News and announcements of the library. No books here.
??Official Chinese channel: t.me/zlib_china_official
? https://singlelogin.re
https://en.wikipedia.org/wiki/Z-Library
? https://twitter.com/Z_Lib_official
? https://mastodon.social/@Z_Lib_official
Last updated 3 months, 3 weeks ago
Intel slava is a Russian News aggregator who covers Conflicts/Geopolitics and urgent news from around the world.
For paid promotions and feedback contact us at: @CEOofBelarus
Last updated 4 weeks ago
?Welcome to the best book channel of Telegram.
✨Buy ads: https://telega.io/c/BooksHub25
✨Contact admin ➠ @Bookshub_contact_bot
✨ Off Topic Community➠ @BooksHubCommunity
✨ Copyright Disclaimer➠ https://telegra.ph/LEGAL-COPYRIGHT-DISCLAIMER-09-18
" ማንበብ ያቆመ ወጣት ማለት የማያድግ ወጣት ማለት ነው። "
በመጨረሻም ነብይ መኮንን ለወጣቶች ስለንባብ ያለውን ምክር አካፈልናቹ።?****
ሀገርህ ናት በቃ!
——
ይቺው ናት ኢትዮጵያ
ሀገርህ ናት በቃ!
በዚች ንፍቀ-ክበብ፤
አይምሽ እንጂ መሽቶ፣ ማታው ከጠረቃ
የነቃም አይተኛ የተኛም አይነቃ።
ይቺው ናት ዓለምህ፤ ብቻዋን የተኛች ከዓለም ተደብቃ!!
አኪሯ ቀዝቅዞ፤ ያንቀላፋች ውቢት ያንተው
የክት ዕቃ!
ምን ትሆን እንግዲህ ሀገርህ ናት እሷ!
ልቧን አታውልቃት አትጨቅጭቃት በቃ፤
አብረህ አንቀላፋ፤ ወይ አብርሃት ንቃ!!
21/8/97 (ለልብ አውልቆች)
ምንጭ:- ስውር – ስፌት በነብይ መኮንን
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
የተሰኘው የማርጋሬት ሚሼል (Margaret Mitchell) አንጋፋ ስራ <ነገም ሌላ ቀን ነው> በሚል ርዕስ ወደ አማርኛ የተተረጎመበትን አስደናቂ ታሪክ ላካፍላችሁ ወደድኩ ።
ዘመኑ የደርግ ዘመነ መንግስት ነው። አንድ ተሳፋሪ ከውጭ ሀገር ወደ ኢትዮጵያ ሲገባ 'የ CIA ተላላኪ' ተብሎ ከቦሌ ኤርፖርት ቀጥታ ወደ ማዕከላዊ እስር ቤት ይታሰራል። ይህን መፅሐፍ በሻንጣው ይዟል። ይህ አንጋፋ ስራ ነብይ መኮንን እጅ የገባው በዚህ የታሪክ አጋጣሚ ነበር።
በመጽሐፉ የተመሰጠው ነብይ መኮንን ይህንን መጽሐፍ ለመተርጎም ይወስናል። መች ይፈታ? ነገ ይሙት... ይኑር ባያውቅም፣ እጁ ላይ ግን ከሰዓት ውጪ ምንም የለም። ስለዚህ ቆረጠ!
እንደ ደርግ አይነት ለመናገርና ለመጻፍ፣ ለየት ያለ አመለካከት ባንፀባርቅክ ቁጥር በጎሪጥ እታያለሁ፣ እገደላለሁ ብለው በሚያስቡበት ዘመን
ከርቸሌ ውስጥ መጽሐፍ መተርጎም ምን ያህል ከባድ እንደሆነ ማሰብ የሚችል ሰው የማያጣው ጉዳይ ነው። ወረቀት ማግኘት ቢቻል እንኳን መዘዙ ብዙ ነው። በዘቦች የትኛው ጊዜ ሊቀደድ፣ ሊወረስ፣ ተቀዶ ሊጣል ይችላል። ሌላም ሌላም....
ታዲያ ወጣቱ ነብይ መኮንን ይህን ሲያሰላስል የዘየደው መላ አስደናቂ ነበር። መጽሐፉን የሲጋራ ፓኬት ውስጥ በሚገኘው ብልጭልጭ አሊሙንየም ፎይል ውስጥ ሊተረጉመው አቀደ። በግቢው ውስጥ ካሉ ሲጋራ ከሚያጨሱ እስረኞች ይህንን እየሰበሰበ፣ ለደህንነቱና ከእስር ቤቱ ዘበኞች ዓይን ለመውጣት ማታ ማታ ብቻ ይጽፋል። ለቦታ ቁጠባ ሲባል፣ ፊደሎቹን ደቃቅና ምስር ምስር የሚያካክሉ አድርጓቸዋል። የተረጎመውንም ለአንዳንዶቹ ያነብላቸው ነበር። በወቅቱ የተሻለ የእንግሊዘኛ እውቀት ካላቸውና ጀነራል ዊንጌት ከተማሩት እንደ ካፒቴን ተስፉ አይነት ወጣቶች እገዛ አግኝቷል።
አጠቃላይ ሁለት አመታትን የፈጀው የዚህ መጽሐፍ ትርጓሜ፥ በደፋር ከእስር ተፈቺዎች እየተቆራረጠ ወደ ነፃው ዓለም የተሻገረ ሲሆን ፤ ይህን ብልጭልጩን ፎይል አጣጥፎ መልሶ ፓኮ ውስጥ በመክተት ፓኮውን መልሶ በማሸግ ያልተፈታ ሲጋራ በማስመስል ነበር። በመጨረሻም ነብይ ሲፈታ እነዚህ የሲጋራ ወረቀቶች ከያሉበት ተሰብስበው ነበር ለህትመት እንዲበቃ የተደረገው። ????
Fun Fact : ''እንዳሻው'' የተባለ ከቦረና የመጣ ሌላ እስረኛ፣ ልክ እንደ ነብይ በእስር ወቅት ያዘጋጀው የኦሮምኛ-አማርኛ መዝገበ ቃላትን ጠርዞ ሊያስወጣው ሲሞክር የእስር ቤቱ ጠባቂዎች ቀዳደው ሊጥሉበት ችለዋል።??
? ምንጭ፡ መዓዛ ብሩ ከጋሽ ነብይ መኮንን ጋር በሸገር ሬድዮ ''የቅዳሜ ጨዋታ'' ላይ ካደረገችው ቃለመጠይቅ ላይ የተወሰደ
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
"ከሞት ጋር ተቃጥረን!"
ከሞት ጋር ተቃጥረን፣ የቆራጥ ቀጠሮ
ካምናም ብሶበታል- ዘገየ ዘንድሮ::
ወትሮም እንዲህ ነው የአበሻ ቀጠሮ!!
ሞት ለካ አበሻ ነው?!
ግና ምን ሆኖ ነው?
እንዴት ቢንቀኝ ነው?
እንዴት ቢፈራኝ ነው?
መንገዱ ረዘመ ወይ መንገዱ ጠፋው?።
የህይወትን አጥር፣ ዳር ዳሩን ይዞራል!
ዕድሜን ደጅ ይጠናል፣
ሞትም እንደሰው ልጅ ቀን ይጎድልበታል?።
በለስ የቀናት'ለት
ህይወት እንደዚህ ናት
ሞትን መገነዣ፣ ስውር ስፌት አላት !!
ነቢይ መኮንን (ስውር-ስፌት ገጽ 114)
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
ምርጥ ሃያ ስለመፅሐፍ የተነገሩ አባባሎች!
(በእኔ የተመረጡ እና የተተረጎሙ)
(እ.ብ.ይ.)
ወዳጆች ዛሬ የንባብ ባህላችን እንዲዳብር ሊያነሳሱን የሚችሉ ስለመፃሕፍት የተነገሩ የተለያዩ ሠዎችን አባባል ዛሬ ልንዘክር ብዕራችንን ከወረቀቱ አገናኝተናል፡፡
መፅሐፍ የሚሠጡት ጥቅም የታወቀ ቢሆንም በማንበብ ብቻ ግን አዋቂ መሆን አይቻልም ባይ ነኝ፡፡ ምክንያቱም መፃሕፍትን ከማንበብ ባሻገር በንባብ ያገኘናቸውን ሃሳቦች ከሃሳባችን ጋር በማስተያየትና በማሻሻል፣ በማሠላሠልና በማስተዋል አዲስ ሃሳብ ካልፈጠርንበት መፅሐፍ ማንበብ ሳይሆን መፅሐፍ መቁጠር ነው የሚሆነው፡፡ ባነበብነው ሃሳብ ተገዝተንና አዲስ የባህሪ ለውጥ ወይም አዲስ ነገር ካልፈጠርንበት ማንበባችን ዕውቀት አይሆንም፡፡ ምክንያቱም ዕውቀት ስንል በተጨባጭ በተግባር የሚገለፅ ነውና፡፡
ለማንኛውም አባባሎቹን እነሆ እላለሁ..! ሃሳብና አስተያየታችሁ የተጠበቀ ነው፡፡ መልካም ንባብ!
‹‹መፅሐፍ አንድ ቁምነገር አለው፡፡ ይሄም እግርህን ከቤትህ ሳታነሳ ዓለምን እንድትዞር ያደርግሃል›› (ጁምባ ራሂሪ)
‹‹አንባቢ ከመሞቱ በፊት አንድ ሺ ኑሮ ይኖራል፡፡›› (ጆርጅ ማርቲን)
‹‹መፅሐፍት ተንቀሳቃሽ አስማቶች ናቸው›› (ስቴፈን ኪንግ)
‹‹እንደመፅሐፍ ያለ ታማኝ ጓደኛ የለም፡፡›› (ኸርነስት ኸርሚንግወይ)
‹‹ አንድ ነገር አንርሳ! አንድ መፅሐፍ፣ አንድ እስኪብርቶ፣ አንድ ሕፃን፣ አንድ መምህር ዓለምን መለወጥ ይችላሉ፡፡›› (ማላላ ዮሶፍዜ)
‹‹ዓለም መፅሐፍ ናት፡፡ ዓለምን ተጉዘው ያላዩ መፅሐፍ ይግለጡ፡፡›› (ቅዱስ አውግስጦስ)
‹‹መፅሐፍ በየዕለቱ የሚያጋጥመንን የህይወት ጉድፍ የሚያስወግድልን የነፍሳችን ማጠቢያ ነው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹ማንበብ ለአዕምሮ ሲሆን አዕምሮም አካላችን ምን ማድረግ እንዳለበት ያቀናጃል›› (ያልታወቀ ሠው)
‹‹መፅሐፍ ከባድ መሆን አለበት፡፡ ምክንያቱም ዓለሙ ሁሉ በእርሱ ታጭቋልና፡፡›› (ኮሜሊያ ፈንክ)
10. ‹‹ዛሬ አንባቢ የሆነ ነገ መሪ ይሆናል፡፡›› (ማርጋሬት ፉለር)
11. ‹‹ዛሬ ልታነበው የምትችለውን መፅሐፍ ለነገ አታቆየው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
12. ‹‹ካነበብኩ መላው ዓለም ለእኔ ክፍት ነው፡፡›› (ሜሪ ማክሎድ ቤቱን)
13. ‹‹አንዳንድ መፅሐፍት ነፃ ይተዉናል፡፡ አንዳንዶቹ ደግሞ ነፃ አድርገው ይሠሩናል፡፡›› (ራልፍ ዋልዶ ኤመርሠን)
14. ‹‹መፅሐፍ ወደፊት ልንሆን የምንፈልገውን የያዘ ህልማችን ነው፡፡›› (ኔል ጌማን)
15. ‹‹ቤተ-መፃሕፍቶች ልክ እንደጥሩ ትዝታ መዓዛቸው ያውደኛል፡፡›› (ጃኩሊን ውድሰን)
16. ‹‹መፅሀፍ አስተሳሰባችንን የሚያቀጣጥል መሣሪያ ነው፡፡›› (አላን ቤኔት)
17. ‹‹እኔ በቀላሉ የመፅሐፍ ጠጪ ነኝ›› (ኤል ኤም ሞንቶጎሞሪ)
18. ‹‹ሌላ ሠው ያነበበውን ብቻ እያነበብክ ከሆነ ሌላ ሠው የሚያስበውን ብቻ ነው እያሠብክ ያለኸው፡፡›› (ሐሩኪ ሙራካሚ)
19. ‹‹ቤት ያለመፅሐፍት ማለት አካል ያለነፍስ ማለት ነው፡፡›› (ሲስሮ)
20. ‹‹ተራ ሠዎች ትላልቅ ቲቪ አላቸው፡፡ ብልህ ሠዎች ግን ቤተመፃሕፍት ናቸው፡፡›› (ያልታወቀ ሠው)
__
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ማግሠኞ ታሕሳስ ፲፯ ቀን ፳፻፲ ዓ.ም
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
?የሁለት ደቂቃ ንባብ
አትተርጉሙ!
አንድ አባት ከልጆቹ ጋር ወደ አንድ ካፌ ይገባል።ካፌው ውስጥ እንደገቡ ብዙም ሳይቀመጡ ልጆቹ መሯሯጥና እየተጯጯሁ መጫወት ይጀምራሉ።ይሄ ሁሉ ሲሆን አባት አንገቱን ደፍቶ በሀሳብ ጭልጥ ብሏል።ይሄን ሁሉ የሚመለከት አንድ ሰው በልጆቹ እንቅስቃሴ ተረብሾ ልጆቹን ስርአት የማያስይዝ ምን አይነት ቸልተኛ ሰው ነው እያለ በአባታቸውን ይናደዳል።በዚህ ብስጭት ውስጥ ሆኖ የሚሯሯጡት ልጆች ድንገት የእሱን ጠረጴዛ ነክተውት ኖሮ ያዘዘው ሻይ ልብሱ ላይ ተደፋ።ይሄን ጊዜ ንዴቱን መቋቋም አቅቶት ውደ አባትየው ሄደ።ለግጭት እየተጋበዘ ሊያንቀውም እየዳዳው”ምን አይነት የማትረባ ሰው ነህ?ልጆችህን ስርአት አታስይዝም?”ብሎ አምባረቀበት።አባትየው በረጅሙ ተንፍሶ በተረጋጋ አንደበት”ወዳጄ የልጅነት ሚስቴ የልጆቼ እናት ታማ ከምትረዳበት ሆስፒታል አሁን ከመግባታችን ተደውሎ መሞቷን ነገሩኝ።ምን ማድረግ እንዳለብኝና ለልጆቼ ምን እንደምል ግራ ገብቶኛል”አለው።ይሄን የሰማው ሰው በትልቅ ድንጋይ እንደተመታ ሰው ራሱን አመመው።
በህይወታችን ከምንሰራቸው ስህተቶች ውስጥ አንዱ ስለ ሁኔታዎች በቂ ግንዛቤ ሳይኖረን በራሳችን መተርጎምና መፈረጅ ነው።ሰዎች የሆነ ነገር ሲያደርጉ ስለማይወደኝ ነው፣ ስለማያከብረኝ ነው፣ ስልክ ሳያነሱ ወይ የሆነ ነገር ሲያደርጉ ሲቀሩ ደግሞ ሆም ብለው ነው ብለን በራሳችን እንተረጉማለን።የትርጉም ዋናው መዘዝ ከእውነታው አለም ያወጣንና የራሳችንን አለም እንደንፈጥር ያደርገናል።በህይወት ያሉትን ሰዎች እንገላቸውና ክፉ ናቸው አያከብሩኝም የምንላቸውን የራሳችንን ሰዎች በአዕምሯችን እንፈጥራለን።ሀሳባችንን ፊት ለፊት የመናገር ልምድ ስለሌለን በራሳችን ትርጉም በውስጣችንን እንበሰለሰላለን እንጎዳለን።መፍትሄው ምንድን ነው?
1.ምቾት ያልሰጡን ነገሮች ሲኖሩ በራሳችን ከመተርጎም ይልቅ ፊት ለፊት መጠየቅን እንለማመድ።
2.ያሰብኩትና የተሰማኝ ሁሉ ትክክል ነው ማለትን እናቁም።
3.ሰዎች በብዙ ችግርና ውስብስብ የህይወት መንገድ ያልፋሉና ለመረዳት እንሞክር።በዚህ መልኩ ጤናማ ግንኙነታችንን ማዳበር እንችላለን።
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
ኦሾ ስለ ንባብ ባህሉና ስለ መፅሐፎቹ ሲናገር በአንድ ቪዲዮ ላይ እንዲህ ብሎ ነበር፦
<<ከልጅነቴ ጀምሮ ነበር መፅሐፍ ማንበብን የምወደው። በግል ቤተ መፅሐፍቴ ውስጥ 150ሺህ በቀላሉ የማይገኙ መፅሐፎች አሉኝ። 150ሺውንም መፅሐፎች አንብቤያቸዋለሁ። አባቴ ወደ ሞምቤይ በየጊዜው ይመላለስ ነበር። ወደዛ ሲሄድም "ምን ይዤልህ ልምጣ?" ይለኛል። አንድም ነገር እንዲያመጣልኝ ጠይቄው አላውቅም። ይልቁንስ ፡ "ይበልጥ ሰው ሆነህ ና!... ትንሽ ነፃነትንም ይዘህልኝ ና" ነበር የምለው!... ከአባቴ ገንዘብን የምጠይቀው ተጨማሪ መፅሐፎችን ለመግዛት ስፈልግ ብቻ ነው። ደግሞም ለአባቴ ነግሬዋለሁኝ ፣ "ለመፅሐፍ መግዣ ገንዘብን ስጠይቅህ ብትሰጠኝ ይሻልሃል። አለበለዚያ ልሰርቅህ አገደዳለሁኝና" ብዬዋለሁኝ።... አባቴም "መስረቅ አያስፈልግህም። መፅሐፍ መግዣ ገንዘብ በፈለግክ ቁጥር እያነሳህ ተጠቀም" አለኝ።... በየግዜውም መፅሐፍ ስገዛ ቤታችን ሁሉ በመፅሐፍ ተሞላ። ይህን ያስተዋለው አባቴ ፡ "መጀመሪያ አከባቢ ላይ በመኖሪያ ቤታችን ውስጥ ትንሽ ላይብረሪ ነበር። አሁን ግን በላይብረሪ ውስጥ መኖሪያ ቤት አለን!" ይለኝ ነበር!...>>
እያለ ከመፅሐፍና ከንባብ ልምዱ ጋር በተያያዘ ብዙ አጀንዳዎችን ያነሳል። ምንም እንኳን 150ሺህ መፅሐፎችን አንብቤያለሁኝ የሚለው ንግግሩ ትንሽ የተጋነነ መስሎ ቢሰማኝም ፡ የሰውየውን ጥልቅ አንባቢነት ግን መካድ አይቻልም። በሚያራምዳቸው አቋሞች አማካኝነት በአለም ላይ ብዙ ተከታዮችን አፍርቷል። የተከታዮቹን ብዙ እጥፍ የሚሆኑ ተቃዋሚዎችም አሉበት። እንደ አንድ በአምላክ የሚያምን የሀይማኖት ሰው ፡ ከሀይማኖት ጋር በተያያዘ የሚያራምዳቸው አቋሞች ደስ አይሉኝም። አልቀበላቸውምም። ያም ሆኖ ሳለ ግን በእያንዳንዱ ነገር ላይ ያለውን አቋሙን ለመግለፅ የሚሄድበት ርቀትና የማስረዳት አቅሙ ግን ያጅበኛል።
በዕውቀት ላይ የተመሠረተ ጠንካራ መሠረት የሌላቸውን ሰዎችን መነቅነቅ የሚችል አይነት ሰው ነው። ከሀሳቦቹ ውስጥ የምቀበላቸው አሉ።
የማልቀበላቸውም አሉ። አለመቀበል ብቻም ሳይሆን የምጠላለት አስተሳሰቦችም አሉት። የምጠላቸውን አስተሳሰቦቹን እያብራራ ሳዳምጠው ግን እየተናደድኩበትም እንኳን ፡ ሀሳቦቹን ለመግለፅ ከሚሄድበት መንገድ ትምህርትን እወስድበታለሁኝ። ንብን እንደ ሚያንብ ገበሬ ፡ የሰውየውን ንድፊያን በዕውቀትና በማስተዋል እየተከላከልኩኝ ፡ ሰውየው ካለው ማር (መልካም ነገር) ግን እቋደሳለሁኝ። ይህንን ለማድረግ ግን ትንሽም ብትሆን ጠንካራ መሠረት ላይ መቆምን ይጠይቃልና የእኔን አይነት አካሄድን ለሁሉም ሰው አልመክርም።
ይኸው ነው!?
መጽሐፈ ያሬድዋን✍
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
ከቅርብ ዓመት ወዲህ የሚታተሙ መጽሐፎች sexual fantasy ይበዛቸዋል ለምን ይሆን ?
አብዛኞቹ ጽሑፎች ከታች በራሴ ፈጥሬ የፃፍኩት አይነት ናቸው።
ደሞ አንብባቹ ስትጨርሱ በናትህ ይቀጥልልን እንዳትሉ ?
... ሰማዩ ደማምኗል ምድሪቱን በውሀ ሊያረሰርሳት ደቂቃዎች ቀርተውታል እኔ ከቤተሰቦቼ በወረስኩት ሊፈርስ የደረሰ አሮጌ የጭቃ ቤት ውስጥ ጋደም ብየ ፍቅረኛየን በሰመመን አስባታለሁ ከተገናኘን ብዙ ቀናቶች ተቆጥረዋል። ስልኬን አንስቼ ደወልኩላት በሰመመን ዝግ ባለ ድምጽ ሄሎ ፍቅር ሄሎ ትላለች እያቃሰተች የተወሰኑ ደቂቃዎች ቆየት አልኩና ፈራ ተባ እያልኩ ሜሪየ እንዴት ነሽ በጣም ናፍቀሽኛል ዛሬ አትመጭም እቤቴ? አልኳት።
እንዴታ ዛሬ እኮ ካላንደር ይዘጋል በዛ ላይ ምንም የምሰራው ስራ ስለሌለኝ ከአንተ ጋር መጥቼ አሳልፋለሁ አለችኝ።
በጣም ደስ አለኝ ሰውነቴን ሞቀኝ በደስታ ብድግ ብየ ሻወሬን ወሳስጄ ሰንደል ሽቶየን አርከፍክፌ ቤቴን አፀዳድቼ አልጋየ ላይ ጋደም ብየ ጠበኳት ከተወሰኑ ሰዓቶች በኋላ ቀጭ .. ቋ .. እያለች ወደ ቤት ዘው ብላ ገባች ዘልየ አቀፍኳት ሳምኳት ለተወሰኑ ደቂቃዎች አንገቷ ስር ተርመሰመስኩ የአንገቷ መዓዛ ሽታ የሆነ ደስ የሚል ሊወራ ፣ ሊገለጽ የማይችል ደስታ አለው። በጀርባዋ አስተኛኋትና ከአንገቷ ጀምሬ ቀስ እያልኩ በዝግታ ሳምኳት እንብርቷ አከባቢ ስደርስ ከዚ ቀደም የሆነ የማላውቀው አተነፋፈስ ስትተነፍስ እሰማታለሁ በየመሀሉ የኔ ውድ ተው የኔ ፍቅር ይቅርብን ተው ትላለች እያረፈች ቀስ እያልኩ እጄን ጭንና ጭኖቿ መሀል ላይ አደረኩት ኤርታሌ እንደዛ የሚሞቅ አይመስለኝም አይኖቿ ሲቀሉ ጡቶቿ እንደ ጦር ተሰብቀው ሳያቸው ደስታና ድንጋጤ ፍርሀት ተደበላልቀው ወረሩኝ ስሜቷ እንደ ፈላ ቡና ሊገነፍል ጫፍ ደርሷል እኔ ምን አገባኝ ይገንፍላ ቀስ ብየ ልብሶቿን አወጣጥቼ ... ?
ኧ... ከዛስ ?
➝ ወዳጄ እንዲህ አይነት የኂስ መቀስ ያልነካው መጽሐፍ 300 እና 400 ብር አውጥተህ አትግዛ።
➝ ከአንተ የተሻሉ ስለ መጽሐፍ የሚያውቁ ጓደኞችህን ጠይቃቸው የተሻሉ መጽሐፎችን ይጠቁሙሀል።
#????-????? - ???????? ?✍
እናተስ ምን ትላላቹሁ?
???
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
— የአራት ኮሜዲያኖች መጻሕፍት—
? — ???? ? ????? : ?????? ????
በአፓርታይድ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ ከስዊዝ አባቱና ከደቡብ አፍሪካዊ እናቱ የተወለደው ትሬቨር ኖሃ የተኖረ ሕይወቱን ውብ አድርጎ ጽፎታል። እጅግ በጣም ወድጄው ነው ያነበብኩት። ያስቃል። ያሳዝናል። ያሳስባል። ትሬቨር አሪፍ ኮሜዲያን ብቻ ሳይኾን ጥንቅቅ ያለ ስቶሪ ቴለር ነው። ያላነበባችሁ አንብቡት።
? — ???????, ?????? ??? ??? ??? ???????? ????? : ?????? ?????
ማቲው strictly ኮሜዲያን ባይሆንም (በተለይ የመድረክ) የተጫወታቸው ገጸ-ባሕርያት በተለይም የፍሬንድሱ “chandler bing” ይጠቀሳል። በመጽሐፉ አይዋሽም ፥ ስሕተቶቹን አንድ በአንድ ያምናል። ሕይወቱን ሱስ እንዴት እንዳመሰቃቀለው ይተርካል። The big terrible thing ያለው “Alcoholics” (የመጠጥ ሱሰኛ) መሆኑን ነው። ሳነበው ማቲው አሳዝኖኛል። እርሱ ራሱ ላይ እንደጨከነው አልፈረድኩበትም። ትንሽ የሳሱ ቦታዎች ቢኖሩትም አንብቡት።
?— ? ???’? ???? ???? ??: ????? ????
ኬቨን ፊልሞቹና የሚሰጣቸው ኢንተርቪዎች ጥሩ ናቸው። የመድረክ ስታንዳፖቹ ግን ችክ ይሉብኛል። ሕይወቱ በትግል የተሞላ ነው። ይህንን ትግሉን እያሳሳቀ ጽፎልናል። inspire ያደርጋል። የትሬቨርን ግማሽ ያህል እንኳ ውብ ባይሆንም አሪፍ መጽሐፍ ነው። አንብቡት
?— ??? ???? ????? ??????? : ??????? ???????
ቲፋኒ በግድ ኮሜዲያን የሆነች ሰው ናት —አጉል ድርቅና አለባት። በጣም ቅጥ ታጣለች። ቅጥ ማጣቷ አያስቅም ያሳቅቃል። ሁሉን sexualize በማድረግ ታታክታለች። መጽሐፍ የጻፈችው kevin hart መጻፉን አይታ መሰለኝ። አንድም የሚነገርም የሚረባም ታሪክ የላትም። የማደጎ ቤት ( foster care) ቆይታዋን እየለጠጠች አጉል ልታሳዝንና gangster ለመምሰል ትሞክራለች። መጽሐፏ sheer trash ነው። አታንብቡት። ?
ሄኖክ በቀለ እንደ ፃፈው ✍
⛵️⛵️⛵️
"ማንበብ ፋሽን ነው።"
Join us @noahbookdelivery
News and announcements of the library. No books here.
??Official Chinese channel: t.me/zlib_china_official
? https://singlelogin.re
https://en.wikipedia.org/wiki/Z-Library
? https://twitter.com/Z_Lib_official
? https://mastodon.social/@Z_Lib_official
Last updated 3 months, 3 weeks ago
Intel slava is a Russian News aggregator who covers Conflicts/Geopolitics and urgent news from around the world.
For paid promotions and feedback contact us at: @CEOofBelarus
Last updated 4 weeks ago
?Welcome to the best book channel of Telegram.
✨Buy ads: https://telega.io/c/BooksHub25
✨Contact admin ➠ @Bookshub_contact_bot
✨ Off Topic Community➠ @BooksHubCommunity
✨ Copyright Disclaimer➠ https://telegra.ph/LEGAL-COPYRIGHT-DISCLAIMER-09-18