩኸታችንን የማይሰማ ውሻ ሊያጋጥም ይችላላ!
ታዲያ ምን ይሻላል?
ቀላሉ ዘዴ ከውሻ ጋር ከመታገል የሞተውን ነገር አንስቶ መቅበር ነው። ካጠገብ ማራቅ ነው።
አጋንንት እንደ ውሻ ተመላላሾች ናቸው። በምን እንመልሳቸዋለን? የሞተ ነገር ያዩበትን የልቡና ሜዳ እንደፈለጉ ይፈነጩበታል።
ወንድሜ ሆይ! አጋንንትን እና ውሻን ቁጭ ብለህ ጠብቀህ አታመልጥም። እነሱ የማያንቀላፉ ዘወትር ያንተን መዘንጋት፣ ያንተን መተኛት ሲጠባበቁ የሚኖሩ ናቸው።
በበትር ማለትም በጸሎት በአገልግሎት እመልሳቸዋለሁ ብለህም ከሆነ አንዳንድ ጊዜ በትር እንደማይመልሰው ክፉ ውሻ በጸሎት በጠበል ቢባሉ ማይወጡ አጋንንት አሉ።
በቀላሉ ለማባረር ከፈለግህ ባጠገብህ ያለውን የሞተ ሕይወት መቅበር ነው።
ነፍስ የተለየው በድን ይዘህ እየዞርህ አንተ ባለህበት አካባቢ ሁሉ አጋንንት ይረባረባሉ።
ከውሻ ጋር ከመታገል ውሾችን ሊጠራቸው የሚችለውን ጥምብ ነገር አርቆ መጣል።
የሞተ ክርስትና ይዞ እየዞሩ ሰይጣን ተፈታተነኝ አይባልም። የታወቀ ነዋ! የሞተ እንስሳ ካለ ውሾች አሞሮች ይጠፋሉ?
ሽታው አይደል የሚሰበስባቸው?
እንደዚሁ ሰይጣንስ በበጎ ሥራ መጥፋት ምክንያት የሞተ ክርስትና ካላቸው ሰዎች ዘንድ ማንም ሳይነግረው ያንዣብባል።
ምንም እንኳን ከእግዚአብሔር አጠገብ ቢቀመጥም ሰይጣን ከይሁዳ ልብ እንዴት ሊርቅ ይችላል?
አይቷላ የሞተች ነፍስ።
ብታባርሩትም ይመለሳል።
አይገርምም ግን?
የሚሻለው ምንድነው ካላችሁኝ ሰይጣንን ሊጠራ የሚችል ርኩስ ነገርን ካጠገባችን ማራቅ ነው።
የሞተ እንስሳ ቤተ መንግሥት ውስጥ ቢኖር አሞሮችን ከመሰብሰብ የሚከለክላቸው ማነው? ቤተ መንግሥትም ሆነ ቄራ የሞተ እንስሳ ካለ ለውሾችና ላሞሮች አንድ ነው።
አጋንንትም እንዲሁ ናቸው።
ቤተክርስቲያንም ውስጥ ብንኖር ገዳምሞ ብንደበቅ የሞተ ነገር በውስጣችን ካገኙብን ያችን እያሸተቱ ይዞሩናል።
የሚሻለው ርኩስ የሆነውን አውጥቶ መጣል ነው።
#You_tube #Instagram #Facebook_pages subscribe እና share እያደረጋችሁ አገልግሎታችንን ተደራሽ በማድረግ አግዙ🙏🙏🙏
“አብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ወልድም ከመንፈስ ቅዱስ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ መንፈስ ቅዱስም ከአብ ከወልድ ተለይቶ የኖረበት ዘመን የለም፤ ሥሉስ ቅዱስ በዘመኑ በቀኑ ሁሉ በግብርም በስምም ሳይለወጥ ሳይፋለስ ጸንቶ ያለ ነው እንጂ።
ጥንት የሌለው ቀዳማዊ ልጅ ያለው እግዚአብሔር አብ ብቻ ነው ።ዳግመኛ እርሱ ወልድም አይመረመርም ማንም መርምሮ አያገኘውም።
አብ ከዘመን በኋላ አልወለደውም እርሱ ቀዳማዊ ወልድ ከአብ ጋር በቅድምና የነበረ ነው:: እንጂ የማይሞት ከአብ ጋር ፈጣሪ ነው፤ እንደ አብም ሁሉን የፈጠረ ነው።
እንዲሁ መንፈስ ቅድርስም ከአብ ከወልድጋር በቅድምና የነበረ ቀዳማዊ ነው፤ በሥራውም ሁሉ ከአብ ከወልድ ጋር አንድ ነው።
ጉባኤ የቆመላት ቤተክርስቲያን የተቀበለችው ሐዋርያት ያስተማሩት እውነኛ ትምህርት ይህ ነው።
አምነውበት ጸንተውበት ይኖሩ ዘንድ የተነገረው ነገር ሁሉ በየክፍሉ ያለው ምክንያቱ ምን እንደሆነ ዘንድ ላልተማሩት ዕውቀት እንድትሆን አባቶቻችን በኒቂያ የወሰኗት የደነገጏት የከበረች ሃይማኖት ይህች ናት:: “
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 12 hours ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 5 months, 1 week ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month, 3 weeks ago