Why Pay for Entertainment? Access Thousands of Free Downloads Now!

Coffee and Scribblings

Description
Short stories, thoughts, anything & everything by Loza Admassu @lozacas
Advertising
We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago

2 months ago

There is only one way to live life: to live.

Deavis Musiu
@coffeeandscribblings

2 months ago

On talking to 49 people... each for 3 minutes...

Thrilling. It is amazing how everyone shows up in the world very differently. Different accents. Different fears. Different hairs. Different clothes.
Different stories.

No two people are the same.

Not even Helen and I.

On talking to 49 people... each for 3 minutes...

Scary. Because you never know what the other one will say. You never know what someone will tell you and change the way you see things.

Someone lived in a place where you can smell the rice as it grows. I didn't even know... rice has a smell.

Someone talked about being a mother and a wife.

One has been to Accra and sold artisans work. She said Accra is as safe as Kigali.

Someone gave me a hug.

The other had been in politics to represent sportsmen more.

Many others I can’t even remember as I sit down to write.

But…

Here is a thought.

Talking to 49 people made me think about God. I revert to that whenever something profound happens to me.

And I once had asked someone I love, if I were God and you were my only creation, and I am omnipotent and living in glory, would I have come as the poor thing a human is and be born in the barn just to save you?

And I didn’t know then.

But if I had the time and the power and if I wasn’t so scared, I would want to have a personal relationship with everyone. And love them. And be dramatic  enough to be born in the barn for them.

Human beings are as ridiculously amazing as that.

Or that Dostoyevsky has gone to my head.

Mar 17,2024
@coffeeandscribblings

2 months ago

In a way, the human world is but a set of different conversations.

@coffeeandscribblings

3 months, 3 weeks ago

በልጅነት ማንበብ በአዋቂነት ከማንበብ በጣም ይለያል።

የልጅ አንባቢ ጭንቀቱ ብዙ ነው።

ልጅ እያለሁ ቀጣዩን መጽሐፍ ከየት እንደማመጣው ይጨንቀኝ ነበር። የሚያበድሩኝ ልጆች እንዳይቀየሙኝ ቶሎ ቶሎ አንብቤ መመለስ ነበረብኝ። አለበለዚያ ቀጣዩ መጽሐፍ ከየት ይመጣል? ገንዘብ ከየት ይመጣል? ሲጀመር መጻሕፍት ቤት የት የት ነው የሚገዙት? አላውቅም።

ዘመድ ቤት ስወሰድ አይኖቼ መጻሕፍት ላይ ይንከራተታሉ። ልጆች ሲጫወቱ እኔ መሄጃ ሰዐት እስኪደርስ ቶሎ ቶሎ አነብ ነበር። ያዘኑልኝ ዘመዶቼ ውሰጂ እና አንብቢ በቃ ይሉኛል።

አክስቴ ትዝ ትለኛለች አሮጌ መጻሕፍት አይን ያጠፋሉ እያለች ታስነሳኝ ነበር።

ያላሉኝ አሉ። ጀምሬ ያልጨረስኋቸው መዐት ታሪኮች አሉ። እነሱን ይሆናል የምጽፈው እላለሁ አንዳንዴ።ፐ

ትምህርት ቤቶ፣ በምሳ ሰዐትም ቤትም እረፍት አልነበረኝም። በጣም እጓጓ ነበር ለማንበብ። አባቴ፣ ጥሩ መጽሐፍ ሲኖረኝ የሚጣፍጥ ምግብ እየጠበቀኝ ይመስለኛል ይላል። በጣም ገረመኝ። እኔም እንደዛ ነበር የማስበው። ሌላው ሌላው ሁሉ ቁምነገር መስሎ አይታየኝም ነበር።

መምህራን ይቆጡኝ ነበር። ከትምህርት ትሰንፊያለሽ። ያለእድሜሽ ትጨምቻለሽ ይሉኝ ነበር።

የክፍል ስራ በፍጥነት ሰርቼ ወደ መጽሐፍ ነው የምመለሰው። የሚቆጡኝ መምህራን ሲሆኑ በመማርያ መጽሐፍ ሸፍኜ አነብብ ነበር። አንዲት አስተማሪ ነበረችን። ትቀማኝና አንብባ ስትጨርስ ትመልስልኛለች። ቀምታኝ ፈንጠር ብላ ስታነበው እያየሁ አዝን ነበር።

በዛው ልክ ደግሞ መጻሕፍት የምታመጣልኝ አስተማሪ ነበረችኝ።

ደግሞ የሚያስጨንቁኝ መጻሕፍትም ነበሩ። አልገባ ይሉኛል። የሚያስረዳኝ አልነበረም። የምመርጠው መጽሐፍ አልነበረም። አሁን እንደዚህ ሳማርጥ ይገርመኛል። ትርጉም ምናምን አልልም። ከተገኘ ማንበብ ነው። አንዳንዱ ግራ ያጋባኛል።

የክፍል ጓደኞቼ ሁሌ አመሰግናቸዋለሁ። በተለይ ጸደንያ የምትባል አራተኛ ክፍል ከእኛ ትምህርት ቤት የወጣች ልጅ ነበረች። አባቴ አንባቢ ነው እያለች በጣም ብዙ መጻሕፍት ታመጣልኝ ነበር። አመሰግናለሁ።

ክረምት እወድ ነበር። ማን አይወድም? ግን ሰቆቃ የለም። መጻሕፍት አበዳሪ ቤቶች ይከፈታሉ። በቃ ይዘንባል። ቁጭ ብሎ መኮምኮም ነው።

እና፣ እንዲህ በልጅነቱ ያነብ የነበረ ሰው ሳገኝ እፈነጥዛለሁ። የእኔና የእህቴ አለም ብቻ ሳይሆን ሌላም የኖረበት መሆኑ ደስስስ ያሰኘኛል። አስኳል፣ ከቡስካ በስተጀርባ፣ እፎይታ፣ ምንዱባን፣ ምስኪኗ ከበርቴ ምናምን እያለ የመጻሕፍት ርዕስ ከጠራልኝ በቃ ሞትሁ።

ድጋሚ በህይወት እና በሰው ልጅ እምንንን አደርጋለሁ።

@coffeeandscribblings

3 months, 3 weeks ago

I really liked the book. It made me want to close my eyes... you know. One sad thing is you can't close your eyes and read.

[Line from some scribbling I found. I wonder which book this is]

@coffeeandscribblings

4 months ago
5 months, 3 weeks ago

ትንሽ ተናግሮ ብዙ የሚያናግረኝ ጓደኛዬ፣ ካስባለኝ ነገሮች አንዱ፣
Man is a polygon but you don't know 'n' ነው።

ያስባለኝ የምለው፣ ዝም ብሎ ሲያዳምጠኝ የምላቸው ነገሮች ስለሚገርሙኝ ነው። ከእኔ ማሰብ ብቻ ሳይሆን ከእሱ ማዳመጥም የወጡ ናቸው። የሀሳቤ ፈታይ ነው። ፈትል ከጥጡ ብቻ ሳይሆን ከፈታይዋም እንዲወጣ።

ብቻ እንደዚያ ካልኹ በኋላ የሌላው ቢቀር የራሴን 'n' ልወቅ እላለሁ።

አልደርስበትም።

መዐት ነኝ። በየቀኑ የምትወልደኝ አለችን? ኋላ እንዴት በየቀኑ አዲስ ሆንሁ? ስለራሴ የማላውቀውን እያወቅኹ ነው ወይስ እንደአዲስ እየፈጠርኹ?

የዛሬ አመት ቀርቶ የዛሬ ሳምንት እንዴት ያለሁ ሰው ነበርኹ?

ከዛ ስለሌሎች አስባለሁ።

የሌላ ሰው ነፍስ ጨለማ ቦታ ነው ብሏል ዶስቶየቭስኪ።

የሌላ ሰው ነፍስ እንቆቅልሽ ነው። ጨለማ እና ጠመዝማዛ ነው። ያለበትም የሌለበትም አይታወቅም።

ሌላ ሰው፣ ነፍሳችን እስከሚወጣ ብንወደው እንኳን ሌላ ቋንቋ የሚነገርበት ሌላ አለም ነው።

እና ይደንቃል።

ሁላችን ሁሉም ነገር በውስጣችን ያለ አለሞች ነን።

ዛሬ ይሄን አሰብሁ።

ህዳር 12/16
@coffeeandscribblings

5 months, 4 weeks ago
5 months, 4 weeks ago

https://youtu.be/s1gzaAE6_Tw?si=aUyVX8e7n7IjLec

My other life as a podcaster... please subscribe to our YouTube channel and support us.

YouTube

የስነተዋልዶ ጤና በሰብዓዊ ቀውሶች

በአለማችን በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት የመጠበቅ ፣ የመማር እና ከጉዳት ነፃ ሆኖ የመኖር #ሰብአዊመብቶች በይበልጥ እየተጣሱ ይገኛሉ። የታንኳ ቤተሰብ ሄቨን እና ሚኪያስ እውነታው ምን እንደሚመስል ያስረዳሉ። In today's world, the #FundamentalRights of millions of children - to be protected, educated and live their lives free from…

7 months ago

You may now leave your thoughts and comments @lozacas

We recommend to visit

https://www.hulepay.com/

Last updated 1 week, 3 days ago

🍿የ VIP ቻናላችንን በአነስተኛ ክፍያ በመቀላቀል ሁሉንም ፊልሞችን ማግኘት ትችላላቹ።
🍿 CHANNEL ~> @Wase_Records
🍿 BOT ~> @Wase_Records_Bot
🍿 OWNER ~> @The_hacker_person
🍿 VIP ~> @The_hacker_person

Last updated 3 days, 8 hours ago

አፍሪወርክ ቢዝነሶች እና የግል ቀጣሪዎች ለስራቸው ከሚፈልግዋቸው ፍሪላንሰሮች ፣ ቋሚ ሰራተኞች እንዲሁም የትርፍ ጊዜ ሰራተኞች ጋር በቀጥታ የሚገናኙበት ፕላትፎርም ነው።

አሰሪዎች ስራ ለመልቀቅ @freelanceethbot ይጠቀሙ

Afriwork in English @freelance_ethio

Last updated 1 month, 3 weeks ago