የቢሻራው በር✍

Description
በፍቅር ቀለማት ወደ ፍቅር ሐድራ!
Advertising
We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago

1 month ago

#ተፋዑል
#የኸሚስ_መጃሊስ
#ድልን_መጠባበቅ_አምልኮ_ነው

አንድ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፦

[ ሰዎች የፈለገ የጸሐይ ብርሐን ቢያስፈልጋቸው ጸሐይ መጥለቋ አይቀርም። በመጥለቋ ምክንያትም የሚያለቅስ ኾነ የሚያዝን የለም ምክንያቱም ነገ ተመልሳ እንደምትወጣ ስለምናውቅ፤ ይህ "መተማመን" ይባላል። የጸሐይን ዳግም መውጣት አምናችሁ፥ በተከታዩን የአላህን ቃል «ከችግር ጋር ምቾት አልለ።» አልኢንሺራሕ፤06 በሚለው አልተማመናችሁም? አላህ ከችግር በኋላ እርሱ በፈለገው ነገር ይገላግልሃል። በተከታዩ የአላህ ቃልስ አልተማመንም?! « አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው።» ጠላቅ፤03 ]

ሰዎች የወደፊታቸውን የመመለከት ዕድል ቢኖራቸው ዛሬያቸው ምንም ይኹን ያመሰግኑታል ይወዱታል። አላህ ለነገ ከመስራትና ከመልፋት ጋር በውስጣችን ለነገ ከመጨነቅና ሐሳብ ውስጥ ከመግባት እንድንቆጠብ ግን አዝዞናል። "ሪዝቅ" በሰፊው ትርጉሙ ከሰማይ የሚመጣ ነገር ነው። ሰማይ ማለት የዱዓ፣ የራሕመት፣ የበረካ ቂብላ (መቅጣጫ) ነው። ትዳር፣ ልጅ፣ ገንዘብ፣ ጤንነት ከብዙ የሪዝቅ ዓይነቶች መካከል ናቸው። ብቸኛ ግን አይደሉም የኢማንን ሪዝቅ ሳንሰጥ የሐብት ሪዝቅ ቢሰጠን ጎዶሎ ነው። ስንጠይቅ የተሟላ ሪዝቅ መጠየቅ ደግ ነገር ነው። ሰዎች የሚያማርሩትና ወደ አላስፈላጊ ትዕግስት ማጣት የሚገቡት የተሰጣቸውን ሪዝቅና የሚያስፈልጋቸውን ሪዝቅ ባለመረዳታቸው ነው። ስንት ጸጋ በእጃችን እያለ ወደ ማማረር እና አለማመሰገን የሚያስገባን ሸይጧን ነው። እርሱ (ሸይጧን) ወደዚህች ዐለም የመጣበት ዋነኛ ዐላማ ሰዎችን እንዳያመሰግኑ ማድረግ ነው። ካላመንከኝ የአዕራፍ አንቀጽን አንብብ። ከሰይጣን ጉትጎታ (ወስዋስ) በላይ ደግሞ የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) አደጋ ነው። የለንበት ደረጃ ምንም ይኹን እናመስግን፣ ችግር ላይ ብንወድቅ ራሱ ከዚህ ችግር አላህ እንጂ ማንም እንደማየወጣን እንመን። የሰው አንመለከት፣ በአንደበታችን በድርጊታችን የሰው ልብ ላይ ወስዋስ የሚፈጥር ነገር ላለማድረግ እንጣር።

ሰዎች የዚህን የተውሒድ እሳቤ ባለመረዳታቸው ሳቢያ ለነፍሳቸው ክፋት ይጋለጣሉ። በመጨረሻም የሰይጣንና የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) መረብ ውስጥ ይገቡና የሚኖሩት በርሱ ክበብ ውስጥ ይኾናል።

ወደ ተጨባጩ ስንወስደው ምንም ያላጣና ፏ ብሎ የሚሰራን ወጣት ምን ነካው ሳይባል ተነስቶ ይሰደዳል። ተረጋግተው በፍቅር በሚኖሩ ጥንዶች መካከል የረባ በማይባል ቀውስ ፍች ይፈጸማል፣ ተረጋግቶ የሚነግደው ነጋዴ ባልረባ የስነምግባር ቀውስ ሕይወቱ ይናጋል። ሌሎች በርካታ ችግሮች መምጫቸውን ብናጤን ባልተገባ መንገድ ለማደግ ከመከጀል፣ ያለንን ባለማወቅና ባለማመስገን፣ የገጠሙንን ችግሮች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲወገዱ ዕድል ባለመስጠት የሚመጡ የችኮላ ውጤቶች ሆነውም እናገኛቸዋለን።

ችግር ውስጥ ነህ? አላገባህም? ባለዕዳ ነህ? ድኽነት አስቸገረህ? ወደ መፍትሔ እንጂ ራስህንም ኾነ ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር ውስጥ አታስገባ፤ ታግሶ ይህን ነገር ከአላህ መጠባበቅ በራሱ አምልኮ ነውና። በተጨማሪ ራሳችንን በአምልኮ በዚክር እንዲሁም ካላስፈላጊ ሰይጣናዊ ሐሳብ ለማራቅ ኢማን ላይ መሰንበት ጥሩ መውጫ መንገድ ነው።

አላህ ያስረዳና

እርሱ ይፈርጀና

1 month, 1 week ago

ዘካተል ፊጥር ለአዲስ አበባና ለአካባቢዋ ለአንድ ሰው 200 ብር ነው። ወደ ክፍለሀገርሮች ስሌቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን ስለሚችል በአካባቢው ያሉ ዐሊሞችን አማክሩ።

ሠራተኛንና ዘበኛን ጨምሮ በምታስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ልክ ተሰልቶ ዛሬና ነገ በፍጥነት ማውጣት ለተቀባዮች ለዒድ ዝግጅት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል።

https://t.me/hassentaju

1 month, 2 weeks ago

በሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በተውበቱ ላይ ቋሚ ያልነበረ፣ ሁሌም እየቶበተ ተመልሶ እዚያው የሚነከር የኔ ቢጤ ነበር። ሃያ አመት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። እኔስ ብሆን ስንት ዓመቴ በዚህ መልኩ ስኖር?!…
:
አላህ ሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ላይ ራእዩን አወረደ። "እገሌ ለሚባለው ባርያዬ ንገረው። እኔ ተቆጥቼበታለሁ!" አላቸው።…
ሰይዲና ሙሳ መልእክቱን አደረሱ። ሰውየውም እጅግ አዘነ። ደነገጠ። እንዲህ እያለ ወደ ሜዳ ወጣ: ‐
«ኢላሂ! እዝነትህ አልቆ ነው?! ወይስ ኃጢኣቴ ጎድቶህ?! የይቅርታ ካዝናህ ነጠፈ?! ወይስ በባሮችህ ላይ ሰሰትክ?! የቱ ወንጀል ነው ከይቅርታህ የሚገዝፈው?!…
ቸርነት ቀዳሚ ጠባይህ ነው።…
መናጢነት፣ ኃጢኣት የመጤው "እኔ" ተከሳች ጠባይ ነው።…
ታዲያ የኔ ጠባይ ካንተ ጠባይ ሊያይል ይችላል?!…
ባሮችህን ከረሕመትህ ከጋረድክ ማንን ይከጅላሉ?!…
አንተ ካባረርካቸው ወደ ማን ይሸሻሉ?!…
ኢላሂ! እዝነትህ ካለቀና ቅጣትህን መቅመሴ የግድ ከሆነ የባሮችህን ኃጢኣት በሙሉ እኔ ላይ አድርግ። በነፍሴ በዥቻቸዋለሁ!… »
:
አዛኙ አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ሙሳ ሆይ! ሰውየው ዘንድ ሂድና እንዲህ በለው: ‐ «ኃጢኣትህ ሰማይና ምድርን ቢሞላ እንኳን እምርሃለሁ። በሙሉ ኃያልነቴ፣ በሰፊው ይቅርታዬ፣ በማይነጥፍ እዝነቴ እና በማያልቀው ምህረቴ እስካወቅከኝ ድረስ ምሬሃለሁ!»
:
ታሪኩን ኢማም አል‐ገዛሊይ "ሙካሺፈቱል‐ቁሉብ" ላይ አውርተውታል።
tewfik bahiru
https://t.me/fiqshafiyamh

[…አሏሁምመ ኢነከል ዐፉው፣ ቱሒቡል ዓፉው ፈዓፉ አንና…ያ ራሒም!❤️…]

2 months, 3 weeks ago

#ሦስት_ታላላቅ_የልብ_ሥራዎች

ተህሊል_ተስቢሕ_ኢቅራር አዝዘንብ

لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ

« የዓሳውንም ባለቤት ተቆጥቶ በኼደ ጊዜ (አስታውስ)፡፡ በእርሱም ላይ ፈጽሞ የማንፈርድበት መኾናችንን ጠረጠረ፡፡ (ዓሳም ዋጠው)፡፡ በጨለማዎችም ውስጥ ኾኖ ከአንተ በቀር ሌላ አምላክ የለም፡፡ ጥራት ይገባህ፡፡ እኔ በእርግጥ ከበዳዮቹ ነበርኩ በማለት ተጣራ፡፡» አልንቢያእ፣87

ዑለሞች በዚህች የተባረከች ለሊት የነብዩ ዩኑስን (ዐለይሂ ሰላም) ‘ላ ኢላሀ ኢላ አንተ ሱብሓነከ ኢኒ ኩንቱ ሚነ ዟሊሚን’ የሚለውን ዱዓ ማብዛትን ይመክራሉ።

ይህች ልመና ውስጥ ሦስት ነገሮች ግልጽ ብለው ይታያሉ። የመጀመሪያው ተውሒድን የምናጸናበት ኢማንን የምናድስበት ተህሊል (ላኢላሀ ኢለላህ) ሲኾን ሁለተኛው ደግሞ አላህን ማጥራት (ተስቢሕ) ነው። ሦስተኛው ጥፋትን (ወንጀልን) አምኖ መቀበልና ወደ አላህ መመለስን የሚረጋግጥ ነው። አብዝተን እንበለው ኒያችንን ደጋግመን እናድስ። በ "ላኢላሀ ኢለላህ" ኢማን ይታደሳል።

አላህ ይወፍቀን

لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ
لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ
لَّا إِلَٰهَ إِلَّا أَنتَ سُبْحَانَكَ إِنِّي كُنتُ مِنَ الظَّالِمِينَ

2 months, 3 weeks ago
2 months, 3 weeks ago

ኒስፈ ሻእባን
የዛሬዋ ለሊት የ ሸዐባን አጋማሽ ነች።
""''''''''''"""""
በዚህ በሸእባን ወር በጣም የተላቀችና የተከበረች ለሊት ትገኛለች። እሷም የሻእባን አጋማሽ(ኒስፈ ሻእባን) ለሊት ነች። በዚህች ለሊት አላህ ባሮቹን ሙሉ በሆነ እዝነቱና ረህመቱ ይሸፍናቸዋል። ይቅርታን ለጠየቀ ይቅር ይለዋል፡ ለጠየቀም ይሰጠዋል፡ የተቸገረን ከችግሩ ያላቀዋል፡ ለባሮቹ ስራቸውንና ሲሳያቸውን ይጽፍላቸዋል።
የሻእባን አጋማሽ ለሊትን አስመልክቶ ብዙ የሀዲስ ዘገባዎች ሰፍረው ይገኛሉ፡ ከነዚህ ዘገባዎች ውስጥ ሶሂህ፡ ሀሰንና ዶኢፍ የሆነ አለ። በኡለሞች የሀዲስ ሚዛን ሶሂህ እና ሀሰን ከተባሉት የተወሰኑትን ብቻ ልጥቀስ።
የአላህን መልእክተኛ(ሶለሏሁ አለይሂ ወሰለም) የሚከተለውን ብለዋል፡-

  1. "አላህ በሻእባን አጋማሽ ለሊት ለባሮቹ ረህመቱን ይገልጣል፡ ሙሽ-ሪክና ሙና-ፊቅ የሆኑት ሲቀሩ ለሁሉም ምህረት ያደረጋል" (ጦበራኒይና ኢብኑ ሂባን)

  2. "ጂብሪል(አለይሂ ሰላም) መጣና 'ይህች የሻእባን አጋማሽ ለሊት ናት፡ በአላህ ይሁንብኝ በዚህች ለሊት በከሊብ ጎሳ በጎ ጸጉር ቁጥር ልክ ከእሳት የሚድኑ ሰዎች አሉ፡ አላህ ወደ ሙሽሪኮች፡ ሙናፊቆች፡ ዝምድና ቆራጭ ወደሆኑት፡ ልብሳቸውን ጎታች ወደሆኑት(ልብሳቸውን ማያሳጥሩ ወንዶች)፡ ወላጆቹን ወደሚበድል፡ አስካሪ መጠጥ ወደሚጠምቅ. . . . አይመለከትም" (በይሀቂይ)

3."የሻእባን አጋማሽ ለሊት ሲሆን ተጣሪ ይጣራል 'ማርታ የሚፈልግ ምህረት የማደርግለት፡ የሚጠይቀኝ የምሰጠው' ይላል። በዚህች ለሊት አንድ ባሪያ ጠይቆ የሚከለከለው ነገር የለም በብልቷ ዝሙትን የፈጸመች እና ሙሽሪክ የሆነ ሲቀር" (በይሀቂይ)

አላህ በዚህ ወር፡ በዚች የተከበረች ለሊት ከሚምራቸው ባሮቹ ያድርገን። ረመዷንንም በሰላም ያድርሰን።

ምንጭ፡- 'ማዛ ፊ ሻእባን' ከተሰኘው ከሀረመይኑ(ከሁለቱ ሀረሞች) ሙሀዲስ ሙሀመድ ቢን አለዊይ(ረሂመሁሏህ) ኪታብ

ጸሐፊ፦ ሙዓዝ

5 months ago

#የማይገመተው_ሕዝብ
#ሥልጣኔ
#ሰውነት

ይህ የመጨረሻው ዘመን ሕዝብ ካሉት ስያሜዎች መካከል አንዱ "የሙሐመድ ሕዝብ" የሚለው አንዱ ነው። የዚህ ሕዝብ አባል መኾን ክብር መኾኑ የገባቸው የቀደሙ ነብያት ሳይቀር ካሉበት የነብይነት ማዕረግ ወርደው ተራ የዚህ ሕዝብ አባል መኾንን ተመኝተዋል። ይህ ሕዝብ ከሚታየው ተዓምሩ በላይ የተደበቀው የሚበልጥበት ልዩ ነገር አለው። የዘመን ሥልጣኔ ይህን ሕዝብ እርካታና ሐሴቱን ለመጠበቅ ደስታን ለመሥጠት ዘወትር የተለያዩ ዐዳዲስ የሚባሉ ነገሮችን ቢያቀርብም የሰው ልጆችን ውስጣዊ ፍላጎት ግን እንዲህ በቀላሉ የሚረታ አልኾነም።

አብዝተው ለሕዝባቸው ውስጣዊ ዕድገት ለመንፈሳዊ ከፍታው መድኽን የሚጨነቁት ነብዬ የሕዝቦችን ከፍታና የውሰጣዊ ምጥቅት የትኛውም ዘመን አመጣሽ ሥልጣኔ ላይደርስበት ሰቀለውታል።

ሓዳራ ማለት በዐረብኛ ሥልጣኔ ማለት ነው። ሓድራ ማለት ደግሞ መጣድ ማለት ነው። የሰው ልጆች መንፈሳቸው ከአላህና ከመልእክተኛው ጋር ሲገናኝ ሕሊና በዚህ መንገድ ንቁ ሲኾን ሓደረ (ተጣደ) ይባላል። ዑለሞች ሥልጣኔ (ሐዳራ) የሰፊው ሐድራ አንድ ክፍል ነው የሚሉት። ምክንያቱም ይህ የምናየው ዓለም ሥልጣኔ በዚህ ምድር ላይ በተፈጠሩ የአላህ ፍጥረታት ላይ ተነስተው ነው ዐዲስ ነገር ለመከወን የሚሞክሩት እንጂ ከፍጥረቱ በፊት ስላለው ሆነ ስለዘላለማዊው ነገሮች ያላቸው ዐቅም የተገደበ ነው።

ቁስን በመገንባት የሠለጠኑ ሥርዓቶችን በማየት መንፈሳዊነት ላይ አትዳከሙ። እነ ፊርዓውን የገነቡት ሥርዓት ሀይልና ጉልበት እንዲሁም ቁሳዊነት ላይ የሰው ልጆችን ሊገዛና ሊያንበረክክ የሚጥር ነበር። ግና አላህ ምስኪኑን ሙሳ አንዲት በትር ሰጥቶት ሥልጣኔያቸው እንዲወድም በማድረግ ሕዝቡን እንዲያድን እንዳደረገው አዘውትረን የምናነበው ነው።

የነቢ ኡመት እርሳቸው በዘረጉት መንገድ ይጠበቃል። ዐረቦች ከሕዝቦች ኹሉ የተናቁ በነበሩበት ጊዜ እርሳቸው ሲወለዱ ብርሃን አገኙ። እርሳቸውንም ስለያዙ የበላይ መኾንም ቻሉ። የሁለቱም ዓለም የበላይነት ያለው በመንገዳቸው ብቻ ነው። እውነተኛው ሥልጣኔም ዕውን የሚኾነው በመንገዳቸው ሕያው በመኾን ነው።

ብዙ ሰዎችን ገብሮ ጥቂቶችን የሚያበለጽገው የግንብ ድርድሮችን  የሚያሳካውን የምዕራቡ ኾነ የምስራቁ ስልጣኔ ሰውን ልጅ መሥራት ኾነ መጠበቅ አልቻለም።

የነብዩ (ሰዐወ) ፍጹም ምጡቅ ሥልጣኔ ግን ቅድሚያ የሰራው የሰውን ልጅ ነው። ሥልጣኔውንም መሠረት የሚያደረገው ሙሉ ሰው መፍጠር ነው። በኹሉም ነገር አደግን የሚሉት ኹሉ የቸገራቸውም ይኸው የሙሉ ሰው የመኾን እክል ነው። ሰውነት ደግሞ በእርሳቸው መንገድ ተረጋገጠ።

የአላህ መልእክተኛ ስለሕዝባቸው ጥብቅነት ስለሞራሉና ስለኹሉም ነገሩ አዛኝነት የተላበሱ ገራገር ነበሩ። በዚህ ጉዳይ ከተናገሯቸው ብዙ ማሳሰቢያዎች መካከል አንዱን ላውሳና ላጠናቅቅ።

በዘመን ዕድገት ውስጥ የተለያየ ሰዋዊ የኾነ ነገር በማየት ሕዝብ እንደ ሕዝብ ተስፋ እንዲቆርጥ የሚጣሩ ሰባኪዎች እንዲጠነቀቁ ተከታዩን ሐዲስ መላልሰው እንዲያነቡ ይመከራል።

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦ « አንድ ሰው  " ሰዎች አለቁ፣ጠፉ" ብሎ ያለ እንደሆን እርሱ ነው ያጠፋቸው።» በሌላ ገለጻ «የጠፋው ራሱ ነው።» የሚልም ይገኝበታል።

ዑለማዎች ሲያብራሩ መሰል ንግግሮች ለግለሰቡ ራሱን ከሌሎቹ እንዲያስበልጥ ሲያደርገው  ሌሎችን ማሳነስና መናቅ ውስጥ በማስገባት ነፍሲያ ይፈጥርበታል።

በመሠረቱ የነብይን ኡመት (ሕዝብ) የሚያውቀው እርሳቸው ሙሐመድ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ብቻ ናቸው። የሰው ልጆችም ኾነ ጂኖች የእርሳቸው ሕዝብ እንደመኾናቸው በዕዉሩ ዓይናችን በምናየው ግማሽ እውነት ነገር ላይ ተመስርተን ሕዝብ ላይ በጭፍኑ መፍረድ ኡመታቸው ላይ ማጠባበቅና ማክበድ ነውና ጥንቃቄ ያሻዋል።

አላህ የእርሳቸውን ጥበቃ ከሚያገኙት ባሮች ውስጥ ይዶለና

5 months, 1 week ago

°| በአንድ ወቅት አንድ ትዕቢተኛ መኳንንት አንድ አቢድ ሱፍይን ጎበኘ።. . . |°

መኳንንቱ ወደ ሱፍዩ ተጠግቶ “ነፍሶችን ታነፃላችሁ(ታበራላችሁ) ሲባል ሰምቻለሁ፣ ግን እንዴት ሊሆን ይችላል?
እያንዳንዱ ነፍስ መለኮትን የምታንጸባርቅ መስታወት አይደለችምን? ምን ልትጨምሩበት ትችላላችሁ?” ሲል ጠየቀ

ጠቢቡ ሱፊይ ፣ መኳንንቱን በትህትና ወደ መኖሪያው ጋበዘው። ሁለት መስተዋቶች ወደተሰቀሉበት ክፍል መራው።

አንደኛው መስታወት ግልጽና ንጹህ ነበር።
ሌላኛው በወፍራም አቧራ እና በቆሻሻ የተሸፈነ ነበር።

ጠቢቡ "እነዚህን መስተዋቶች ተመልከት" አለው።

"ሁለቱም ምስሎችን እንዲያንፀባርቁ ተደርገዋል።
አንዱ በጥሩ ሁኔታ ሲያከናውን ሌላው ደግሞ ሳይሳካለት ይቀራል። ለምንድነው? "

መኳንንቱ " ይሄማ ግልጽ ነው አቧራማ መስታወቱ መጽዳት ያስፈልገዋል!” በማለት መለሰ።

አቢዱም እንዲህ አለው፣
" በትክክል! ሁሉም ነፍስ መለኮትን የምታንፀባርቅ መስታወት ነች።
ግና ከጊዜ በኋላ አቧራውን ይሰበስባል-
የነፍስያ ፣ የኩራት ፣ የስስት ፣ የውሸት ፣ የረዥም ምኞት ፣ የምቀኝነት ፣ የጭፍን ጥላቻ
ና የአለማወቅ አቧራን ትላብሳለች።

ሙረቢ(መንፈሳዊ መምህር) ለነፍስ ምንም አይጨምርም። ይልቅ ላደፈች ነፍስ መለኮታዊ ባሕርያት በግልጽ እንዲገለጡላት እነዚህን ቆሻሻዎች ለማጸዳዳት ይረዳል። በዚክር መጥረግያ!

___
ۖ فَاسْأَلُوا أَهْلَ الذِّكْرِ إِن كُنتُمْ لَا تَعْلَمُونَ
የማታውቁም ብትኾኑ የመጽሐፉን ባለቤቶች ጠይቁ፡፡

አብዱ ሩሚ

5 months, 3 weeks ago

#ዓሪፎች_እና_የሀብት_ፍልሥፍናቸው

«እናንተ ሰዎች ሆይ! እናንተ (ሁል ጊዜ) ወደ አላህ ከጃዮች ናችሁ፡፡ አላህም እርሱ ተብቃቂው ምስጉኑ ነው፡፡» አልፋጢር፥15

አህሉላህ ወአህሉል ሐቅ በሚል ተቀጽላ በታሪኽ ገጽ ላይ የሚታወቁት "ሱፍያዎች" ራሳቸውን ፉቀራእ (ከጃይ) ሲሉ ይገልጻሉ።

በኒሳቡር ከተማ ይታወቁ የነበሩት ታላቁ ሱፍይ ሸይኽ የሕያ ቢን ሙዓዝ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ድኽነት ምንድነው ተብለው ተጠየቁ። እንዲህ አሉ፦

«ድኽነትን (ማጣትን) መፍራት!» ሲሉ መለሱ።

ድኽነትን መፍራት ማለት ሁሉን ነገር የኔ ነው በሚል ስሜት ስቁንቁን መኾን ማለት ነው። ድኽነትን (ከጃይነትን) ወደ ፈጣሪ ማረጋገጥ ማለት ግን ወደ አላህ ከጃይ የመኾን ትርጉም ነው።

የአላህ መልእክተኛ (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦ "ከሙታን ጋር ከመቀማመጥ ወየውላችሁ!"

"አንቱ የአላህ መልእክተኛ ሆይ! (ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሙታኖች እነማን ናቸው?"

እንዲህ ሲሉ መለሱ፦ "ሐብታሞች"

በዚህ ዐለም ላይ (በዱንያ) መጠቃቀሚያዎች ብቻ ተጠቃቅሞ በእርሷ ተጽዕኖ ውስጥ የገባ አካሉ ሕያው ሲኾን መንፈሱ የሞተ ነው። ንግግሩና ሐሳቡ በሙሉ ስለቅርቢቱ ዓለም (ዱንያ) ብቻ ይኾናል።
ግና በአላህ ላይ ባለው መጠጋት የተብቃቃ ወደርሱ ከጃይ (ድኻ) የኾነ ነው። እነዚህኞቹ የማይሞቱ (ሕያው) ናቸው።

በኢማሙ ጁነይድ (ቀደሰላሁ ሲረሁ) ዘመን የነበሩት አንጋፋዉ ሱፍይ ዓሊም ሺብሊ ድኽነት ምን እንደሆነ ተጠየቁና እንዲህ አሉ፦ "አንድ ሰው በአንዳች ነገር ከአላህ ውጭ ሊብቃቃ ይችላልን?!"

በትዕግስትና ምስጋና መካከል ያለው ሚዛን በድኽነትና ሀብት መካከል ያለውን ነገር የምንለካበት ነው።

ያህያ ቢን ሙዓዝ እንደሚሉት ነው። ሰይጣናትና ጭፍሮቻቸው ቢሰባሰቡ በሚከተሉት ሦስት ነገሮች የሚያስደስታቸውን ያህል በምንም ነገር አይደሰቱም።

① የአማኞች እርስ በእርስ መጋደል
② የአንድ ባርያ በክህደት ላይ ሳለ መሞት
③ የአንድ ሰው ልብ ውስጥ የድኽነት ፍራቻ መኖር

ቀጥለውም እንዲህ ይላሉ፦ « ፍጡር በፍጡር ላይ ጥገኛ የመኾን ምሳሌው እስረኛ በእስረኛ ላይ ከጃይ እንደሚኾነው ነው።»

"እስር ቤት" ማለት በአህሉ ተሰውፍ ዘንድ ይህች ዓለም (ዱንያ) ማለት ነው።

እስልምና ሥራን በብርታት መሥራትን የሚያበረታታውን ያህል ያለን የምንለው የአላህ ሀብት እንደኾነ እንድናምንና ወደርሱ ድኾች እንድንኾን ያዝዛል።

በቁርኣኑም ስለ ሀብት በለቤትነት ሲያወሳ በአልኑር ምዕራፍ ቁጥር 33 እንዲህ ይላል፦ "ከአላህም ገንዘብ ከዚያ ከሰጣችሁ ስጧቸው።"

በእስልምና አስተምህሮት "ሀብታሙ ኹኑ" የሚል ስብከት ሳይኾን የሚታወቀው ሀብት ማለት በአላህ ላይ መጠጋትና ያለን ኹሉ የእርሱ እንደኾነ መተማመን ማለት ነው። በአንጻሩ ድኽነት ማለት ከፈጣሪ መሸሽ፣ በፍጡራን ላይ መወከል፣ ደካማነትና ስልቹነት ነው። በጥቅሉ ከስብ (ሥራ)፣ ንግድ ጠንካራ መኾን ነብያዊም ኾነ ኢስላማዊ ፈለግ (ሱና) እንደኾነ ከማመን ጋር አለን በምንለው ዱንያዊ ጸጋ መወከልና በሰበቦች ጥገኛ መኾን ግን ከባድ የውስጥ ድኽነት ይቀሰቅሳል።

በየጊዜው ካለንበት ሁነትና ከምናስመዘግበው ኢኮኖሚያዊና ማሕበራዊ ለውጦች በላይ አስፈላጊው ባሕርይ ወደ አላህ የምናሳየኸው ድኽነትና መጠጋት ዋነኛው መንገዳችን ነው።

ምሽቱ የጁምዓ ዋዜማ የኸሚስ ምሽት ነው። በሰለዋትና በዚክር መቀማመጥን ማዘውተር ልብ ወደ አላህ የሚያደርገውን ድኽነት ያረጋግጣል። ምሽቱን ነይተን ቤታችንን በሰለዋት፣ በሐለቀተ ዚክር ወልቁርኣን ማድመቅ ለቤት ብርሀን ይለግሳል።

አላህ የእርሱ ባርያ ያድርገን

ይወፍቀን

5 months, 3 weeks ago
አንዴ አንድ ሰው ሉቅማንን በተከታዮቻቸው ተከበው …

አንዴ አንድ ሰው ሉቅማንን በተከታዮቻቸው ተከበው ይመለከትና በመገረም እንዲህ በማለት ይጠይቃቸዋል፦ «የእገሌ አገልጋይ አልነበርክ እንዴ? የእገሌ እገሌን በግ ትጠብቅ አልነበር? አሁን ላይ እንዴት ነው በሰዎች ዘንድ እንደዚህ አይነት የተከበረ ቦታ ያገኘኸው?» አላቸው! ሉቅማን'ም ፦ «እውነተኛ ንግግር እና በማይመለከተኝ ጉዳይ ላይ በሚኖረኝ ረጅም ዝምታ!» በማለት መለሱ። 😊

እውነት ነው! አላህ እና ውዱ መልዕክተኛው ﷺ የማይነሱበት መቀማመጦች የቀልብ ድርቀትን ያመጣሉ። እንቶ ፈንቶዎችን ማብዛት እና ያለ እረፍት ሰዎችን በመጥፎ ማማት፤ ቀልድ እና ዛዛታን ማዘውተር የውስጥ ሰላማችን ያሳጣናል! ለዛም አይደል ጌታዬ ቁርኣን ላይ ይህን ያለን፦ «የአል -ረሕማን ባሮች እነዚያ በምድር ላይ በዝግታ የሚኼዱት:ባለጌዎችም (በክፉ) ባነጋገሩዋቸው ጊዜ ሰላም የሚሉት ናቸው።» [አል ፉርቃን፡63]🤎
ያስረዳና! 😊

https://t.me/One1Tube
nadia biya❤️

We recommend to visit

★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን

💌 Contact us, @Modenyazbot

»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።

° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °

° ° Creator @Teke_Man ° °

Last updated 2 weeks, 1 day ago

☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!

➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !

➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc

📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!

Last updated 2 weeks, 2 days ago

እንኳን ወደ # ሉሲ የቴሌግራም ቻናል በደህና መጡ
#የሉሲ /LUCY DINKINESH E/ቤተሰብ ሰለሆኑ ደስብሎናል።

መረጃ መስጠት የምትፈልጉ በዚ አድርሱን 👉 @CACA77

# የኢትዬጵያዊነት የአሸናፊነት መገለጫ አርማችን ነው!
ነፃነታችንን 💪በፈርጣማው ጡንቻችን ይረጋገጣል
👉 ኢትዬጵያዊነት አርበኝነት የማንነት አርማች ነው
🙏🙏🙏

Last updated 1 month, 3 weeks ago