★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago
ለነቢ ረሱለሏህ (ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) በሚኖር ውዴታ’ና ቅርበት የሚገኙ እድያዎች፣በቁጥር ከማይዘለቁ፣ሕይወትን ከሚለውጡ ተዓምራዊ በረከቶች አንዱ…
«ነቢ ረሱለሏህን ወዶ የቀረበ ኹሉ፣የላቀ ክበር’ና ራሕመትን መቋደሱ ነው።»ከሰው ዘር የሶሓቦቹ ማሳያ ነው። ጨለምተኛ ነበር ብርሃኃን ሞሉት። ለክብረቱ ምሳሌ ሰይዲና ቢላልን ያነሷል።ነቢ በመውደዱ ከውርደት ወጣ።በክብር ዙፋን ተደላደለ። ነቢን አገኘ’ና ተውሒድን፣ ኑርን፣ ጀነትን ተጎናፀፈ። ገድሉን ታሪክ ለፊት ገፁ፣አድምቆ ሚዘክረው ሰው ሆነ።
ሀሳቡ ከሰው ልጅ ውጪ ሲታይ ልብ ገዥ ነው።የቴምር ጉቶ ተላምዷቸው በልሳን ከማውራት ጀነት እስከመሰጠት።ለፍቅር ታሪክ ሕያው ማሳያ ሆኖ መወሳት አገኘ።
"ያዕፈር"? የሚባለው መጓጓዣ አሕያቸው የአብሮነት ታሪክ ስለነበረው በዘገባዎች፣ የእስልምና ጉዞ ታሪክ ተካፋይ ሆኖ በክብር እየተወሳ ይኖራል።አፍቃሪዋ ግመላቸው ቀስዋ ስለ ነቢ ረሱለሏህ ፍቅር ተምሳሌታዊ ምስክር በመሆን፣ከልዩ ክብርና ስስት ጋር ስሟ ይወሳል።ከክፍለ ዘመናት በኋላ ሳይቋረጥ እንደ ሁሉም አፍቃሪ ፍቅሯ በክብር ይተረካል።
የተገለገሉበትት ቁስ፣የተጓዙበት መንገድ፣ ያረፉበት ዋሻ፣ የለበሱት፣የኖሩበት ሌላም ሌላው ግዑዝ እቃ እንኳን…በዑመቱ ልብ ውስጥ ቅዱስ ቅርሶች ሆነው ለመከበር ያበቃቸው፣ በነቢ ረሱለሏህ ዙርያ መገኘታቸው፣ከነቢ መቅረባቸው፣በሳቸው መነካታቸው ነው። ምናልናት የ አንድ ጊዜ የመዳፋቸው ዳበሳን በመታደላቸው!
አሏህም ይኸው እድያ በሁሉም ዘመን የማይቋረጥ እንዲሆን፣ወደ’ሳቸው ፍቅር መጠጊያ ትልቁን የቅርበት ገመድ የሆነውን ሰላዋትን ለዑመታቸው ከመስጠቱ። በረካው ማ’ድ የተደረገ የፍቅር፣የራሕመት ግብዣ ጥሪ ነው!
አላሁመሰሊ ወሰሊም ወባሪክ ኣላ ሰይዲና ሙሐመድ!💜
« በአንድ በጎ ባርያ ላይ የሚሰፍን የአሏህ ውዴታ በቃላት ሊገለጽ የማይችል ስሜት አለው።
እጅግ በጣም ቀዝቃዛ እና ብርድ በሆነ ሌሊት ሞቅ እንዳለ ብርድ ልብስ ልብህን ያካብባል። ወይም የመለኮታዊ ብርሃን ብልጭታ ነውና ወዳንተ ዘልቆ፣ በደም ስርህ ውስጥ ይጓዛል..…ይቆጣጠርሃል።…ከዚያም ስሙን በምላስህ ማዘወተር፣ጣፋጭ ሱስ ይሆንብሃል! »
«በየ ኹሉም የኑሮ ሒደት ውስጥ…በየ ሰዓቱ የምትደጋግመው…ጣፋጭ ስም የርሱ ስም ይሆናል። የስሙ ጥፍጥና የሚሰጥህ ጥልቅ የመደድ መንፈስ የፍቅር ምናኔ ውስጥ ያስገባሃል።ስሙ ቀልብህ ለይ ኢማንን፣ ሩሕ ዘንድ ሰኪናን፣ ጀሰድህ ላይ ደግሞ የኑር ጀማላን ፈገግታን ውበትን…ሞልቶ ያሸበርቅልሃል!»
ስሙን ብቻ መጥራት ህያው ኑር ያለብሳል…
الله🩵
[…አንተ የኔ አሏህ 1…]
ፍቅርህ ብርሓናማ ነው! በ’ኛ አድማስ ላይ የተጋረደው ድቅድቅ ፅልምት ባሻገር ኃያል፣አሸናፊው፣እና ንጉሱ የሆንከው አሏሃችን ያንተ ህያው ብርኃን አለ።ወደ’ኛ የሚወነጨፈው ፍቅርህ በሩሓችን ላይ ደማቅ መንፈሳዊ ሕያው ብርሓንን ያኖራል። የኑር ብራቅህን ወደ ባዶው እኛነታችን ሰንዝረህ እንድናስብህ አደልከን። መድረስ ወዳንተው ነው፣ ማድረስም ያንተ ነው።አላህዬ☺️
እኛም…አሰብንህና ደግሞ…ካንተ ውጪ ላለ ለሁሉም ነገር ምንም ግድ አጣን
የወደቅንበትን፣የባዘንንበትን የስቃይ አረንቋ ዘንግተን ፍካት በልባችን ተሞላ።አንተን በማሰብ ውስጥ ተጠመድን። እኛማ በምን አቅማችን…! አንተው አሰብኸን ኣሳሰብኸንም፣ እንድናስብህ ኣደረግኸን። ልታድነን ስትፈልግ።ከዚያ በኃላ…አንተ ፈቅደህ፣በኛ ላይ እንዲሆን የሻኸው ሁሉ እንዲጣፍጠን ሆነ። በሁሉም መከራ ውስጥ ጥበብህ…ፍቅር ውዴታህ አዛኝነትህ ይታየን ጀመር።እናም ያኔ ስለ ሁሉም ነገር ግድ የለንም። ግድ የሚሰጠን "አሏህ…አሏህ" ማለት ሆነ!
الله…!💚
Share ዘላለማዊው ብርሃን.pdf
#ተፋዑል
#የኸሚስ_መጃሊስ
#ድልን_መጠባበቅ_አምልኮ_ነው
አንድ ዓሊም እንዲህ ይላሉ፦
[ ሰዎች የፈለገ የጸሐይ ብርሐን ቢያስፈልጋቸው ጸሐይ መጥለቋ አይቀርም። በመጥለቋ ምክንያትም የሚያለቅስ ኾነ የሚያዝን የለም ምክንያቱም ነገ ተመልሳ እንደምትወጣ ስለምናውቅ፤ ይህ "መተማመን" ይባላል። የጸሐይን ዳግም መውጣት አምናችሁ፥ በተከታዩን የአላህን ቃል «ከችግር ጋር ምቾት አልለ።» አልኢንሺራሕ፤06 በሚለው አልተማመናችሁም? አላህ ከችግር በኋላ እርሱ በፈለገው ነገር ይገላግልሃል። በተከታዩ የአላህ ቃልስ አልተማመንም?! « አላህ ፈቃዱን አድራሽ ነው።» ጠላቅ፤03 ]
ሰዎች የወደፊታቸውን የመመለከት ዕድል ቢኖራቸው ዛሬያቸው ምንም ይኹን ያመሰግኑታል ይወዱታል። አላህ ለነገ ከመስራትና ከመልፋት ጋር በውስጣችን ለነገ ከመጨነቅና ሐሳብ ውስጥ ከመግባት እንድንቆጠብ ግን አዝዞናል። "ሪዝቅ" በሰፊው ትርጉሙ ከሰማይ የሚመጣ ነገር ነው። ሰማይ ማለት የዱዓ፣ የራሕመት፣ የበረካ ቂብላ (መቅጣጫ) ነው። ትዳር፣ ልጅ፣ ገንዘብ፣ ጤንነት ከብዙ የሪዝቅ ዓይነቶች መካከል ናቸው። ብቸኛ ግን አይደሉም የኢማንን ሪዝቅ ሳንሰጥ የሐብት ሪዝቅ ቢሰጠን ጎዶሎ ነው። ስንጠይቅ የተሟላ ሪዝቅ መጠየቅ ደግ ነገር ነው። ሰዎች የሚያማርሩትና ወደ አላስፈላጊ ትዕግስት ማጣት የሚገቡት የተሰጣቸውን ሪዝቅና የሚያስፈልጋቸውን ሪዝቅ ባለመረዳታቸው ነው። ስንት ጸጋ በእጃችን እያለ ወደ ማማረር እና አለማመሰገን የሚያስገባን ሸይጧን ነው። እርሱ (ሸይጧን) ወደዚህች ዐለም የመጣበት ዋነኛ ዐላማ ሰዎችን እንዳያመሰግኑ ማድረግ ነው። ካላመንከኝ የአዕራፍ አንቀጽን አንብብ። ከሰይጣን ጉትጎታ (ወስዋስ) በላይ ደግሞ የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) አደጋ ነው። የለንበት ደረጃ ምንም ይኹን እናመስግን፣ ችግር ላይ ብንወድቅ ራሱ ከዚህ ችግር አላህ እንጂ ማንም እንደማየወጣን እንመን። የሰው አንመለከት፣ በአንደበታችን በድርጊታችን የሰው ልብ ላይ ወስዋስ የሚፈጥር ነገር ላለማድረግ እንጣር።
ሰዎች የዚህን የተውሒድ እሳቤ ባለመረዳታቸው ሳቢያ ለነፍሳቸው ክፋት ይጋለጣሉ። በመጨረሻም የሰይጣንና የሰዎች ጉትጎታ (ወስወሳ) መረብ ውስጥ ይገቡና የሚኖሩት በርሱ ክበብ ውስጥ ይኾናል።
ወደ ተጨባጩ ስንወስደው ምንም ያላጣና ፏ ብሎ የሚሰራን ወጣት ምን ነካው ሳይባል ተነስቶ ይሰደዳል። ተረጋግተው በፍቅር በሚኖሩ ጥንዶች መካከል የረባ በማይባል ቀውስ ፍች ይፈጸማል፣ ተረጋግቶ የሚነግደው ነጋዴ ባልረባ የስነምግባር ቀውስ ሕይወቱ ይናጋል። ሌሎች በርካታ ችግሮች መምጫቸውን ብናጤን ባልተገባ መንገድ ለማደግ ከመከጀል፣ ያለንን ባለማወቅና ባለማመስገን፣ የገጠሙንን ችግሮች ወቅታቸውን ጠብቀው እንዲወገዱ ዕድል ባለመስጠት የሚመጡ የችኮላ ውጤቶች ሆነውም እናገኛቸዋለን።
ችግር ውስጥ ነህ? አላገባህም? ባለዕዳ ነህ? ድኽነት አስቸገረህ? ወደ መፍትሔ እንጂ ራስህንም ኾነ ሕዝብን የሚጎዳ ተግባር ውስጥ አታስገባ፤ ታግሶ ይህን ነገር ከአላህ መጠባበቅ በራሱ አምልኮ ነውና። በተጨማሪ ራሳችንን በአምልኮ በዚክር እንዲሁም ካላስፈላጊ ሰይጣናዊ ሐሳብ ለማራቅ ኢማን ላይ መሰንበት ጥሩ መውጫ መንገድ ነው።
አላህ ያስረዳና ♥
እርሱ ይፈርጀና ♥
ዘካተል ፊጥር ለአዲስ አበባና ለአካባቢዋ ለአንድ ሰው 200 ብር ነው። ወደ ክፍለሀገርሮች ስሌቱ ከዚህ የተለየ ሊሆን ስለሚችል በአካባቢው ያሉ ዐሊሞችን አማክሩ።
ሠራተኛንና ዘበኛን ጨምሮ በምታስተዳድሯቸው ቤተሰቦች ልክ ተሰልቶ ዛሬና ነገ በፍጥነት ማውጣት ለተቀባዮች ለዒድ ዝግጅት የበለጠ ጠቃሚ ይሆናል።
በሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ዘመን በተውበቱ ላይ ቋሚ ያልነበረ፣ ሁሌም እየቶበተ ተመልሶ እዚያው የሚነከር የኔ ቢጤ ነበር። ሃያ አመት በዚህ ሁኔታ ቆይቷል። እኔስ ብሆን ስንት ዓመቴ በዚህ መልኩ ስኖር?!…
:
አላህ ሰይዲና ሙሳ (ዐለይሂ ሰላም) ላይ ራእዩን አወረደ። "እገሌ ለሚባለው ባርያዬ ንገረው። እኔ ተቆጥቼበታለሁ!" አላቸው።…
ሰይዲና ሙሳ መልእክቱን አደረሱ። ሰውየውም እጅግ አዘነ። ደነገጠ። እንዲህ እያለ ወደ ሜዳ ወጣ: ‐
«ኢላሂ! እዝነትህ አልቆ ነው?! ወይስ ኃጢኣቴ ጎድቶህ?! የይቅርታ ካዝናህ ነጠፈ?! ወይስ በባሮችህ ላይ ሰሰትክ?! የቱ ወንጀል ነው ከይቅርታህ የሚገዝፈው?!…
ቸርነት ቀዳሚ ጠባይህ ነው።…
መናጢነት፣ ኃጢኣት የመጤው "እኔ" ተከሳች ጠባይ ነው።…
ታዲያ የኔ ጠባይ ካንተ ጠባይ ሊያይል ይችላል?!…
ባሮችህን ከረሕመትህ ከጋረድክ ማንን ይከጅላሉ?!…
አንተ ካባረርካቸው ወደ ማን ይሸሻሉ?!…
ኢላሂ! እዝነትህ ካለቀና ቅጣትህን መቅመሴ የግድ ከሆነ የባሮችህን ኃጢኣት በሙሉ እኔ ላይ አድርግ። በነፍሴ በዥቻቸዋለሁ!… »
:
አዛኙ አላህ እንዲህ አለ: ‐ «ሙሳ ሆይ! ሰውየው ዘንድ ሂድና እንዲህ በለው: ‐ «ኃጢኣትህ ሰማይና ምድርን ቢሞላ እንኳን እምርሃለሁ። በሙሉ ኃያልነቴ፣ በሰፊው ይቅርታዬ፣ በማይነጥፍ እዝነቴ እና በማያልቀው ምህረቴ እስካወቅከኝ ድረስ ምሬሃለሁ!»
:
ታሪኩን ኢማም አል‐ገዛሊይ "ሙካሺፈቱል‐ቁሉብ" ላይ አውርተውታል።
✍ tewfik bahiru
https://t.me/fiqshafiyamh
[…አሏሁምመ ኢነከል ዐፉው፣ ቱሒቡል ዓፉው ፈዓፉ አንና…ያ ራሒም!❤️…]
የመለያው ቀን
እያንዳንዱ ስልጣኔ ከማበቡና የልቅና ማማ ላይ ከመድረሱ በፊት ወሳኝ ታሪካዊ ክስተት ያሳልፋል፡፡ ለሙስሊሞች ይህ ወሳኝ ክስተት ረመዳን 17 2ኛ ዓ.ሂ የተካሄደውና በቁርአን ስሙ የተጠቀሰው ታላቁ የበድር ጦርነት ነው፣ አላህ ይህን ዕለት የውመል ፉርቃን(የመለያው ቀን) ብሎ ጠርቶታል፣ እውነትና ውሸት የተለዩበት የየራሳቸውን ጎራ ይዘው ፊት ለፊት የተያዩበት ዕለት ነው፡፡
‹‹...በዚያም እውነትና ውሸት በተለየበት ቀን፣ ሁለቱ ጭፍሮች በተገናኙበት(በበድር) ቀን…››አል አንፋል 41
የአላህ መልእክተኛ ሰ.ዐ.ወ የቁረይሾችን የንግድ ቅፍለት ለመቆጣጠር ከተወሰኑ ሰሃቦች ጋር ሆነው ከመዲና ወጡ፤ የቅፍለቱ መሪ የነበረው አቡ ሱፍያን ይህ ወሬ ሲደርሰው ወደ መካ መልእክተኛ ላከ፡፡ ቁረይሾችም 1300 የጦር ሰራዊት፣700 ግመሎችና በቁጥር የበዙ ፈረሶችን ይዘው ተንቀሳቀሱ፡፡ የሙእሚኖች ብዛት ከ313-319 ሲሆን 70 ግመል እና 2 ፈረስ ብቻ ነበር የያዙት፡፡ ነቢ ሰ.ዐ.ወ የባልደረቦቻቸውን ሃሳብ መስማት ፈለጉና ውጊያ እናድርግ ወይስ እንመለስ ብለው አማከሯችው፤ ምክንያቱም አወጣጣቸው ቅፍለቱን ለመማረክ እንጂ ለጦርነት አልነበረም፡፡ በመጀመሪያ አቡበክር ተነሱና ጥሩ ንግግር አደረጉ፤ ዑመርም በመቀጠል ተናገሩ፤ ከዚያም ሚቅዳድ ኢብን ዐምር ተነሳና፡-
‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ፡ አላህ ያመላከተዎትን ተግባር ይፈፅሙ እኛ ከጎንዎ ነን፤ በአላህ እምላለሁ እስራኤሎች ለሙሳ ‹አንተና አምላክህ ሂዱና ተዋጉ፤ እኛ አዚህ ተቀምጠን እንጠብቃችኋለን› እንዳሉት እኛ አንልዎትም፡፡ ይልቁንም እርሶና አምላክዎ ሄዳችሁ ተዋጉ፤ እኛም ከናንተ ጋር እንዋጋለን፡፡ በእውነት በላከዎ ጌታ እምላለሁ ወዳሻዎ ቦታ ብትወስዱንም እስከመጨረሻው እንከተሎታለን፡፡›› አለ፤ ነቢ ሰ.ዐ.ወ በንግግሩ ተደስተው ጥሩ ብለሀል አሉትና ዱዓእ አደረጉለት፡፡ ሁሉም ሰሀቦች እንደ ሚቅዳድ ታዛዥ እንደሆኑ ያውቃሉ፤ ነገር ግን አሁንም ደግመው ሀሳባቸውን ጠየቋቸው፤ ‹‹እናንተ ሰዎች ሆይ፡ አስተያየታችሁን ስጡኝ›› አሉ፡፡ አንሳሮችን ማለታቸው ነው፤ ምክንያቱም አንሳሮች ከነቢ ሰ.ዐ.ወ ጋር የዐቀባን ስምምነት በተዋዋሉ ጊዜ መዲና መጥቶ የሚያጠቃቸውን ጠላት እንጂ ከመዲና ውጪ ወጥተው እንዲዋጉ አያስገድዳቸውም፡፡
ሰዐድ ኢብን ሙዓዝ ‹‹የአላህ መልእክተኛ ሆይ፡ የኛን አስተያየት ነው የፈለጉት? ›› ብሎ ጠየቃቸው እሳቸውም አዎ አሉት፡፡ እሱም አንሳሮችን ወክሎ እንዲህ ተናገረ፡-
‹‹ በእርሶ አምነን እውነት ብለን ተቀብለንዎታል፤ ያመጡት መልዕክት እውነት ስለመሆኑም መስክረናል፤ እርስዎን ለመታዘዝ ቃልኪዳን ገብተናል፤ የአላህ መል/እክተኛ ሆይ፡ የሚፈልጉትን ይፈፅሙ በእውነት በላክዎ አምላክ እምላለሁ ይህን ባህር ሰንጥቀን እንድናልፍ ቢያዙን እንኳ እናልፈዋለን፤ ከመካከላችን አንድም ሰው ወደኋላ አይቀርም ነገ ከጠለት ጋር ብንፋለም የምንጠላ አይደለንም በጦርነት ላይ ታጋሾችና ፅኑዎች ነን፤ ከኛ የሚደሰቱበትን ነገር አላህ ያሳይዎ ይሆናል በአላህ በረከት የታየዎትን ይፈፅሙ፡››
ነቢ ሰ.ዐ.ወ በሰዕድ ንግግር ተደሰቱ፤ ወኔያቸውም ይበልጥ ተነሳሳ፤ “ተጓዙ አይዟችሁ አላህ ከሁለት በጎ ነገሮች አንዱን እንደሚገጥመኝ ቃል ገብቶልኛል፤ በአላህ እምላለሁ ሰዎች (ጣኦታውያን) ሲረፈረፉ ይታየኛል” አሉ፡፡
የዛን ቀን ምሽት አላህ ሱ.ወ ዝናብ አወረደ ከሀድያንን ያዳክመች፣ ለሙእሚኖች ጥንካሬ የጨመረች ዝናብ አዘነበ፡፡ “ ከርሱ የሆነን ሰላም ሊለግሳችሁ በእንቅልፍ በሸፈናችሁ ጊዜ፣ እንዲሁም በርሱ ሊያፀዳችሁ፣ የሰይጣንንም ጉትጎታ ሊያስወግድላችሁ፣ ለልቦቻችሁም ጥንካሬን ሊያጎናፅፍና እግሮቻችሁንም (ውጊያ ላይ) ሊያፀና ከሰማይ ውሃን ባወረደ ጊዜ (የሆነውን አስታውሱ) አል አንፏል 11
ጣኦታውያን ሲገለፁና ሁለቱ ሀይሎች ሲተያዩ የአላህ መልዕክተኛ ሰ.ዐ.ወ እንዲህ ብለው አላህን ለመኑ፡-
“አላህ ሆይ ቁረይሾች ከነ ትዕቢትና ኩራታቸው አንተን ለመቀናቀን እና መልእክትህን ለማስተባበል እነሆ ታድመዋል፤ አላህ ሆይ ቃል የገባህልኝን ድል ስጠኝ፤ አላህ ሆይ ሽንፈትን አከናንባቸው›› የሰራዊታቸውን ረድፍ አስተካክለው ከጨረሱ በኋላም አምላካቸውን አጥብቀው ከመማፀን አልተቆጠቡም፤ “አላህ ሆይ ቃልህን እንድትሞላ እማፀንሀለው›› እያሉ ይለምኑት ነበር፤ ጋቢያቸው ከትከሻቸው እስኪወድቅ ድረስ ዱአቸው በረታ፤ አላህም ለመላእክቱ እንዲህ የሚል መልዕክት አስተላለፈ፡-
“እኔ ከናንተ ጋር ነኝ እማኞችን አጠናክሩ፤ በነዚያ በካዱት ሰዎች ልቦች ውስጥ ፍርሀትን እለቃለሁ….›› አልአንፋል 12 ለመልዕክተኛውም እንዲህ ሲል አበሰራቸው፡
“ተከታትለው በሚወርዱ ሺህ መላዕክት እገዛ አልክላችኋለሁ”
“አዎን ብትታገሱና ብትጠነቀቁ ከዚህም ፍጥነታቸው (ጠላቶቻችሁ) ቢመጡባችሁ፡ ጌታችሁ ምልክት ባላቸው አምስት ሺህ መላእክት ይረዳችኋል›› አሊ ዒምራን 125፡፡ መላእክት በወረዱ ጊዜ ነቢ ሰ.ዐ.ወ ይህንን የቁርአን አንቀፅ አነበቡ
“ስብስበቸው ድል ይምመታል፡ ጀርባዎቻቸውንም ይዞራሉ” አልቀመር 45፡፡
በእጃቸው እፍኝ አፈር ቆነጠሩና ወደ ቁረይሾች አቅጣጫ በመዞር “ፊቶቻችሁ ይበላሹ” እያሉ በተኑት፤ አሸዋው በእያንዳንዱ ጣኦታዊ አይንና አፍንጫ ውስጥ ገባ፡፡
ጦርነቱ በጣኦታውያን ከባድ ሽንፈት፡ በሙስሊሞች አንፀባራቂ ድል ተደመደመ፡፡ ከሙስሞች 14 ሰማዕታት ሲኖር ከጣኦታውያን 70 ሰዎች ተገድ' ለው 70ዎቹ ተማረኩ፤ ከሙታንም ሆነ ከምርኮኞች አብዛኛዎቹ መሪዎችና በላባቶች ነበሩ፡፡
በሸኽ ሺብሊ እንደተተረከው፦ አንድ ጎረቤታቸው ከሞተ በኋላ በህልም ያዩታል ፣ ከዚያም ለጎረቤታቸው "አላህ ምን አደረገህ?" በማለት ጠየቁት
እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ - “ሼኽ ሆይ! በመቃብር ውስጥ በጣም አስፈሪ ነገሮችን ተመለከትኩ በዚህም ሰቀቀን ውስጥ ገባሁ መልአክቱ ሙንከርና ነኪር ስመለከት ደሞ የምናገረውም ጠፋብኝ ፣ ለራሴም ‘ዋ.. ጥፋቴ አከተምልኝ አልኩ’ "በዱንያ ላይ ሙስሊም ነበርኩ የሞትኩትም በእስልምና ነበር ,
ከዚያም ሁለቱ መላእክት ጥያቄዎቻቸውን በከፍተኛ ድምፅ ጥያቄዎቻቸው እንድመልስ ጠየቁኝ." በድንገት አንድ መልከ–መልካም እና ጥሩ መዓዛ ያለው ሰው ብቅ አለ ፤
የሁለቱን መላእክት ጥያቄዎች በተሻለ መንገድ መልስ ለመስጠት በእኔ እና በሁለቱ መላእክት መካከል እራሱን ሰየመ, ከዚያም አላህ ይዘንልህና “አንተ ማን ነህ? አልኩት"
እርሱም፦ እንዲህ ሲል መለሰ - “እኔ [ሶለዋት] አላሁመ ሶሊ 'ዓላ ሰይዲና ሙሐመድ ወ'ኣላ ኣሊ ሰይዲና ሙሐመድ' ነኝ ..የትም ብትሆን በፈለከው ጊዜ አንተን ለመርዳት እና ለማዳን ሃላፊነት ተሰጥቶኛል” አለ።
?—كتاب الصلوات مفتح حل المشكلات، علي قزويني، ص : 96.
©
ኢብኑ ነሕዊይ ይናገራሉ رحمه الله
አንድ ቀን ኢብኑ ዓጣኢ'ላሂ‐ሰከንደሪ መጅሊስ ላይ ተገኘሁ ፣ የዛኔ የዘመኑ ታላቅ ሸይኽ ነበሩ
በአድናቆት ሆኜ ዕውቀትና ሊቅነታቸውን እየተመለከትኩ ለራሴ ይህን አልኩ
"እንደው የትኛው መቃም* ላይ ይሆኑ ይሆን?"
ወደኔ ተመለከቱና " ወንጀል ሰርተው ምህረትን ከሚለምኑት" አሉ
በነገሩ በጣም ተገርሜ ከግርማ ሞገሳቸው የተነሳ ጭጭ አልኩ ! ከዛም ሰላምታ አቅርቤ ሄድኩኝ
በዛው ለሊት በህልሜ ነብዩን ﷺ ከፍ ያለ ስፍራ ላይ ሆነው በዙሪያቸው የተከበሩ ሰሓቦች ተሰብስበው አየሁ
ነብዩም ﷺ
« የታለ ታጁዲን ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ አሉ »
"አቤት አለሁ ያ ረሱለላህ ﷺ" አሉ
ነብዩም ﷺ
«ተናገር አላህ ንግግርህን ይወዳል »አሉ
ከእንቅልፌ ባነንኩ ፣ ባየሁት ነገርም በጣም ተደነቅሁ !
ወደ ሰይዲ ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ ዘንድ ስመጣ
በህልሜ ነብዩ ﷺ ፊት ሲናገሩ የሰማሁትን ሲናገሩ አገኘኋቸው !
ለራሴም በውስጤ
"በአላህ እምላለሁ ይህ ነው መቃሙ" አልኩ።
ኢብኑ ዓጣኢ'ላህ ወደኔ ተመለከቱና
"አንተ ላይ`ኮ የተደበቀው የላቀው ነበር" አሉኝ።
መደድድድድድድድ ያ አህለል‐ኡንሲ ቢላሂ
✍tof nas yusuf ❤️
★ሰውን በማዝናናት የብቃት ማረጋገጫ ያለው ብቸኛው ቻናል ሁሌም Telegram ላይ በጥበብ ደምቀን እናሸበርቃለን
💌 Contact us, @Modenyazbot
»የተመረጡ እና ማንም ያላያቸው የአማሪኛ ቀልዶች እንዲሁም የሚያስደንቁ ስዕሎችንና ቪዲዮ ያገኛሉ።
° ° [ ሙድ እንያዝ በእኛ የአራዶች መዝናኛ ] ° °
° ° Creator @Teke_Man ° °
Last updated 2 months, 1 week ago
☕ ስለ ኢትዮጲያ ቡና የሚወጡ ወቅታዊና ትክክለኛ የክለቡ መረጃዎች አዚህ ያገኛሉ!
➪የዝዉዉር ዜና
☞የአሰልጣኞች አስተያየት
➪ጎሎች እና ቪዲዮዎች
☞የተጨዋቾች የህይወት ታሪክ
➪ጨዋታዎችን በቀጥታ ስርጭት ከየስታድየሙ !
➡መወያያ ግሩፓችን @Ethiopia_coffee_Sc
📩ሀሳብ ወይም አስተያየት ካሎት
በዚህ 👉 @EthiopianCoffeeScBot ✍
BOT ማድረስ ይችላሉ!
Last updated 4 months, 3 weeks ago
ማንኛውንም የማስታወቂያ ስራ ለማሰራት የምትፈልጉ(only promotion) inbox @Eyyiba
ሌሎች ጥያቄዎችን ለማድረስ
@Ethiodailyvacbot
Last updated 1 month ago