እናት ፓርቲ - Enat Party

Description
እንኳን ወደ እናት ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ገጽ በሰላም መጡ።
ስለተቀላቀሉን እናመሰግናለን።
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago

3 weeks, 4 days ago
[#በወላይታ\_ሁምቦ\_እና\_አበላ\_አባያ](?q=%23%E1%89%A0%E1%8B%88%E1%88%8B%E1%8B%AD%E1%89%B3_%E1%88%81%E1%88%9D%E1%89%A6_%E1%8A%A5%E1%8A%93_%E1%8A%A0%E1%89%A0%E1%88%8B_%E1%8A%A0%E1%89%A3%E1%8B%AB) **ወረዳዎች ከሰሞኑ የተፈጠሩ ኹለት ክስተቶች …

#በወላይታ_ሁምቦ_እና_አበላ_አባያ ወረዳዎች ከሰሞኑ የተፈጠሩ ኹለት ክስተቶች ትኩረት ይሻሉ!

ፓርቲያችን ከቦታው በደረሰው መረጃ በወላይታ ዞን፣ አበላ አባያ ወረዳ፣ አባያ ክላስተር በሚባል የእርሻ ልማት ከሲዳማ ክልል መጡ በተባሉ የልዩ ኃይል አባላት እንደተከፈተ በተገለጸ ተኩስ የሰው ሕይወት ጠፍቷል፤ በርካቶችም ቆስለው ሆስፒታል ይገኛሉ። እስከ አኹንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት እንደነገሰ መሆኑን መረዳት ችለናል። "ችግሩ ትኩረት ሰጥቶ የሚፈታው አጥቶ እንጂ የሰነበተ ነው" የሚሉት ነዋሪዎች "የአኹኑ ግን ኃይል የቀላቀለና ለአገር ብዙ ውለታ የዋሉ የቀበሌው አስተዳደር ጭምር በተኩስ የተገደሉብት ጭምር ነው" በሚል የችግሩን ሥር ሰደድነት ያስረዳሉ። ፓርቲያችን ለሟች ቤተሰቦች ሐዘኑን ይገልጻል፤ መጽናናትንም ይመኛል።  

እንዲኹ በዚያው በወላይታ ዞን፣ ሁምቦ ወረዳ፣ ጠበላ ከተማ አስተዳደር ሥር ከጥምቀተ ባህር ይዞታ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ ውጥረት እንዳለ ፓርቲያችን መረዳት ችሏል። ከዚኽ ቀደም ከጥንት ጀምሮ የጥምቀተ ባህር የነበረ ይዞታ በቀበሌው አስተዳደር ድፍረት በተሞላበት አኳኋን ጠረጴዛ ልማት ማኅበር ለሚባል የተወሰነ ቆርሶ የሰጠና ልማት ማኅበሩም ቀጥሎ ሙሉ በሙሉ በማጠሩ በተፈጠረ ችግር ተበደልን ባሉ ካህናትና ምዕመናን ላይ ፖሊስ እሥርና ከፍተኛ እንግልት እያደረሰ እንደሚገኝ ከአካባቢው ኗሪዎች መረዳት ችለናል። መለየት በሚያስቸግር አኳኋን ተዋልዶና ተፋቅሮ በሚኖር ማኅበረሰብ መሐል ኹኔታውንም ሃይማኖታዊ ለማስመሰል የቀበሌው አስተዳደርና የፀጥታ ኃይሉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውቷል።  

በተጠቀሱ በኹለቱም አካባቢዎች በማኅበረሰቡ ላይ እየደረሰ ያለው እንግልት በአካባቢውም ከአካባቢውም ውጭ ሕዝቡን እረፍት መንሳት ሲሆን በተጠና መልኩ ለአሥርት ዓመታት እየተተገበረ ያለውና ሕገ መንግሥታዊ  ማዕቀፍ ያለው የከፋፍለህ ግዛ ፖሊሲ ውጤት እንደሆነ እናት ፓርቲ በጽኑ ያምናል።

ፓርቲያችን የተፈጠረውን ችግር የክልሎቹ መንግሥታት እንዳላዩ ከማለፍ በአፋጣኝ ገለልተኛ፣ ሚዛናዊና ሕጋዊ መፍትሔ እንዲሰጡ፤ ማኅበረሰቡም በክልሉም ከክልሉም ውጭ እረፍት የሚያገኝበትን ኹኔታ እንዲመቻች በአጽንዖት ያሳስባል። 

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ! 

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፳፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://www.facebook.com/share/p/1H8B3UUt3s/

1 month ago
**የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)**እና **እናት …

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ)እና እናት ፓርቲ

ለኢትዮጵያ አገራዊ ምክክር ኮሚሽን
አዲስ አበባ

ጉዩዩ፦ በአማራ ክልል የታቀደው የአጀንዳ ማሰባሰብ ሥራን ይመለከታል

በቁጥር 1/ሀ.ም.ኮ/3/31655 ኅዳር ፳፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. እንደተጻፈ በተጠቀሰና ታኅሣስ ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. በደረሰን ደብዳቤ ኮሚሽኑ በአማራ ክልል ቀንና ቦታው ወደፊት የሚገለጽ ሆኖ የአገራዊ ምክክር አጀንዳ የማሰባሰብ ሥራ እንዳቀደና ለዚሁ ፓርቲዎቻችንን ወክለው በአጀንዳ ልየታው የሚሳተፉ ተወካዮችን እንድናሳውቅ መጠየቃችን ይታወሳል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ እኛ በትብብር የምንሠራ ፓርቲዎች ኢትዮጵያ አገራችን ከገባችበት መከራ ያላት ብቸኛ መውጫ ምክክርና ምክክር ብቻ መሆኑን መኢአድ ከሃያ ዓመታት በላይ ሌሎቻችን ደግሞ ከተመሠረትንበት ጊዜ ጀምሮ በተገኘው አጋጣሚ ኹሉ ድምጻችንን ስናስተጋባ ብሎም ምክክሩ የአገር አጀንዳ ሆኖ ወደ ውሳኔው ጠረጴዛ እንዲመጣ ጉልህ ድርሻ እንደነበረን በገሃድ የሚታወቅ ነው። የምክክሩ አካሄድ ከአዋጁ አጸዳደቅ ጀምሮ የተለያዩ የጎሉ ችግሮች የነበሩበት ቢሆንም ችግሮቹ ላይ ተጠምደን ከመቆዘም ምክክሩ ለአገር ሊያመጣ የሚችለውን ውጤት ታሳቢ በማድረግ የምክክሩን ሂደት “ችግሮቹ እየተቀረፉ ይሄዳሉ” በሚል እሳቤና ተስፋ ደግፈን ስንጓዝ ቆይተናል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ምክክሩ እውነተኛ ምክክር ሆኖ አገር በእጅጉ የምትሻውን ውስጣዊ ሰላምና ለሕዝባችን አንድነትን እንዲያመጣ ከተፈለገ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው የእርስ በርስ ጦርነት በገለልተኛ አካል አሸማጋይነት እልባት እንዲያገኝና በአንድ እጅ ጠመንጃ በሌላ እጅ የምክክር አጀንዳ ይዞ መጓዝ እንደማይቻልና ከኹሉ አስቀድሞ በትግራይ ክልል የተካሄደው ጦርነት በፕሪቶሪያ ስምምነት እንደተቋጨ ኹሉ አሁንም በሌሎች የአገራችን አካባቢዎች በኦሮሚያና በአማራ ክልሎች እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች ቀደም ሲል በተቋጨበት መልኩ ተቋጭተው ወደ ምክክር ሊኬድ እንደሚገባ ይህ ሊሆን ባልቻለበት ኹኔታ የአገራችንን ቀጣይ እጣ ፋንታ ምናልባትም አገራዊ ምክክሩ ሳይሆን የጦርነቶቹ ሂደት ሊወስን እንደሚችል በተደጋጋሚ ጊዜያት በአገኘነው አጋጣሚ ኹሉ ሥጋታችንን በመግለጽ ምክረ ሀሳብ ስናቀርብ ቆይተናል።

የምክክሩ አጀንዳ ልየታ አዲስ አበባ ላይ በይፋ በተጀመረበት ወቅት ይህንኑ ሥጋታችንን በድጋሚ ገልጸን አጀንዳዎቻችንን እንደምናቀርብ ነገር ግን እየተካሄደ ያለውን የእርስ በርስ የወንድማማቾች ጦርነት ጨምሮ በወቅቱ ያስቀመጥናቸው ችግሮች ሊፈቱ እስካልቻሉ በአገራዊ ምክክሩ ለመሳተፍ እንደምንቸገር መግለጻችን ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለና የአማራ ክልል ኹሉም ዞኖች በሚባል መልኩ የጦርነት ቀጠና ሆነው የክልሉ ሕዝብ በመንግሥት የጸጥታ ኃይሎች በአየርና በምድር በከባድ መሣሪያና በተደጋጋሚ በሰው አልባ አውሮፕላን (Drone) ጥቃት ጭምር እያለቀ ባለበት በዚህ ወቅት፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የተደነገገበት ጊዜ ያበቃ ቢሆንም ክልሉ ሙሉ በሙሉ በኮማንድ ፖስት እየተዳደረ ባለበት ኹኔታ፣ በርካታ ዜጎች በፖለቲካ አመለካከታቸውና ማንነታቸው ታሥረው በሚገኙበት ሁኔታ፣ ጦርነቱ መጠኑን አሥፍቶ እየተባባሠ በመጣበትና የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ አልፎ አልፎ ሙሉ በሙሉ እንዲገደብ በሚደረግበት ኹኔታ በክልሉ በተቀሰቀሰው የትጥቅ ትግል ምክንያት መንግሥት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በድርቅ ለተጎዱ ወገኖቻችን እርዳታ የማድረስና የመታደግ ፍላጎት በራቀበትና በዚህ ምክንያት ሕዝቡ በአንዳንድ አካባቢዎች ለአስከፊ ረሃብ በተጋለጠበት ኹኔታ በክልሉ የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማስብ ከፈረሱ ጋሪው የቀደመበትና ኮሚሽኑ እውነተኛ ምክክር የማድረግ እንቅስቃሴ ሳይሆን የሥርዓት ዓላማ ማስፈጸሚያ መሣሪያ ወደ መሆን ገባ ወይ? እንድንል አስገድዶናል።

በትብብር የምንሠራ ፓርቲዎች በዚህ መልክ በተጠቀሰው የአጀንዳ ልየታ ለመሳተፍ መሞከር እውነተኛ ምክክር አድርጎ ለአገር የሚበጅ መፍትሔ ለማምጣት ሳይሆን የተጠና ተውኔት አካል ከመሆንና ራስን ከማታለል የዘለለ ለአገር የሚያመጣው መፍትሔ እንደሌለው በውል እንረዳለን። በተጨማሪም ክልሉ በዚህ ሁለንተናዊ ምስቅልቅል ውስጥ ባለበት ኹኔታ ተወካዮቻችንን ልከን በአጀንዳ ልየታ ተሳተፉ ማለት ሕወሓት ከከፈተው ጦርነት ጊዜ ጀምሮ በመከራ ውስጥ እያለፈ በሚገኝው የክልሉ ሕዝብ እንዲሁም የሚበሉት አጥተው አጽማቸው ገጥጦ የሚታዩ ሕጻናት ላይ እንደመሳለቅና በታሪክም የሚያስጠይቅ ጭምር በመሆኑ በተጠቀሰው የክልሉ የአጀንዳ ልየታ እንደማንሳተፍ ለኮሚሽኑ በአክብሮት እንገልጻለን።

በአንጻሩ ኮሚሽኑ በሰው ቁስል እንጨት ከመስደድ ዓይነት አካሄድ ይልቅ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ውለታ መዋል ቢገባው ከዓለም አቀፍ ማኅበረሰብ እንዲሁም ከመንግሥት ጋር ያለውን መልካም ግንኙነት ተጠቅሞና ጫና አድርጎ በገለልተኛ አካላት አሸማጋይነት በገለልተኛ አገር እውነተኛ ሰላምን ሊያዋልድ የሚችል ድርድር እንዲደረግ በኹሉም ወገኖች ላይ ጫና በማድረግ ታሪክ የሚዘክረው ሚና እንዲጫወት እናሳስባለን።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!   

ማሙሸት አማረ            ሰይፈ ሥላሴ አያሌው (ዶ/ር)
የመኢአድ ፕሬዚደንት         የእናት ፓርቲ ፕሬዚደንት

??????
https://www.facebook.com/share/p/15QRi692WZ/

1 month ago
[#ዜና\_ላዕላይ\_ምክር\_ቤት](?q=%23%E1%8B%9C%E1%8A%93_%E1%88%8B%E1%8B%95%E1%88%8B%E1%8B%AD_%E1%88%9D%E1%8A%AD%E1%88%AD_%E1%89%A4%E1%89%B5)

#ዜና_ላዕላይ_ምክር_ቤት

በከፍተኛ ጉጉት ይጠበቅ የነበረው የእናት ፓርቲ ላዕላይ ምክር ቤት የተለያዩ ውሳኔዎችን አሳለፈ። አፈ ጉባኤና ምክትል አፈ ጉባኤ መርጧል።

ምክር ቤቱ እንዳይሰበሰብ አባላቱን በማስፈራራት ጭምር ከፍተኛ ርብርብና እንቅፋት ሲፈጠር እንደነበር ይታወሳል።

ምክር ቤቱ ቅዳሜ ታኅሳስ ፲፪ ቀን ፳፻፲፯ አስቸኳይ ጉባዔ አድርጎ በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት በማድረግ ውሳኔዎችን አሳልፏል። በዚሁ መሠረት ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አቶ ያየህ አስማረና ምክትል አፈ ጉባዔ አቶ ብርሃኑ ጸሐይን ጨምሮ ተልዕኮ በመቀበል ጭምር በአባላት መካከል የሀሰት መረጃ በመንዛት ፓርቲውን ለመክፈል ሲንቀሳቀሱ ነበሩ ያላቸውን ስምንት አባላት በፓርቲው መተዳደሪያ ደንብ መሠረት ከያዙት ኃላፊነት እንዲሁም ከአባልነት ሙሉ በሙሉ እንዲሰናበቱ በሙሉ ድምጽ ወስኗል። የስንብት እርምጃ በተወሰደባቸው አመራሮች ምትክ ወ/ሮ ሀብታም ግለጠውን የፓርቲው ላዕላይ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ወ/ሮ ሐረገወይን ዘሪሁንን ደግሞ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባዔ ሆነው እንዲያገለግሉ መርጧል።

ምክር ቤቱ በመቀጠል በተለያዩ ምክንያቶች ኃላፊነታቸውን መወጣት ባልቻሉና በጎደሉ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ምትክ የቀረቡ የፓርቲውን ብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ሹመት ያጸደቀ ሲሆን የፓርቲውን የ፳፻፲፮ የሥራ አፈጻጸም በመገምገምና የ፳፻፲፯ የሥራ ዕቅድንም መርምሮ አጽድቋል።

በተጨማሪም ከፓርቲዎች ጋር የሚደረግን ቅንጅት በተመለከተ ሰፋ ያለ ውይይት ከተደረገበት በኋላ ሥራ አስፈጻሚውን የሚያግዝ ሦስት አባላት ያሉት ቴክኒክ ኮሚቴ ሰይሞ አስቸኳይ ስብሰባውን አጠናቋል።

በዚሁ አጋጣሚ ለተመራጭ አፈ ጉባዔና ምክትል አፈ ጉባዔ እንዲሁም የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ አባላት ውጤታማ የሥራ ዘመን እንመኛለን።

እግዚአብሔር አገራችን ኢትዮጵያንና ሕዝቧን ይጠብቅ!

እናት ፓርቲ
ታኅሣስ ፲፭ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

https://www.facebook.com/share/p/17uuKNoGwJ/

1 year, 10 months ago

1000328531783
Enat Party CBE Account

61984698
Enat Party Abyssinia Account

በተመቻችሁ እንጀምር

1 year, 10 months ago

#፶_ሎሚ
ድምጽ የሆናቸው ያውቁናል፣ የተከለከልነው ዝም እንድንል ነው፤ እኛ ግን ከችግር በላይ ነን!
ዛሬ ምሽት 1ሺህ ሰዎች እያንዳንዳቸው 100 ብር በመስጠት 100ሺህ ብር ለመሰብሰብ ቆርጠናል።
ለ10ሰዎች t.message ይላኩ

1000328531783 Enat party CBE

ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን እናጸናለን

1 year, 10 months ago

#አስቸኳይ
ለሥራ፣ ትምህርት በውጭ ሀገር ያሉ ዘመድ አዝማድ፣ ጓደኛ የምታውቋቸው ካሉ ሙሉ ስማቸውን inbox አድርጉልን። የተሻለ የውጭ ሰዎችን ያውቃል ብላችሁ የምታስቡትም ካላ እንዲሁ ስልክ ላኩልን።
ቸር ዋሉ

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

? Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

?ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ ? @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 5 months, 3 weeks ago

ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot

Last updated 2 months, 1 week ago